ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, August 8, 2018

የጉዳያችን ገጽ በያዝነው ነሐሴ ወር ሰባተኛ ዓመቷን ታከብራለች::


መንደርደርያ  
=======
የጉዳያችን ገጽ www.gudayachn.com)  የዛሬ ሰባት ዓመት  የመጀመርያ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ጽሁፍ መልቀቅ የጀመረችው በያዝነው ነሐሴ ወር ውስጥ ነበር::በእነኝህ ሰባት  አመታት ውስጥ ከ800 በላይ ርዕሶች ላይ ፅሁፎች፣ዜናዎች እና ሃሳቦች ተለጥፈዋል።ይህ ማለት በወር በአማካይ ከአስር በላይ  በዓመት ከአንድ መቶ በላይ ርዕሶች እና ጉዳያችን አውጥታለች። በእዚህም ሳብያ በአሁኑ ሰዓት በሚልዮን የሚቆጠሩ አንባቢዎች ከኢትዮጵያና መላው ዓለም አፍርታለች::ብዙዎች በተለይ ሀይማኖት እንጂ ፖለቲካ አንሰማም ያሉ ወጣቶች በሀገራቸው ስለሚደረገው ጉዳይ በማሳወቅ ጉዳያችን ባለውለታችው  እንደሆነች ሲናገሩ ይሰማሉ:: ጉዳያችን በብቸኝነት ተፅኖ የፈጠረችባቸው ጉዳዮችን አሁን አንድ ሁለት ብዬ መጥቀስ የምችላቸው አሉ።እነኝህ ወደፊት የሚገለጡ ይሆናሉ። 

ከእዚህ ሁሉ ጋር ማንኛውም ሥራ ከእንቅፋት ውጭ አይደለም።በፅሁፎቹ ሳብያ ካላቸው የፖለቲካ ወገንተኝነት አንፃር የከፋቸው የሉም ማለት አይደለም።በአካል ሳይሆን በስነ ልቦና ተፅኖ ለመፍጠር የሞከሩ ሁሉ ነበሩ።አንዱ ከእኛ ማኅበረሰብ  የታዘብኩት አንድ ሰው የሚሰራውን ሥራ ከማበረታታት ይልቅ ስራህን የሚጠሉት (ከፖለቲካ ወይንም ከጎሳ ስሜት ሊሆን ይችላል) በርታም፣ተውም ሳይልህ  በጥላቻ እንደሚያይህ እንዳይታወቅበት በፈገግታ እያጠገበህ ግን ደግሞ ወዳጅ መስሎ ሌላ ሌላውን እያወራህ ነገር ግን ያንተ ጉዳይ ሲከታተል ገንዘቡን እና ጊዜውን የሚያጠፋ ብዙ መኖሩን ነው።በእርግጥ ብዙዎች በሞራልም በሃሳብም ድጋፍ የሆኑ አሉ።

ጉዳያችን ሰባተኛ ዓመቷን እንዴት ታክብር?               
========================  
ጉዳያችን በያዝነው ነሐሴ/2010 ዓም  ሰባተኛ አመቷን በማስመልከት ከእዚህ በፊት በገጿ ላይ የወጡትን ጽሁፎችና ቪድዮዎች በማስታወስ እና በማኅበራዊ ሚድያ በመለጠፍ ታከብራለች:: ወደፊት ግን በስብሰባ አዳራሽ የተለያዩ ምሁራንን እና አንባብዎቿን  ጋብዛ  እንዲተቿት እና ሃሳብ እንዲሰጧት መርሐግብር ታዘጋጃለች።
                   
ጉዳያችን ከአዲስ አመት በኃላ 
=================  
በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙርያ ትልቁ እና ውዱ ሀብት አዲስ ሃሳብ የማምጣት ጉዳይ ነው።የምዕራባውያን የኤሌክትሮኒክስ እና ሚድያ ባለሙያዎች ድካማቸው ለሀገራቸው አዳዲስ ሃሳቦችን ማነፍነፍ ነው።የሐሳብ ድርቀት ሀገር ይጎዳል።ትውልድ ያቀጭጫል።

ጉዳያችን ከአዲስ አመት በኃላ አሁን በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ምክንያት በማድረግ "ጉዳያችን አዲስ ሀሳብ" በሚል ለሀገር በሚጠቅሙ ሀሳቦች ላይ ያተኮረ ሀሳብ የሚቀርብበት አጫጭር ጽሁፎች ትጀምራለች::እነኝህ ሃሳቦች ከወጡ በኃላ ከመንግስት ጀምሮ የሚመለከታቸው አካላት ጠቃሚ መስሎ ከታያቸው እና  የተገበሯቸውን በዓመቱ መጨረሻ ላይ ሪፖርት ታደርጋለች።ትኩረት ካላገኙ ሃሳቦቹን ደግማ ታቀርባለች።በእዚህ መልኩ በ2011 ዓም ለሀገር የሚጠቅም ተፅኖ ፈጣሪ ሚናዋን ትወጣለች።


ምስጋና 
=====
ባለፉት ሰባት ዓመታት የጉዳያችን ፅሁፎች ምንጭ በመጥቀስ ለሌሎች እንዲዳረሱ የተጋችሁ በተለይ በአሜሪካን ሀገር ሀገር የሚገኘው የዘሐበሻ ድረ ገፅ እና ሌሎችም ከፍ ያለ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ጉዳያችንን ከፍተው ያለፉ ዓመታት ጽሁፎችና ቪድዮዎች ያንብቡ÷ይመልከቱ ለሌሎች ያካፍሉ:: 

ጌታቸው በቀለ 
የጉዳያችን ገፅ አዘጋጅ 

ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...