ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, December 20, 2018

የህወሓት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን የመቃወም ምክንያት፣ የድብቅ አፍራሽ አጀንዳ መኖር ነው::


ጉዳያችን / Gudayachn 
ታኅሳስ 11/2011 ዓም (ደሴምበር 21/2018 ዓም)

በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ የሚከተሉት ንዑስ ርዕሶች ይገኛሉ። 

  • የኮሚሽኑ መመስረት መሰረታዊ ዓላማ እና ምክንያት ምንድ ነው? 
  • ኮሚሽኑን ለመመስረት የወጣውን አዋጅ ረቂቅ (ሙሉ ፅሁፍ)
  • የህወሓት አፍቃሪ እና የጥቅም ተጋሪዎች ለምን የኮሚሽኑን መመስረቻ ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ለምን አስፈራቸው ?
  • ቅንነት ያድናል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታኅሳስ 11/2011 ዓም የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።አዋጁ ከእዚህ በፊት ለውይይት ቀርቦ ለውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ተመርቶ ቆይቶ ነበር።ይህ የኮሚሽን መመስረቻ ረቂቅ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት ከህወሓት መንደር ማጉረምረም ተሰማ።ኮሚሽኑ ውሳኔ ሰጪ አለመሆኑ፣ሕገ መንግስትን የማይቃረን መሆኑ እየታወቀ እና በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ቦታዎች የሚነሱ የሃያ ሰባት ዓመት የጎሳ ፖለቲካ ውላጅ የሆኑ ግጭቶች ሺዎችን ከቦታቸው እያፈናቀለ እና ለእርስ በርስ እልቂት እየዳረገ መሆኑ እየታወቀ ህወሓት ለምን የኮሚሽኑን ምስረታ ለመቃወም ደፈረች? የሚለው ጥይቄ መሰረታዊ ጥያቄ ነው። 

በእርግጥ እስካሁን ህወሓት እንደ ድርጅት በኮሚሽኑ ምስረታ ላይ የወጣ ድርጅታዊ መግለጫ (ይህ ፅሁፍ እስከሚፃፍ ድረስ) አልታየም።ሆኖም የህወሓት ቅጥር አክትቪስቶችን ጨምሮ ''የትግራይ ኦን ላይን'' በዶ/ር አብይ ላይ የከፈቱት የስም ማጥፋት ዘመቻ  ጎን ለጎን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ያሳለፈው የኮሚሽኑ መመስረቻ አዋጅ ማፅደቅ ላይ አዲስ የማጥላላት ዘመቻ  ከፍተዋል። ለምሳሌ ''ትግራይ ኦን ላይን''  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሚሽኑን መመስረቻ ውሳኔ ባሳለፈ በሰዓታት ውስጥ በእንግሊዝኛ ''የኢትዮጵያ ፓርላማ ህገ ወጥ እና ኢ-ሕገ መንግስታዊ ውሳኔ አሳለፈ'' በሚል ርዕስ የፃፈው ፅሁፍ የኮሚሽኑን ምስረታ የማጥላላት እና የማጠልሸት ሥራ ላይ ተጠምዶ መመልከት አፍቃሪ ህወሓት ልሳኖች የኮሚሽኑ መመስረት ለምን አስከፋቸው ብሎ ለመመርመር ግድ ይላል።

የኮሚሽኑ መመስረት መሰረታዊ ዓላማ እና ምክንያት ምንድ ነው?  

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሶስተኛ ዲግሪ መመረቅያቸውን የሰሩት  የማኅበራዊ ካፒታል (ዕሴት) ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ለግጭቶች መፍቻ ሊውል እንደሚችል በሚያመለክት የጥናት ሥራ ላይ ነበር።ኢትዮጵያ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ለገጠማት ህወሓት ሰራሽ ህገ መንግስት ከፋፋይ ፖሊሲ እንዴት መውጣት እንደምትችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ለረጅም ጊዜ ስያጤኑት አልነበረም ማለት አይቻልም።የእዚህ የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑ ደግሞ ከሁለት አስር አመታት በላይ ለተሸረቡ ግጭቶች የቅርብ ክትትል ለማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጠው መልካም ዕድል ነው።

የኮሚሽኑ አላማ እና ረቂቅ ስንመለከት እጅግ ቅን የሆነ ማንም ጤነኛ የሆነ ሰው አቃቂር ሊያወጣበት የሚገባ አይደለም።ይህ ማለት ለምን ተተቸ ለማለት አይደለም።መተቸት እና ቀድሞ በማጥላላት ላይ የተመሰረተ ዘመቻ መክፈት ይለያያሉ። የተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገመንግስት አንቀጽ 55(1) መሰረት አፅድቆ ለፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ለፊርማ የቀረበው የመመስረቻ ረቂቅ አዋጅ መግቢያ ላይ የኮሚሽኑ መመስረት አስፈላጊነት ሲገልጥ የሚከተሉትን ምክንያቶች በዋናነት ያስቀምጣል : -

  •  ፌዴራል ስርዓቱን በማጠናከር እየተገነባ የመጣውን የብሔር ብሔረሰብ እና ህዝብ ብዝሃነት ማጎልበት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
  • በክልሎች የአስተዳደር ወሰንራስን በራስ ማስተዳደርና በማንነት ጥያቄዎች ዙርያ በተደጋጋሚ የሚታዩ ችግሮችን አገራዊ በሆነና በማያዳግም መንገድ መፍታት በማስፈለጉ፣
  • ከአስተዳደር ወሰን ጋር ተያይዞ የሚነሱ ውዝግቦች በተለያዩ ብር፣ ብረሰቦችና ህዝቦች መሃል የቅራኔ ምንጭ መሆናቸውን በመገንዘብ፣
  • ከአስተዳደር ወሰን ጋር ተያ የሚነሱ ግጭቶች ከተኛ ለሆነ አለመረጋጋት መንስዔ በመናቸው፣ ለነዚህ ችግሮች ገለልተኛ በሆነ፣ ከፍተኛ ሞያዊ ብቃት ባለውና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍትሄ ማፈላለግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
የኮሚሹ ዋና ዓላማ ላይ ረቂቁ እንዲህ ያስቀምጠዋል።

የኮሚሽኑ ዓላማ
ኮሚሽኑ አሳታፊ፣ ግልጽ፣ አካታችና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከአስተዳደር ወሰኖችራስን በራስ ማስተዳደር እና ከማንነት ጋር የተያይዙ ግጭቶችንና መንስኤያቸውን በመተንተን የመፍትሄ ሃሳቦችን ለህዝብ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአስፈጻሚው አካል ማቅረብ ነው።

የህወሓት አፍቃሪ እና የጥቅም ተጋሪዎች የኮሚሽኑን መመስረቻ ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ለምን አስፈራቸው ?

የህወሓት አፍቃሪዎች እና የጥቅም ተጋሪዎች የኮሚሽኑን መመስረት የሚቃወሙበት ሶስት ምክንያቶች አሉ። የመጀመርያው ምክንያት የሽፋን ምክንያት ሲሆን የቀሩት ሁለቱ ግን ድብቅ አጀንዳዎች ናቸው። የመጀመርያውና አሁን በአደባባይ የኮሚሽኑን መመስረት የሚቃወሙበትን ምክንያት ሕገ መንግስቱን የሚቃረን ነው፣ የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 39 (የክልሎችን የመገንጠል መብት የተመለከተው) የሚቃረን ነው የሚል ነው።

በዛሬው የምክር ቤት የኮሚሽኑ መስራች ረቂቅ አዋጅ ላይ ድምፅ መስጠት ስነ ስርዓት ላይ የህወሓት ወኪሎች ቁጥራቸው 33 የሚሆኑ እንዲቃወሙ በተሰጣቸው ድርጅታዊ መመርያ መሰረት አዋጁ እንዳይፀድቅ ድምፃቸው ሲሰጡ አብዛኛው የምክር ቤቱ አባላት እጅግ በከረረ መልክ ተቃውመዋል።አንድ የምክር ቤት አባል የህወሓት አባላት ለሰጡት አስተስያየት ሲመልሱ -
''ሰዎች በእስር ቤት ሲሰቃዩ ሕገ መንግስት ተጣሰ ብለን የማናውቅ ዛሬ ሕገ መንግስቱን የማይፃረር ጉዳይ ላይ የምክር ቤቱን ደረጃ የማይመጥን ንግግር መናገር አይገባም'' ብለዋል።
ሌላ የምክር ቤት አባልም ''የእዚህ ኮሚሽን መመስረት ይህ ምክር ቤት ላለፉት ዓመታት ለሰራው ስህተት አንዱ የማስተካከያ ነጥብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ህዝብም ያለንን ክብር የምንገልጥበት መልካም አጋጣሚ ነው '' ብለዋል።

የኮሚሽኑ መመስረቻ ረቂቅ አዋጅ መፅደቅ የህወሓት አፍቃሪዎች እና የጥቅም ተጋሪዎችን ያሳሰቧቸው ሁለት ድብቅ ምክንያቶች ህወሓት ለመስፋፋት ከያዘችው ድብቅ ዓላማ አንፃር በእዚህ ኮሚሽን አማካይነት የግጭት ቦታዎች ለምሳሌ የወልቃይት፣ራያ አካባቢ ሕዝብ ችግሩን በእራሱ ለመፍታት ከተነሳ በአካባቢው ላይ ህውሃት ላለፉት አርባ ዓመታት የሰራቸው ወንጀል ሕዝብ ውስጥ ሊገለጥ መሆኑ እና ሕዝብ ሲታረቅ ህወሓት እንደምትንሳፈፍ ስለገባት ሲሆን ሁለተኛው ድብቅ ምክንያት ደግሞ ህወሓት በቅርቡ ወደ የመጨረሻ ተስፋ የቆረጠ መንገድ ማለትም በእየክልሉ በውክልና የለኮሰችውን ግጭት ወደ አንድ መድረክ አምጥቶ አጠቃላይ ቀውስ ለመፍጠር በዝግጅት ላይ እያለች ባለበት ሰዓት በመሆኑ ነው። ይህ በእንዲህ እያለ ህወሓት በተለይ የአክራሪ ብሔረተኞችን በማስተባበር በኮሚሽኑ መመስረት ላይ ተቃውሞ በማስተባበር ከዶ/ር አብይ የለውጥ ኃይል ጋር ለመጋጨት አመቺ የመጫርያ ነጥብ ያገኘች መስሏት ላይ ታች ብትልም ከአክራሪ ብሄርተኞች ቀርቶ እራሷ ውስጥም በቂ ድጋፍ አለማግኘቷ ህወሓት ምንም ተፅኖ የመፍጠር አቅም ላይ አለመሆኗን ከምን ጊዜም በላይ ፍንትው ብሎ የታየበት ታሪካዊ ወቅት ሆኗል።

ቅንነት ያድናል

የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን መስራች ረቂቅ አዋጅ ሃሳቡም ሆነ የአዋጁ ይዘት (ከስር ሙሉ ረቂቅ አዋጁን ያገኙታል) ቅንነት የተላበሰ ብቻ ሳይሆን ማንንም ጎሳ ያማያጠቃ፣ይልቁንም ኢትዮጵያ ከገባችበት ህወሓት እና መሰሎቹ ውላጅ የጎሳ ፖለቲካ ግጭት ቀስ በቀስ ችግሮቹን እየነቀሰ የመፍታት መልካም እና ወሳኝ ጅማሮ ነው። ቅንነት ያልጎደለው እና ኢትዮጵያን ከክፍለ ዘመን ወደ ክፍለ ዘመን በሕብረት እንድትሻገር የሚፈልግ ሁሉ ከቀውስ እና ከግጭት የመውጫውን መንገድ መፈለጉ ሊያስከፋው አይገባም።ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ውስጥ ሕዝብ ከህዝብ በማጋጨት የተካኑ ባለሙያዎች አሰልፎ፣በከፋፋይ ፖሊሲ አስደግፎ ሕዝቧን ሲያባላ የኖረ የሙሉ ሰዓት ተከፋይ እና ቢሮ ከፍቶ የሚሰራ የደህንነት አካል የቀለድባት ሀገር የችግሯን ሰንኮፍ ደረጃ በደረጃ ለመንቀል ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማንነት እና የአስተዳደር ወሰኖችን ችግር ከባህል፣ከፖለቲካ፣ከታሪካዊ እና መልከአ ምድራዊ ሁኔታዎች አንፃር ሁሉ የሚያጠኑ ባለሙያዎች የተካተቱበት፣ መመስረት እና ምክረ ሀሳብ ለውሳኔ ሰጪው አካል የሚያቀርብ ኮሚሽን መመስረቱ የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆነ እና ነገን አሻግሮ ለሚመለከት ሁሉ እጅግ አስደሳች የመንግስት ክንውን ነው።

ከእዚህ በታች ኮሚሽኑን ለመመስረት የወጣውን አዋጅ ሙሉ ረቂቅ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

አስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋየወጣው አዋጅ
አዋጅ ቁጥር -----/2011
አስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋየወጣ አዋጅ
የፌዴራል ስርዓቱን በማጠናከር እየተገነባ የመጣውን የብሔር ብሔረሰብ እና ህዝብ ብዝሃነት ማጎልበት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
በክልሎች የአስተዳደር ወሰንራስን በራስ ማስተዳደርና በማንነት ጥያቄዎች ዙርያ በተደጋጋሚ የሚታዩ ችግሮችን አገራዊ በሆነና በማያዳግም መንገድ መፍታት በማስፈለጉ፣
ከአስተዳደር ወሰን ጋር ተያይዞ የሚነሱ ውዝግቦች በተለያዩ ብር፣ ብረሰቦችና ህዝቦች መሃል የቅራኔ ምንጭ መሆናቸውን በመገንዘብ፣
ከአስተዳደር ወሰን ጋር ተያ የሚነሱ ግጭቶች ከተኛ ለሆነ አለመረጋጋት መንስዔ በመናቸው፣ ለነዚህ ችግሮች ገለልተኛ በሆነ፣ ከፍተኛ ሞያዊ ብቃት ባለውና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍትሄ ማፈላለግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገመንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
1 አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ‹‹ አስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅቁጥር --------/211›› ተብሎሊጠቀስይችላል፡፡
2 ትርጓሜ
1/ የአስተዳደር ወሰንማለት ራስን በራስ ማስተዳደርከማንነት ጥያቄ እና ከሌሎች ተመሳሳይ ክስተቶች ጋር በተያይዘ የሚነሱ የወሰን ጉዳዮች ነው
2/ ኮሚሽንማለት በዚህ አዋጅ አንቀፅ 3(1) መሰረት የተቋቋመ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጥያቄ ጉዳዮች ኮሚሽን ነው፡፡
3 መቋቋም
1/ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን (ከዚህ ኋላ ኮሚሽን እየተባለ የሚጠራ) በዚህ አዋጅ ተቋሟል።
2/ ኮሚሽ የአስተዳደር ወሰንራስን በራስ ማስተዳደ ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጽህፈት ቤት እና አስፈላጊ ሰራተኞችይኖሩታል፡፡
3/ የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል፡፡
4 የኮሚሽኑ ዓላማ
ኮሚሽኑ አሳታፊ፣ ግልጽ፣ አካታችና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከአስተዳደር ወሰኖችራስን በራስ ማስተዳደር እና ከማንነት ጋር የተያይዙ ግጭቶችንና መንስኤያቸውን በመተንተን የመፍትሄ ሃሳቦችን ለህዝብ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአስፈጻሚው አካል ማቅረብ ነው።
5 የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር
ኮሚሽኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
1/ ከአስተዳደራዊ ወሰኖች አከላለልራስን በራስ ማስተዳደር እንዲሁም ከማንነት ጥያቄ ጋር የተገናኙ ማናቸውንም ችግሮችንና ግጭቶችን በጥናት ለይቶ አማራጭ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤ ፖርት ያቀርባል
2/ በህዝቦች እኩልነትና ፈቃድ ላይ የተመሰረት አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር ለማድረግ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ማሻሻያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክረ ሃሳቦችን ያቀርባል
3/ አስተዳደራዊ ወሰኖች በቀጣይነት የሚወሰኑበትንና የሚለወጡበትን መንገድ በተመለከት አግባብነት ያላቸውን ህገ-መንግስታዊ መርህዎች ያገናዘበ፣ ግልጽና ቀልጣፋ ስርትወይም የህግ ማሻሻያ እንዲዘረጋ ጥናት በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክረ ሃሳብ ያቀርባል
4/ ጎልተው የወጡና በፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በፌዴራል መንግስት የሚመሩለትን የአስተዳደራዊ ወሰን ውዝግቦችን ርምሮ ውሳኔ ሃሳብ ለጠቅላይ ሚኒስት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል
5/ ከአስተዳደራዊ ወሰኖች ጋር በተያያዘ የተነሱ ግጭቶች ተፈተው፣ በአጎራባች ክልሎች መሃከል ያለው መልካም ግንኙነት የሚታደስበትና የሚጠናከርበትን መንገድ ያመቻቻል
6/ በቀጣይነት አስተዳደራዊ ወሰኖች የግጭት መንስዔ እንዳይሆኑ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤ ክረ ሃሳብ ያቀርባል
7/ አስተዳደራዊ ወሰኖችና አካባቢያቸው አስተማማኝ ሰላም የሰፈባቸው የልማትና የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሂድባቸው እንዲሆኑ አስተዳደራዊ ወሰኖች የተመለተ የፖሊሲ ማእቀፍ ያመነጫል
8/ የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮችን በተመለከት የህዝብ አስተያየት ይሰበስባል

9/ ጉዳዮ ከሚመልከታቸው የክልልና የፌደራል የስራ ሃላፊዎች፣ የፖለቲካ ቡድኖች፣ እንዲሁም ሌሎች ባላድርሻ አካላት አሰትያየትና ለጥናቱ የሚሆን ግብዐት ይሰብስባል
10/ ከህዝብ ግብዐትና አስተያየት የሚሰበሰብበትን አካሄድ የሚያሳይ፣ ሂደቱ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ መሆኑን የሚያረጋገጥ ስትራትጂና ዝርዝር እቅድ ያዘጋጃል።
6 የአስተዳደር ወሰን የማንነት ጥያቄዎች
ማንኛውም የአስተዳደር ወሰን ውሳኔራስን በራስ ማስተዳደር የማንነት ጥያቄ በኮሚሽኑ ተጠንቶ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርቦ እልባት ያገኛል፡፡
7 ኮሚሽን አባላት አሰያየም
1/ የኮሚሽኑ አባላት ቁጥር በመንግስት የሚወሰን ይሆናል፡፡
2/ በኮሚሽኑ አባል ተደርገው የሚሰየሙ ግለሰቦች በስነ ምግባራቸውበትምህርት ዝግጅታቸውበስራ ልምዳቸው በማህበረሰቡ የተመሰገኑና መልካም ስም ያተረፉ ይሆናሉ፡፡
3/ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ምክትል ሰብሳቢ እና ሌሎች አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሰየማሉ
8. ኮሚሽኑ ስብሰባ
1/ ኮሚሽኑ መደበኛ ስብሰባ በየአስራ አምስት ቀኑ ይካሄዳልሆኖም እንደየ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡
2/ ኮሚሽኑ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከተገኙ ምልዓተ-ጉባኤ ይሆናል፡፡
3/ ኮሚሽኑ ምክረሃ ሳቦች በስምምነት ያልፋሉ፡፡
4/ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ኮሚሽኑ የራሱን የስብሰባሥነ-ሥርዓት ደንብ ሊያወጣይችላል፡፡
9 የሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር
የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፡-

1/ አጠቃላይ የኮሚሽኑን የስራ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል
2/ ለኮሚሽኑ አስፈላጊ የሆኑ የድጋፍ ሰጭ ሠራተኞችንይመድባል
3/ ኮሚሽኑን በመወከል ከሌሎች አካላት ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡
10 የምክትል ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር
የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ፡-
1/ ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ ሰብሳቢዉን ተክቶ ይሰራል
2/ በሰብሳቢው የሚሰጡትንተግባራትይፈጽማል፡፡
11. የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት
1/የኮሚሽኑ ዋና ጽህፈት ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል፡፡
2/ የኮሚሽኑ ጽ/ቤት በመንግስት የሚመደብ የጽ/ቤት ሃላፊ ይኖረዋል፡፡
12 የጽህፈት ቤትስልጣንናተግባር
የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤቱ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
1/ ለኮሚሽኑ አጠቃላይ የአስተዳደርና ፋይናንስ አገልግሎት ይሰጣል
2/ ለኮሚሽኑ የምርምርና ጥናት አገልግሎት ይሰጣል
3/ ለኮሚሽኑ የህዝብ ተሳትፎና ምክክር መድረኮችን የሎጅስቲክስ ድጋፍ ይሰጣል
4/ የኮሚሽኑን ቃለ ጉባኤዎችን፣ ውሳኔዎችንና ሰነዶችን አጠናቅሮ ይይዛል
5/ የኮሚሽኑን ስራ ለማሳለጥ አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል።
13 የጽህፈት ቤት ሃላፊ
1/ የጽ/ቤቱን ሰራተኞች እናሃ ብትያስተዳድራል፡፡
2/ ለኮሚሽኑ አባላት የሚሰጡትን የሴክሪታሪያል እና ሎጅስቲክ ድጋፎች በበላይነት ይመራል፡፡
3/ የኮሚሽኑ እቅድና በጀት ያዘጋጀል በኮሚሽኑ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
4/ ጽ/ቤቱን በመወከል ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡
14 የኮሚሽኑ ገለልተኝነት

ሚሽኑ ስራውን በነፃነትና በገለልተኝነት ያከናውናል።
15 የኮሚሽኑየሥራ ዘመን
1/ የኮሚሽኑ አባላት የስራ ዘመን እስከ እስከ 3 ዓመት ነው።
2/ በዚህ አንቀፅ ዑስ አንቀ(1) የተጠቀሰው ቢኖርም የኮሚሽኑ የስራ ዘመን እንሁኔታው ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊያራዝመው ይችላል።
16 የመተባበር ግዴታ
ማንኛውም ሰው ኮሚሽኑ በዚህ አዋጅ የተሰጠውን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ለሚያቀርበው ማንኛውም ህጋዊ እንቅስቃሴ ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
17 ጠቋሚዎችና ምስክሮችን ስለመጠበቅ
1/ ማንኛዉም ሰው በኮሚሽኑ ፊትቀርቦ በሚሰጠው ቃል መሰረት ክስ ሊመሰረትበት እንደዚሁም የሰጠው ቃል በእርሱ ላይ ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብበት አይችልም፡፡
2/ ለጠቋሚዎችና ለምስክሮች ጥበቃ ለማድረግ የወጣ ሕግ ለኮሚሽኑ ቃላቸው እና መረጃ ለሚሰጡሰዎችም ተግባራዊ ይሆናል፡፡
18 በጀት
የኮሚሽኑ በጀት በመንግስት ይመደባል፡፡
19 ስለሂሳብ መዛግብት
1/ የኮሚሽኑ ጽ/ቤት የተሟላና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል፡፡
2/ የኮሚሽኑ የሂሳብ መዛግብት እና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ፡፡
20 ደንብና መመሪያ የማውጣትሥልጣን
1/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
2/ ኮሚሽኑ ይህንን አዋጅና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የወጡ ደንቦችን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡

21 አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸናይሆናል


አዲስ አበባ ..... ቀን 2011 .

ሳህለወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...