ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, July 5, 2012

ሁል ጊዜ የማትረሳኝ ቃል አለች ''ብሔራዊ ጥቅም!'' (National Interest) የምትል::


ሰሞኑን አንድ ግለሰብ በ ባህር ማዶ ካሉት የመገናኛ ብዙሃን በ አንዱ እና በ ዝነኛው ''ኢሳት'' ቀርበው በሃገር ቤት መደረግ ካለበት ትግል ውስጥ አንዱ ''በ ኢትዮዽያ አየር መንገድ ላይ የ ኢኮኖሚ እቀባ ማረግ ይገባል።ሰዎች በ አየር መንገዱ እንዳይጠቀሙ ማድረግ ፤ እኛም መሳፈር የለብንም ወዘተ'' ሲሉ ተደምጠዋል።
 ሆኖም ግን በ ፖለቲካው ዓለም ሁል ጊዜ የማትረሳኝ ቃል አለች ''ብሔራዊ ጥቅም!'' (National Interest)  የምትል:: ብሔራዊ ጥቅም ለድርድር የሚቀርብ አለመሆኑን ነው ሳይንሱ የሚያስተምረን::

 የ ''ያ ትውልድ'' ፖለቲካን (የ መለስ እና የ ኢሳያስ ትውልድ ጨምሮ )  ከምንወቅስበት ምክንያት አንዱ' ብሔራዊ ጥቅምን እና የ ሃገር ገጽታን ደምስሶ ምን አይነት ኢትዮዽያን እየናፈቅን ነው?' ለሚለው ፈታኝ ጥያቄ መመለስ አለመቻሉን ነው።

 በ  'ኢሳት' ጋዜጠኛ ስለ ጉዳዩ ትክክለኛነት ማብራርያ እንዲሰጡ ደጋግመው ሲጠየቁ ''የ ኢትዮዽያን አየር መንገድ በኪሳራ እንጣለው'' ባዩ ሰውዬ አጥጋቢ መልስ መስጠት ሲያቅታቸው ተመልክቻለሁ።

ግለሰቡ ከ እዚህ በፊት ብዙ በጎ ሃሳቦች ሲሰጡ እና የ ሃገር ፍቅራቸውን ሲገልጹ አይቻለሁ፣  ሰምቻለሁ። እዚች ላይ ግን ለእኔ አልገባህ አለኝ ወይም እንዳይገባኝ አርገው ነው የነገሩኝ።
የ ኢትዮዽያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነኩ ሂደቶች በሙሉ ሁለት ሶስት ጊዜ መከለስ አለባቸው። እረጅም እድሜ ለ ኢትዮዽያ አየር መንገድ!




5 comments:

Anonymous said...

Awo gen teyakew yemihonew ;ewnet ye Ethiopia airlines ye behzrawin tekem eyastebeke new???
Wodedenem telanem ayer mengedu tedakeme malet WOYANE bekedaminet tedakeme malet new.Woyane tedakmo wodeke malet degmo,agerachin netsa wotach endihum ager alba kemehon endenalen malet new.

Anonymous said...

Ye sewyewn sim lemin alteqeskm?Sewyew Elias Kifle new. Yanesahewin hasab betam edegifalehu. Elias eko le Shabia yemisera le Ethiopia yeqome yemimesl achenabari sew new. Ahun degmo wist wistun ESAT lay were eyaswera new. Weyane ashebari blotal gin teteqmobet sibeqaw new. Lehulum neqe mebal yalebet sew new.

Anonymous said...

Ye sewyewn sim lemin alteqeskm?Sewyew Elias Kifle new. Yanesahewin hasab betam edegifalehu. Elias eko le Shabia yemisera le Ethiopia yeqome yemimesl achenabari sew new. Ahun degmo wist wistun ESAT lay were eyaswera new. Weyane ashebari blotal gin teteqmobet sibeqaw new. Lehulum neqe mebal yalebet sew new.

Anonymous said...

የሚገርም ነው።
የ ኢሳት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ለ ሴቷ ተጠያቂ ያቀረበው ጥያቄ አለመመለሱን ሲገነዘብ መልሶ ለ ኤልያስ ያቀረበው እንዲህ የሚል ጥያቄ ነበር-''የኢትዮዽያ አየር መንገድ በ ኢህአዴግ ዘመን የመጣ ድርጅት አይደለም በሃይለ ስላሴም ሆነ በ ደርግ ዘመን የነበረ ብዙ ኢትዮዽያውያን እንደ ቅርስ የሚያዩት ድርጅት ነው እና ዛሬ እናንተ ተነስታችሁ እቀባ እናርግ ስትሉ ልክ አይደለም ለሚላች ሁ ምን መልስ አላችሁ?'' ኤልያስ ለማምለጫ የተጠቀመበት መልስ ''ወደፊት በሰፊው እንመጣበታለን'' የሚል ነው። ይህን ''ሃገር እናፍርስ'' ኤልያሳዊ አስተሳሰብ ማንም የተቃዋሚ ሃይል አይደግፍም። በ ኢህአዴጋዊ ድርጅቶች ላይ ለምሳሌ ኤፈርት እና የ ልጅ ልጆቹን ድርጅቶች እንጂ አየር መንገዳችንን ለቀቀቅ አርግልን ኤልያስ።

Anonymous said...

Ethiopian Airlines was a sponsor to DALLAS Ethiopian sport festival.

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...