ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, April 24, 2012

ምስጋና


ለተከበራችሁ የ ''ጉዳያችን '' ጡመራ ገፅ  አንባቢዎች በተለያየ የ መገናኛ ዘዴ ለሰጣችሁኝ አስተያየት ሁሉ አመሰግናለሁ።
እስካሁን ድረስ ከ ሰላሳ አምስት  በላይ ከ ሆኑ ሀገሮች (ከኢትዮጵያ፣ደቡብ አፍሪካ፣ኬንያ፣ኡጋንዳ፣እስራኤል፣ጀርመን፣እንግሊዝ፣ኢጣልያ ፣ሩስያ እና ስዊድንን አካቶ)  እያነበቡ መሆኑን ለመከታተል ችያለሁ።

ከ አንባቢ ቁጥር አንፃር ገና ልጅ መሆኑን እረዳለሁ።ሆኖም ግን በ አንድ ወር ውስጥ ብቻ  እስከ አንድ ሺ አንባቢን ይዞ እስካሁን በድምሩ ከ 3,800 በላይ አንባቢዎች እንደጎበኙኝ   ልረዳ ችያለሁ።በእርግጥ ለ አንዳንድ የ ጡመራ መድረኮች ይህ ብዙም ላይገርማቸው ይችላል።እኔ ግን ለማስተዋወቅ ያደረግሁት ጥረት አንፃር እና ካለምንም  መረጃ ''ጉግል'' ገብተው ''gudayachn'' የምትለውን ቃል ብቻ በመፃፍ ያነበቡትን ከመመልከት አንፃር መሆኑን ልብ በሉልኝ።እናም  ስላነበባችሁልኝም አመሰግናለሁ።

በ እዚህ የ መረጃ ዘመን ''የ ተደበቀ የማይታወቅ፣የተሰወረ የማይገለጥ የለምና'' ሃሳብን በ ጡመራ መልክ ማስነበብ አንድ ሰው በ አስር ጣቶቹ ተጠቅሞ ጊዜውን ሰውቶ የሚሰራው  በጣም ትንሽ ግን ትልቅ ግንዛቤ የሚፈጥር ሥራ እንደሆነ አምናለሁ።
በ አንዳዶቹ ፅሁፎች ላይ ፖለቲካዊ ይዘት በመያዛቸው ብዙ ሰዎች  በፅሁፎቹ  ቢደሰትበቱበትም  ሃሳብ ለመስጠት ሲሳቀቁ ተገንዝብያለሁ። በተለይ ከ ሀገርቤት ''አኖንመስ'' ብሎ መስጠት በራሱ የሚያስፈራቸው ግን ሃሳባቸውን የምረዳላቸው ብዙዎች አሉ።

ሀገር  በ አንድ ሰው ሃሳብ እና ትዛዝ ሊሻሻል  አይችልም። የ ብዙ ሰዎች ሃሳብ አንድ የተሻለ ነገር ማሳየቱ ብሎም ሌላ ያልታየ መንገድ ማመላከቱን  የተማርነው ከምንኖርባት ዓለም ያለፈ ታሪክ ነው።በ አንድ የብሎግ ጥናት ላይ ግብፅ ብቻ በ ሺህ የሚቆጠር የ ጡመራ መድረክ እንዳሏት ማንበቤን አስታውሳለሁ ። ይህን ያህል የ ሃሳብ መንሸራሸር በራሱ የ ጤናማ እድገት ምልክት ይመስለኛል። ''ተናጋሪው አስር ሰሚውም አስር'' እንዲሉ በቂ የመውያያ መድረክ  ለሌላት እና የመገናኛ ብዙሃኗ በ አይነቁራኛ ለምትጠበቅ ሀገራችንማ  ስንት ሺ የ ጡመራ መድረክ ያስፈልጋት ይሆን?

ለሁሉም ግን መማማር አንድም በ ቃል ሌላም በፅሁፍ ነውና፣ ሰው ካልፃፈ ወይም በቃሉ ካልተናገረ (ሃሳቡ እረባም አልረባም)  ወደ ሁለተኛ ሰው ወይንም ሰዎች ሊተላለፍ የሚችልበት መንገድ ለጊዜው ስለሌለ (በምልክት የተግባቡትን አልዘነጋሁም) ይህንኑ የመፃፍ መንገድ ተጠቅመን መማማር ግዴታ የማይሆንበት ምክንያት ያለ አይመስለኝም።
አሁንም በድጋሚ ለመከራችሁኝ፣ሃሳባችሁን ላካፈላችሁኝ፣ ላነበባችሁልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ እግዝያብሄር ይስጥልኝ ።
አበቃሁ
ጌታቸው
ኦስሎ


1 comment:

Sahle said...

Dear Gecho,
Even if a number of people are reading your blog. DONOT EXPECT MUCH COMMENT FROM DIASPORA BECOUSE EVERY BODY IS BUSY TO COMMENT.

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...