ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, December 7, 2020

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በኬንያ ጉብኝት ያደርጋሉ።Gudayachn Exclusive - In this week,Ethiopian PM Abiy Ahmed will visit Kenya.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ እና ፕሬዝዳንት ኡሁሩ 


ጉዳያችን ዜና - 
ኅዳር 28/2013 ዓም (ደሴምበር 7/2020 ዓም)
=======
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በያዝነው ሳምንት አጋማሽ ማለትም በመጪው ረቡዕ ወደ ኬንያ እንደሚሄዱ እና ጉብኝት እንደሚያደርጉ ጉዳያችን ሰምታለች።ይህ ጉብኝት በትግራይ የሕግ ማስከበር እርምጃ ከተጀመረ ወዲህ የመጀመርያው የውጪ ጉዞ ነው የሚሆነው።በእዚህ ጉዞ ላይ ከኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን ሁለቱ መሪዎች በሞያሌ  የተከፈተውን አዲሱን የሁለቱን ሀገሮች መንገድ ይመርቃሉ።መንገዱ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል በሚኖረው የመሬት ላይ ጉዞ አንድ ቦታ ብቻ የሚቆምበት እና ከእዚህ በፊት ከነበራቸው ግንኙነት በተሻለ መንገድ የሁለቱንም ሀገሮች ህዝቦች ግንኙነት እንደሚያቀላጥፍ ታምኖበታል።

በሌላ በኩል ሁለቱ መሪዎች በእዚህ ግንኙነታቸው በገንባት ላይ ያለውን ለኢትዮጵያ እና ለደቡብ ሱዳን አገልግሎት እንዲሰጥ የታሰበውን የላሙ ወደብ ሥራ ይጎበኛሉ።የላሙ ወደብ የኬንያ የባህር ዳር ወደብ ስትሆን ከሞምባሳ ወደብ በተሻለ ለኢትዮጵያ እና ለደቡብ ሱዳን ቅርበት ያላት ወደብ ነች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በመጪው ረብዕ በቀጥታ የሚሄዱት ወደ ሞያሌ ሲሆን፣የኬንያው ፕሬዝዳንትም አቀባበል የሚያደርጉላቸው በእዚችው በመርሳ ቤት ክፍለሀገር ውስጥ በምትገኘው የኬንያ ዝነኛ የወደብ ከተማ ነው።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የ1ነጥብ 2 ሚልዮን ዶላር ገንዘብ ድጋፍ ወደ አዲሱ የኬንያ ወደብ እና ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚዘረጋ በሚጠበቀው የባቡር መስመር ግንባታ የመጀመርያ ጥናት የሚውል አግኝታለች።የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ የወደቡን ሁኔታ ለመገምገም አንዱ አጋጣሚ እንደሚሆን ታምኖበታል።ኢትዮጵያ እና ኬንያ በአሁኑ ጊዜ እጅግ የሰመረ ግንኙነት ካላቸው ሀገሮች ውስጥ የሚመደቡ ሀገሮች ናቸው።በህወሓት ዘመን ኬንያን ጨምሮ የብዙ ጎረቤት ሀገሮች ጭንቀት ከምር የማያምኗቸው ባለስልጣናት በአዲስ አበባ ቤተ መንግስት መኖር ነበር።

ጉዳያችን 
===========================
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ የሚችሉበት አዲስ ቴክኖሎጂ ጉዳያችን ማስተዋወቅ ጀምራለች።
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...