ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, December 12, 2020

ትግራይ ወደ አዲስ እና የተሻለ ሕይወት ጉዞ ጀምራለች።የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቤኔ በ24 ሰዓት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባል።በትግራይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ሥራ ይጀምራሉ።



In Ethiopia,Tigray region interim Government Cabinet will start its function within 24 hours.On Monday all civil servants of the region will be back to work.Government office will be open. 
------------------------------------
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቤኔ ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ አስታወቁ።የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በትግራይ ክልል ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ከሚለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ለህዝብ ክፍት እንዲሆኑና ነዋሪዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ እለት ተለት እንቅስቃሴያቸው እንዲመለሱ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ የክልሉን ካቤኔ ማዋቀሩን የገለጹት ዶክተር ሙሉ፤ ካቤኔው ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ አረጋግጠዋል።

በህወሃት ጁንታ ተግባር ተደናግጠው ስራ ያቆሙ የመንግስት ሰራተኞችም ከፊታችን ሰኞ ጀምረው ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ዶክተር ሙሉ አሳስበዋል።

በተጠቀሰው ቀን ወደ ስራ ገበታው የማይመለስ የመንግስት ሰራተኛ ካለ በገዛ ፈቃዱ ስራውን እንደለቀቀ ተደርጎ እንደሚወሰድም አስገንዝበዋል።

“የመንግስት ሰራተኞች የህዝብ አገልጋይ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ አጀንዳ አስፈጻሚ አይደሉም” ያሉት ዶክተር ሙሉ፤ ሰራተኞች ይህን ተገንዝበው ሙያዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

መቐለን ጨምሮ አብዛኛው የክልሉ ከተሞች ላይ ሰላምና መራጋጋት መፈጠሩን ጠቁመው፤ “የንግድ ድርጅቶች ከነገ ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራቸው መመለስ አለባቸው” ብለዋል።

በተጨማሪም በህጋዊም ሆነ በህገ ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ የታጠቀ ማንኛውም ግለሰብ እስከማክሰኞ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ትጥቁን በአቅራቢያው ለሚገኝ የጸጥታ አካል እንዲያስረክብ ዶክተር ሙሉ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

“ከማክሰኞ በኋላ የቤት ለቤት ፍተሻ እንደሚደረግ ጠቁመው፤ በፍተሻው ትጥቅ የተገኘበት ግለሰብ ሲያጋጥም ተጠያቂ ይሆናል” ብለዋል።

ጊዜያዊ አስተዳዳሩ ክልሉን ወደ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት ላይ የክልሉ ነዋሪዎች የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ - ዋልታ 




ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ የሚችሉበት አዲስ ቴክኖሎጂ ጉዳያችን ማስተዋወቅ ጀምራለች።
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...