ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, July 31, 2020

በዳግማዊ ምንሊክ ላይ የተከፈተው የፅንፈኞች ዘመቻ ሶስት አካላት እና ድብቁ ምክንያታቸው

ዳግማዊ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ 

ጉዳያችን/Gudayachn

የሸዋው ንጉስ ኃይለመለኮት በ1855 ዓም እአአቆጣጠር ከሞቱ በኃላ የሸዋ ሰራዊት በዳግማዊ ቴዎድሮስ ድል ሲሆን የንጉሥ ኃይለመለኮት ልጅ የ11 ዓመቱ ልዑል ሣህለ ማርያም በመያዣነት ወደ ጎንደር በቤተ መንግስት እንዲያድግ ተወሰደ።ታዳጊው ወጣት ሳህለ ማርያም በቤተ መንግስቱ በሚደረጉ ማናቸውም ውድድሮች ሁሉ የላቀ ወታደራዊ ተሰጥኦ እያሳየ እና ሁሉን እያስደመመ  እንደ ቤተሰብ አብሮ አደገ።በመቀጠል አፄ ቴዎድሮስ ልጃቸውን ልዕልት አልጣሽን ዳሩለት።ይህ ሁሉ ሲሆን አፄ ቴዎድሮስ ከልዑሉ ጋር አብረው የመጡትን የሸዋ ጎበዛዝት እንዳይለዩት አድርገው ነበር።

እየቆየ ግን በአፄ ቴዎድሮስ ላይ የሚሸፍተው በዛ በእዚህ ጊዜ ሸዋም ማጉረምረሙ ተሰማ።አፄ ቴዎድሮስ ስለሰጉ ልዑል ሳህለ ማርያም መቅደላ ላይ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተወሰነ።ሆኖም ልዑሉ አብረውት ካሉት የሸዋ ጎበዛዝት ጋር እንዴት እንደሚያመልጥ ሲያሰላስል አፄ ቴዎድሮስ ላይ ያቄመችው የወሎ ገዢዋ ልዕልት ወርቂት ከመቅደላ እንዲያመልጥ ልዑሉን እረዳችው እና አመለጠ።አምልጦም ወደ ሸዋ ገሰገሰ።ወደ ሸዋ ሲሄድ በአፄ ቴዎድሮስ ሸዋ እንዲገዛ የተሾመው በዛብህ ጋዲሎ መንገድ ለመዝጋት ቢሞክርም ልዑሉ ከወሎ ከልዕልት ወርቂት ያገኘው ሸኚ ሰራዊት እና ሸዋ ከገባ በኃላ አልጋ ወራሽነቱን አምኖ የከተተው ሕዝብ ጋር ልዑሉን የምቃወመው አልተገኘም።

ልዑሉ ከድሉ በኃላ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1865 ዓም ምኒልክ ንጉሰ ሸዋ ተብለው ነገሱ።ከቴዎድሮስ በኃላ የነገሱት አፄ ዮሐንስ የምንሊክን ንጉሰ ሸዋነት ያፀደቁት በ12ኛው ዓመት በአዋጅ ''ልጅ ምኒልክን የሸዋ ንጉስ አድርጌ አንግሸዋለሁ።እሱንም እንደኔ ልታከብሩት ይገባል'' በሚል ቃል ነበር።

ምንሊክ በሸዋ ላይ ቢነግሱም ሀሳባቸው ሩቅ፣መንገዳቸው ረጅም እንደሆነ አውቀዋል።ምንሊክ ለነገሮች የማይቸኩሉ ነገር ግን ስልት አዋቂ ነበሩ።የአፄ ዮሐንስ መንገስ አላስበረገጋቸውም።ይልቁንም በሰላም ንግስናቸውን ሳይጣሉ እርሳቸው የሩቅ ዓላማቸው የሆነውን ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ግብ ይዘው ተንቀሳቀሱ።ለእዚህ ሃሳብ ከቤተ መንግስት ስርዓት እስከ አውሮፓውያን ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች በአፄ ቴዎድሮስ ቤተ መንግስት የተመለከቱት ሁሉ ትምህርት ሆኗቸዋል።ስለሆነም ብዙ ችግሮችን በድርድር ለመፍታት ሲሞክሩ የማይሆነውን ደግሞ በጦር ይፈቱት ነበር።

ንጉስ ምንሊክ የኢትዮጵያ ንጉስ ከመሆናቸው በፊት ካደረጉት ትልቁ ጦርነት ወደ ሐረር የተደረገው ዘመቻ ነው።ከእዚህ ዘመቻ ሁለት ዓመት ቀደም ብሎ ግብፆችን ከሐረር ሲወጡ አብዱላሂ ሐረርን እንዲገዛ አመቻችተውለት ነበር።እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጥር 6/1887 ዓም ከእንጦጦ የተነሳው የምንሊክ ጦር ሐረር ግብቶ ከተማዋን አረጋጋት።በመቀጠል ወሎን ካስገበሩ በኃላ የአፄ ዮሐንስ በደርቡሾች መገደል ከተሰማ በኃላ ነው ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ተብለው የነገሱት።

በአፄ ምንሊክ ንግስና ወቅት የኢትዮጵያ ዙርያ ገባ ምን ይመስላል?

አፄ ምንሊክ ከንግስናቸው በፊትም ሆነ በኃላ የሀገር ውስጥን ብቻ ሳይሆን የውጭውን ፖለቲካ እና ወታደራዊ ሁኔታ መረጃ ይሰበስቡ ነበር።ወቅቱ ጀርመን በርሊን ኮንፍረንስ በመባል የሚታወቀው የቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ለመቀራመት ውል የተዋዋሉበት፣ፈረንሳይ በጅቡቲ፣እንግሊዝ በሱዳን በኬንያ እና በሱማሌ ላንድ በኩል ጣልያን በሰሜን ኤርትራ በኩል ሰፍረው ኢትዮጵያን ቀለበት ያስገቡበት ወቅት ነበር።ስለሆነም ንጉስ ምንሊክ የፀጥታ ዞናቸውን ማስፋት እና የኢትዮጵያ ሕዝብ በእነኝህ ቅኝ ገዢዎች እጅ እንዳይወድቅ በዘመነ መሳፍንት የተከፋፈለውን ሀገር ወደ አንድ ንጉሰ ነገስት ግዛት ማምጣት ነበረባቸው።ስለሆነም ከሐረር ዘመቻ ጀምሮ ወደተቀሩት  ደቡባዊ እና ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል እየዘመቱ በኢትዮጵያ ስር መሆናቸውን ማረጋገጥ ነበረባቸው።

አፄ ምንሊክ ፈድራልዝምን አስተዋውቀዋል።

በኢትዮጵያ ንጉሳዊ አስተዳደር ውስጥ በቀጥታ ከንጉሡ ተሹመው የሚሄዱ ሃገረ ገዢዎች የመኖራቸውን ያህል የሀገሩ ገዢዎች በዓመት ግብር ለንጉሡ እየላኩ የቀረው የውስጥ አስተዳደሩን ግን በራሳቸው ገዢዎች የሚተዳደሩ አያሌ ነበሩ።ከእነኝህ ውስጥ በምሳሌነት የጅማውን አባ ጅፋር ማንሳት ይቻላል።አባ ጅፋር የጅማው ገዢ ሲሆኑ በውስጥ አስተዳደራቸው ውስጥ የአፄ ምንሊክ መንግስት ገብቶ አይፈተፍትም ጥፋት ሲኖር ንጉሡ መልክተኛ ወይንም ደብዳቤ እየላኩ ምክር ይለግሱ ነበር።ለምሳሌ በባርያ ንግድ ላይ አባ ጅፋር መሳተፋቸውን የሰሙት ንጉስ ምንሊክ ይህንን እንዲተዉ የሚመክር ደብዳቤ ልከው ነበር።ከእዚህ ውጭ አባ ጅፋር በዓመት የሚላክ ግብር ከማስገባት እና የንጉሰ ነገሥቱን የኢትዮጵያ ንጉስነት እስካወቁ ድረስ ሌላ አስገዳጅ ተግባር የለባቸውም።ይህንን ወደ ዘመናዊ የፈድራል አስተዳደር ስንመነዝረው ብዙ እርቀት የሄደ አሰራር ሆኖ እናገኘዋለን።

በዳግማዊ ምንሊክ ላይ የተከፈተው የፅንፈኞች ዘመቻ ምስጢር

አሁን ባለንበት ዘመን በዳግማዊ ምንሊክ ላይ የተከፈቱ የማጥላላት ዘመቻዎች በተለይ በሶስት አካላት ማለትም ከኦሮሞ ብሔር እንደወጡ ከሚናገሩ፣ ከፅንፈኛው የእስልምና አራማጆች እና ከጀርባ አቀንቃኞች  በኩል ደጋግሞ ይሰማል።ለእዚህ ማጥላላት ምስጢሩ ግልፅ ነው።

  1) ከኦሮሞ ብሔር እንደወጡ ከሚናገሩት 

ዳግማዊ ምንሊክ በዓማራው ብሔር ከሚታወቁት እና ከታቀፉበት የረጅም ጊዜ የስልጣን ዘመን አንፃር ስናይ በኦሮሞ ማኅበረሰብ ውስጥ ለረጅም ዘመናት ያላቸው ገናና ስም እና ክብር ይበልጣል።ምናልባት ይህንን በኢህአዴግ ዘመን ለተወለዱ ልጆች አይረዱት ይሆናል።እውነታው ግን ይሄው ነው።አፄ ምንሊክን እምዬ ምንሊክ ብለው ስም ያወጡላቸው የአዲስ ዓለም ኦሮሞዎች ናቸው እንጂ የአማራ ብሔር ተወላጆች አይደሉም።እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በምንሊክ ስም የሚምሉ የኦሮሞ አባቶች ከአምቦ እስከ ሐረር ብትሄዱ ታገኛላችሁ።በሂደት ደርግ ያለፈው ስርዓት በሚል ኢህአዴግ/ህወሓት የነፍጠኛ ስርዓት እያለ በኢትዮጵያ የቅርቦቹ መስራች አባቶች ላይ የከፈቱት ዘመቻ የኢትዮጵያን አባቶች ክብር እና ዝና ለመሸፈን ብዙ ደክሟል።

ከኦሮሞ ብሔር እንደወጡ የሚናገሩት የዘመኑ የኢህአዴግ/ህወሓት ትውልዶች አፄ ምንሊክን ለማጥላላት የሚሞክሩበት ዋናው ምስጢር ዳግማዊ  ምንሊክ ቀድሞ የነበረውን በኦሮሞ እና በሌላው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማለትም ከደቡብ፣ከሱማሌ እና ከአማራ ጋር የነበሩ የጠበቁ ማኅበራዊ፣ደማዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነት መልሶ እንደብረት የጠነከረ እንዲሆን ያደርጉ በመሆናቸው ነው።ምንሊክ ከጦር ሹማምንቶቻቸው እስከ እንደራሴዎች፣ከአድዋ ዘመቻ እስከ ሐረር ዘመቻ ኦሮሞ ያልተሳተፈበት ትግል አላደረጉም። ይህንን ሲያደርጉ ደግሞ በፍፁም መከባበር፣ኢትዮጵያዊ ስሜት እና አለአንዳች አድልዎ ነበር። ይህ ትስስር በአሁኑ ዘመን ያሉ የብሔር አቀንቃኞች እና ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ለመለየት የሚፈልጉ ፅንፈኞች አልተመቻቸውም።ስለሆነም ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ደግም እንዲዋሃድ ያደረገውን የ19ኛው እና 20ኛው ክፍለ ዘመን ንጉስ ዳግማዊ ምንሊክን ከሕዝቡ ልቦና ለማውጣት እየደከሙ ይገኛሉ።

2) የፅንፈኛ እስልምና አራማጆች ናቸው።

እስልምና በራሱ ፅንፈኛ አይደለም።ነገር ግን በማንኛውም ሃይማኖት ማለትም በክርስትና እና ሌሎች ውስጥ እንዳለው ሁሉ በእስልምና ስም የፅንፍ ፖለቲካ የሚያራምዱ ኃይሎች በኢትዮጵያም በዓለም አቀፍ ደረጃም ይንቀሳቀሳሉ። በኢትዮጵያ ያለው ይህ ኃይል የኢትዮጵያ መከፋፈል ለዓላማው እንደምረዳው ያስባል።ስለሆንም በዋናነት የኢትዮጵያ መስራች አባቶችን የማጥላላት እና ኢትዮጵያ አንድ የምትሆንበት ማናቸውንም ሃሳብ ያወግዛል። በመሆኑም አፄ ምንሊክ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አንድ አድርጎ የሚያየው ኃይል ሁለቱም ላይ ዘመቻ ከፍቷል።

3) የቅኝ ግዛት ህልማቸው የከሸፈባቸው ቂመኛ ሀገሮች እና ኃይሎች 

ዳግማዊ ምንሊክ ከመንገሳቸው በፊት ኢትዮጵያን ዙርያዋን የከበቧት ኃይሎችን ቀድመው በመቅረብ እና የኢትዮጵያን የፀጥታ ቀጠና በማስፋት ቀጥሎም በአድዋ ዘመቻ የማያዳግም ቅጣት በመስጠት ቅኝ ግዛትን የቀበሩት አፄ ምንሊክ ዛሬም ድረስ በአንዳንድ የቅኝ ግዛት ስነ ልቦና ውስጥ ባሉ ሀገሮች ቂም ተይዞባቸዋል። በተለይ የአድዋ ድል ንዝረት ዛሬ ድረስ ለመላው ጥቁር ህዝቦች እና በእጅ አዙር አገዛዝ ለሚማቅቁ ሀገሮች ሁሉ ዛሬ ድረስ መሰማቱ እና ኃይል መሆኑ የአፄ ምንሊክ ታሪክ ላይ በመዝመት  እና የሚዘምቱትን ከጀርባ በመርዳት ቂማቸውን ለመወጣት የሚያስቡ ሀገሮች እና ኃይሎች አሉ።ከእነኝህ ውስጥ አንዷ ከሐረር ያባረሯት ግብፅ ተጠቃሽ ነች።ግብፅ በአፄ ምንሊክ ላይ የሚደረጉ ዘመቻዎችን ከጀርባ በማገዝ ትታማለች።ከግብፅ በተጨማሪ በምኒሊክ የአፍሪካ የነፃነት ፋና ወጊነት ላይ ኢትዮጵያውያንን ከፋፍለው ለማዝመት የሚሰሩ አካላትም አሉ።

ባጠቃላይ ዳግማዊ ምንልክን ለማጥላላት የሚሞክሩ ሶስቱ አካላት ምን ያህል ቢደክሙ እውነተኛውን ታሪክ መቼም ሊደብቁት አይችሉም።ንጉሡ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም በማድረጋቸው የሚመሰክሩላቸው ሕያው ምስክሮች ዛሬም አሉ።እውነተኛ ታሪክ ደግሞ እየደመቀ እንጂ እየደበዘዘ አይሄድም።

ምንሊክ ጥቁር ሰው በድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን 



Tuesday, July 28, 2020

Academician and professional Ethiopians and Norwegian nationals of Ethiopian origin residing in Norway letter to The Norwegian Nobel Committee

27/07/2020 

The Norwegian Nobel Committee, 
The Norwegian Nobel Institute Henrik Ibsens gate 51
0255 Oslo, Norway 

 RE: Nobel Laureate Abiy Ahmed Ali and recent political development in Ethiopia 

Dear Honorable members of The Norwegian Nobel Committee, 

We,a group of Ethiopians and Norwegian nationals of Ethiopian origin residing in Norway, are gravely concerned about the current atrocities and destruction that befell on innocent civilians in Ethiopia that seem to be premeditated and masterminded by extreme ethnic based political groups and individuals. Our group is composed of academicians and professionals with PhD, serving in various Norwegian institutions for a great portion of our professional life. We do not represent a homogeneous interest and therefore stand independent from government, political faction, ideology, economic interest and religious beliefs. However, we are not impartial on Ethiopia’s disintegration and extreme radicalization of the political discourse. 

We write this letter to the Norwegian Nobel Committee to express our concern about the recent political developments in Ethiopia that have been misconstrued as fault lines of Prime Minister (PM) Dr. Abiy Ahmed Ali and his government, while the reality is far from the unfounded accusations. 

We unequivocally condemn the assassination of artist Hachalu Hundessa and leave the investigation to the police and judiciary system in Ethiopia. However, we also believe that the assassination was a well-orchestrated and planned action for a political gain. Since his assassination, the country has seen large-scale unrest, particularly in Shashemene, Agarfa, Arsi Negele, Dera, and Batu (Ziway) in the Oromia Regional State. Innocent people who struggle for their daily lives, who have neither the knowledge of the situation nor the association to any political party or group, have been intimidated, injured, slaughtered, and killed. Properties were burned and vandalized. Thousands were (and are being) displaced and left homeless. The killing of people and vandalizing of properties is aided by a list with the names of individuals and households labeled as “non-locals”. Just after the assassination of the artist, radical groups, individuals and their media outlets began to broadcast calling for unrest and hate speech. Many shreds of evidence of audios, videos, and texts calling for the killing of targeted societies are disseminated through social media. This led us to believe that the whole process of the assassination of the artist and the atrocities that followed are premeditated by radical ethnic based political groups and individuals. 

It is not a secret that PM Dr. Abiy’s government came to office in 2018 with the popular uprising and the political rupture within the ruling party, the Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front (EPRDF), which is an ethnic federalist political coalition. This avoided a looming civil war, averted turmoil in Africa’s second largest populated nation, with large ramifications to the already fragile Horn of Africa and kept the country to function. 

As early as PM Dr. Abiy assumed office, he took bold decisions to release all political prisoners, opened up the political space, and invited all exiled opposition parties (including the most radical political parties and individuals) to the country in an unprecedented manner. His invitation of the previously imprisoned and exiled personalities like Bertukan Mideksa and Daniel Bekele to lead the most contentious Election Board and the Human Rights Commission has created an atmosphere of hope in that he showed his willingness to be scrutinized by outsiders. Equally reputable deed is the fact that he appointed women to half of his government's ministerial posts and the Federal Supreme Court is now led by an independent and high-profile female judge, Meaza Ashenafi, coming from the private sector. The peace with Eritrea and the mediation effort of PM Dr. Abiy in Sudan are vivid examples of what a peacemaker leader can achieve within a short time after assuming office. We believe that these good attributes have earned him the Nobel Prize Peace recognition from your office in 2019. 

While institutional and political reforms are being undertaken, Ethiopia’s accumulated political problems have persisted in the last two years of PM Dr. Abiy’s administration which if not wisely controlled, can lead the situation into an unpredictable and fluid trajectory. The roots of the problems, which we are currently witnessing, are much more complex. It is well-known that Ethiopia is a mosaic of more than 80 ethnic groups. For the last 27 years, since the advent of the EPRDF, the Ethiopian political arena has been dominated by ethnocentric political discourses. The implemented federal system has had ethnic identity and language as its central criteria for self-administration. The way the federal system was exercised severed social fabrics, created intolerance, polarization, mistrust and rift between societies, and thus contributing to the current humanitarian crises and political unrest in the country. This is more so with the youth that are younger than the birth of the ethnocentric politics in the country and those who have been brainwashed by hate and mistrust, who have been the victims of narrow nationalism and myopic political views. In the last two years of Ethiopia’s post EPRDF society, the instability in the country has been characterized by intimidation, killings and destruction of the livelihoods of the minorities in each regional state, more so in Oromia regional state than others. Sadly enough, the loss of lives perpetrated by the hate mongers and the youth vigilantes seem to be the works of organized radical ethnic based political groups and individuals that preached unrest and instability until and unless their vague demands have been met.

Part of the political manipulations is sponsored by ethnocentric radical political parties and individuals whose views preach that the Oromo people -one of the largest ethnic groups in the country- have been dominated and exploited by the century old “neftegna” statehood and the viewpoint that undermines the Oromo personhood. While the struggle has brought the pre-2018 into fruition, by bringing PM Dr. Abiy into office who himself is an Oromo, the cause that the same Oromo people continue to be subjected to the same old institutional and policy discrimination is a farce and without any touch to reality. 

The term “neftegna’’ was excavated out of the long-forgotten memories of past Ethiopian feudal system, minted and spread by the tribalist and division-monger of the previous regime, in its sinister political architecture to create mistrust, intolerance and hate between the two largest ethnic groups-the Amhara and the Oromo- so that its minority regime grips on power as long as it wishes. To some extent, the strategy has worked to prolong the life of the regime for 27 years, but it has also led to a vicious cycle of violence, never ending even after the previous regime is toppled down. Unfortunately, the term “neftegna’ resonates with the youth Oromo population and the radical Oromo politicians who want to incite violence and marginalization of the minorities in the Oromia regional state. The term is tagged on minorities who in fact are no different from the local people. What has evolved over time is the fact that the killings, intimidation and eviction of people in Oromia Regional State include all other ethnic groups who are labeled as “non-locals”. Indeed, one can observe PM Dr. Abiy’s challenges of striking the balance between answering this age-old ethnic question and leading a country of diverse ethnic groups. He is often heard saying that his belief is to ensure the equality of his Oromo ethnic group with the rest of ethnic groups in Ethiopia, and not dominance over others. However, he has been accused of being a sell-out, who cares less for the Oromo people and their cause. 

We value the Norwegian Nobel Institute's decision to award PM Dr. Abiy based partially on his promising engagements and leadership role in building peace and democracy in Ethiopia and setting an analogous pace in the Horn of Africa and beyond. We, therefore, would like the Nobel Institute to understand that the accusations targeted at the PM Dr. Abiy are unfair and based on false narratives. In our opinion, PM Dr. Abiy is working tirelessly to strengthen the unity, peace and security of the country under difficult political circumstances. As stated above, the planning and execution of violence in the Oromia Regional State are premeditated and masterminded by the extreme tribalist political groups and individuals who have been making calls of violence in broad daylight. All the Prime Minister and his government did was to contain the wildfires of ethnic cleansing, which need to be understood within the context of the 27 years of exclusion, divide and rule and ethnic hegemony. The call by certain groups to revoke the Nobel Peace Prize awarded to PM Dr. Abiy is ludicrous by all accounts. We strongly believe that the two years of PM Dr. Abiy’s administration has been a tumultuous journey with so many inherited problems that need a national project of its own, for which the Prime Minister should be supported by the international community. 

Sincerely yours, 

A group of academician and professional Ethiopians and Norwegian nationals of Ethiopian origin residing in Norway 

CC 
    Honorable Ine Eriksen Søreide, Minister of Foreign Affairs 
    Honorable Dag-Inge Ulstein, Minister of International Development 
    Honorable members of the standing committee on foreign affairs and defense Norwegian         
    Civil Organizations 
    2019 Nobel Laureate Abiy Ahmed Ali

Sunday, July 26, 2020

ኢትዮጵያዊነት ምንድነው? ሊመለከቱት የሚገባ እጅግ በጣም ጠቃሚ ውይይት በብ/ጄ/ካሣዬ ጨመዳ እና ሙ/ጥ/ዲ/ን ዳንኤል ክብረት (ቪድዮ)





ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

በኦስሎ፣ኖርዌይ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የበጎ አድራጎት ክፍል ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦ/ ተ/ ቤ/ ክርስቲያን ምእመናንን ሕይወት እና ንብረት ላይ ለደረሰው ጥፋት ከምእመናን ገንዘብ ማሰባሰብ ጀምሯል።ኢትዮጵያውያን እጃቸውን እንዲዘረጉ ተጠይቀዋል።


በእዚህ ስር እርዳታ ሊያደርጉ የሚችሉባቸው አማራጮች ማለትም   
>> እርዳታ የሚያደርጉበት ጎፈንድ-ሚ አካውንት ሊንክ ፣
>> እርዳታ የሚያደርጉበት የቪፕስ ቁጥር፣
>> የቤተ ክርስቲያኗ የባንክ ቁጥር  እና 
>> ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ለምእመናን ያስተላለፉት ትምህርታዊ ጥሪ ቪድዮ ያገኛሉ።

ሰሞኑን በተለይ ኦርቶዶክሳውያንን ላይ ያነጣጠረ፣ በኦሮምያ ክልል በተለይ በአርሲ፣በባሌ እና በሻሸመኔ በሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ሕይወት እና ንብረት ላይ በብሄር እና የፅንፍ ጥላቻ በተነሳሱ የጥፋት ኃይሎች አማካይነት በደረሰ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ እና የንብረት መውደም እስካሁን በስም የተለዩ 52 ምእመናን (ስማቸው እየተለየ ያሉ ስላሉ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል) በአሰቃቂ ሁኔታ በእነኝሁ አረመኔያዊ ድርጊት ፈፃሚዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣የጣልያን እና ፈረንሳይ አካባቢ ሊቀጳጳስ እና የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እና የበላይ ጠባቂ ዛሬ ሐምሌ 19/2012 ዓም በቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤልን ዓመታዊ በዓል (ሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል) ለማክበር ለተሰበሰቡ ምእመናን አስታውቀዋል።ብፁዕነታቸው በእዚሁ መልዕክታቸው በተመሳሳይ መንገድ በሀገረ ስብከታቸው በጣልያን እና በአካባቢው በሚገኙ ምእመናን እስካሁን 70 ሺህ ኢሮ መሰብሰቡን እና በእዚህ ሳምንትም ምእመናን ማዋጣታቸውን መቀጠላቸውን ገልጠዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በጎ አድራጎት ክፍል በእዚህ ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ ለጀመረው የገንዘብ ማሰባሰብ መርሃግብር ምእመናን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በስካንድንቭያን አገሮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ሊቀ ጳጳስ የላኩትን መልእክት ጨምረው  መልእክት አስተላልፈዋል። 

 የተከፈተውን ጎፈንድ-ሚ ሊንክ፣የቪፕስ ቁጥር እና የቤተክርስቲያኑ የባንክ ቁጥር  ከስር ያገኛሉ የበኩልዎን አስተዋፅኦ ያድርጉ።
 

2) የቪፕስ ቁጥር = 616461 

3) የቤተ ክርስቲያኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር = 1203 19 01535

አቡነ ሕርያቆስ ዛሬ  ሐምሌ 19/2012 ዓም ለምእመናን ያስተላለፉት ትምህርታዊ ጥሪ ቪድዮ 






 

Friday, July 24, 2020

ቱርክ፣ ኢስታምቡል የምትገኘው ጥንታዊቷ ሃጊያ ሶፍያ ካቴድራል ከሙዜምነት ወደ መስጊድነት መቀየሩ ውጥረት ፈጥሯል።ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ የጁማ ስግደት ተሰግዶባታል።

ቱርክ፣ ኢስታምቡል የምትገኘው ጥንታዊቷ ሃጊያ ሶፍያ ካቴድራል 

>> ቱርክ ቦታውን ወደ መስጊድ ከቀየረች በኃላ የመጥፊያዋ ዘመን ይጀምራል የሚል ትንቢት እንዳለ በሕዝቧ መሃል የሚናገሩ አሉ።

በቱርክ፣ዋና ከተማ ኢስታምቡል በ6ኛው ክ/ዘመን በቤዛንታይን ስርወ መንግስት ማለትም ከ532 እስከ 537 እኤአ የተገነባች ቤተክርስቲያን ነች።ቤተክርስያኗ በውበቷም ሆነ በሕንፃ ጥበቧ ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈች እና ቱርክ ከመመስረቷ በፊት ቀድማ የተገኘች እና ነቢዩ መሐመድ ከመወለዳቸው በፊት በቱርክም የክርስትና ማዕከል አሻራ ማሳያ ሆና ኖራለች።

ቤተክርስቲያኗ ከዘመነ ሰማዕታት ማብቃት በኃላ በታላቁ ንጉስ ቆስጠንጥኖስ (ደመራ ደምራ የክርስቶስን እውነተኛ መስቀል ያገኘችው የንግሥት ዕሌኒ ልጅ) የገነባት ቤተክርስቲያን ነች።ቤተክርስቲያኗ የኦቶማን ቱርክ ወረራ  በ1453 ዓም እስክትወረር ድረስ በቤተ ክርስቲያንነት አገልግላለች።በክርስቲያኑ ዓለም በትልቅነቱ ከሚጠቀሱት ካቴድራሎች ውስጥ ቀዳሚ መሆኗ የሚነገርላት እና በዩኔስኮም በቅርስነት ተመዝግቦ የሚገኘው ካቴድራል በ1935 ዓም በቱርክ ምንግሥት ውሳኔ መሰረት እና መንግስት የ ''ሴኩላር'' መርህ የሚያከብር መሆኑ በማወጁ  ቤተክርስቲያኗ ወደ ሙዜምነት ተቀይራ ከኖረች ከ85 ዓመታት በኃላ ዛሬ ሐምሌ 17/2012 ዓም (ጁላይ 24/2020 ዓም) የቱርክ መንግስት ወደ መስጊድነት ቀይሮት የመጀመርያው የጁማ ስግደት ተደርጎባታል።

የቱርክ መንግስት ዛሬ ቤተክርስቲያኗን ወደ መስጊድነት ሲቀይር የቱርክ  መስራች አባት ሙስጠፋ ከማል አታቱርካ  (Mustafa Kemal Ataturk) በ1934 ዓም የደነገገውን በፍርድ ቤት ሽሮ ነው ጁማ ያሰገደበት።በቱርክ ለረጅም ጊዜ  ቱርክ መልሳ ቤተክርስቲያኑን ወደ መስጊድነት ከቀየረች የመጥፍያዋ ጊዜ መጀመርያ ነው የሚል ንግርት እንዳለ በሕዝቡ መሃል ሲነገር ነው የኖረው።የቱርክ መስራች አባት ሙስጠፋ ከማል ቤተክርስቲያኑ ወደ መስጊድ መቀየሩን ቀርቶ በሙዜምነት እንዲቀየር ሲያደርጉ ይህንኑ ንግርት ሰምተው ለመሆኑ ወይንም ላለመሆኑ የታወቀ ጉዳይ የለም።

ቱርክ በ1923 ዓም እኤአ 1.5 ሚልዮን የሚሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ከሀገር እንዲባረሩ ከተደረጉ በኃላ የቀሩት 150 ሺህ የሚሆኑ ክርስቲያኖች በ1955 ዓም እኤአ በተነሳው ፀረ-ክርስቲያን እንቅስቃሴ እንደገና ከሀገር በግፍ ተባረዋል።ዛሬ በመላዋ ቱርክ ያሉት ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ከ40 ሺህ አይበልጥም።ሃጊያ ሶፍያ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በተመለከተ የእንግሊዝኛ ዶክመንተሪ ፊልም ከእዚህ በፊት ጉዳያችን ላይ የወጣ ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

በዛሬው የመጀመርያ የጁማ ስግደት በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ 500 ሰዎች ብቻ የተፈቀደላቸው እና የሰገዱ ሲሆን።የቱርክ መንግስትን ውሳኔ የራሷ የቱርክ ዜጎችም የተቃወሙት እንዳሉ ነው የተሰማው።የቱርክ መንግስት ድርጊትም በዓለም አቀፍ ደረጃም ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።ጉዳዩ በተለይ ከግሪክ እና ሩስያ ኦርቶዶክስ አባቶች ከፍ ያለ ተቃውሞ ያስከተለ ሲሆን የግሪክ አቴንስ ሊቀጳጳስ ሌሮንሞስ የዛሬውን ቀን የሃዘን ቀን በማለት ጠርተውታል።ሊቀጳጳሱ በተጨማሪም ዓለም በጅኦ-ፖለቲካ እና ጅኦ-ስትራቴጂ ስር ተደብቆ ጉዳዩን ችላ ማለቱ አሳዛኝ ነው በማለት ለ''ግሪክ ሲቲ ታይምስ'' ገልጠዋል።

በሶፍያ ካቴድራል ዛሬ የጁማ ስግደት ሲደረግ (Photo =CNN)

በመጨረሻም ዛሬ የቱርክ መንግስት ወደ መስጊድነት ቀይሮ ጁማ እንዲሰገድባት ያደረጋት ሃጊያ ሶፍያ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የውስጥ መልክ የሚያሳይ ፊልም ከእዚህ በታች ይመልከቱ።






Wednesday, July 22, 2020

የኖርዌዩ የ2011ዓም እኤአ እልቂት ዛሬ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር በተገኙበት ተዘከረ።

 
Victims of the 22-July terrorist attacks in Norway
በኡቶያ ደሴት ጥቃት ህይወታቸውን ያጡት ፎቶዎች
ጉዳያችን ዜና   

የዛሬ ዘጠኝ ዓመት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሐምሌ 22/2011 ዓም በኖርዌይ የሆነው ልብ የሚሰብር ነበር።ኡቶያ ( Utøya ) በተሰኘው ደሴት በእየዓመቱ ይሰበሰቡ የነበሩ የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ ወጣት ክንፍ አባላት በተሰበሰቡበት አንድርያስ በቭሪክ በተባለ አክራሪ ዘረኛ በጥይት እንደቅጠል እረገፉ።

በእዚህ ስብሰባ ላይ ከ600 ያላነሱ ወጣቶች የሚሰበሰቡበት ሲሆን በእዚህ ጥቃት 77 ወጣቶች በግፍ ተገድለዋል ።ከእነኝህ ውስጥ 69 ወዲያው በደሴቱ ላይ ሕይወታቸው ሲያልፍ ከእንኝህ ውስጥ 33ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነበር።

ዛሬ ሐምሌ 22/2020 ዓም እኤአ የሰማዕታቱን ዝክር ለመዘከር የኖርዌይ ብሔራዊ ቴሌቭዥን በቀጥታ ለሕዝብ እያስተላለፈ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሰራተኛ ፓርቲ ሊቀመንበር እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በደሴቷ ወጣቶቹ በሞቱበት ቦታ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡ ሲሆን ፣የሰማዕታቱ ወጣቶቹ ስም በየተራ እየተጠራ እንዲታወሱ ተደርጎ ነበር።ከእዚህ በተጨማሪ  ንግግሮችም ተደርገዋል።ከንግግራቸው በኃላ የኖርዌይ ቴሌቭዥን ያናገራቸው የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር አርና ሱልበርግ ሲናገሩ ''ይህ ክስተት የዲሞክራሲ እና የምርጫ አስፈላጊነት ምን ያህል ዋጋ ያለው መሆኑንም ለማስተማር እንጠቀምበታለን'' ብለዋል። 

 የኦቶያ ደሴት እኤአ በ1893 ዓም በቀኝ አክራሪ ፖለቲከኛ የንስ ብራትሊ የተገዛ ንብረትነት ከቆየ በኃላ በ1933 ዓም የኖርዌይ ሰራተኛ ማኅበር ኮንፈድሬሽን ገዝቶት የሰራተኛ ማኅበሩ ንብረት መሆን ችሏል።


 ወንጀለኞች ሁል ጊዜ የሚወክሉት እራሳቸውን እና የተበላሸ አእምሮአቸውን እንጂ የወጡበትን ማኅበረሰብ ፈፅሞ ሊወክሉ አይችሉም።በቭሪክም የኖርዌይን ማኅበረሰብ አይወክልም።የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ወንጀሉን የፈፀመው በቭሪክ እድሜ ልክ ተፈርዶበት በእስር ቤት ሲሆን፣በድንገቱ ልጆቻቸውን  እና ወዳጆቻቸውን ያጡ ብዙ ኖርወያውያን ግን ዕለቱን በተሰበረ መንፈስ ያስቡታል።ድርጊቱ የሰውን ዘር በሙሉ የሚያሳዝን አረመኔያዊ ድርጊት ነው። 

በኢትዮጵያም ሰሞኑንም ሆነ ቀደም ብለው በአክራሪ ብሔርተኞች እና ፅንፈኛ የሙስሊም እንቅስቃሴ በሻሸመኔም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ህይወታቸው ለተቀጠፈ ሁሉ የመታሰቢያ መርሃግብር ማዘጋጀት ያስፈልጋል።ክፉ ድርጊት መዘከሩ ያለፈውን ለማሰብ ብቻ አይደለም ለነገውም እንዳይደገም ለማስተማር ጭምርም  ነው።ለሰማዕታቱ ዕረፍተ ነፍስ ይስጥልን።


Monday, July 20, 2020

እስክንድር ነጋ 'የመልክዓ' እስክንድር ደጋሚዎችን አያደንቅም

 እስክንድር ነጋ 
  
ለአስራ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያን ከአስተዳደረው የደርግ ስርዓት በኃላ በኢትዮጵያ የሕትመት ገበያ ውስጥ የአራት ኪሎን ቤተመንግስት የሚያንቀጠቅጥ የኅትመት ውጤቶች ውስጥ  የእስክንድር ነጋ  ኢትዮጲስ ጋዜጣ አንዷ ነበረች።በእየሳምንቱ ጋዜጣዋ ይዛ የምትወጣው ዜና ለሕወሃት/ኢህአዴግ መንግስት አዳዲስ አጀንዳ መፍጠር ችላ ነበር።የጋዜጣዋ የመጀመርያ አዘጋጆች የነበሩት ተፈራ አስማረና ጋዜጠኛ ወርቁ አለማየሁ ነበሩ።በተለይ የተፈራ አስማረ በአንድ ወቅት ''ጎንደር ጦርነት አለ'' የሚለው ከፊት ገፅ የወጣው ዜና ህወሓትን የማበድ ያህል ወሰድ አድርጎ የመለሳት ርዕስ ነበር።ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ጎንደር በወቅቱ የነበረውን ጦርነት የሚያሳይ ማስረጃ ይዞ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ማዕከላዊ ከመውረድ ግን አላዳነውም።በቀጣይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም በሚፅፋቸው ቱባ ቱባ አራት ኪሎ አንቀጥቅጥ ፅሁፎች ህወሓት/ኢህአዴግንም ሆነ አቶ መለስን እረፍት አሳጣቸው። ለእዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት የጋዜጠኛ እስክንድር አጀንዳ ለቤተ መንግስቱ የመስጠት አቅሙን አቶ መለስም ሆኑ አቶ በረከት ስላልቻሉት ነበር። 

እስክንድር ከሁለት ዓመት ወዲህ በመጣው ለውጥ በተለይ ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ የፅንፍ ኃይሎች እንቅስቃሴ በመሞገት፣በመቃወም እና ባላሰቡት መንገድ አጀንዳ በመስጠት  አሁንም ባለው የፖለቲካ መንደር ውስጥ የሚፈሩት አይደለም ማለት አይቻልም።እስክንድር አጅንዳ መስጠት ከፈለገ የትም ቦታ በመሄድ አጀንዳ መስጠት ይችላል።ድንገት ተነስቶ ስታድዮም መግባት ብቻ ፖሊስ እንዲሰጋ እና የሚያደርገው እንዲያጣ ማድረግ ይችላል። ስታድዮም በሩ ላይ ሲደርስ ፖሊሶች አናስገባው እናስገባው እያሉ ሲወዛገቡ እርሱ በሩን አልፎ ሊገባ ወደፊት እየተራመደ ነበር። ሲያስቡት ስታድዮም ገብቶ በመቀመጡ ብቻ ትልቅ አጀንዳ እንደሚሆን ፈሩ እና ከለከሉት።እስክንድር  የካራማራ ድል ድንገት ብቅ ብሎ አበባ በማስቀመጥ ሊያስጨቅ ይችላል።በእነኝህ  ሁሉ ሒደቶች፣ እስክንድር አጀንዳ በመፍጠር ወደ የሚፈልገው የፖለቲካ ግብ መድረስ የሚችል ነው። በፖለቲካ ውስጥ አጀንዳ ተቀባይ ከሆንክ ምንም አቅም የለህም።አጀንዳ ሰጪ ከሆንክ ግን እያጠቃህ ነው ማለት ነው። እስክንድር በዘመነ ህወሓት/ ኢህአዴግ በእስር ቤት በመግባቱ ብቻ ለስርዓቱ ቢያንስ በየስድስት ወሩ አጀንዳ ሰጥቶ እረፍት ነስቷል።ዓለም አቀፍ የሽልማት መዥጎድጎድ  እና እስክንድር የበለጠ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱ በራሱ የማይጋፉት እና የማይመልሱት አጀንዳ ነበር።

እስክንድር እውቅና ያልሰጣቸው የመልክዓ እስክንድር ነጋ ደጋሚዎች

እስክንድር የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ አይደለም።እስክንድር ኢትዮጵያ 'ፓትርዮት' የምትለው ሰው ነው።ከሀገረ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ በሀገር ፍቅር ስሜት እንጂ በጎሳዊ ፖለቲካዊ ቅኝት አይደለም።በተለያየ ጊዜ በሰጣቸው መግለጫዎች እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶቹ ሁሉ በጎሳዊ ፖለቲካ አራማጅነት አይደለም።አዲስ አበባን በተመለከተ የሚያንፀባርቀው የፖለቲካ መንገድ በአዲስ አበባ እና በኦሮምያ በሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች ላይ የፅንፍ አስተሳሰብ የሚያራምዱ አካሎች ግፊት ውጤት ነው።በእዚህ ግፊት ላይ እስክንድር የበለጠ አዲስ አበቤያዊ ስሜቱን አንሮት ህዝቡ እራሱን ለአከላከል መውሰድ ያለበት እርምጃ ያላቸውን አንፀባርቆ ይሆናል። ስለ አዲስ አበባ መቆም ለብሄር ፖለቲካ መቆም አይደለም።አዲስ አበባ አንድ ወጥ ጎሳ የላትም።ለአዲስ አበባ ስትቆም ለሽሮ ሜዳ ሰፈር የወላይታ እና ዶርዜን፣ተክለሃይማኖት ሰፈር ያሉ የአክሱም ተወላጆችን፣መርካቶ የሚወጡ የሚወርዱ የጉራጌ ማኅበርሰብ አባላትን  እና ሌሎችንም የመወከል ሁሉ ሂደት ነው።አዲስ አበባ የሁሉም ብሔር ሀገር መሆኗን አምኖ እስክንድር የአዲስ አበባን ጉዳይ አደባባይ ይዞ ብቅ እንዳለ መጠራጠር አይገባም።

እስክንድር በቅርቡ የድምፃዊ ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ተመልሶ ለእስር መዳረጉን መንግስት መግለጡ ይታወቃል።እስሩ በተለይ የፅንፍ ኃይሎች በአዲስ አበባ ላይ የድምፃዊ ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ሊከሰት የነበረው ጥቃት አንፃር እስክንድር እንደግጭት ፈጣሪ ሆኖ የቀረበበት  ጉዳይ ነው።ዝርዝር ጉዳዩን ለሕግ ባለሙያዎች እንተወው እና ሕጉ ሌሎችን ሊያጠቁ በመንቀሳቀስ እና ስፍራን ሳይለቁ ከተማን ለመከላከል መንቀሳቀስ መሃል በሚለው ልዩነት መሃል የሰማይ እና የምድር ያህል ልዩነት እንዳለው ማወቅ ቀላል ነው።

የእስክንድር ጉዳይ ከአዲስ አበባ በላይ  የፖለቲካ ንግድ  ማጧጧፍያ እና መተዳደርያ የሆነው ግን በሀገረ አሜሪካ ነው።እዝያ እራሱ እስክንድር የማይቀበለው ብቻ ሳይሆን  አንገብጋቢው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ የፅንፈኞች እንቅስቃሴ መግታት ነው ወይንስ እስክንድር በተመለከተ ከጧት እስከ ማታ አጀንዳ ማድረግ የቱን ታስቀድማለህ? ተብሎ እስክንድር ቢጠየቅ የሚሰጠው መልስ  የኢትዮጵያ ጉዳይ ቅድምያ ማግኘት አለበት ነው።ይህ የእስክንድርን ስብዕናም ሆነ ልዕልና ዝቅ የሚያደርግ አይደለም። ይልቁንም አስተዋይነት የሚለካበት ነው።እስክንድር ከእርሱ አስተሳሰብ እና ፍላጎት በላይ የእስክንድር መልክዓ  በመድገም የራሳቸውን ዝና ለመገንባት የሚፈልጉትን ይፀየፋቸዋል።እስክንድር አንገታቸውን በካራ ከተቆረጡት ጋር እኩል አድርጉኝ አላለም።እስክንድር ቤታቸው ከጋየባቸው እና መድረሻ ካጡ ወገኖች እኩል ተንከባከቡኝ አላለም። እስክንድርም የሚፀየፈው  የዲሞክራሲን የበላይነት ትቶ የመልክዓ እስክንድር ነጋ ደጋሚዎችን ነው።

''Gudayachn'' report on Ethiopian top English News paper - Ethiopian Herald የጉዳያችን ዜና ሪፖርት በኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ላይ


The Ethiopian herald July 19,2020

ADDIS ABABAB – “… I am glad to hear that the authorities have now managed to get a certain control over the situation, and at the same time upheld the principles.”

The remark was given on Wednesday, by Jorunn Elisabet Representative of Christian Democratic Party with the Norwegian Parliament, while addressing Ethiopians residing in Norway who staged demonstration opposite the parliament to denounce the killing of Hachalu Hundessa and the violence ensued that claimed scores of lives while damaging public and private property.

According to Gudayachin Media, Communication and Consultancy, a Norway based website, the Ethiopians residing in Norway have also denounced the actions of those forces who strive to tackle the ongoing reform in the country. They have also requested the government to bring to court the culprits.

Jorunn Elisabet further expressed her party’s readiness to support the ongoing reform in the country and noted that the efforts to bring justice and democracy should be practical.

“But we in the Christian people’s party will stand together with Ethiopia in their fight for more democracy and social justice. This should not only be done with words, but also through concrete action. That’s why I’m very happy that we will continue with our project supporting democratization in Ethiopia.”

Representatives of various Ethiopian religious institutions, Ethiopian communities have also attended the demonstration, it was learnt.

Similarly Ethiopians in Maryland, Virginia and Washington DC areas of USA had also been holding demonstrations to denounce the adverse acts of TPLF, OLF/Shinee and other forces in what they said have attempted to disintegrate Ethiopia. They have also expressed support to the swift actions the government took to foil the plots of the anti-peace forces and to safeguard the sovereignty of the country by apprehending the culprits.

The demonstrators also condemned the actions of the anti-peace elements for attempting to stir ethnic and sectarian violence while requesting the government to take actions on groups that are trained and armed in a way that is not allowed by the constitution.

They also urged the government to take tangible actions to promote nationally shared values as well as to rehabilitate civilians that were victims of the recent mob attacks.

Furthermore, they have acknowledged the achievements of Prime Minister Dr. Abiy Ahmed for his efforts of creating favorable image of the nation at a global stage while hailing the successful development endeavors including the Unity Park and fast pace of the construction of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD).

Demonstrators also requested the ruling to bring to justice officials of the previous administration who are suspected of human rights violations and embezzlement. The participants of the demonstrations have also warned individuals and media abroad to refrain from their acts of disintegrating the nation.

They have also urged the US government to recognize Ethiopia’s commitment of fighting terrorists and ensure peace in the continent, and take action against individuals and media who possess American citizenship and incite ethnic violence at home.

The Ethiopian herald July 19,2020

BY STAFF REPORTER

Source = Ethiopian Herald English News Paper (https://www.press.et/english/?p=25080#



Wednesday, July 15, 2020

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ ፓርላማ ፊት ለፊት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

ሰልፉ በከፊል 
ጉዳያችን ልዩ ሪፖርታዥ 
''የኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሂደት ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ኃይሎች ጎሳን መሰረት ላደረገ እና በኃይል በታገዘ ሁከት ባስነሱት አመፅ ለጠፋው 200 የሰው ሕይወት ተጠያቂ ናቸው።'' በኖርዌይ የፓርላማ የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ ተወካይ ወ/ሮ ዮርን ኤልሳቤት (Jorunn Elisabet)
በእዚህ ጽሁፍ ስር የሚከተሉትን ያገኛሉ - 
>> በሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት ስም ዝርዝር እና ኃላፊነት 
 >> በኖርዌይ ፓርላማ የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ (Krf) ተወካይ ወ/ሮ ዮርን ኤልሳቤት (Jorunn Elisabet)
ለሰልፈኛው ያደረጉት ንግግር ፅሁፍ ቅጂ (በኖርዌጅኛ እና እንግሊዝኛ ትርጉም) ፣
>> ለኖርዌይ ፓርላማ የገባው ደብዳቤ በፅሁፍ (በኖርዌጅኛ)፣
>> የሰልፉ የአቋም መግለጫ በፅሁፍ (በአማርኛ) እና 
>> የሰልፉ ሙሉ መርሐግብር ቪድዮ ዩቱብ ሊንክ የገኛሉ።


ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 8/2012 ዓም በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ ፓርላማ ፊት ለፊት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።ሰልፉ የወቅቱን የኮሮና ወረርሽኝ ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ እርቀታቸውን ጠብቀው በተገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን የታጀበ ነበር።በኖርዌይ የሚኖሩ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ማኅበርሰብ የተገኘበት እና በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በኖርዌይ የተስተባበረው የእዚህ ሰልፍ ዋና ምክንያት እና ዓላማ በኢትዮጵያ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ በተፈፀመው ግድያ ተከትሎ በሽብርተኛ ተግባር ላይ በተሰማሩ ወጣቶች ከ200 ያላነሱ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ሕይወት መቀጠፉ፣ንብረታቸው መውደሙ እና መፈናቀላቸውን በመቃወም፣የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ለመጠይቅ፣በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ የሚሞክሩ የፅንፍ ኃይሎችን ለመቃወም እና በሃጫሉ ላይ የተፈፀመውን ግድያም ለማውገዝ ነው።

በሰልፉ ላይ ተገኝተው ንግግር ካደረጉት ውስጥ -

- የኢ/ ኦ/ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣የጣልያን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ እና አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ 
- በኖርዌይ ፓርላማ የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ (Krf) ተወካይ ዮርን ኤልሳቤት ( Jorunn Elisabet)
- የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን በኖርዌይ መሪ ፓስተር ዮሐንስ ተፈራ፣
- የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮሚኒቲ) በኖርዌይ ሰብሳቢ አቶ ፍቅሩ አሕመድ፣
- የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ኮሚንቲ በኖርዌይተወካይ አቶ ሽኩሪ፣
- ከሴቶች ወ/ሮ ዙፋን፣
- ከኦሮሞ ማኅበረሰብ ኦቦ አንዱዓለም፣
- ከኤርትራ ማሕበረሰብ አቶ ንጉሴ ለተብርሃን፣
- ከኢዜማ አቶ ፍቅሬ አሰፋ፣
- ከኢትዮጵያውያን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በኖርዌይ ተወካይ አቶ ኤፍሬም እና 
- በመጨረሻም የሰልፉን የአቋም መግለጫ አቶ ጌታቸው በቀለ አንብቧል።
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ 

ከእዚህ በተጨማሪ በዕለቱም የዕለቱን መርሐግብሩን አቶ ለማ ደስታ የመሩ ሲሆን፣ አርቲስት ይድነቃቸው ተፈሪ እና ወ/ሮ አዲስ ኢትዮጵያ የሚለውን የድምፃዊት ሂሩት በቀለ ዜማ አብረው ከሰልፈኞቹ ጋር ያሰሙ ሲሆን አቶ ልዑል ደግሞ እጅግ ቀስቃሽ በሆኑ መፈክሮች ሰልፈኛውን  ወቅታዊ በሆኑ መፈክሮች አነቃቅተዋል።  

በዛሬው ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ሌላው ዓበይት ተግባር የኢትዮጵያውያን ጥያቄ በተመለከተ ለኖርዌይ ፓርላማ የተዘጋጀ ደብዳቤ ከፓርላማ ለተወከሉት ተወካይ በሰልፈኛው ፊት ተሰጥቷል።በእዚሁ በኖርዌይ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኃላ ከ8 ሰዓት እስከ 10:30 በዘለቀው ሰልፍ ላይ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ የተገኘ ሲሆን ሰልፈኛው በኢትዮጵያ የፅንፍ ኃይሎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ እየፈፀሙ ያሉትን ግድያ፣ዘረፋ እና ማፈናቀል በከፍተኛ ሁኔታ አውግዞ፣የለውጥ ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሞክሩትን በሙሉ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በማለት ድምፁን አሰምቷል።

በመጨረሻም ከእዚህ በታች ሰላማዊ ሰልፉን የተመለከቱ የሚከተሉትን የጽሑፍ እና የቪድዮ መረጃዎች ያገኛሉ። እነርሱም - 

>>  በኖርዌይ ፓርላማ የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ (Krf) ተወካይ ዮርን ኤልሳቤት( Jorunn Elisabet Gleditsch Lossius)ለሰልፈኛው ያደረጉት ንግግር ፅሁፍ ቅጂ (በኖርዌጅኛ እና እንግሊዝኛ ትርጉም) 
>> ለኖርዌይ ፓርላማ የገባው ደብዳቤ በፅሁፍ፣
>> የሰልፉ የአቋም መግለጫ በፅሁፍ እና 
>> የሰልፉ ሙሉ መርሐግብር ቪድዮ ዩቱብ ሊንክ የገኛሉ።
======================
በኖርዌይ ፓርላማ የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ (Krf) ተወካይ ዮርን ኤልሳቤት ( Jorunn Elisabet Gleditsch Lossius)
ለሰልፈኛው ያደረጉት ንግግር
የኖርዌጅኛው 

 የፓርላማ አባሏ ንግግር እንግሊዝኛ ትርጉም 

Dear all of you,
Thank you to Ethiopian Association in Norway for the invitation to this marking.
On behalf of the Christian people's party, I want to say that we stand together in solidarity with you and other people in the difficult time you are now standing in.
The situation in Ethiopia is serious. Unfortunately, there are forces that want to stop the democratic, economic and political development of the climate crisis. These powers are responsible for over 200 people have lost their lives through ethnic based violence earlier this month. Such actions we must take a strong distance from and condemn.
Yet, I am glad to hear that the authorities have now managed to get a certain control of the situation, and at the same time preserved the the principles.
Ethiopia transisjon for a flerpartidemokrati is not going to be easy, and it's going to take time.
But we in the Christian people's party will stand together with Ethiopia in their fight for more democracy and social justice. This should not only be done with words, but also with through concrete action. That's why I'm very happy that we will continue with our project supporting democratization in Ethiopia.
በኖርዌይ ፓርላማ የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ (Krf) ተወካይ ዮርን ኤልሳቤ

ለኖርዌይ ፓርላማ የገባው ደብዳቤ 

Re: Appell om Norsk støtte og bidrag for den politiske reform og rettferdig bruk av Nilen 

Vi, etiopiere i Norge fra etiopiske sivilsamfunnsorganisasjoner, foreninger, tro og livssynsamfunn, skriver til dere av stor sorg og bekymring om siste utviklingen i hjemlandet vårt, Etiopia. 

Etiopia gjennomgår en voldsom politisk overgang med håp om bredere demokratisering i landet. Etter at Abey Ahmed tok makten, ble tusenvis av fanger løslatt og mange eksilerte opposisjonsgrupper, inkludert de som ble ført væpnet kamp, ​​ble invitert til å kjempe fredelig. Et demokratisk valg var planlagt i august 2020, frem til nylig kansellering på grunn av koronapandemien.

Etiopias statsminister Abiy Ahmed Ali som tiltrådte i april 2018 ga uttrykk for fred med Eritrea. Han tok fredsinitiativet som medførte tilnærming mellom Etiopia og Eritrea som ble markert med en fredsavtale i juli 2018, og grensen ble gjenåpnet etter 20 år i september 2018. I november 2019 ble Etiopias nesten 30-årige etnisk-basert styrende koalisjon - EPRDF - fusjonerte til et enkelt enhetsparti kalt Prosperity Party, men et av de fire konstituerende partiene TPLF som nektet å delta. TPLF hadde maktmonopol i det tidligere EPRDF partiet. 

Selv om det ble oppnådd enorme endringer i landet i løpet av de siste to årene, ble det også registrert utbredt vold og risiko for statlig kollaps. Dette er hovedsakelig resultatet av tre tiår gammel fullblåst institusjonalisering av identitet og etnisk politikk.

På tross av utstrakt lokal uro under hans ledelse, har Abiy Ahmed Ali støtte fra majoriteten av det etiopiske folket. Vi mener at han er den riktige lederen som kan samle befolkningen, og har visst ved gjentatte reformer at han makter å roe ned konflikter.

Tigray Peoples Libration Front (TPLF)  anklager Abiy Ahmed med overlegg å forfølge personer tilhørende tigray-gruppen etter at en rekke tidligere TPLF militære ledere ble arrestert og anklaget for korrupsjon. TPLF og radikale Oromo grupper står nå sammen for å presse statsministeren ut av posisjon. 

Den siste uken ble vi imidlertid vitne til historien om et forestående prosjekt med etnisk renselse der mer enn 166 sivile ble drept i et blodig voldsutbrudd etter mordet på en berømt Oromo-kunstner Hachalu Hundesa 29. juni 2020. Uskyldige sivile ble målrettet i Oromia-regionen av Oromo vigilante-grupper og eiendommer ble vandalisert og ødelagt.

Den etiopiske regjeringen kunngjorde at drapet på Hachalu var godt planlagt og gjennomført av kjente ekstremistgrupper. Hovedmålet med attentatet var å innlede vold fra hans støttespillere og beundrere og skape totale kaos i landet; og derved forstyrrer overgangsprosessen ledet av statsminister Abey Ahmed.

Konfrontasjonen med regjerings troppene kunne ha blitt berserk hvis det ikke hadde vært for den taktfulle arrestasjonen og demobiliseringen av hoved personer bakk denne konspirasjonen. 

Kringkasting av hatfylte og voldssporende meldinger:

  1. Oromia Media Network (OMN)

Før og etter dødsfallet av Hachalu var Oromia Media Network (OMN) i spissen for å kringkaste hatfylte og voldssporende meldinger om at medlem av en etnisk gruppe (hovedsakelig Amhara) har drept artisten. Kodeord som “unitarister” “neftegnas” og “nybyggere” ble alternativt brukt for å antyde at Amharas sto bak drapet. Det var åpne invitasjoner til vold der folk ble bedt om å sperre gater, angripe og “fullføre” nybyggere, forbrenne eiendommene sine. Vi har arkiverte klipp og opptak fra disse OMN-sendingene allerede. OMN sender nå fra utlandet fortsatt meldinger om at Hachalu, ble myrdet av unitarister som Abiy Ahmed. Noen av OMN-forståsevennene har også tråkket inn en annen grunnløs påstand om at artisten ble myrdet av eritreiske kommandoer. Det er denne falske (unøyaktige) og harselende sendingen som ofte retter seg mot ikke-Oromos som nå styrker noen av protestene og medieaktivitetene til Oromo-høyre-gruppen. 

  1. Tigray Media House (TMH), Tigray TV and Dimsti Woyane

Tigray Peoples Libration Front (TPLF) er fullstendig klar over tillitsunderskuddet på siden av Oromo-offentligheten og spiller derfor rollen som en styrkermultiplikator på medias økosystem. TPLFs medieøkosystem reiser imidlertid gripende politikk og ideologiske spørsmål langt mer enn OMN. 

Kort sagt, mens OMN forvirrer Oromo-publikum og tar sikte på å delegitimere regjeringen i øynene til Oromo, forsøker TPLFs medieøkosystem å gi alliansen med OMN / OLF-leiren et ideologisk plagg. 

Enkeltpersoner og grupper av etiopisk opprinnelse som bor i Europa, Amerika og Australia er eiere og sponsorer medier, som OMN som sprer hatefulle meldinger i landet. Oromo medienettverk og TPLF medier er spiss i retning av hatefull propaganda i Etiopia og innleder vold mellom etniske grupper. Dens rolle kan sammenlignes med Radio-TV Libre des Mille Collines (RTLMC) når det gjelder å oppfordre til genocide i Rwanda. Oromo-samfunnet som er bosatt i Norge er blant de viktigste inntektskildene for OMN. Erstatter Mr. Jawar Mohamed, en veldig kontroversiell politiker, Girma Gutema fra Bergen, Norge fungerer for tiden som manager for OMN i Etiopia. 

Vi fredselskende etiopiere i Norge er dypt bekymret for den nåværende utviklingen i Etiopia og ber det norske myndigheten og parlamentet om å stå sammen med statsminister Abey Ahmeds administrasjon for å løse utfordringene Etiopia for øyeblikket står overfor.

Etiopia er et land for mer enn 110 millioner innbyggere. Blant 110 millioner etiopiere er det bare en tredjedel som får strøm. For å lindre denne alvorlige kraftmangelen og minimere beslektede økonomiske begrensninger, har Etiopia investert sine magre ressurser i å konstruere Grand Etiopian Renaissance Dam (GERD). Etiopias forsøk på å fullføre GERD er dessverre ikke likt av den Egyptiske regjeringen. Forhandlingene mellom Etiopia, Egypt og Sudan mislyktes stadig.

Vi etiopiere i Norge ber den norske regjeringen og det norske parlamentet om å stå sammen med den Etiopiske regjeringen for rettferdig andel og utnyttelse av Nilen-farvannene.

Til slutt, vi appellerer at Norge

  • støtter reformen i Etiopia 

  • støtter Etiopias rettferdige sak om GERD 

  • ta hånd om diaspora baserte media og finansering som ødelegger for Etiopia


Med vennlig hilsen,

Etiopiere og Norsk-Etiopiere i Norge


የሰልፉ የአቋም መግለጫ



የሰልፉ ሙሉ ቪድዮ ዩቱብ ሊንክ

https://www.youtube.com/watch?v=kvnP0ZxZJyE



=======================/////================









Monday, July 13, 2020

በኖርዌይ፣ ኦስሎ እና በዙርያዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ የቀረበ ጥሪ - ለትውልድ የምትቆይ ኢትዮጵያን ለማቆየት ሁለት ሰዓታትን ለኢትዮጵያ ከመመስከር ያነሰ አይደለም።

ኢትዮጵያ ዛሬ በስሜት ከቤቱ የሚናደድ፣የሚቆጭ እና እንዲህ ቢሆን እያለ የሚያወራ ሰው አይረባትም።ወቅቱ ቢያንስ ለሀገር በአደባባይ የመመስከር እና የጋራ ድምፅን የማሰምያ ጊዜም ነው።ወቅቱ በዓለም አደባባይ ''ኢትዮጵያ ትውደም'' (ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ) እያሉ የሚሞላቀቁ 'የጉድ ትውልዶች' የታዩበትም ጊዜ ነው። 
በእዚህ ጊዜ ከቤተሰብ ጋር ወጥቶ ለኢትዮጵያ አለመመስከር ትልቅ ስህተት ነው።በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ ጋር በከተማዎች ይመላለሳሉ።ከእዚህ ጊዜያቸው ውስጥ ሁለት ሰዓታት ለኢትዮጵያ እንዲመሰክሩ ለመጪው ረቡዕ ጁላይ 15/2020 ከ 14 እስከ 16 ሰዓት ባለው ጊዜው ውስጥ ኦስሎ የሚገኘው የኖርዌይ ፓርላማ Karl Johans gate 22 / 0026 Oslo በመገኘት ለኢትዮጵያ ድምፅ እንዲሆኑ ይጠየቃሉ።






Friday, July 10, 2020

የንፁሃን ደም እና እንባ ይጣራል!ፍጅት የፈፀሙት እና ያስፈፀሙት በሙሉ በልዩ ችሎት ለፍርድ ቀርበው ቅጣታቸውን ሲቀበሉ ሕዝብ መመልከት አለበት።


>> በውጭ ሀገር ኦነግ ሸኔ እና ህወሓትን ደግፎ የሚሰለፍ እጆቹን  በንፁሃን ደም እንደነከረ ሊያውቀው ይገባል።

>> የእዚህ ዓይነት ወንጀል ላይ የሚሰጠው ፍትሕ ትውልድ አስተማሪ መሆን አለበት።ወደፊት የወንጀሉ ታሪክ ሲዘከር፣የተሰጠው ፍርድ ከወንጀሉ ካነሰ የዘላለም ጠባሳ ነው።
=================
በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ተከትሎ በኦሮምያ ክልል የደረሰው የዘር ፍጅት እና የንብረት መውደም እጅግ አሰቃቂ ነው።ጥቃቱ ለምሳሌ በአርሲ አምስቱ ዞኖች፣በሻሸመኔ፣አምቦ ጥቃቱን ለመፈፀም የተደረጉ ዝግጅቶች የታዩት ገና ሰኞ ምሽት 3:30 ላይ ሃጫሉ ከመገደሉ በፊት መሆኑ የጉዳዩን ተያያዥነት ያሳያል የሚሉ ብዙዎች ናቸው።በሰሞኑ በኦሮምያ ብቻ ከ200 በላይ ንፁሃን ሕይወታቸውን ማጣታቸው የሚታወስ ነው።

በአርሲ አምስቱ ዞኖች ውስጥ ከተፈፀሙት ወንጀሎች ውስጥ የሁለቱን ማለትም በቀርሳ እና ዴራ ወረዳ የደረሰው ዘርን እና ሃይማኖትን የለየ የዘር ማጥፋት ተግባር በሌሎች ቦታዎች ለተፈፀሙት ማሳያ ነው።የቢቢሲ ዘገባ እንደሚከተለው ይነበባል።

''የቀርሳ ነዋሪ ሦስት የቤተሰቦቻቸውን አባላት ደረሰባቸው ባሉት ጥቃት አጥተዋል። "የአክስቴን ልጅ፣ ልጁንና አማቹ ተገድለዋል" የከፋ ችግር የነበረው በአርሲ ዞን በቀርሳ ሙኔሳ ወረዳ ነበር ያሉት ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰብ የደረሰውን ሲገልፁም፤ ሙኔሳ ዳሞት ቅምቢባ የሚባል ገበሬ ማኅበር የጥቃቱ እምብርት ነው ይላሉ።በአካባቢው የሚገኝ ወደ 40 ገበሬ ማኅበር ላይ ጥቃቱ እንደደረሰ መረጃ አለን የሚሉት እኚህ ግለሰብ ግድያና ዘረፋ የተካሄደው ዳሞት ቅምቢባ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ ነው ብለዋል።ጥቃቱ የደረሰው ድምጻዊ ሃጫሉ መገደሉ በተሰማበት ሰኞ ሌሊት መሆኑን የሚገልፁት እኚህ ግለሰብ ጥቃት አድራሾቹ የታጠቁ እንደነበሩ ይናገራሉ።"ፊታቸውን ሸፍነው ነበር፤ የሚፈልጉትን ሰው በስም እየጠሩ በሩን እያንኳኩ ነበር የሚያስወጡት" በማለትም ገጀራ፣ ስለት ያላቸው ነገሮችና ጦር መሳሪያ መያዛቸውን ያስረዳሉ።በዚህ አካባቢ ሰባት ሰዎች በገጀራና በጥይት መገደላቸውን በመግለጽ ሁለት ሰዎች ከባድ መቁሰል ጉዳት ደርሶባቸው በአሰላ ሆስፒታል እንደሚገኙ ነግረውናል።"ሁለት ሰዎች (ስማቸውን ጠቅሰዋል) ሞተዋል ብለው ጥለዋቸው ሄደው ነው በህይወት የተገኙት" በማለት በአሁኑ ሰአት በአሰላ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እያገኙ መሆኑን ገልፀዋል።

በማግስቱ ማክሰኞ ረፋድ ላይ ፖሊስ መምጣቱንና የሞቱና የቆሰሉትን ሰብስቦና ማኅበረሰቡን አረጋግቶ መሄዱን ያስታውሳሉ። ነገር ግን በስፍራው የፖሊስ ኃይል አለመኖሩን በመገንዘባቸው ጥቃት አድራሾቹ በድጋሚ መምጣታቸውን የሚናገሩት እኚህ ግለሰቡ የአካባቢው ሰው ሸሽቶ ሙኔሳ ገብርኤል ወደሚባል አካባቢ ሄዶ ማደሩን ገልፀዋል።''

በአርሲ ዴራ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና ልጃቸውን ያጡት ግለሰብ ልጃቸው ከአዳማ ሊጠይቃቸው የመጣው ሰኞ ዕለት ማታ እንደሆነ ይናገራሉ። ለማክሰኞ አጥብያ የሃጫሉን ሞት ተከትሎ በአካባቢያቸው ረብሻ መከሰቱን ተናግረዋል። ልጃቸው በአጥር ዘሎ ወደ ጎረቤት ጊቢ ሲያመልጥ ከዚያ ጎትተው በማውጣት መንገድ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን ለቢቢሲ ተናግረዋል።400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤታቸው፣ እስከነ ሰርቪሱ፣ ሱቃቸው እስከነ ሙሉ እቃው መዘረፍ መቃጠሉን እንዲሁም ከብቶቻቸውን መንዳታቸውን ይናገራሉ።ሌላኛው ልጃቸው መፈንከትና ስብራት እንደደረሰበት ገልጸዋል።ግለሰቡ የሚሉት በከተማዋ ላይ በደረሰው የቤት ቃጠሎ ወደ 300 የሚደርሱ ቤቶች መውደማቸውን ገልፀው። በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ይናገራሉ።በከተማዋ የጸጥታ ኃይል ቢኖርም፣ ከአሰተዳደሩ ምንም ዓይነት መፍትሄ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።''

ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ጥቃት መሰረት ያደረገው ከዓማራ እና ጉራጌ ተወላጅ ናችሁ የሚል እና ከኦሮሞም ቢወለዱ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ተከታዮች ናችሁ በሚል ነው።በተመሳሳይ መንገድ በሻሸመኔ፣ባቱ፣አምቦ፣ሐረር እና ሌሎች የኦሮምያ ክልል ቦታዎች ሰሞኑን ጥቃት ተፈፅሞ ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን አጥተዋል።

በሻሸመኔ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት እና የሽብር ተግባር በተመለከተ ከእዚህ በታች ያለው በጀርመን ድምፅ ራድዮ የተዘገበው እና በአደባባይ ሚድያ የተዘጋጀው ማጠቃለያ የጥፋቱን መጠን ያሳያል። 


የፍትህ ሂደቱ በቶሎ መጀመር፣ በግልጥ ለሕዝብ መታየት እና አስተማሪ መሆን አለበት።

የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ከሰሞኑ እየወሰደ ያላቸው ዕርምጃዎች አበረታች እና ሊደገፍ የሚገባው ነው።ክስተቶቹ በሀገር ላይ ሊያመጡ የነበሩት አደጋዎችን ተጋፍጦ የወሰደው አፋጣኝ እርምጃ በሙሉ ሊያስመሰግነው ይገባል።በእስር ሂደቱ ላይ ከጉዳዩ ጋር ሊገናኙ አይችሉም የተባሉትን ሁሉ ጨምሯል መባሉ መጣራት ያለበት ሁኔታ ነው።በሌላ በኩል ግን  አሁን በሚታየው የኦሮምያ ክልል የመንግስት መዋቅር ውስጥ የፍትህ አካሉም ሆነ ፖሊሱ እምነት የሚጣልበት አይደለም።ከላይ በዘገባው ላይ እንደተገለጠው ፖሊሶች የድርጊቱ ተባባሪ ከመሆን አልፎ ሕዝቡን ለጥቃት ያጋለጡ ሆነዋል።ስለሆነም አሁን ተያዙ የተባሉትም በአካባቢያቸው በቂ የፍትህ ውሳኔ ላያገኙ እና የማድበስበስ ተግባር ሊፈፀም ይችላል።ስለሆነም በወንጀሉ የተሳተፉትን የፍትህ ሂደት በልዩ ሁኔታ በተመሰረተ ችሎት ፍርድ መስጠት ያስፈልጋል።ለድርጊቱ ተባባሪ የሆኑትም ላይ እንዲሁ።

ሕዝብ በማንነቱ ሲገደል፣ንብረቱ ሲወድም እና ሲሰደድ ከደረሰበት በደል በላይ የፍትህ ሂደቱ ኢፍትሓዊ ከሆነ ሌላ በደል ነው።ስለሆነም በመጀመርያ በድርጊቱ የተጠረጠሩት ከተያዙ በኃላ እንዳይለቀቁ በቂ ቁጥጥር ማድረግ፣ በመቀጠል የፍትህ ሂደቱ ግልጥ እና አስተማሪ የሆነ (በወንጀሉ መተባበራቸው ለተረጋገጠባቸው እስከ የሞት ቅጣት የሚደርስ ፍርድ) ከፍትሕ ሰጪው አካል ሕዝብ ይጠብቃል።የእዚህ ዓይነት ወንጀል ላይ የሚሰጠው ፍትሕ ትውልድ አስተማሪ መሆን አለበት።ወደፊት የወንጀሉ ታሪክ ሲዘከር፣የተሰጠው ፍርድ ከወንጀሉ ካነሰ የዘላለም ጠባሳ ነው።

ለማጠቃለል የሰሞኑ የግፍ ተግባሮችም ሆኑ የቀደሙት ግድያዎች ሁሉ የአንድ ሰሞን ሥራ አይደሉም።ህወሓት/ኢሕአዴግ የዘራው የጥላቻ ዘር፣አክራሪ ኃይሎችን ወደ ስልጣን የማምጣት ደካማ አሰራር፣የፀጥታ ኃይሉን በሚገባ በአካባቢ ደረጃ አለማደራጀት፣ወደ መቀሌ የሸሸው ህወሓት ስውር እጅ ከኦነግ ሸኔ ጋር እና ከፅንፍ አክትቪስቶች ጋር በጥምረት የቀሰቀሱት ቅስቀሳ ሁሉ ውጤት ነው። በመሆኑም የፍትሕ ሂደቱ ከሀገር ቤት እስከ ውጭ ሀገር በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በሙሉ የሚመለከት መሆን አለበት። በውጭ ሀገር ኦነግ ሸኔ እና ህወሓትን ደግፎ የሚሰለፍ እጆቹን  በንፁሃን ደም እንደነከረ ሊያውቀው ይገባል።

========/////===========


Wednesday, July 8, 2020

ጆሮ ጠገብ ያልሆኑ ኢትዮጵያን የተመለከቱ ዜናዎች

ሐምሌ 2/2012 ዓም (ጁላይ 9/2020)
================
ኢትዮጵያ የዓባይን ግድብ ውሃ መሙላት በሚስጥር  ጀምራለች ተባለ።

ኢትዮጵያ በሚስጥር የአባይ ግድብን መሙላት ጀምራለች ሲል ''ግብፅ እንዲፐንዳንትን'' ጠቅሶ ''ኢነርጂ ሚክስ ዶት ኮም'' ገልጧል።እንደ ድረ ገፁ ዘገባ የሱዳን እና የግብፅ ምንጮች እንደገለጡት ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት መጀመሯ ተሰምቷል ብሏል።በሌላ በኩል የግብፅ የውሃ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውሃውን እየሞላች እንደሆነ ተከታታይ መረጃዎች እንደደረሱት ነው ድረ ገፁ የዘገበው።ሆኖም የመስርያቤቱ ቃል አቀባይ መሐመድ አልሰባይ የግብፅ እንዲፐንዳንት ዘገባ አልተረጋገጠም ብለዋል።ይህ በእንዲህ እያለ የካይሮ ዩንቨርስቲ አንድ መምህር ግድቡ እየተሞላ እንደሆነ የሚያሳይ የሳተላይት ፎቶዎች ማሳየታቸውን ዘገባው ያትታል።''ኢነርጂ ሚክስ ዶት ኮም'' በናይጄርያ የነዳጅ እና ሌሎች የኃይል ምንጮች ላይ የሚዘግብ ድረ ገፅ ነው።

ሩስያ ለዓባይ ግድብ ድርድር ቴክኒካል እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኗን ገልጠች 

የሩስያ ዜና አገልግሎት ''ታስ'' ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 1/2012 ዓም እንደዘገበው ሩስያ ለዓባይ ግድብ ድርድር ቴክኒካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጠዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌ ላቭሮቭ ይህንን ያሉት ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣የግብፅ እና የደቡብ አፍሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በቪድዮ ከተነጋገሩ በኃላ መሆኑን ታስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሜሪካም ለተደራዳሪዎቹ አገልግሎት መስጠቷን አገራቸው በበጎ እንደምታየው ገልጠው፣ሩስያም አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት እንደምትችል ተደራዳሪዎች ሊያውቁት ይገባል ካሉ በኃላ ሩስያ የግድቡ ጉዳይ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት በቀረበ ጊዜ የሁሉንም ወገኖች የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ስምምነት መደረስ እንደሚገባ መግለጧን አስታውሰዋል።

ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ለሳውዲው  የዜና ቻናል ''አል-አረብያ'' ጋር ቃለ መጠይቅ አደረጉ።
''በግድቡ ምክንያት ግብፅ እና ሱዳን ፈፅሞ ውሃ አይጠሙም'' አቶ ገዱ አንዳርጋቸው 

አቶ ገድ በእዚህ መግለጫቸው ሱዳን እና ግብፅ ፈፅሞ በግድቡ ሳብያ ጭንቀት ውስጥ ሊገቡ አይገባም ካሉ በኃላ የግብፅ የተጋነነ እና ትክክል ያልሆነ ጥያቄ መታረም እንዳለበት እና ለችግሩ መፍትሄው መነጋገር ብቻ መሆኑን ገልጠዋል።ይላል የአል-አረብያ'' የእንግሊዝኛ ድረ ገፅ።ድረ ገፁ ሌላውን የቃለ መጠይቅ ይዘት ምንም ሳያቀርብ ወደ ግድቡ ታሪክ ገብቷል።ይሄው ድረ-ገፅ የአቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ያወጣበት ሁኔታ ደረጃውን ያልጠበቀ እና በራሱ ከሚድያ ስነምግባር የራቀ ነው።ቻናሉ የቃለ መጠይቁን ይዘት በገፁ ላይ ይዞ ላይወጣ ቃለ መጠይቅ ያደረገው መረጃ ለማግኘት ነው ወይ? ያስብላል።ድረ ገፁ የአቶ ገዱ ፎቶ በሸራተን ሆቴል ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መግለጫ ሲሰጡ (ከፋይሌ) ብሎ የለጠፈው ፎቶ ከስር ተመልከቱት። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱን አስታወቀ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮቪድ -19 በኃላ ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱትን አስታወቀ።አየር መንገዱ ወደ ዱባይ በረራውን ረቡዕ ሐምሌ 1/2012  የጀመረ ሲሆን ወደ ጅቡቲም በመጪው ሳምንት በረራው እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል።አየር መንገዱ አገሮች የአየር ማረፍያቸውን መክፈት መቀጠላቸውን ተከትሎ አገልግሎቱን እንደሚቀጥል ገልጦ፣በረራው በሚደረግባቸው አገሮች ያለውን የጤና መስፈርት እና ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቁ መስፈርቶችን ተከትሎ አገልግሎቱን እንደሚሰጥ እና ደንበኞች ይህንኑ የተመለከተ መረጃ ከአየር መንገዱ ድረ ገፅ ላይ መመልከት እንደሚችሉ አሳስቧል።

=============
  
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
Gudayachn Multimedia, Kommunikasjon og Konsultent 


Monday, July 6, 2020

በምዕራባውያንም ሆነ በግብፅ ትንተና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሸንፈው ወጥተዋል፣በመሆኑም ግብፅ ከሰሞኑ ትለሳለሳለች።የአቶ ኢሳያስ አፈወርቅ የግብፅ ጉብኝት ምንነት?


አቶ ኢሳያስ እና አልሲሲ በካይሮ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ

በእዚህ ፅሁፍ ስር - 

>>  በምዕራባውያንም ሆነ በግብፅ ትንተና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሸንፈው ወጥተዋል።
>>  አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ባሳለፍነው ሳምንት በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ምንነት።
>>  ነፍሰ ጡር በምጧ ጊዜ እንድትጨነቅ ሁሉ ኢትዮጵያም የጎሳ ፖለቲካን አሽቀንጥራ ለመጣል የመጨረሻ የመገላገያ ጊዜዋ 
        ላይ ነች የሚሉ ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።

ከልክ ያለፈው ትዕግስት 

ከ1983 ዓም በፊትም ሆነ በኃላ ብዙዎቹ የጮሁለት፣የተሰደዱለት እና የሞቱለት ኢትዮጵያን ከከፋፋይ እና የእልቂት የጎሳ ፖለቲካ የማላቀቅ የመጨረሻው ምዕራፍ ትግል ተጀምሯል።ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ ሁሉን አቃፊ ሆኖ ሰንብቷል።የኦነግ ዓርማ በአዲስ አበባ ሲውለበለብ እና የጎሳ ፖለቲካ ሲሰበክ እንዲሁም ሚድያዎች በአዲስ አበባ ቢሮ ከፍተው በግልጥ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ሲሳደቡ በትግስት ታልፏል።በቦሌ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው አዲስ አበባ እና ሐዋሳ ላይ መከፋፈልን በአደባባይ የሰበኩ፣በሕዝቡ ላይ የዛቱ ለወራት ዝም ተብለው ሰንብተዋል።

ይህ ሁሉ የፈለጉትን የመሆን መብት ግን በራሱ ገደብ አለፈ።ጀዋር መሐመድ ከበቀለ ገርባ ጋር እንዲሁም ልደቱ አያሌው ኃላፊነት በጎደለው መንገድ በዓደባባይ መንግስት ከመስከረም 30 በኃላ አይኖርም ማለት ጀመሩ።ይህ አባባል ቀደም ተብሎ ''ሁለት መንግስት ነው እዚህ ሀገር ያለው'' በማለት ጀዋር ደጋግሞ ከተናገረ በኃላ መሆኑ ነው።ቀደም ብሎ ብዙ ነገሮችን ሲያስታምም እና ሕግ ባለማስከበሩ በከፍተኛ ደረጃ የተወቀሰው መንግስት ከመስከረም 30 በኃላ አናውቀውም የሚል ንግግር ሲነገር፣ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መንግስት ትዕግስቱ እያለቀ መሆኑን በመግለጥ ማስጠንቀቅያ ሰጡ።ሆኖም ከቃላት ዝልፍያ የተጀመረው መንግስትን አናውቅም ስድብ ወደ መሬት የወረደ የሴራ ፖለቲካ ተሸጋግሮ አንድ አመፅ ለማቀጣጠል የሚረዳ አንዳች ምክንያት (Immediate Cause) መፈለግ ተያዘ።ለእዚህም ጉዳይ የድምፃዊ ሃጫሉ ሞት ተመረጠ።ስለሆነም የዛሬ ሳምንት ሰኞ ሰኔ 22/2012 ዓም አዲስ አበባ ላይ ተገደለ።በደቂቃዎች ውስጥ ኦኤምኤን እና የህወሓት ሚድያዎች የጎሳ ግጭት የሚያስነሱ የቅስቀሳ ዘገባዎች ጀመሩ።

በምዕራባውያንም ሆነ በግብፅ ትንተና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሸንፈው ወጥተዋል

የለውጡ ሂደትን በአንክሮ የሚከታተሉ የምዕራባውያንም ሆኑ የኢትዮጵያ ባላንጣ ግብፅ በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ልደናቀፍ የሚችልባቸው ሶስት ምክንያቶች ይኖራሉ ብለው ያስቡ ነበር።እነርሱም -

የመጀመርያው ምክንያት፣ የጦር ኃይሉ በዋናነት በህወሓት አፍቃሪ መኮንኖች የተሞላ ስለሆነ በቀላሉ የጦር ኃይሉን ሊቆጣጠሩ አይችሉም የሚል ግምት ነበር።ሆኖም ግን ይህ ግምት ስህተት መሆኑ ለመጀመርያ ጊዜ ምልክት በማሳየት የታወቀው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ጋር በቤተ መንግስት የጦሩን ኤታማጆር  ጀነራል ሳሞራን በክብር ጠርተው እና ሸልመው ሲያሰናብቱ እና በደህንነት መስርያ ቤቱ ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ እየመጣ መሆኑ ሲነገር ነበር።

በሁለተኛ ደረጃ የምዕራባውያንም ሆነ የግብፅ የለውጡ ሂደት ድልድዩን አይሻገርም የሚለው ግምት እና ጥርጣሬ የራሱ የኢሕአዴግ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? የሚል ሲሆን በአጭር ጊዜ ግንባሩ ሊከስም ስለማይችል ኢትዮጵያ ትከፋፈላለች የሚል ዕሳቤ ነበር።በእርግጥም በወቅቱ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት ለሚከታተል ሰው ትልቅ ፈተና እና መውጭያ መንገዱም ድቅድቅ ጨለማ ይመስል ነበር።ለእዚህ መንገድ ግን ቀድመው አቅደው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በለውጡ ሰሞን በሐዋሳ በተደረገው የኢሕአዴግ ጉባኤ ላይ እንደዋዛ ወደ ጉባኤው ማብቅያ ላይ አንዲት ነገር ጣል አደረጉ።ይሄውም ጉባኤው ኢህአዴግ ወደ አንድ የፖለቲካ ኃይል የሚቀየርበትን ሂደት (ከእዚህ በፊትም ተነስቶ ስለነበር) አጥንቶ ለማቅረብ ስልጣን እንዲሰጠው የሚጠይቅ ነበር።እንደዋዛ ቀለል አድርገው ያነሱትን ነገር ጉባኤው በጭብጨባ ተቀበለ። በእዚህ መሰረት ኢህአዴግ ከስሞ ብልፅግና ተመስርቶ ቀድሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሂደት ላይ ፖሊሲ የማውጣት ዕድል ያልነበራቸው ክልሎች እንደ አፋር፣ቤንሻንጉል፣ሱማሌ እና ጋምቤላ በብልፅግና ፓርቲ በአንድ ግንባር ተሰባሰቡ።ይህ ለኢትዮጵያ አንድነት ከሰላሳ ዓመታት በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ አንዱ እና ዓይነተኛ መሰረት የጣለ ሂደት ሆኗል።በእዚህም የምዕራባውያንም ሆነ የግብፅ ግምት ትክክል አለመሆኑን አመኑ። 

ሶስተኛው እና የመጨረሻው ጉዳይ በኦሮሞ የፅንፍ ኃይሎች በተለይ በጀዋር እና መሰሎቹ ዙርያ ያለው የኃይል ሚዛን መንግስትን የሚገዳደር ባይሆን አመፅ የመፍጠር እና ወደ አደገኛ መስመር ኢትዮጵያን የመምራት አደጋ አለው።በእዚህ ሳብያ የለውጡ ሂደት ይደናቀፋል የሚል ግምት ነበር።ይህንን ሃሳብ ብዙዎች በስጋት የሚመለከቱት እና ኢትዮጵያን ወደ አላስፈላጊ ኪሳራ እንዳይከት በማለት መንግስት በቶሎ ነገሮችን ማስተካከል እንዳለበት ሲወተውቱ ነበር።ይህ ጉዳይ ግን የድምፃዊ ሃጫሉን የግፍ ግድያ ተከትሎ በተነሳ ግጭት መንግስት ሕግ ለማስከበር በአዲስ መንፈስ እንዲነሳ እና ለሕዝቡም ቃል እንዲገባ ምክንያት ሆነ።በእዚህም መሰረት ጀዋር እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካቶች በአመፅ ሂደት እና ሴራ ውስጥ ገብተው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን በቁጥጥር ስር አዋላቸው።እስሩን ተከትሎ በበርካታ የኦሮምያ ክልሎች የኦሮሞ የፅንፍ ፖለቲካ አራማጆች በንፁሃን ላይ የግፍ ጥፋት ቢያደርሱም መንግስት እንደመንግስት ግን ሁኔታዎችን በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየወሰደ ያለው እርምጃ በራሱ በጣም አበረታች ነው።በእዚህም የምዕራባውያን እና የግብፅ የኢትዮጵያ ለውጥ ሊደናቀፍ ይችላል ያሉት ጉዳይ በመንግስት የበላይነት ቁጥጥር ስር መዋሉ የለውጡ ሂደት በሚገባ እየሄደ ለመሆኑ የማረጋገጫ ማሕተም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። 
 

አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ቀደም ብሎ በሱዳን ባሳለፍነው ሳምንት በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ምንነት።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ከሳምንት በፊት ሱዳንን፣ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ደግሞ ግብፅን ጎብኝተዋል።የአቶ ኢሳያስ ጉብኝት በኤርትራ ዜና ማሰራጫዎች እንደተገለጠው በሁለቱ ማለትም ኤርትራ  ከሱዳን እና ከግብፅ ጋር ያላት ግንኙነት ዙርያ ተወያዩ ከማለት በቀር ዝርዝር ጉዳይ ያወሩት የለም።በኤርትራ የሚድያ ነፃነት ካለመኖሩ አንፃር ከእዚህ የበለጠ ሊያወሩ አይችሉም።ሚድያዎቹ አይደሉም በአቶ ኢሳያስ የስልጣን ወንበር ላይ ያሉም ዝርዝሩን የማወቅ እድሉ አይኖራቸውም።አቶ ኢሳያስ በሚያደርጉት ጉብኝት ረዳታቸውን አቶ የማነን አስከትለው እንጂ ሌሎች ሚኒስትሮችን አስከትለው አይሄዱም።ሌሎቹን ጉዳዮች አቶ ኢሳያስ ከጉብኝት ወደ  አስመራ ሲመጡ መጥነው እስክነግሯቸው መጠበቅ አለባቸው።

የአቶ ኢሳያስ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ግብፅ ያደረጉት ጉብኝት በኤርትራ በኩል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳለህ፣ አቶ የማነ ገብረአብ እና አምባሳደር ፋሲል ገብረስላሴ የተገኙ ሲሆን በግብፅ በኩል ደግሞ የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሽኩሪ፣ የደህንነት ሚኒስትሩ አባስ ከማል እና  የእርሻ ሚኒስትሩ መሐመድ ማርዙቅ ተገኝተዋል።የአቶ ኢሳያስ በሱዳንም ሆነ በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ዓላማዎች ሁለት  ናቸው።

የመጀመርያው ዓላማ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ወገን ወግና በግብፅ እና በሱዳን ላይ እያሴረች አለመሆኗን እና እንደ ገለልተኛ ሀገር እንድትታይ ለማድረግ ነው። አቶ ኢሳያስ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረጉት መቀራረብ በግብፅ እና በሱዳን ዘንድ የተገለሉ እንዳይሆኑ ይፈልጋሉ።ስለሆነም አንድ ዓይነት የዲፕሎማሲ ሥራ  ማድረግ ነበረባቸው።

ሁለተኛው ዓላማ፣ የግድቡ ጉዳይ የአካባቢው ሀገሮችን የትብብር ዕቅድ እንዳያሰናክል ጉዳዩን ማለሳለስ ነው።እዚህ ላይ አቶ ኢሳያስ አሳማኝ ነጥቦችን ይዘው ካልሄዱ በግድቡ ጉዳይ ያለውን ውጥረት ማለሳለስ አይችሉም።ስለሆነም ሁለት ነጥቦችን ይዘው ነው ወደ ሱዳን እና ግብፅ የሄዱት።አንዱ ለአካባቢው ዋና ስጋት የህወሓት የታጠቀ ኃይል መኖሩ መሆኑን ማስረዳት ሲሆን ሁለተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን በሚገባ አልተረዳችሁትም፣እርሱ ፈፅሞ ግብፅን እና ሱዳንን የሚጎዳ ሥራ አይሰራም።ይልቁንም እርሱ እስካለ ድረስ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ማተኮሩ የተሻለ ነው የሚሉ ሃሳቦች ናቸው።እነኝህ ሃሳቦች ከኤርትራ መምጣታቸው ግብፅን በተወሰነ ደረጃ አያሳምንም ማለት አይቻልም።ባያሳምናትም አሁን ባለችበት ደረጃ ምንም ልታደርግ አትችልም። ሆኖም አቶ ኢሳያስን ''አንተ ካልክ'' በሚል ከኤርትራ ጋር  ወዳጅነቷን ለማቆየት ትጠቀምበታለች።አቶ ኢሳያስ ግብፅን ከአልሲስ  በላይ ያውቃሉ።የሻብያ እንቅስቃሴ ዋና መነሻ ካፒታል የተፈጠረባት ሃገርን ሊረሱ አይችሉም።በመሆኑም የግብፁን ፕሬዝዳንት በአካባቢው ለረጅም ጊዜ እንደቆየ ሽማግሌ መሪ ፕሬዝዳንት አልሲስን ቆጣ እያሉ እንዴት ነው ዓብይን የማትረዳው? ቢሉ ላያንስባቸው ይችላል።

ይህ በእንዲህ እያለ ግብፅ የኢትዮጵያን የመልማት እና የመብራት የማግኘት መብት በማይቃረን መልኩ አዲስ የስምምነት ፕሮፖዛል አለኝ ማለት መሰማቱ ቀድሞም በውስጥ ኢትዮጵያን ለማበጣበጥ ከመሞከር በላይ ምንም ልታደርግ ያልቻለችው ግብፅ የአቶ ኢሳያስ ጉብኝትን እንደ አንድ ምክንያት ልትጠቀምበት ትችላለች።ግብፅ ከሰሞኑ በዓባይ ጉዳይ ባልተጠበቀ ሁኔታ ልትለሳለስ ትችላለች።የምትለሳለሰው ግን በአቶ ኢሳያስ ጉብኝት አይደለም።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ እና የለውጥ ኃይሉ ለለውጥ ሂደቱ ስጋት የነበረውን የመጨረሻውን የኃይል ሚዛን በአሸናፊነት ስለተወጣው ነው።


ነፍሰ ጡር በምጧ ጊዜ እንድትጨነቅ ሁሉ ኢትዮጵያም የጎሳ ፖለቲካን አሽቀንጥራ ለመጣል የመጨረሻ የመገላገያ ጊዜ ላይ ደርሳለች 

ባጠቃላይ አሁን በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ወደ የከፋ መስመር የሄደ ቢመስላቸውም ዕውነታው ግን ተቃራኒ ነው። በእርግጥ ነው ብዙዎች በፅንፈኛ የኦሮሞ አክራሪዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣የንግድ ቤታቸው እና መኖርያቸው ወድሟል።ሆኖም ግን ነፍሰ ጡር በምጧ ጊዜ እንድትጨነቅ ሁሉ ኢትዮጵያም የጎሳ ፖለቲካን አሽቀንጥራ ለመጣል የመጨረሻ የመገላገያ ጊዜዋ ላይ ነች። ስለሆነም ህመም አለው።ህመሙ ግን የአጭር ጊዜ ህመም ነው።ተመልሳ ወደ የጎሳ ፖለቲካ የማትገባበትን የጋራ ቃል ኪዳን የምታፀናበት ብሩህ ጊዜም እየመጣ ነው።መታመማችን ለበጎ ነው።ጎሰኘነትን መልሶ የሚጭን የፖለቲካ ስርዓት ፈፅሞ የማይሸከም ሀገር እና ሕዝብ ከእዚህ ሁሉ ፈተና መሃል ጠንክሮ ይወጣል።

ጉዳያችን 




ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...