ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, December 5, 2023

በአማራ ክልል በሚደረገው ጦርነት ሳብያ የአማራ ክልል ህዝብ ላይ እየደረሰ ስላለው ሰቆቃ ያልሰማነው ከሰማነው ይበልጣል።


  • መከላከያ ክልሉን ለቆ ይውጣ የሚለው  አባባል የአማራ ክልል ጥያቄ ነው?
==========
ጉዳያችን ምጥን
=========

ወቅታዊው ሁኔታ

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ትልቁ አጀንዳ በአማራ ክልል በታጣቂዎች እና በመከላከያ መሃከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ነው።''ሁለት ሰዎች ሲጣሉ ችግሩ ቀላል ሊሆን ይችላል።ሁለት ሺህ ህዝብ ከሁለት ሺህ ህዝብ ጋር ሲጣላ ግን ጉዳዩ ጦርነት ነው '' የሚል አባባል አለ። በኢትዮጵያ አሁን እየሆነ ያለው ከተራ ግጭት ባለፈ ትርጉም የማይሰጥ የወንድማማቾች አሳዛኝ ጦርነት እየተደረገ ነው። ጦርነቱ ከመከላከያም ከታጣቂዎችም ሆነ ከሰላማዊው ህዝብ የሚወድቀው ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ የማትተካው ውድ የሰው ህይወት ነው። በአማራ ክልል አሁን ያለው ጦርነት መነሻ ምክንያት እና መፍትሄው በተመለከተ ከስድስት ወር በፊት ጉዳያችን ላይ ''የኦነግ/ኦህዴድ እና የህወሓት ጽንፈኝነት የአማራ ጽንፈኝነትን ወለደ። ኢትዮጵያን መልሰን ወደ አንደኛ ክ/ዘመን እንዳንከታት መንግስት የኃይል መንገድን ብቻ ከማሰብ ይልቅ ቀድሞ መከወን ያለበት ተግባር ላይ ያተኩር።'' በሚል ርዕስ ላይ ለመግለጽ ስለሞከርኩ እርሱን እዚህ ላይ ለመድገም አልፈልግም።ከእዚህ ይልቅ በወቅታዊው የአማራ ክልል ሁኔታ አንጻር ህዝቡ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ዙርያ የተወሰኑ ነጥቦችን ላንሳ። እዚህ ላይ በአማራ ክልል ህዝብ ላይ በእዚህ ጦርነት ሳብያ እየደረሰ ያለውን ፈተና በውጭ የሚገኙ ዩቱበሮች ፈጽመው አያነሱትም።ዩቱበሮቹ ''ታጣቂዎች ይህንን ያዙ'' የሚል ዜና ላይ እንጂ በእዚህ ጦርነት የክልሉ ህዝብ የደረሰበት ማኅበራዊ፣ምጣኒያዊ ሐብታዊና ስነልቦናዊ ችግር ጥልቀት የሚናገር የለም።

አሁን በአማራ ክልል በሚደረገው ጦርነት ሳብያ የአማራ ክልል ህዝብ ላይ እየደረሰ ስላለው ሰቆቃ ያልሰማነው ከሰማነው ይበልጣል።

በአማራ ክልል ከተነሳው ጦርነት በኋላ የህዝብ ትራንስፖርት በአብዛኛው የክልሉ ከተማና ገጠር መሃል ግንኙነት ተቋርጧል፣ኢንተርኔት ለተወሰኑ ተቋማት ከመፈቀዱ በላይ ባብዛኛው ቦታ አይሰራም፣ከሁለት ሚልዮን ያላነሱ ህጻናት፣ታዳጊዎችና ወጣቶች ወደ ትምህርት ቤት እየሄዱ አይደለም።በጦርነቱ ሳብያ ከታጣቂዎችም ሆነ ከመንግስት ድሮን ጭምር የሚወነጨፉ አረሮች ሰላማዊ ህዝብንም ለሞት እየዳረገ ነው።የድሮን ጥቃቶቹን ተከትሎ ቢቢሲ ያነጋገራቸውን ጨምሮ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን አረጋግጠውታል።

የክልሉ ህዝብ መከራ ግን በእዚህ አላበቃም ጉዳያችን በክልሉ ከሚገኙ ሦስት ከተሞች ለማጣራት እንደሞከረችው በአማራ ክልሎች ውስጥ የሚኖረው ህዝብ በቀትር ፀሐይ በሚዘርፉ ሌቦች ችግር ላይ ነው።''ቀን በቀን ይዘርፉሃል።'' አለ አንድ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ነዋሪ የሆነ ወጣት ለጉዳያችን አሁን ያለውን ሁኔታ ሲናገር።'' መንገድ ላይ ጩቤ አውጥቶ ሞባይል ይሁን ምንም የያዝከውን ይዘርፍሃል።'' በማለት ቃሉን ሰጥቷል። ወጣቱ ማን እንደሚዘርፍ ሲጠየቅ ''ማን እንደሆኑ አይታወቅም። ዝርፍያው በምሽትም ነው።አጋጣሚውን ተጠቅሞ ለመክበር የሚፈልግ አለ።'' በማለት አብራርቷል።

በተመሳሳይ በምስራቅ ጎጃም ነዋሪ ከሆነ ወንድሙ ጋር የተገናኘ የጉዳያችን አንባቢ በከተማዋ ያለውን ሁኔታ ሲገልጽ ወጥተን መግባት ስጋት ሆኖብናል።ከየት እንደተተኮሰ በማታውቀው ጥይት የመሞት አደጋ በራችን ላይ ነው በማለት የነገረውንና ከወጣቱ አንደበት የሰማው ከፍተኛ የፍርሃት፣የተስፋ መቁረጥና የሃዘን ስሜት ባነጋገረው ወቅት እንደተረዳ ሲገልጽ። '' እኔ በባህር ማዶ እያለሁ።ከርሱ ጋር ባደረኩት ንግግር እስካሁን ያጋባብኝ የሃዘን ስሜት አልለቀቀኝም'' በማለት ነበር የገለጸው።

አሁን በአማራ ክልል ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የጦር ሜዳው ገባ ወጣ ዜና ነው እንጂ የህዝቡን እውነተኛ ሰቆቃ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ግብ ተብሎ በዩቱበርም በመንግስት ሚድያም አይነገርም። ይህ በራሱ የሚያም ትልቅ ስብራት ነው።በአማራ ክልል ውስጥ ያለው ህዝብ ከረሃብ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የሃብት ውድመት እና ስነልቦናዊ ጥቃት ደርሶበታል።መንግስት በሚጠራቸው ስብሰባዎች ላይ የተለየ ሃሳብ ቢናገር ከታጣቂዎቹ ደጋፊዎችም ሆነ ከመንግስት ካድሬ ነገ እንዲህ ሊያደርጉኝ ይችላሉ በሚል ተሳቆ እውነቱን ለመናገር ተቸግሯል።

የክልሉ ህዝብ አሁን የናፈቀው ሰላም መቼ ነው የሚመጣው የሚለውን ጥያቄ የሚመልስለት ነው።ጉዳያችን ያነጋገረችው የደቡብ ጎንደር ነዋሪም ስራ ሁሉ መቆሙን ህዝብ ያለበትን የፈተና ደረጃ ከገለጸ በኋላ ችግሩ የሚፈታበት መንገድ እንዳይመጣ አንዱ ሽማግሌ ሃሳብ ቢያነሳ የመንግስት ደጋፊ ፋኖ ስለሆንክ ነው ይሉታል፣ ስለሰላማዊ ሃሳብ የሚያነሳ ሲሆን ደግሞ የብልጽግና ካድሬ ነህ ይሉታል።ስለሆነም የችግሩ ስፋት እንዲህ ቀላል አይደለም።በማለት አብራርቷል።በምስራቅ ጎጃም ነዋሪን ያነጋገረው የጉዳያችን አንባቢም ተመሳሳይ ሃሳብ አግኝቷል።በምስራቅ ጎጃም ነዋሪ የሆነው የክልሉ ነዋሪ ከሁሉም ያናደደው በክልሉ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በውጭ ያሉ ዩቱበሮች እንደማይናገሩ መስማቱን ነበር። ኢንተርኔት ከመጥፋቱ በፊትም ሆነ አሁን በሚሰራበት መስርያቤት አልፎ አልፎ በሚለቀቀው የኢንተርኔት መስመሮች በውጭ የሚኖሩ ዩቱበሮች ስለ ታጣቂዎቹ እንጂ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ስላለው መከራ አንዳች አለማውራታቸው በስማችን የሚነግዱ ለመሆናቸው ማስረጃ ነው በማለት በብሽቀት ገልጾለታል።

አንዳንዶች ይህ ተራ የስም ማጥፋት ወይንም የዩቱበሮቹን አመለካከት ለመጻረር የቀረበ ሊመስለው ይችል ይሆናል።ነገ ህዝቡ የሚናገረው እውነት ይሄው እንደሚሆን ጊዜ ያሳየናል።በክልሉ እየሆነ ያለው ብዙ ያልተነገረ ጉዳይ አለ።ከዘረፋው ወደትምህርት ቤት መሄድ ካልቻለው በላይ በክልሉ ከአስር ሺህ በላይ ቀዶ ጥገና ቀጠሮ ያላቸው የክልሉ ነዋሪ ህሙማን በጊዜ ቀዶ ጥገና ማድረግ ባለመቻላቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑን የራሱ የክልሉ ሚድያ የዘገበው ነው።ችግሩ የትዬለሌ ነው።ይህንኑ ግን የሚነግረን ሚድያ የለም።

መከላከያ ክልሉን ለቆ ይውጣ የሚለው  አባባል የአማራ ክልል ጥያቄ ነው?

''መከላከያ ክልሉን ለቆ ይውጣ'' የሚለው አባባል በመጀመርያ ህወሃት በትግራይ ሲያቀነቅነው ነበር። ዛሬ ላይ ደግሞ ሸኔ ይህንኑ በኦሮምያ እንዲደረግ ሲጠይቅ ተሰምቷል። ይህንን ጥያቄ የአማራ ክልል ህዝብ እንደጠየቀ ተደርጎ በአንዳንድ ዩቱበሮች ሲነገር መስማት ደግሞ የቅርቡ ክስተት ነው።የአማራ ክልል ህዝብ ከመከላከያው መሃል ህዝብ የበደሉ ለፍርድ ይቅረቡ ይላል እንጂ መከላከያ ክልሉን ለቆ ወጥቶ የመንግስት መዋቅር ለቆ እንዲወጣ አይፈልግም።መከላከያ አንድ ክልል ለቆ ወጣ ማለት ትርጉሙ ምን ማለት ነው? ይህንን ተከትሎ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖር ክልል ምን ሊገጥመው ይችላል? አሁን ከደረሰበት ፈተና መልኩን ቀይሮ በምን ዓይነት የከፋ ችግር ላይ እንደሚወድቅ ለመተንበይ ሊቅ መሆን አይጠይቅም። ዛሬም ግን በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ በሚጠይቁ ሳይቀር መከላከያ ከ''ክልሉ ይውጣ'' ንግግር ሲነገር እየሰማን ነው።መከላከያ ከክልሎች ለቆ ይውጣ በራሴ ታጣቂ እተዳደራለሁ ማለት ሌላ ምንም ትርጉም ያለው ሳይሆን ኢትዮጵያ ትፍረስ፣በእየጎጣችን እንግባ የማለት ያህል ነው። አንዳንዶች ይህ ሲነገር ጉዳዩን ከጦርነቱ ጋር አያይዘው ብዙ ጉዳዮች ሊያነሱ ይችላሉ። ይህ መከላከያ ለቆ ይውጣ የሚለው አባባል ሶርያዎችም፣ሊብያዎችም ሆኑ የመኖች ከመፍረሳቸው በፊት የነበረ ዜማ ነው። አንዳንዴ አጀንዳዎቹን እነማን ከየት ቀድተው እንደሚያቀብሉን እየተረዳን ያለን አንመስልም።

ለማጠቃለል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሌላው ዓለም የተለየ ችግር አልገጠመውም።መፍትሄ የሌለው ችግርም የለም። የችግሮቻችን መነሻ ምክንያቶች በዛሬዋ ቀን ወይንም ምሽት የተፈጠሩባት አይደሉም።የረጅም ጊዜ የከመርናቸው የተሳሳቱ ትርክቶች፣የውስጥ ሴራዎች እና የባዕዳን እጅ ጭምር ናቸው። በእዚህ ጹሑፍ መነሻ ላይ በተያያዘው ሊንክ ላይ እንደተገለጸው በአማራ ክልል ላለው ችግር መነሻው በኦሮምያ ክልል የተነሳው የጽንፍ ኃይልና ይሄው ኃይል ደግሞ በመንግስት መዋቅር ውስጥ እንደፈለገ መስራቱ እንደሆነ ተብራርቷል።ወደመፍትሄው ለመምጣት ግን አሁንም ከእዚህ በፊት የክልሉ ግጭት ሲጀምር በነሐሴ ወር በጉዳያችን ላይ ቢወሰዱ ያልኳቸው የመፍትሄ ሃሳቦች አሁንም ዳግም ቢታዩ በማለት ይህንን የጉዳያችን ምጥን እቋጫለሁ።የመፍትሄ ሃሳቡ ሊንክ ''በአማራ ክልል የተነሳው አለመረጋጋትን በፍትሐዊ እና ርቱዕ በሆነ መንገድ ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማድረግ የሚገባቸው ሦስት ተግባራት።'' በሚል ርዕስ የጻፍኩትን ሳላስታውስ አላልፍም።

==================//////==========

Sunday, November 26, 2023

በውግዘት ውስጥ ላሉት፣አሁንም በድፍረት ለሚሄዱት ለትግራይ የቀድሞ ጳጳሳት አልቅሱላቸው።


  •  አክሱም ጽዮን በክርስትና ታሪክ ለሁለት ሺህ ዓመታት ያህል ያላየችውን የድፍረት ስራ በቅዱስ ሲኖዶስ በተወገዙት የትግራይ አባቶች እያየች ነው።
  • የእነርሱን አካሄድ እየተመለከተ ዝም ብሎ የሚገለገለው የትግራይ ምዕመን፣ የእዚህ ዓይነት አካሄድ ከአባቶቻችን አልተማርንም ተዉ! ማለት ይገባዋል።

እራሳቸውን ከቅዱስ ሲኖዶስ ለይተው፣ክርስትናን በመንደር ለመመተር የሚሞክሩት የትግራይ አባቶች ከቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት እና ስልጣነ ክህነት መያዝ በኋላም አባ ሰረቀን ጵጵስና ሾመናል ብለዋል። ይህ የድፍረት ስራ አክሱም ጽዮን በክርስትና ታሪክ  ለሁለት ሺህ ዓመታት ያህል ያላየችውን የድፍረት ስራ በትግራይ አባቶች እያየች ነው።

ይህ በትግራይ ያሉ አባቶች እያደረጉት ላለው አዕምሮውን የሳተ ሰው ስራ ምንም ሃተታ አያስፈልገውም።ድርጊቱ ስንት የበቁ አባቶች ዘግተው ቀን ከሌሊት ለዓለም የሚጸልዩ አባቶች ባሉባት የትግራይ ክልል እና በአክሱም ጽዮን ፊት የተፈጸመ ድፍረት ነው።ጥፋት በበለጠ ጥፋት አይስተካከልም።በውግዘት ውስጥ ላሉት፣አሁንም በድፍረት ለሚሄዱት ለትግራይ የቀድሞ ጳጳሳት አልቅሱላቸው።አሁን ለአባቶች የሚያስፈልጋቸው ለቅሶ ነው።ከልቦናቸው አይደሉም።ከልቦናው የሆነ አባት ቅዱስ ፓትርያሪክ በብዙ ድካም ከደጁ ሲመጣ የቤተክርስቲያን ደጅ ዘግቶ አይሸሸግም፣ቡራኬ ሊቀበል እየተጣደፈ ሄዶ ጉልበት ስሞ ይባረካል።

አሁን የትግራይ አባቶች ከቀልባቸው አይደሉም።ምን እያደረጉ እንደሆነ፣ምን እየሰሩ እንደሆነ ከአዕምሯቸው ጋር ስላልሆኑ አያውቁትም። አሁን የሚያስፈልጋቸው የሚያደርጉትን አያውቁምና የሚያለቅስላቸው፣ ወደ ቀልባቸው መልሳቸው ብሎ የሚያነባላቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል። የእነርሱን አካሄድ እየተመለከተ ዝም ብሎ የሚመለከተው የትግራይ ምዕመንስ? ቢያንስ የእዚህ ዓይነት አካሄድ ከአባቶቻችን አልተማርንም አይልም? በመንደር ተሰባስቦ ከቅዱስ ሲኖዶስ አንድነት ወጥቶ እንደፈለጉ በመሄድ የሚሰጥ ስልጣነ ክህነትን የትግራይ ምዕመናን ከአባቶቻችን አልተማርነውም።ከየት አመጣችሁት ብሎ አይጠይቅም? 



Saturday, November 25, 2023

Tuesday, November 21, 2023

አቡነ ኤርምያስ ከተናገሩት ውስጥ እውነት ያልሆነ አንድ ቃል ማግኘት አልቻልኩም።

አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
  • ''በማንም ተጽዕኖ ውስጥ ወድቄ በማንም ተናገር ተብዬ የተናገርኩት የለም.።ወደፊትም እናገራለሁ ብዬ አላስብም።መንፈስቅዱስ ይጠብቀኝ። '' አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ

=========
ጉዳያችን ምጥን
=========

የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ኤርምያስ ሰሞኑን ከላስታ ላሊበላ ህዝብና ካሕናት ጋር በተደረገ ስብሰባ ላይ የተናገሩትን መነሻ በማድረግ ሁሉም ለምን የእኔን ሀሳብ አላንጸባረቁም? በሚል የተለያዩ ስሞታም፣ወቀሳም አለፍ ሲልም ዘለፋ ሲዘነዘር እየሰማን ነው። በሌላ አንጻርም አቡነ ኤርምያስ የተናገሩት እውነት መሆኑን የተናገሩም፣የመሰከሩም አሉ።በአቡነ ኤርምያስ ከተናገሩት አንዳንዶችን የከነከናቸው ነገር ግን በቀጥታ ጉዳዩን ሳያነሱ ዙርያ ጥምጥም የሚሄዱባቸው ሦስቱን ነጥቦች ብቻ እንመልከት።ወደ ሦስቱ ነጥቦች ከመሄዴ በፊት ለሁሉም ግንዛቤ እንዲሆን ሁለት ነጥቦች ላንሳ።

የመጀመርያው ነጥብ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የስነ መንግስት ጉዳይ የማይገባቸው እንዲያው ካለ እውቀት እንደተናገሩ አስመስለው የሚያቀርቡ በጣም እንደተሳሳቱ ማስረዳቱ ጥሩ ነው።የአባቶች ብቃት ከዓለማዊው ትምሕርት ባለፈ መንፈስቅዱስ ባወቀ የሚረዱትን የመረዳት አቅምም መኖሩን ማሰብ ተገቢ ነው።

ሁለተኛው ነጥብ፣የስነ መንግስትን ጉዳይ መግፋት የቤተክርስቲያን ጉዳይ አይደለም።ይህም ሆኖ በነባራዊው ዓለም ላይ የምትኖር ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ዘመንም የመንግስት ጉዳይ አንስተው ክርስቶስን ለመፈተን ''ከፈሪሳውያንና ከሔሮድስ ወገን ሰዎችን ላኩ'' በማለት  መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለው ቃል ይነግረናል። ንባቡ እና የአባቶቻችን ትርጓሚ እንደሚከተለው ነው።

የማርቆስ ወንጌል 12፣14 - 17  ''መጥተውም። መምህር ሆይ፥ የሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለን፤ ለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? እንስጥን ወይስ አንስጥ? አሉት። እርሱ ግን ግብዝነታቸውን አውቆ። ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አየው ዘንድ አንድ ዲናር አምጡልኝ አላቸው። እነርሱም አመጡለት። ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው፤ እነርሱም። የቄሣር ናት አሉት።ኢየሱስም መልሶ። የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው። በእርሱም ተደነቁ።''

በአባቶቻችን ትርጓሜ ጌታችንን ለመፈተን የመጡት ግብር መስጠት ተፈቅዷል ካለን ይሄ ምድራዊ ነው እንጂ ሰማያዊ አይደለም ስለምድራዊ ግብር ያወራል ሊሉት፣ ግብር አትስጡ ቢላቸው ደግሞ ለመንግስት ሄደው ግብር አትክፈሉ የሚል ተነስቷል ብለው ሊከሱት እንደሆነ አውቋልና ዲናሯን አምጡ ብሎ ዲናሩ ላይ ያለችውን ጽሕፈት አሳይቶ የቄሳርን ለቄሳር፣የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሄር ስጡ ብሎ በመመለሱ የሚከሱበት አጡ በማለት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አብራርታ ታስተምራለች።

ቤተክርስቲያንን ከፖለቲካ ዕይታቸው አንጻር ለመለወስ እና ጥፋት ነቁጥ ለመንቀስ የሚደክሙ በየትኛውም የጎሳ ስብስብ ውስጥ ቢሆኑ ከላይ ከተጠቀሱት ከፈሪሳውያንና ከሔሮድስ ወገን አስተሳሰብ የተለዩ አይደሉም። አቡነ ኤርምያስ የአባትነታቸውን የተናገሩትን እውነት ለአንዳንዶች የራስ ምታት ቢሆንባቸውም ዕውነትነቱ ላይ ግን የሚያመጣው አንዳች ለውጥ የለም።

አቡነ ኤርምያስ ከተናገሩት ውስጥ እውነት ያልሆነ እስኪ አንዲት ቃል አውጡ? 

''አራት ኪሎ ቢገባስ''

አንዳንዶች የአቡነ ኤርምያስን እውነት አልዋጥ ካላቸው ውስጥ በቀጥታ አያናገሩትም እንጂ ከላይ በተጠቀሰው መድረክ ላይ ከተናገሩት  ቀደም ብለው ችግሮች እንዳይፈጠሩ ለእርቅ የሄዱበት መንገድ እንደነበርና በኋላ አንድም ካህን ቢመጣ በጥይት እንለዋለን ድረስ የሚሉ ቃላት በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በኩል መሰማቱን በመጠኑ ጠቁመው፣ በታጣቂዎቹ አካሄድ ላይ ግን እንደማይስማሙ አባታዊ ምክራቸውን ሲለግሱ እንዲህ ብለዋል ''በወንድሞቼ አካሄድ አልስማማም። ደግሞስ አራት ኪሎ ቢገባስ'' ካሉ በኋላ ዘላቂ  መፍትሄ እንደማይሰጥ ይህ ደግሞ ሌላው እስኪዘጋጅ እንጂ ዘላቂ ሀገራዊ ሰላም እንደማያመጣ መክረዋል። ከእዚህ ዕውነት ውስጥ ምን ውሸት መንቀስ ይቻላል? በ21ኛው ክ/ዘመን ስልጣን በጠበንጃ በመነጣጠቅ መፍትሄ እንደማይመጣ ከእዚህ ይልቅ ሌሎች የሰላማዊ የትግል መንገድ መከተል አስፈላጊነት ላይ ምን ስህተት ይወጣለታል?

''ላሊበላ ለምን ከተሙ?''

አቡነ ኤርምያስ ያነሱት ሌላው ነጥብ ላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ ብቻ ሳይሆኑ ከተማዋ በራሷ ከተማ ሳትሆን የተቀደሰ ቦታ ነች።መገዳደል ያስቀስፋል በሚል የገለጹበት እውነት ነው። በእዚህም ላሊበላ መክተም ለምን? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ እና ከገዳሙ አውጥቶ መግደል ምን ዓይነት ህሊና እንደሆነ የገለጹበት መንገድ ምን ነቁጥ ይገኝበታል?

''ውጪ ሆነው ሬሳ እየሸጡ የሚኖሩ''

ይሄ ውሸት ነው? የዩቱበር ሸቀጥ ለመሸቀጥ ያልሞተ ሞተ፣የወደቀውን ተሰበረ፣ እያለ በውጭ ሀገር ሶፋ ላይ ተቀምጦ የራሱን ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እየላከ በአማራ ክልል ከሦስት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ልጆች እስከ ኅዳር ወር መጀመርያ ድረስ በጸጥታ ችግር አለመመዝገባቸው ትንሽ ቅሬታ ያልፈጠረበት፣ነገር ግን ''በለው!'' እያሉ ሲፎክሩ የሚውሉ እያየን አይደለንም እንዴ? እነኝህ አስከሬን ካልታየ ዩቱባቸው ይሸጣል? ይህንን እውነት ለምን እንክዳለን? የህወሓት አድናቂዎች በትግራይ ምስኪን ህዝብ ሞት ከውጭ ሆነው ሲያበረታቱ የነበሩ ዛሬ ሞቶን እና መርዶውን ለምስኪን የትግራይ እናቶች አስታቅፈው እነርሱ ዛሬ የት ናቸው? በአማራ ክልልስ እየሆነ ያለው በወሬ የሬሳ ሽያጭ መነገድ የተለየ ነገር አለ? 

''በጦርነት ሰላም አይመጣም፣ ወንድም ወንድሙን አጥቅቶ፣ፋኖ መከላከያን አጥቅቶ ወሰን ሊያስከብር አይደለም፣ ጉዳዩ ይህ እንደ ሀገር ያሰጋል።''

እዚህ ላይ የሚነቀስ ምን ውሸት አለ? እውነቱን ከሚናገሩት ጥቂቶች በቀር፣ ሁሉም ''ካድሬ ይሉኛል'' ብሎ አፉን ይዞ ነው እንጂ ምንም ይሁን ምን መከላከያውን የበላ ህዝብ የሚበላው ጠላት ዕለቱን መጥቶ እንደሚበትነው፣ እርስ በርሱም ወደ የማያባራ ጦርነት እንደሚገባ ከሶርያ ባንማር፣ከሊብያ፣ከሊብያ ባንማር ከየመን፣ ከእነኝህ ሁሉ መማር ቢያቅተን እንዴት ከቅርብ ጎረቤታችን ሱዳን መማር አቃተን። አቡነ ኤርምያስ ሀገር እንዲህ መሄድ የለበትም ሲሉ አለመስማት ብቻ ሳይሆን ለስድብ አፍን ማሾል ምን ዓይነት መረገም ነው?

አቡነ ኤርምያስ በእዚሁ መድረክ ላይ መንግስትንም በተገቢ ቃላት ወቅሰዋል።በአማራ ክልል የሚገኙ ታጣቂዎችን ጉዳይም ለመንግስት በሚገባ አካሄዱን እንዲፈትሽ ሲያሳስቡ ከተናገሩት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል 
  • የተቆጡ ወገኖች አሉ።ሁላችንም እኔንም ጨምሮ ተቆጥተናል።
  • እነኝህ ወገኖች ከመከላከያ ጋር አብረው የተዋደቁ ናቸው።
  • መንግስት ዝቅ ብሎ ለእነኝህ ወገኖች የሚመጥን መድረክ መንግስት አዘጋጅቶ መፍትሄ ማምጣት አለበት።
  • ክርስቶስ ዝቅ ብሎ መጥቶ አዳምን አድኖ የነበረበትን መንገድ ምሳሌ ጠቅሰዋል።
  • መከላከያ ከገባ በኋላ ተፈጽሟል የተባለውን ዘረፋ መከላከያ አጣርቶ ይህንን ያደረጉትን እንዲቀጣ አሳስበዋል።
  • ''የመረረው ድሃ ይገባል ከውሃ'' እንዲሉ መንግስት ባለበት ሀገር ዛሬ ከዋና ከተማዋ ተነስቶ ሰው እንዴት ለመሄድ የሚፈራበት ሁኔታ ይፈጸማል?
እና ሌሎችም ምክረሃሳቦችን አቅርበዋል።

ለማጠቃለል፣ከአቡነ ኤርምያስ ምክረሃሳብ ውስጥ የሚገኝ አንድ ውሸት ካለ እስኪ አውጡ? ስለሌለ የምታወጡት አንድም ውሸት የለም። በእዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከተሳታፊዎች ደጋግሞ ከተነሳው ቅሬታ ውስጥ አንዱ እና ህዝቡን ያስቆጣው ጉዳይ ግን ነበር። የከባድ መሳርያ ድምጽ በእዚያ መጠን ለምን እንዲተኮስ ተደረገ የሚለው ገዢው ሃሳብ ነው። ይህንን ጉዳይ መከላከያ በከፍተኛ ትኩረት ሊመለከተው የሚገባ ነው።አሁንም ወደ ህዝቡ ወርዶ የሚሰጠው ማብራርያ ካለ ጉዳዩን ማብራራት አለበት።ይህ ጉዳይ የአብዛኛው ተሳታፊን እና ካሕናቱን አስተያየት የሸፈነ ነበር። አቡነ ኤርምያስ ዘግይተው በሰጡት ማብራርያ ደግሞ ''በማንም ተጽዕኖ ውስጥ ወድቄ በማንም ተናገር ተብዬ የተናገርኩት የለም.።ወደፊትም እናገራለሁ ብዬ አላስብም።መንፈስቅዱስ ይጠብቀኝ። '' በማለት ተናግረዋል።ሀገርን ያለ አንድ መስካሪ ባዶ አይተዋትም። 

የአቡነ ኤርምያስን እና የተሳታፊዎችን አስተያየት የያዘው ቪድዮ



 

Tuesday, November 14, 2023

በአጼ ቴዎድሮስ፣ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴና ኮ/ል መንግስቱ ላይ የሰራነውን የመሪዎቻችንን በጎ ሀሳብ የመጎተት ክፉ ባሕል በጠ/ሚ/ር ዐቢይ ላይ አንደግምም!


ፎቶ - አጼ ቴዎድሮስ፣አጼ ኃይለስላሴ፣ኮ/ል መንግስቱና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
  • ዛሬ አጼ ቴዎድሮስ፣ቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ፣ ኮ/ል መንግስቱ እያልን ስንጣራ መሪዎቹን ክነበረ ህልማቸው በየዘመናቸው ያልጎተትን  ጨዋዎች እንመስላለን።
============
ጉዳያችን ምጥን
============

የመሪዎቻችንን በጎ ሀሳብ ጎታቾቹ እኛ!

ኢትዮጵያ በታሪኳ ድንቅ መሪዎች መርተዋታል። የመሪዎቿን አስደናቂነት እኛ ከጻፍነው በላይ በየዘመኑ ''ሰለጠኑ'' ከሚባሉ ሀገሮች የመጡ ጸሐፊዎች የጻፉት እና አድንቀው የገለጡበት መንገድ ይበልጣል። ድንቅ የተባሉ መሪዎቻችንን ርዕይ በመጎተት ወደፊት እንዳይሄዱ በማድረግ ግን የሚያክለን የለም።

አጼ ቴዎድሮስ

አጼ ቴዎድሮስ በቀድሞ ስማቸው ካሣ፣ከቋራ ምዕራብ ጎንደር ተነስተው የኢትዮጵያ ንጉሰነገስት ለመሆን ሲነሱ አንዱና ዋናው ዓላማቸው  በዘመኑ በዘመነ መሳፍንት ታውካ የነበረችው ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ እና ወደ የቀደመ ክብሯ መመለስ መሆኑን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መናገራቸውን የታሪክ ድርሳናት ያሳዩናል። ንጉሱ ከነገሱ በኋላ በወረራ ውስጥ ያለች ኢየሩሳሌምን ገና ነጻ ያወጣሉ ተብሎ ይነገርላቸውም ነበር። ይህንንም አዝማሪ ሳይቀር
 '' ካሳ ብሎ ፈረስ ካሳ ብሎ ስም፣
    ዓርብ፣ዓርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም።''

እያለ የሚያበረታታቸው የመኖሩን ያህል፣ ሌት ተቀን እጁን በአፉ ላይ አድርጎ ሲያማ የሚውልም ነበር። ንጉሱ አይቻልም የሚሉት ነገር የለም።ኢትዮጵያ ከመላው ዓለም ጋር የነበራት ግንኙነት ከ16ኛው ክ/ዘመን በኋላ በጣም በተዳከመበት ዘመን የነበሩት ንጉስ ከአውሮፓ የሚመጡ ጥቂት ሰዎች ጋር በጥልቅ በመወያየት ስለ ቴክኖሎጂ በመረዳታቸው ሴቫስቶቮል የተሰኘ መድፍ ለማሰራት ጥረት ያደርጉ መሪ ናቸው። እኝህ የኢትዮጵያን አንድነት ከዘመነ መሳፍንት በኋላ ለመመለስ ህይወታቸውን ሰጥተው የታገሉ መሪ፣ኢትዮጵያን ከዘመኑ የቅኝ ገዢዎች በደከሙበት የአንድነት ትግል መሰረት የጣሉ እና ኢትዮጵያን ለማሻገር ቀን ከሌሊት ያለሙ መሪ በመጨረሻ ላይ እኛ ጎታቾቹ እንግሊዞች ሲወሯቸው መቅደላ ላይ ብቻቸውን አጋፍጠን፣ እራሳቸውን እንዲሰዉ ከማድረግ በላይ ልጃቸውና ባለቤታቸው ታግታ ስትወሰድ ያጀብን መሆናችንን ማሰብ አለብን። በወቅቱ ከንጉሱ በኢትዮጵያ ላይ ከነበራቸው ህልም ይልቅ የመንደር ቂጣ መጉደል ከትልቅ ነገር ወስደው በንጉሱ መሞት ላይ የፈነደቁ ነበሩ። የእኛ ታሪክ ለኢትዮጵያ ህልም የነበራቸውን መሪዎች እግር መጎተት የነበረ አሳፋሪ ታሪካችን ነው።

አጼ ኃይለሥላሴ 

አጼ ኃይለሥላሴን እግር የመጎተት ሥራ የተጀመረው ገና አባታቸው ራስ መኮንን የአጼ ምንሊክ ባለሟል ሆነው ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ የጀመረ ነው።አጼ ኃይለስላሴ ከአልጋወራሽነት ዘመናቸው በኋላ የጣልያን ጦር ተሸንፎ እንደወጣ የገጠማቸው የእግር ጉተታ ይህ ነው የሚባል አይደለም። ንጉሱ በሱዳን፣በኦሜድላ በኩል ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ጎጃም ላይ ከነበሩት አርበኞች ውስጥ በላይ ዘለቀ አንዱ ነበር። ንጉሱ በጎጃም በተዘጋጀ የእንኳን ደህና መጡ ሰልፍ ላይ አርበኞች በንጉሱ ፊት ሰላምታ እያቀረቡ ሲያልፉ በላይ ዘለቀ ግን የንቀት መልክ አሳይቶ ማለፉን ይህንን ታሪክ የሚያውቁ አባት የነገሩትን የእዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ሰምቷል። ከእዚህ በኋላ ንጉሱ በክብር አስጠርተው ደጋግመው በላይ ዘለቀን አነጋግረውታል። በአንድ ወቅት ንጉሱ ምናልባት በትምሕርት ብዙ አለመግፋቱ ይሆናል እኛ የምናየው የኢትዮጵያ አደጋ ለእርሱ ያልታየው አሁንም ለመሸፈት ያስባል የሚል ዜና ንጉሱ ደርሷቸው በነጻ ወደ ትምሕርት ቤት ከመግባትና የማዕረግ እና የ ሀገር ሹመት የትኛውን እንደሚመርጥ ለበላይ ዘለቀ እስከማቅረብ ንጉሱ ደርሰው ነበር።

ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ኢትዮጵያን ለማሳደግ ጊዜ አትሯቸው ይሮጣሉ። በሌላ በኩል ግን የገበሬ አመጽ አንድ ጊዜ ከጎጃም፣ሌላ ጊዜ ከባሌ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከትግራይ ቀዳማዊ ወያኔ የተነሱ የገበሬ አመጾች ኢትዮጵያን ወደ ዘመናዊ ምዕራፍ ለማሻገር የገጠሟቸው የእግር ጉተታ ፈተናዎች ነበሩ።ንጉሱ በቀረ ዘመናቸው እነኛን ሁሉ የእግር ጉተታዎች አልፈው በእርጅና ዘመናቸው ቀድመው የስልጣን ወንበሩን ሳያስተካክሉ ቢቀሩም በመጨረሻ በተነሳው አብዮት ግን መፍትሄ እንዲሆን የመርማሪ ኮሚሽን ተቋቁሞ ነገሩን በህግ ለመምራት ቢያስቡም፣ወታደሩም መፈንቅል በአራተኛ ክ/ጦር ተሰብስቦ እያደረገ መሆኑን እየሰሙ እና የክብር ዘበኛ ሄደን እንዋጋ ቢላቸውም ''ተዉ! እኛው ያስተማርናቸው ናቸው '' ለክፉ አይጥሉም በሚል ቤተመንግስታቸው ተቀምጠው ቢጠብቁም፣ በመጨረሻ እኛ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ እና ለዓለም ድንቅ ሥራ የሰሩ መሪ ክብራቸውን ያዋረድን መስሎን በቮልስዋገን መኪና ጭነን ከመሳለቅ ባለፈ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርገን እና የቀሩ 60 ባለስልጣኖችን እና ለኢትዮጵያ መልካም የሰሩ ልጆቿን በአንድ ቅዳሜ ምሽት ገድለን  አብዮት ተካሄደ ብለን የፎከርን የአሳፋሪ ታሪክ ባለቤትም ነን። የመሪዎቻችንን እግር መጎተት የነበረ ክፉ ባህላችን ነው።

ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም 

ኮ/ል መንግስቱ የንጉሱን መንግስት ተክተው ''ታሪካ የጣለብን አደራ ነው '' በሚል የወታደራዊ ደርግ እየመሩ ኢትዮጵያን መሩ። ኮ/ል መንግስቱ በመጀመርያ የስልጣን ዘመናቸው ኢትዮጵያ በተለይ ከሱማልያ ለገጠማት ወረራ ያደረጉትን ጥሪ ህዝብ ሰምቶ ኢትዮጵያን ታድጓል።በመቀጠል ከኮ/ል መንግስት የአስተዳደር ግድፈት እንዳለ ሆኖ ነገር ግን የደርግ መንግስት በመራቸው በሦስት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አድምቶ ቢሰራበት ኖሮ እና ከእግር ጉተታ ብንድን ኖሮ ኢትዮጵያን በብዙ መንገድ እናሳድጋት ነበር። ይሄውም የደርግ መንግስት ያቀዳቸው የሰፈራ እና መንደር ምስረታ ( የመለስተኛ ከተሞች ፈጠራ)፣ የመሰረተ ትምሕርት ዘመቻ እና የኢትዮጵያ በቀይባሕር ላይ ያላት ታሪካዊ ባለቤትነት የሚሉት ይጠቀሳሉ። ሆኖም ግን በእነኝህ ቁልፍ ዳዮች ላይ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመደረጉ የመንግስት ተቀያያሪነትን ተገንዝቦ የልማት ፕሮጋራሞቹን ግን ወደፊት ይዞ  ከመሄድ ይልቅ በማጥላላት ላይ ውለን አደርን። ውጤቱ ግን ኢትዮጵያ ከረሃብ ያልተላቀቀች ብቻ ሳይሆን የነበራትን ወደብ ያጣች ሀገር ሆነች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 

በያዝነው 21ኛው ክ/ዘመን መጀመርያ ላይ ኢትዮጵያ ባለችበት የለውጥ ሂደት ላይ ኢትዮጵያን የመምራት ዕድል ያገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአስተዳደራቸው ሂደት ላይ የቱንም ያህል ጥያቄ ያለው ሰው ቢኖር መጠየቁ እና ይህ ይስተካከል፣ ይህ ይታረም ማለቱ እና በምክንያታዊ መንገድ መሞገት በራሱ ጥፋት አይደለም። ይልቁንም ከሴራ አስተሳሰብ በራቀ መንገድ ሙያዊ ሙገታ እና እንዲስተካከል በሰላማዊ መንገድ መታገሉ ሊኖር የሚገባው ነው። ከእዚህ ባለፈ ዛሬም እየደገምነው ያለው የነበረ ክፉ ባሕላችን ግን አሁንም በዩቱበሮች እና የነገን ሳይሆን የዛሬን ከከንፈር እስከ አፍንጫ ብቻ የሚያይ አስተሳሰብ ይዘን ግዙፍ የሆኑ እና ትውልድ አሻጋሪ የሆኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሀሳቦች ላይ ቁጭ ብሎ አቃቂር በማውጣት ከአጼ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ የተሰራውን የእግር ጉተታ እኩይ ተግባር ለመድገም የሚደረገው እሽቅድምድም ሌላ አሳፋሪ የታሪካችን አካል እንዳይሆን ሁሉም ይህ ክፉ ታሪክ እንዳይደገም ለኢትዮጵያ ልዕልና ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዘመን ተሻጋሪ ሀሳቦች ጋር አብሮ መቆም ተገቢ ነው።ስለ የኢትዮጵያ የባሕር በር ሲነሳ የኢትዮጵያን እንጀራ በልቶ እንዳላደገ ሰው ሀሳቡን ችላ ማለት፣ ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ተክል እናልብሳት ሲባል የሚያሾፍ፣ የከተማ ወንዞችን እናልማ ሲባል አቃቂር የሚያወጣ፣ መጻሕፍት ቤት ሙዜየም ሲሰራ ለማቃለል የሚጣደፍ ይህ ሁሉ እግር ጎታችነት ብቻ ሳይሆን የነበረ እኩይ ባሕላችንን የመድገም ሙከራ ነው።ኢትዮጵያውያን አንጸባራቂ ታሪክ ያለንን ያህል የመልካም እና ብሩህ አዕምሮ መሪዎቻችን ለሀገራቸው ያላቸውን መልካም ርዕይ ለማኮሰስ የምንሮጠው ሩጫ እና የእግር ጉተታ አሳፋሪ ነው።የመሪዎች መልካም ርዕይ ትውልድ ተሻጋሪዎች እንጂ የአንድ መንግስት ዕድሜ የሚኖራቸው አይደለም። ስለሆነም ከመሪዎች መልካም ርዕይ ጎን መቆም እና ትውልድ ተሻጋሪ ስራዎች ላይ ሁሉ መተባበር ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን ማወቅ አለብን።


ለመጠቅለል፣ በአጼ ቴዎድሮስ፣ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴና ኮ/ል መንግስቱ ላይ የሰራነውን የመሪዎቻችንን በጎ ሀሳብ የመጎተት ክፉ ባሕል በጠ/ሚ/ር ዐቢይ ላይ አንደግምም። ኢትዮጵያ እንደቀደሙት ዘመናት አትታለልም። ትውልዱም ካለፈው ስህተት በብዙተምሯል።ከዘመን እና ትውልድ አሻጋሪ የመሪዎች ሀሳብን በማንም የባዕዳን እና የባዕዳን ቁራሽ ተመጽዋች እግር ጎታች ሀሳብ አንቀይረውም።
=====================/////===============

Monday, November 6, 2023

የአማራ ክልል ህዝብ የወደቀበትን የመከራ መአት የሚያወራለት አንድም ''ዩቱበር'' አጥቷል። ህዝብ የገባበት ማጥ ሌላ፣ በውጭ ሃገር ሆነው የጥይት ባሩድ የማይሸታቸው የሚያወሩት ሌላ ሆኗል።ስለ የህዝቡ መከራ የሚናገር የለም።ዩቱበሮች ጦርነት ህዝብ የማይጎዳበት አበባ የመበተን ያህል አስመስለው ሲናገሩት ''አጀብ'' ያሰኛል።

ጃናሞራ መሸሃ እርዳታ ሲከፋፈል መስክረም፣2023
  •  ''ከ3 ሚልዮን በላይ ተማሪዎች እስካሁን ትምሕርት ለመጀመር አልተመዘገቡም'' አቶ መኳንንት አደም የክልሉ ምክትል ትምሕርት ኃላፊ፣
  •  ከፍተኛ ረሃብ በክልሉ በተለይ በጃናሞራ መግባቱ ተሰምቷል።የምክር ቤቱ አባል በአቶ ባያብል ሙላቴ የተራቡትን ለመደገፍ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። 
  •  ክልሉ ከአሁኑ ጦርነት በፍጥነት መውጣት ካልቻለ በተጨማሪ የወራት ጦርነት በልማት 60 ዓመታት ወደኋላ ሊቀር ይችላል። 
  • ዝምታው ይሰበር።

============
ጉዳያችን ምጥን
============

 በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት የክልሉን የንግድ፣ኢንዱስትሪና ማኅበራዊ ተቋማት በከፍተኛ ደረጃ እያሽመደመደ ነው።ከአንድ ወር በፊት ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ መስተጓጎሉ የተገለጸ ሲሆን ከትናንት በስቲያ የክልሉ ምክትል ትምሕርት ኃላፊ አቶ መኳንንት አደም እስካሁን ከ3 ሚልዮን በላይ ተማሪዎች የዘንድሮን ትምሕርት ለመማር እስካሁን እንዳልተመዘገቡ ገልጸዋል።ከእዚህ በተጨማሪ ክልሉ የወባ በሽታ አደጋም ተጋርጦበታል።የክልሉ ረሃብ በተመለከተ የተወሰኑ ዜናዎች በመንግስት መገናኛ ብዙኃን ለአንድ ሁለት ቀናት ያህል ከተሰማ በኋላ ስለረሃቡ ብዙም አይሰማም።

ከእዚህ ሁሉ በተለየ በጃናሞር ያለውን የድርቅ ጉዳት ለመደገፍ  በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጃናሞራ ተወካይ አቶ ባያብል ሙላቴ እያስተባበሩ የሚገኙት የቴሌግራም ግሩፕ ላይ በጎ አድራጊዎች የቻሉትን እያደረጉ ይገኛል። የገንዘብ ማሰባሰብያ የባንክ ሂሳብ በጥምረት ማለትም በአቶ ባያብል ሙላቴ፣ፕሮፌሰር ጌታሁን መንግስቱ እና በወ/ሮ እኝሽ ገብሬ እንዲንቀሳቀስ የተደረገ ሲሆን በቴሌግራሙ ገጽ ላይ የተለጠፈው የሂሳብ ቁጥርም ከስር እንደሚከተለው ይታያል።
================================================================
ለጠለምት፣ ጃናሞራና በየዳ ህዝብ ፈጥነን እንድረስት📣

የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 
1️⃣0️⃣0️⃣0️⃣5️⃣7️⃣9️⃣0️⃣9️⃣3️⃣5️⃣6️⃣4️⃣

በሰሜን ጎንደር ዞን (ጃናሞራ በየዳና ጠለምት) ቆላማ ቀበሌዎች በተከሰተው ድርቅና ርሃብ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ባንክ ሂሳብ ተከፈተ።

የባንክ ሂሳቡ ፈራሚዎች
1.ፕሮፌሰር ጌታሁን መንግስቱ
2.ወ/ሮ እንይሽ ገብሬና
3. አቶ ባያብል ሙላቴ ናቸው

በመሆኑም ለወገን ደራሽ ወገን ነውና በሃገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሞት አፋፍ የሚገኘውን ወገናችንን ለመታደግ የምንችለውን እንድናደርግ የድጋፍ ጥሪ እናቀርባለን።
=====================================

የተከበሩ አቶ ባያብል ሙላቴ የጃናሞራ ህዝብ ተወካልይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት


ይህ በየምክር ቤት አባል አቶ ባያብል እና የአካባቢው ተወላጆች የተጀመረው የተራቡትን የመርዳት ስራ እጅግ ሊበረታታ የሜገባው እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ሊሳተፉበት የሚገባ ነው።''ጨለማን ሲረግሙ ከመዋል አንድ ሻማ ማብራት '' የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየ አርአያነት ያለው ተግባር ነው።
  
የአማራ ክልል ያለው ግጭት በቶሎ መፍትሄ ካላገኘ ክልሉን ወደ የከፋ አደጋ ከመምራት ባለፈ የኢትዮጵያን አንድነት በከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ለእዚህ ደግሞ ዋነኛው ማሳያ የሚሆነን በአጭር ጊዜ ውስጥ የደረሰው ጥፋት ብቻ ሳይሆን ከህዝቡ ብዛት፣የመልክዐ ምድሩ አቀማመጥ የሚያዋስናቸው ክልሎች ብቻ ሳይሆን ከሀገሮች ጋርም መዋሰኑ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው።

አሁን የመንግስት ሚድያዎች ስለ የአማራ ክልል ጦርነት ዕለት ከዕለት ዜና እያሰሙ አይደለም። ስለ ክልሉ ጦርነት እየነገሩን ያሉት ዩቱበሮች ናቸ። ዩቱበሮቹ ግን ስለ የህዝቡ ሰቆቃ አያወሩም። ረሃቡን ደብቀዋል፣የወባ በሽታውን አይናገሩም፣ከሦስት ሚልዮን በላይ ተማሪዎች እንዳልተመዘገቡም አያወሩም።እነርሱ አሽትተውት ስለማያውቁት ባሩድ ከባሕር ማዶ ተቀምጠው እያወሩ፣በፊልም የሚያውቁትን ጦርነት ከአሜሪካ ሆነው በለው፣በለው! እያሉ ያሟሙቃሉ።

ክልሉ እየወረደበት ስላለው የመከራ ዶፍ የሚተነፍስ ዩቱበር የለም። ይህ ክልሉ በጸጥታ ወደ ከፍተኛ ቀውስ የመግባት አደጋ ላይ ነው።''ከትናንት ቢዘገይ ከነገ ይቀደማል '' እና ዛሬም የክልሉ ባለሃብቶች፣ሙሑራን እና የሃይማኖት አባቶች በጋራ ተሰብስበው በነፍጥ የሚመራ ክልል እንዳይሆን እና ያሉት ጥያቄዎች አግባብነት ባለው መልክ ቀርበው በምክክር እና በሰላም እንዲፈታ ጥረት ካላደረጉ ጉዳዩ በባዕዳን እጅ ገብቶ ኢትዮጵያን በከፋ መልኩ ወደ ኋላ 60 ዓመት ሊጎትተው ይችላል።የክልሉ ጉዳይ የሚመለከተው የተወሰኑ ዩቱበሮችን ሊሆን አይገባም። በመከራው ጊዜ የሚያወራለት የሌለው ህዝብ ዓይናችን እያየ አንዳችም ምሑራዊ ውይይት አድርገው ለችግሮች መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ በቀለጠ ፕሮፓጋንዳዊ ስራ ላይ የተጠመዱ ዩቱበሮች መከራውን እንዲደብቁ እና ክልሉን ፍጹም ሲወድም አያየን በመመልከት ወደ የባሰ ጥፋት ሲመሩ ሊሰጣቸው አይገባም። ዝምታው ሊሰበር ይገባል!
===================/////==============


Friday, November 3, 2023

Ethiopia’s prime minister wants a Red Sea harbour

November 2/2023








            



Nerves are jangling once again in the Horn of Africa, just a year after the end of a brutal civil war in Ethiopia that led to the deaths of perhaps 385,000-600,000 people. Now foreign diplomats and analysts fear that in his bid to get a port on the Red Sea, Abiy Ahmed, Ethiopia’s prime minister, risks sparking another conflict, this time next to one of the world’s busiest shipping routes.

In a jingoistic documentary aired on state television on October 13th, Abiy argued that landlocked Ethiopia must acquire a port on the Red Sea to break its roughly 120m people out of a “geographic prison”. Turning to history, he quoted a 19th-century Ethiopian warrior who had proclaimed that the Red Sea was the country’s “natural boundary”.

Ethiopia, Abiy noted, had indeed been a sea power with a navy and two ports, Massawa and Assab. It lost these along with the rest of its coastline in 1993, when Eritrea seceded to form a new country. Now, Abiy suggested, the moment was nigh to right a historic wrong. “It’s not a matter of luxury,” he insisted, “but an existential one.” Foreign diplomats say this reflects what Abiy has been declaring in private for months.

Ethiopia’s neighbours are rattled, particularly because Abiy had not raised the issue with them before making his threats. “The whole country thinks the man is mad,” says an adviser to Somalia’s president. A fight over ports would further destabilise a region already in turmoil. Sudan, Ethiopia’s neighbour to the west, has been plunged into what the un calls “one of the worst humanitarian crises in recent history”. Fighting between two warlords there has forced almost 7m people from their homes. And Ethiopia itself faces simmering rebellions in Oromia, its largest and most populous region, and Amhara.

Abiy says that Ethiopia’s demands can be met through peaceful negotiations with its neighbours. Better to discuss the matter now, he argues, than to risk an armed conflict in the future. But Abiy has reportedly said in private that he is ready to use force if talks fail. “If it is not achieved by other means, war is the way,” says an Ethiopian official. A few days after the broadcast Abiy flexed his muscles with a military parade in the capital, Addis Ababa, in which the army displayed its new weapons including a Russian-made electronic-warfare system. Troop movements have been detected along both sides of Ethiopia’s border with Eritrea in recent weeks. A well-connected source in Addis Ababa says that the armed forces are exercising in preparation for another conflict. On October 22nd the head of the air force warned his troops to ready themselves for war.

Ethiopia’s Red Sea conundrum dates back to at least the start of its bloody border war with Eritrea in 1998. Though a ceasefire was reached in 2000, the two countries remained at loggerheads. Ethiopia could not ship goods through Assab and Massawa. Now 90-95% of its external trade flows through Djibouti, to which it pays some $1.5bn a year in port fees.

In 2018, soon after Abiy came to power, he ended the nearly two decades-long stand-off with Eritrea by signing a peace deal with its dictator, Issaias Afwerki. Though the contents of the deal were never made public, it was generally understood that Ethiopia would regain tax-free access to Eritrea’s ports in exchange for returning disputed territories it had occupied since the end of the war. The following year Abiy was awarded the Nobel peace prize.

But plans for Ethiopia to use Eritrea’s ports never materialised. Instead, two years later, a power struggle between Abiy and Tigray’s ruling party, the Tigrayan People’s Liberation Front (tplf), sparked civil war. Eritrean troops joined in on Abiy’s side to fight against the tplf, which Issaias has long hated.

The two leaders have fallen out since then, possibly because Ethiopia signed a peace deal with the tplf in late 2022. Each sees the other as a threat to their influence over the region. “Abiy and Issaias cannot co-exist in this region,” says an Ethiopian opposition leader. “War is inevitable.”

Increased tensions with Eritrea could exacerbate Ethiopia’s existing internal conflicts. Under the peace deal Abiy struck with the tplf last year, it was supposed to disarm and demobilise its fighters while Eritrea was meant to withdraw its forces from Tigray. But Eritrea remains in control of at least 52 districts of northern Tigray, according to the region’s interim administrators. In recent weeks, Eritrean troops have expanded their presence along the border areas, reports a visiting foreign researcher. Tigrayan forces have handed over most of their heavy weaponry to the Ethiopian army. But they still have some 200,000 men and women under arms.

Another party in the multi-sided civil war in Tigray was Ethiopia’s Amhara regional government, which sent its own militias and troops to fight alongside Abiy’s federal forces. These troops were also supposed to have withdrawn from disputed territories inside Tigray that they occupied at the start of the war. But they have yet to do so. Instead, they have turned on Abiy’s government, accusing it of betraying Amhara’s interests. In August they fought federal forces for control of several towns.

Shifting alliances

With so much bad blood and so many armed groups jostling for influence within Ethiopia, Abiy’s threats are extremely reckless when it comes to his own country’s security. They are damaging to Ethiopia’s relations in the wider region. Djibouti, which now provides Ethiopia’s main access to the sea, has furiously responded that its “territorial integrity cannot be disputed”. Somalia, similarly, insisted its territorial integrity and sovereignty are “sacrosanct and not open for discussion”.

Some Ethiopian officials play down Abiy’s fighting talk. “It’s about diverting attention from domestic issues,” says an ally of the prime minister. Although the Eritrean port of Assab, which was once part of the former Ethiopian Empire, has particular symbolic value for Ethiopians, Abiy has also floated the possibility of negotiating for a strip of land around the ancient port of Zeila in the breakaway Somali region of Somaliland. In exchange, Ethiopia might offer to recognise Somaliland statehood. “Abiy has no interest in being part of another conflict for the moment,” says an analyst in Addis Ababa.

But the Ethiopian prime minister is notoriously unpredictable. “Nobody except himself can be certain if he is serious or not,” says a tplf official. Little more than three years ago Abiy insisted he would not go to war in Tigray. Many diplomats and regional leaders took him at his word, which he soon broke. They would be wise not to make the same mistake again.

==================////===========


Thursday, October 19, 2023

ኢትዮጵያ ባነሳችው የባሕር በር ጉዳይ ላይ አንድም የአውሮፓ፣የሰሜን አሜሪካ፣ደቡብ አሜሪካ፣እስያና አውስትራልያ ሀገር ትክክል አይደለም ያለ መንግስት የለም።

  • የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የተባበሩት መንግስታት በጉዳዩ ላይ ምንም አለማለት፣ሁለቱም በኢትዮጵያ የወደብ ባለቤትነት ጉዳይ ላይ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ እንደሌላቸው በትክክል ያሳያል።
============
ጉዳያችን
============


ኢትዮጵያ ባነሳችው የባሕር በር ጉዳይ ላይ አንድም የአውሮፓ፣የሰሜን አሜሪካ፣ደቡብ አሜሪካ፣እስያና አውስትራልያ ሀገር ትክክል አይደለም ያለ አንድም መንግስት የለም።ለወትሮው አንዲት ሀገር የእዚህ ዓይነት ጉዳዮችን ስታነሳ በቶሎ አስተያየት ለመስጠት እና ለመቃረን የሚጋፉ መንግስታትም ሆኑ ባለስልጣናት የሞሉባት ዓለማችን በኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ አልተፈጠረባቸውም። ይህ ማለት በርካታ የዓለማችን ሀገሮች፣ በጉዳዩ ላይ የሚስማሙበት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ የራሱ የሆነ የኃይል ሚዛን የሚፈጥር እና የቀይ ባሕርና የሜዴትራንያ ባሕር ፀጥታም የሚያረጋጋ ለመሆኑ አንዳችም ጥርጣሬ አልፈጠረባቸውም። ከእዚህ ውጪ ከኤርትራ፣ጂቡቲና የሱማልያ የፓርላማ አባላት፣ጋዜጠኞች የተሰጡ ምላሾች የሚጠበቁ እና ተፈጥሯዊ ምላሾች ናቸው። ከኤርትራ ተሰጠ የተባለውም ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ ለመርሳት ለመሞከር የሚደረግ እራስን የማታለል ዓይነት መግለጫ ነው። ይህም ሆኖ መግለጫው የዓለምን ትኩረት አልሳበም።

በሌላ በኩል በጉዳዩ ላይ ''ያዙኝ ልቀቁኝ '' ትላለች ተብላ የምትጠበቀው ግብፅ በጋዛ እስራኤል ጉዳይ ተወጥራ ''ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ'' ላይ ነች።ከሰሜናዊ ጋዛ እንዲወጡ የተደረጉ ፍልስጤማውያን ጎርፍ እንዳያጥለቀልቃት ጭንቀት ውስጥ ነች።

ዓለም የኢትዮጵያን እውነት በእንዲህ ዓይነት ደረጃ ሲመለከት እራሳቸው የኢትዮጵያ የሆነው ሰፌድና የባዕድ የሆነ ድስት በመልክ መለየት አቅቷቸው እዚህ እና እዝያ እየዘለሉ ግራ ተጋብተው የኢትዮጵያን ሕዝብ ግራ ለማጋባት የሚሞክሩት ዩቱበር ወገኖቻችን ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የኤርትራ ህዝብ ዛሬ ነቅቷል።ከኢትዮጵያም ከኤርትራም ሰው በከንቱ እንዳይወድቅ ካለፈው ተምሯል። ይህም ሆኖ ግን ኢትዮጵያን ካለወደብ አስቀርቶ በሰላም ውሎ ማደር እንደማይኖር ይህም ለማንም እንደማይበጅ ሁሉም በየቤቱ ገብቶታል።ጸብ ብሎ ነገር የለም። ኢትዮጵያም ካለወደብ ውላ ለማደር አትችልም።ይህንን እውነታ ማስታረቅ የግድ ነው።
============////==================

Thursday, October 12, 2023

የቀይ ባሕርን እውነት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ሲናገሩት ስህተት፣ሌላው ሲያወራው እውነት ሊሆን አይችልም። እራሳቸው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የማይክዱትን እውነት ለማስተባበል አንሞክር።




ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ
  • ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ስለ ቀይባሕር አሁን የተናገሩት ''አቅጣጫ ለማስቀየር'' ነው የሚለው አሉባልታ ውሸት ለመሆኑ ግልጽ የሆኑ ማስረጃዎች አሉ።

=========
ጉዳያችን ምጥን
=========

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ስለ ቀይባሕር አሁን የተናገሩት አቅጣጫ ለማስቀየር ነው የሚለው አባባል ውሸት ለመሆኑ ግልጽ ማስረጃ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሰሞኑን ከከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ጋር ያደረጉት ውይይት ላይ ገና ሙሉ ቪድዮው ያልተለቀቀ የቀይባሕርን አስመልክተው በተናገሩት ንግግር የቀይባሕር ጉዳይ የኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው ማለታቸውን የተለያዩ ዩቱበሮች የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ እየተመለክትን ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ ንግግር ገና አልተለቀቀም።ሙሉ ይዘቱ ሲለቀቅ የምንከታተለው ነው። 

ይህ በእንዲህ እያለ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሰሞኑን ስለ ቀይባሕር የተናገሩት አቅጣጫ ለማስቀየር ነው የሚለው ፈጽሞ ውሸት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን እንደመጡ በቅድምያ ከሰሩት ስራ ውስጥ የባሕር ኃይል መመስረት ነው።ከፈረንሳይ እስከ ዱባይ ለባሕር ኃይል ስልጠና ማነጋገር የጀመሩት፣ኢትዮጵያ ከ27 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የባሕር ኃይል አድሚራል ከመሾም ሰልጣኞች እስከ ማስመረቅ ያደረሱት ወደ ስልጣን እንደመጡ በጀመሩት ስራ ነው።

ይህ ብቻ አይደለም የመከላከያ ሚኒስትር ዓርማው ላይ የባሕር ኃይል ዓርማ ያከለበትም ከዓመት በፊት ነው። ከእዚህ በተጨማሪ  ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በፓርላማ የቀይ ባሕርን አስመልክተው የተናገሩት ንግግር ላይ ከአንድ ዓመት በፊት ሲናገሩ የቀይ ባሕር ጉዳይ የማይተው ጉዳይ ነው፣በሰላማዊ መንገድ ባሕር የማግኘት መብት እንዳለን፣ ይህንን አናደርግም የሚሉ ካሉ ቃል በቃል '' እኛም መረበሻችን አይቀርም '' የሚል ቃል አክለው ይህ ሰላም አያመጣም በሚል በግልጽ አማርኛ መንገራቸውን ጉዳያችን ታስታውሳለች።ከእዚህ ሁሉ በላይ ብልጽግና የኢትዮጵያ የእድገት አቅጣጫ የሚጠቁም ሰነድ አስመልክቶ ከአንድ ዓመት በፊት ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ እንደተጠናቀቀ የወጣ መግለጫ ላይም የብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት እንደሚሰራ እና ይህ ተፈጥሯዊ መብቷ እንደሆነ አሁንም በግልጽ አማርኛ ጽፎ ነበር።

ይህ ሁሉ ማስረጃ እያለ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት ''አቅጣጫ ለማስቀየር ነው'' የሚለው አባባል ፈጽሞ ሚዛን አይደፋም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀድመው በግልጽ ተናግረዋል።አቶ ኢሳያስ ይህንን ተረድተው የአሰብ ወደብን ወግ ባለው መልክ ለኢትዮጵያ እንዲከፍቱ ለማግባባት ከሰላም ስምምነት እስከ የአሰብ ወሎ መንገድ ግንባታ እስከ በኤርትራ ላይ የተጣለው እቀባ ይነሳ ብሎ ተመድን እስከመጠየቅ ድረስ ተጉዘዋል። ይህም ሆኖ እስካሁን ለውጥ አለመምጣቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ወቅቱን አንብበው ቀድመው የጀመሩትን ሥራ እንደገፉበት የሰሞኑ ንግግራቸው ያሳያል እንጂ ድንገት ዛሬ የመጣ ሃሳብ እንደሆነ አድርጎ መናገር ሚዛን የማይደፋ እና ማስረጃ አልባ አገላለጽ ነው። ጉዳዩ እውነት ነው። ከአንድ መቶ ሃያ ሚልዮን ሕዝብ በላይ የሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ30 ኪሎሜትር እርቀት ላይ ሆኖ የባሕር በር ሊነፈገው እንደማይገባ ይህ ፈጽሞ ሰላም እንደማያመጣ የኤርትራ ተወላጆችም ሆኑ አቶ ኢሳያስ ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ መገኘቷን ከአሜሪካ እስከ ሩስያ፣ከቻይና እስከ ዱባይ የሚደግፉበት አምስት ምክንያቶች  

  • በዓለም ላይ የሚደረገው ንግድ አውሮፓን ከመካከለኛው ምስራቅና ከሩቅ ምስራቅ ጋር የሚያገናኘው የቀይ ባሕር በተባበሩት መንግስታት ግምት መሰረት በዙርያው አሁን ካለው ህዝብ ብዛት እኤአ 2050 ዓም 343 ሚልዮን የሚደርሰው ይህ አካባቢ አንድ ሺህ ኪሚትር እርዝመት ያለው የባሕሩ ክፍል አስር ሚልዮን የማይሞላ ህዝብ ባላት ኤርትራ ብቻ ሰላሙ ይጠበቃል ብለው ስለማያምኑ፣
  • ቀይባሕርን ለመቆጣጠር አንዳንድ የመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት የያዙት አጀንዳ በምስራቁም በምዕራቡም ሀገራት በተለያየ የስጋት ደረጃ ላይ መውደቁ፣
  • አሜሪካ፣ሩስያ ወይንም ቻይና በቀጥታ የቀይባሕርን በብቸኝነት መቆጣጠር ስለማይችሉ እና አንዳቸው አንዳቸውን ስለሚጠባበቁ ከእዚህ ሁሉ እንደኢትዮጵያ በህዝብ ብዛት ከ120 ሚልዮን ህዝብ ባላት ኢትዮጵያ ቢጠበቅ ያላቸው ፍላጎት መኖሩ፣
  • አቶ ኢሳያስ የዕድሜያቸው መግፋት ተከትሎ በቀጣይ ኤርትራን የሚመራ ጠንካራ አመራር በሌለበት ሁኔታ አቶ ኢሳያስ በድንገት ቢያልፉ በኤርትራ በሚነሳው የስልጣን ሹክቻ ሀገሪቱ ወደየከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ከገባች የቀይ ባሕር ባልተጠበቀ መልኩ በሽብርተኞች እጅ እንዳይወድቅ የሁሉም ኃያላን መንግስታት ስጋት ብቻ ሳይሆን የእስራኤልም ቀዳሚ ስጋት መሆኑ፣
  • የመጨረሻው ምክንያት እጅግ ወቅታዊው የፍልስጤም እስራኤል ጦርነት መልሶ ማገርሸቱ፣አሜሪካ ጦሯን ወደ መካከለኛው ምስራቅ በብዛት መላክ መቀጠሏን አስታኮ የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ከፈነዳ አንዱ ትኩረት የሚሆነው መንግስት አልባዋ የመንን የመፋለምያ ሜዳ አድርጎ ቀይባሕርን የማወከ ተግባሩ ስለሚባባስ ይህንን አሁንም ኤርትራ ለመቆጣጠር በሰው ኃይልም ሆነ በሃብት ፍሰት መቋቋም ስለማትችል አሁንም ለተለያዩ ኃይሎች ጋር በተለይ ጸረ ምዕራብ ከሆኑት ጋር የመዋዋል አደጋው አፍጥጦ በመምጣቱ፣
የሚሉት ዋና ዋና ሃሳቦች ውስጥ ሲሆኑ ቀይባሕር በህዝብ ብዛትም ሆነ በወታደራዊ ግንኙነት ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር ያልተሞዳሞደ እና  የተሻለ ኃይል ያላት ኢትዮጵያ በቀይባሕር መገኘቷ ለሁሉም አንዱ ገላጋይ ሃሳብ መሆኑን ያመኑበት ይመስላል።ለእዚህ ዓይነቱ ጉዳይ በቀዳሚነት የምትቀናቀን ግብፅ ስትሆን አንዳንድ የተዳከመች ኢትዮጵያን ማየት የሚፈልጉ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ከግብፅ ጀርባ የሚኮለኮሉ ይሆናሉ።

ለማጠቃለል ኢትዮጵያ መልሳ ከኤርትራ ጋር ወደ ደም መፋሰስ በባሕር ምክንያት እንድትገባ ኢትዮጵያውያንም ሆኑ የኤርትራ ተወላጆች ፍላጎት አይደለም። ይህ ግን ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር መውጫ የማግኘት መብትና እውነትን አይቀይረውም። ጉዳዩ ለትውልድ የሚሻገር ነው። ሕጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት የሁሉም ግዴታ ነው። ጉዳዩን ግን  ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ሲናገሩት ስህተት፣ሌላው ሲያወራው እውነት ሊሆን አይችልም። እራሳቸው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የማይክዱትን እውነት  ለማስተባበል አንሞክር።
===============////============


Sunday, October 8, 2023

በቋፍ ላይ የነበረው የዓለማችን አጠቃላይ ፀጥታ አደጋ ላይ ወድቋል፣የተፈራው የፍልስጤም-እስራኤል ጦርነት ተቀስቅሷል፣ሀገራት ጎራ መለየት ጀምረዋል።

  • የአሁኑ የፍልስጤም እስራኤልን ጦርነት ለዓለማችን የከፋ ከሚያደርጉት ውስጥ ስድስቱ ምክንያቶች
=========
ጉዳያችን ምጥን
=========

በዓለማችን ላይ ሁሉንም ሀገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይነካል የተባለው ''እምብርት'' የፍልስጤም- እስራኤል ጦርነት ተቀስቅሷል።የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ የአሚሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ለእስራኤል የጦር መሳርያ መላካቸውን እና መንገድ ላይ መሆኑን መግለጻቸው ማምሻውን ተገልጿል። ኢራን ከፍልስጤም ጎን እንግሊዝና ኔቶ ከእስራኤል ጎን መሰለፋቸውን አሳውቀዋል።የተባበሩት አረብ ኢምሬት በተለየ ሁኔታ የገለልተኛነት ቦታ መያዟ ሲሰማ፣ በግብጽ የእስራኤል ቱሪስቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ሲገለጽ አጠቃላይ ክስተቱ በቋፍ ላይ የነበረውን የተከፋፈለ ዓለም ''ጠብ ያለሽ በዳቦ'' ዓይነት ትርጉም የለሽ ግጭት ውስጥ እንዳያስገባ ተፈርቷል። የአሁኑ የሀማስ በእስራኤል ላይ የጀመረው ጥቃት ከቀደሙት የሚለየው እስራኤል በኃይል ይዛቸዋለች ባላቸው ግዛቶች ላይ ሳይሆን ጥቃቱ የፍልስጤም ግዛት ባልሆነው የእስራኤል መሬት ላይም መሆኑ የነገሩ ሰፋ ብሎ መጀመር ያሳያል፣ይህ በቀላሉ በዲፕሎማሲ የሚፈታ እንደማይሆን በራሱ አመላካች ነው።

የአሁኑ የፍልስጤም እስራኤልን ጦርነት ለዓለማችን የከፋ ከሚያደርጉት ውስጥ ስድስቱ ምክንያቶች : 
  • የሩስያ ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በምዕራቡና ሩስያ፣ቻይና መሃል ያለው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ላይ መሆኑ፣
  • የተባበሩት መንግስታት በተዳከመበት እና የዓለምን ጸጥታ ችግር የመፍታት አቅሙ በተደጋጋሚ ተፈትኖ በወደቀበት ጊዜ መሆኑ፣
  •  የጸጥታው ምክር ቤት አምስቱ አባላት በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጋራ አጀንዳቸው በሳሳበት እና ለእዚህም አንድ ዓይነት መፍትሄ ገና ባላገኙበት ወቅት መሆኑ፣
  • የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ሀገሮች ውስጥ አባል የሆነችው ቱርክ በፍልስጤም እስራኤል ጉዳይ የምትወስደው አቋም ለድርጅቱ የራሱ የሆነ ጥላ ማጥላቱ፣
  • ከኮቪድ በኋላ የተጎዳው የብዙ ሀገሮች ምጣኔ ሀብት በፈጠረው የኑሮ ውድነት ሳብያ በብዙ ሀገሮች ያለው የውስጥ ቅራኔ በተባባሰበት ጊዜ መሆኑና ይህም በብዙ ቦታዎች ''ግልገል ጦርነቶች'' የመፍጠር አደጋ መኖሩና
  • የምዕራቡን ዓለም በማስተባበር የመሪነቱ ሚና የነበራት አሜሪካ በአሁኑ ጊዜ ያላት ፕሬዝዳንት የነቃና የተጋ አለመሆን ብቻ ሳይሆን ሰላማዊ መፍትሄ የማምጣት አቅሙ ያነሰ መሆኑ የሚሉት ይጠቀሳሉ።
================//////============
ኢትዮጵያ በቴዎድሮስ ካሣሁን



Thursday, September 21, 2023

''አክቲቪዝም ከጆርናሊዝም'' የደባለቀባቸው ዩቱበሮች በአማራ ክልል የሚፈሰው የመከላከያ እና የአማራ ክልል ህዝብ ደም አልታያቸው ብሏል። በኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሊባሉ ይገባል።


  • የሰው ደም እየፈሰሰ መከላከያና የአማራ ክልል ታጣቂ ኃይል አይነጋገር የሚሉት በውጪ ሀገር ሶፋ ላይ የተቀመጡት መሆናቸውን ልብ ይሏል።
  • የሰላም ንግግሮችን ለማጣጣል የሚሞክሩትን አጥብቀን መቃወም ኢትዮጵያዊ የውዴታ ግዴታችን ነው።
============
ጉዳያችን 
============

ኢትዮጵያ በወንድማማቾች ጦርነት ስትታመስ 50 ሙሉ ዓመት ዘንድሮ ይሞላታል። የኢትዮጵያ አብዮት በ1966 ዓም ከፈነዳ እነሆ በያዝነው 2016 ዓም 50 ዓመት ይሞላዋል።የወቅቱን ለውጥ ተከትሎ ከተነሳው የቀይሽብር እና ነጭ ሽብር ፍጅት ጀምሮ ከሻብያ እና በኋላ የእርሱ ውላጅ የሆነው ህወሓት ጋር ለ17 ዓመታት የተደረገው ጦርነት መቶ ሺዎችን ገብሮ የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት በልቶ፣በጣት የሚቆጠሩ ስደተኞች የነበሯት ኢትዮጵያ ልጆቿ እንደጨው በመላው ዓለም ተዘርተው የወታደራዊ መንግስት ወድቆ የጎሳ ፖለቲካ የሚያቀነቅነው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ሌላ የመከራ ምዕራፍ በኢትዮጵያ ላይ ከፈተ።

በ27 ዓመቱ የጎሳ ፖለቲካ የኢትዮጵያ ልጆች ስደት ከአውሮፓና አሜሪካ እንዲሁም ጎረቤት የአፍሪካ ሀገሮች ወደ መካከለኛው ምስራቅ የኢትዮጵያ የነገ ተስፋ የሆኑ ወጣት ልጆች የስደት ዘመን ሆነ። ከግማሽ ሚልዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ባብዛኛው ወጣት ሴት እህቶቻችን በመካከለኛው ምስራቅ ብቻ ተበተኑ፣ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ባለ 120 ሚልዮን ህዝብ ሆነች። ይህ ሁሉ ጥፋት ከውጭ ብቻ የተሴረ የሴራ ውጤት ብቻ አይደለም። የእኛው በጥቅምና በስልጣን ያበዱ ፖለቲከኞቻችን የተደናበረ የፖለቲካ አዙሪት ውጤትም ነው።

ባለፉት 5 ዓመታትም የኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ ችግር ተባብሶ የጎሳ ፖለቲካው የበለጠ አገንግኖ ወጥቶ የክልሎች የግጦሽ ቦታ እና ትንንሽ መንደሮች የእኔ ነው የእኔ ነው ተራ ንትርክ ሁሉ እስከ ሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን የሚያፈናቅል፣ሺዎችን የሚያሰድድ እና ወደ የበለጠ ድህነት የሚከት ሆነ። ኢትዮጵያ የተሻለ መንገድ ለመያዝ ስትታትር አዳዲስ ግጭቶች እየተፈለፈሉ እና ፖለቲከኞቻችን ደግሞ ዘለው እያቦኩት (እነርሱን እሳቱ አይነካቸውም) ህዝቡን ለበለጠ መከራ እየማገዱ ሀገሪቱን የሽብር ምድር ለማድረግ ከላይ ታች እያሉ ነው።

መንግስት በሌላ በኩል የቆረጠ አቋም እና ወጥ የሆነ አሰራር እና የጸጥታ መዋቅር እንደመመስረት በየክልሉ ያሉ የጎሳ አደረጃጀቶች እና ታጣቂዎች ከወለጋ እስከ ቤኒሻንጉል ከጌድዮ እስከ ቦረና ህዝብ ሲያፈናቅሉና ከተሞች ሲያወድሙ የመረረ እርምጃ ከመውሰድ ጋር የተለየ እና አዲስ አቅጣጫ ማስቀመጥ ስለተሳነው ኢትዮጵያ በጎበዝ አለቃ የምትመራ ሀገር እስክትመስል ድረስ ከአንዱ የሀገሪቱ ክፍል ወደ አንዱ የሀገሪቱ ክፍል መሄድ እንደ ትልቅ ዕድል እንዲቆጠር ሆኗል።

ወደወቅታዊው የሀገራችን ሁኔታ ስንመጣ በአማራ ክልል እና በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ከፍተኛ ቅቡልነት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስት በኦሮምያ ክልል ያለው የብልጽግና የቀድሞው ኦህዴድና በውስጡ የተሰገሰገው የኦነግ ሸኔ ቡድን ባራመዱት የጎሳ ፖለቲካ እና የማንአለብኝነት ጥቃት በተለይ የአማራ ተወላጆች በሆኑት የወለጋ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ የፈጸሙት ግፍ አሁን በአማራ ክልል ለተነሳው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ሆኗል።በእዚህም በብሄርተኝነት የመቀስቀስ ስራው ለብሄርተኞች አመቺ ሆኖላቸዋል።  

''አክቲቪዝም ከጆርናሊዝም'' የደባለቀባቸው ዩቱበሮች በአማራ ክልል የሚፈሰው የመከላከያ እና የክልሉ ህዝብ ደም አልታያቸው ብሏል። በኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሊባሉ ይገባል።

በአማራ ክልል የተነሳው ቁጣ በኦሮምያ ክልል አክራሪ ቡድኖች የፈጸሙት ጥላቻን የተሞላ የግፍ ውጤት መሆኑ ተደጋግሞ ተነግሯል።ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይሏን በራሷ ህዝብ ፈጅታ ሌላ የታሪክ ጠባሳ ይቀመጥ ማለት አይደለም። መንግስት በውስጡ ያሉትን በኦሮሞ ስም የሚነግዱትን አክራሪ ብሔርተኞች ማስወጣት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወደ የለየለት የእርስበርስ ጦርነት የሚከተውን የጎሳ ፖለቲካ እና አደረጃጀት በሕግ የማገድ ውሳኔ ድረስ ካልሄደ ነገሮች ከተበላሹ በኋላ እና ሁሉም ነፍጥ ካነሳ በኋላ ''እንደ 1966ቱ የእንዳልካቸው ካቢኔ '' በኋላ ከረፈደ የጎሳ ፖለቲካ ታግዷል ወዘተ ቢሉት አይሰራም። ሁሉም መከወን ያለበት በጊዜው ነው።

ከእዚህ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ያለው በመከላከያና በአማራ ክልል ታጣቂ (ፋኖ) መሃከል ያለው ግጭት በምንም መልኩ መቆም ያለበትና ያሉት ጉዳዮች ሁሉ ወደ ንግግር መምጣት አለባቸው። ይህ የመነጋገር ጉዳይ ሲነሳ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት አክቲቪዝም ከጆርናሊዝም የተደባለቀባቸው ዩቱበሮች ናቸው። እነኝህ ዩቱበሮች ከውጭ ሆነው ''እስከ መጨረሻው ተጫረሱ'' ዓይነት መልዕክት ብቻ ሳይሆን ወደ ንግግር ይመጣ ሲባል ''ይሄ ባንዳ፣የአማራ ጠላት '' እያሉ ከምሁራን እስከ የሃይማኖት አባቶች በመሳደብ እና በማሸማቀቅ ሰው ለሀገሩ ያለውን ሃሳብ በነጻነት እንዳይሰጥ ከሽብር ያላነሰ ተግባር እየፈጸሙበት ነው። የዛሬ 50 ዓመት በኢትዮጵያ የነበረው ቀይ ሽብር ብቻ አልነበረም።የወቅቱ መንግስት ተቃዋሚዎችም ነጭ ብለው የሚጠሩት ሽብር ነበራቸው። በወቅቱ ሁሉም ለሚሰራው ለራሱ እና ለደጋፊዎቹ '' እንደ ቅዱስ ስራ '' እየተወሰደ ይሞከሻሹበት ነበር። ዛሬም በ21ኛው ክ/ዘመን ተቀምጦ '' ብልጽግና የሆነውን በሙሉ ፍጀው፣በለው'' የሚባልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል። በሌላ በኩል የፋኖ ታጣቂ ብቻ ሳይሆን ለፋኖ የምትደግፉ ናችሁ እየተባሉ ዜጎች ፍዳቸውን እያዩ ነው። ሁሉም እንደየቀይ ሽብር ዘመን የራሱን ያሞግሳል። የአሁኑን የከፋ የሚያደርገው ለአቅመ ጋዜጠኝነት ያልደረሰ ሁሉ ለዩቱብ ክፍያ ብሎ ሀገር ወዳድ መስሎ ግጭቶጭ እንዲጠመቁ ቀን ሙሉ ላይ ታች ሲል መዋሉ ነው። በወንድማማቾች መሃክል ያለ የደም ወሬ በማዛመት ከዩቱብ የተገኘ ገንዘብ ለቤተሰብስ ጤና ይሆናል? ይህንን በጊዜ የምናየው ነው። ዩቱበሮች ስለየምስኪኑ ገበሬ ቁስል አውሮፓና አሜሪካ ተቀምጠው ሊሰማቸው አልቻለም። የእነርሱ ልጆች ትምህርት ቤት እየሄዱ ሃገር ቤት ያለው የገበሬው ልጅ ህይወት ግን ገና አልተሰማቸውም። ይልቁንም ''ከመከላከያ ጋር አንዳች ንግግር ታደርኛ'' እያሉ የማሸማቀቅ እኩይ ተግባራቸውን ቀጥለውበታል። 

ኢትዮጵያ ከእዚህ በላይ የምትሸከመው የጦርነት ትከሻ የላትም። 50 ዓመታት ያህል ደም ፈሶባታል።መንግስት በኦሮምያ ክልል ያለው ጽንፍ የረገጠ አስተሳሰብና የዕብሪት አካሄዶችን አደብ ማስገዛት ብቻ ሳይሆን የጎሳ ፖለቲካውን የሚያከስም የህግ ማዕቀፍ በቶሎ አውጥቶ ስራ ላይ ማዋል አለበት። በአማራ ክልል ያሉት ታጣቂ የፋኖ አባላትም ከመከላከያ ጋር በቶሎ እርቅ ፈጽሞ እና በክልሉ ሰላም እንዲመጣ በመነጋገር የጋራ ኢትዮጵያን ለመጠበቅ መነሳት አለባቸው። ህዝብ ሁሉንም እየታዘበ ነው።ታዝቦ ታዝቦ ለሰላም አልቆም ያለው ማናቸውም ኃይል ላይ ማለትም መንግስት ላይም ሆነ በአማራ ክልል ያለው ታጣቂ ላይ ድንገት ይነሳል። ከእዚህ ሁሉ በፊት ሁሉም አደብ የመግዣ ጊዜው አሁን ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ ደግሞ ከፖለቲከኛው በተሻለ መንግስት ምን ማለት እንደሆነ ያውቃል። የመንግስት ድንበር ይፍረስ የሚል አይደለም። ከመጠን ያለፈ የሕግ መጣስ ያስቆጣዋል። ይህ ቁጣ ግን የታጠፈው ሕግ ተመልሶ ሲዘረጋ ይመለሳል።

ባጠቃላይ የባዕዳን ጣልቃ ያልገባበት የመነጋገር እና ኢትዮጵያ ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር የሚያውጣ የመፍትሄ መንገድ ከመንግስትም ከፋኖም ይጠበቃል። አሜሪካን አውሮፓ ቁጭ ብለው መንግስት ለመገልበጥ ነው መሄድ ያለብህ የሚለው ስብከት ኢትዮጵያን ወደ መበተን ደረጃ የሚያደርስ አደገኛ አካሄድ ስለሆነ ጆሮ ሊሰጠው የሚገባ አይደለም። መንግስት ይቀየራል።የሚቀየረው ግን በጦርነት ክልልን በማውደም አይደለም። ትግል ሲያስፈልግ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰላማዊ ትግሎች መንገዶች አሉ።ከእዚህ ባለፈ የምርጫ ሰሌዳን ተከትሎ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የሚፈልገውን በመምረጥና ድምጹ እንዲከበር በመታገል ወደ የሚፈለገው ለውጥ መምጣት ይቻላል።ቢያንስ በ21ኛው ክ/ዘመን መንግስት ባልሰለጠነ መንገድ በማውረድ ሀገር ከመበተን መታደግ የሁሉም ግዴታ መሆኑን ማወቅ አለብን።ከእዚህ ጋር የሰላም ንግግሮችን ለማጣጣል የሚሞክሩትን አጥብቀን መቃወም ኢትዮጵያዊ የውዴታ ግዴታችን ነው።

+++++++++++++++++++++++++++++


Saturday, September 16, 2023

Is the biblical ark of the covenant hidden in an Ethiopian church?

በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቀው የሙሴ ታቦተ ሕግ በኢትዮጵያ ተደብቋልን? በሚል ርዕስ የኢየሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 5፣2016 ዓም ምሽት የጻፈው አዲስ ጽሑፍ።

ጽሑፉ ተመራማሪዎች ታቦተ ሕጉ በኢትዮጵያ ለ3 ሺህ ዓመታት ተደብቆ እንደሚገኝ ይገልጻሉ በሚል መግቢያ ይጀምራል።

ሙሉውን ጽሑፍ ከስር ያንብቡ።

በቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ የተገነባው የአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን።

Is the biblical ark of the covenant hidden in an Ethiopian church? 

  • Researchers claim the ark hidden for 3,000 years in Ethiopia.
By WALLA! 
Published: SEPTEMBER 16, 2023 19:20
Jerusalem Post
===================
Where is the Ark of the Covenant, the vessel that, according to Jewish tradition and the Bible, safeguarded the Tablets of the Covenant?

The gold-coated ark adorned with a gold wreath once resided in the First Temple until the Babylonian army's destruction in 587 BC. While records don't mention its fate, it's improbable that such a sacred and precious object disappeared unnoticed.

So, did it survive the destruction, and if so, where does it rest today?
The ark, also known as the Ark of God or the Ark of the Testimony, was positioned within the Holy of Holies in the First Temple. It held immense significance, described as the primary "seat of the Shekinah," and it hasn't been seen since the First Temple's ruin.

Sages hold two opinions on its whereabouts.

Rabbi Eliezer and Rabbi Shimon believe the ark was taken to Babylon and destroyed, while Rabbi Yehuda claims it remained in the temple's confines but was later relocated and rediscovered elsewhere. The Ark of the Covenant's location remains a mystery that scholars, adventurers, rabbis, and enthusiasts have sought for over 2,000 years.

A peculiarly shaped stone unearthed years ago in the ruins of an ancient temple near Jerusalem raises the possibility that it may be the "great stone" upon which the Ark of the Covenant rested, housing the sacred Tablets of the Covenant.

On the other hand, a substantial number of Bible scholars propose that the ark's final resting place is a church in Ethiopia. They assert that it was clandestinely transported there from Israel during the reign of King Manasseh of Judah (697 BC to 642 BC), and it has remained hidden there for 3,000 years, meticulously guarded by virginal nuns.

For millennia, the ark's whereabouts, said to possess magical powers and bring death to those who touch it, have been enigmatic. Ethiopian Christians contend that the Ark of the Covenant resides in a chapel within the small town of Axum, where they believe it arrived nearly three millennia ago, watched over by a group of nuns who are forbidden to leave the chapel until their demise.

A report by Fox News suggests that the Church of Our Lady Mary of Zion in Axum houses one of the world's most coveted biblical relics, including the Ten Commandments and Aaron's "staff of miracles."

Numerous Torah scholars are convinced that the Ark of the Covenant was covertly transported from its original resting place beneath the Temple Mount all the way to Africa, carried by Jews expelled from Israel during Manasseh's rule. Since its disappearance, multiple theories about its location have surfaced, including submersion in the Sea of Galilee, concealment beneath the Temple Mount's foundation, surrender to the Americans, and the increasingly supported claim of its presence in Ethiopia.

According to the Bible, the Israelites crafted the Ark of the Covenant in the Sinai desert after leaving Egypt. Its vanishing coincided with the Babylonian conquest of Jerusalem in 587 BC.

One account narrates how the Jordan River stood still as priests carrying the ark crossed it, while other stories describe its role in battles where its mystical powers aided the Israelites. When captured by the Philistines, the ark's presence caused outbreaks of tumors and diseases, compelling them to return it to the Israelites. Some tales even mention death befalling anyone who touched or gazed upon the ark.

As mentioned earlier, certain researchers propose that the Ark of the Covenant traveled extensively before ultimately reaching ancient Israel. According to the Maccabees, it was concealed in a cave on Mount Nebo by the prophet Jeremiah. In Hasmoneans 2, it is recounted how Jeremiah discovered a hidden cave on the mountain and buried the Ark of the Covenant, admonishing exiles not to mark its location until God reunites His people from exile and returns them to their homeland.

Another narrative, currently gaining credence, asserts that the Ark of the Covenant found its way to Ethiopia and now resides in the Church of Our Lady Mary of Zion. According to this belief, Ethiopian Orthodox Christians transported it to Axum through Menelik, the son of the Queen of Sheba and King Solomon of Israel, after Jerusalem's fall in 586/587 BC and the destruction of Solomon's Temple.

Britons also claim the ark's possession, with one theory proposing that the Knights Templar, also known as the Order of the Knights of Solomon's Temple, discovered it in Jebel al-Madhbah in Petra, potentially the biblical Mount Sinai. Some legends suggest the Templars hid the Ark of the Covenant in Ethiopia, while another theory suggests British Baron Ralph de Sudeley, known for generous religious donations, transported it to his estate at Temple (temple) Hardwick. Notably, this location is currently owned by the British Ministry of Defense and is securely sealed.

To this day, no definitive historical theory exists about the Ark's fate, with some researchers even questioning its initial existence.

Curious to find out?

You'll need to wait, as Jewish sources prophesy the ark's revelation near the coming of the messiah. The Ramban wrote that it will be unveiled "in the building of the house or in the future wars before the messianic king."




Sunday, September 3, 2023

የግሪካውያን የኢትዮጵያ ወዳጆች ማኅበር እና በኢትዮጵያ የግሪክ ማኅበረሰብ አመራሮች በጣልያን፣ፈረንሳይና ግሪክ የኢትዮጵያ ክብርት አምባሳደር ዴሚቱ ሃሚሳ ጋር በአቴንስ ከተማ ተገናኙ። የግሪካውያን የኢትዮጵያ ወዳጆች ማኅበር እኤአ መስከረም 30/2023 አቴንስ ላይ ልዩ ዝጅግት አዘጋጅቷል።

ክብርት አምባሳደር ዴሚቱ ከኢትዮጵያ ወዳጆች የግሪክ ኮሚኒቲ አባላት ጋር በአቴንስ፣ግሪክ


  • ''በአዲስ አበባ የሚገኘው የግሪክ ኮሚኒቲ ከመንግስት ጋር የገባውን ችግር በተመለከተ ጉዳዩ በፖለቲካና ዲፕሎማሲያዎ ደረጃ የሚፈታ ነው '' ክብርት አምባሳደር ዴሚቱ ሃሚሳ

==========================
ጉዳያችን ልዩ ዘገባ/Gudayachn Exclusive
===========================
የግሪካውያን የኢትዮጵያ ወዳጆች ማኅበር እና በኢትዮጵያ የግሪክ ማኅበረሰብ አመራሮች በጣልያን፣ፈረንሳይና  የኢትዮጵያ ክብርት አምባሳደር ዴሚቱ ሃሚሳ እና የኤምባሲው ሁለተኛ ጸሐፊ አዲሱ መልካሙ ጋር በአቴንስ ከተማ መገናኘታቸውን ከሰሞኑ ለጉዳያችን ከኢትዮጵያ ወዳጆች ግሪካውያን ማኅበ አመራሮች የደረሳት ዘገባ ያመለክታል።ከክብርት አምባሳደር ዴሚቱ ጋር የነበረው ውይይት በአቴንስ ሜልያ ሆቴል የተደረገ ሲሆን፣በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ወዳጆች የግሪክ ማኅበረሰብ ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ጆርጂዮስ ሚካኤልደስ፣የዳይሬክተሮች ቦርድ ተወካይ ኪሜትሪዮስ ስትራጋሊስ እና ከአዲስ አበባ የግሪክ ኮሚኒ ማኅበር ፕሬዝዳንት ኦዲስየስ ተገኝተው ነበር።  

በእዚህ ውይይት ላይ በቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ ለግሪክ ህዝብ የተከናወነ የግብረሰናይ ተግባር የከወኑበት የአቢሲንያ አደባባይ በአቴንስ ከተማ ምክርቤት ስሙን በቋሚነት የማስመዝገብ ስራ ዙርያ ላይ ምክክር መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።በእዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ወዳጆች የግሪካውያን ማኅበር ቦታው በአቴንስ ከተማ ምክርቤት እንዲመዘገብ ከአቴንስ ከተማ ከንቲባ ኮስታስ ባኮያኒስ ጋር ስለጉዳዩ መነጋገራቸውን እና ከንቲባው በጎ ምላሽ እንደሰጡ ለጉዳያችን የተላከው የማኅበሩ መረጃ ያብራራል።ክቡር ከንቲባው ማኅበሩ በቦታው ላይ ለማቆም ያቀደው የኢትዮጵያና የግሪክን ታሪካዊ ግንኙነት የሚያስታውስ ሃውልት ስራ በተመለከተ ድጋፋቸው መግለጻቸውን ለማወቅ ተችሏል።

የመስከረም 30/2023 ዓም እኤአ በአቴንስ አቢሲንያ አደባባይ ለሚሰራው የኢትዮጵያና ግሪክ መታሰብይ ሃውልት ማስጀመርያ መርሃግብር በተመለከተ ማብራርያ የተሰጠ ሲሆን በዝግጅቱ ለመታሰብያ ሃውልቱ ማሰርያ የገንዘብ ማሰባሰብያ መርሃግብር የሚኖር ሲሆን ለሃውልቱ ማሰርያ ከሚፈለገው በላይ ገንዘብ ከተገኘ በኢትዮጵያ በቦረና ለውሃ ማውጫ ተግባር እንደሚውል ተወስቷል።

ይህ በእንዲህ እያለ በአዲስ አበባ የሚገኘው የግሪክ ኮሚኒቲ ትምህርትቤት ከትምህርት ሚኒስትር ጋር የተገባው ውዝግብ አስመልክቶ ማብራርያ ለክብርት አምባሳደር ተሰጥቷል።በእዚ መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርትቤቱ ጉዳይ ላይ የተነሱትን ውዝግቦች አስመልክቶ ማብራርያ ተሰጥቷል። በአዲስ አበባ የሚገኘው የግሪክ ኮሚኒቲ ትምሕርትቤት በተመለከት ጉዳያችን የዘገብችውን ዝርዝር ጉዳይ በእዚህ ሊንክ ተጭነው ያንብቡ።በእዚሁ ስብሰባ ላይ የአዲስ አበባ ግሪክ ኮሚኒቲ ማህበር ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በኮሚኒቲው ትምህርትቤት ላይ የወሰደውን እርምጃ አስታውሰው እኛ ወደ ፍርድ ቤት መሮጥ የምንፈልግ ማህበረሰብ ሳንሆን የኢትዮጵያን ህግ የሚያከብር ማህበረሰብ ነን ሲሉ አሳስበዋል።

በውይይቱ ላይ አምባሳደር ዴሚቱ በሰጡት ምላሽ :

በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለው የቆየ ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ በቀጣይነትም ተባብረን መቀጠል አለብን። ለብዙ መቶ ዓመታት ወደ የነበሩ ግንኙነቶች እንደነበሩ ጠቅሰው፣ የትምህርት ቤቱ ጉዳይ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲያዊ ደረጃ የሚፈታ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት የማህበረሰቡን ንብረት የመውረስ ዓላማ እንደሌለው አሳስበዋል።

በአቢሲኒያ አደባባይ በሚሰራው ሀውልት ጉዳይ ላይ የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ለትውልድ ለማስተላለፍ ጥረት የሚያመላክት በመሆኑ እጅግ ጠቃሚ ተነሳሽነት ነው በማለት አምባሳደሯ አብራርተዋል። ሀውልቱ በጋራ በኢትዮጵያና ግሪክ ተቀርጾ የሁለቱን ህዝቦች የቆየ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ እንዲሆን እና የሃውልቱ ምረቃ ላይ የሁለቱ ሃገሮች ጠቅላይ ሚኒስትሮች የሚገኙበት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።ከእዚህ በተጨማሪ በጥቅምት ወር ለአበበ ቢቂላ መታሰብያ በአቴንስ አንድዓይነት ዝግጅት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነስቷል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በግሪክ ማኅበር በቀጣይ ከአምባሳደሯ ጋር በማኅበሩ ጽህፈት ቤት ዳግም እንደሚገናኙና በጋራእራት እንደሚመገቡ ተስፋቸውን ገልጸው እጅግ መግባባት ለሰፈነበት ስብሰባ ምስጋናቸውን አቅርበው የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።

ከእዚህ በታች የኢትዮጵያውያን ወዳጆች የግሪካውያን ማኅበር ለጉዳያችን ውይይቱን አስመልክቶ የላከው የግሪክኛ ቋንቋ ትርጉም ከእዚህ በታች ይመልከቱ።
=================

MEETING OF THE ASSOCIATION OF GREEKS OF ETHIOPIA (A.G.E.) WITH THE ETHIOPIAN AMBASSADOR

On Thursday, August 24th, at the MELIA Hotel in Athens, a delegation of the Board of Directors of A.G.E., consisting of the 2nd Vice President Mr. Georgios Michaelides, the Treasurer Mr. Theodoros Panas and the member of the Board of Directors Mr. Dimitrios Stragalis, together with the President of the Greek Community Association of Addis Ababa Mr. Odysseas Parris, had a meeting with the Ambassador of Ethiopia to Italy who is accredited in Greece Mrs. Demitu Hambisa Bonsa, who was accompanied by the Second Secretary of the Embassy Mr. Addisu Melkamu Kebede.

The 2nd Vice President, referred to the intervention of the A.G.E. to the Municipality of Athens when rumors circulated about renaming of the historic Abyssinia Square in Monastiraki and the assurance of the Mayor of Athens Mr. Kostas Bakoyannis that there is no such intention. The Mayor supported the proposal of A.G.E. for the placement of a memorial monument and signage.

The 2nd Vice President noted the positive response of the Ethiopian Community living in Greece to the initiative to create this monument that will mark the long-standing relations between the two peoples. He said that the cost will be covered by sponsorships and actions of members and friends of S.E.A and Ethiopian Communities living in Greece and other countries abroad. He stressed that if the amount raised exceeds the cost of the monument, the remaining amount will be allocated to the BORENA area for the creation of a drinking water well, according to the wish of the Ethiopian Community in Greece.

The September 30, 2023 event at Abyssinia Square will mark the beginning of the celebrations for a century of the renaming of the Square by decision of the Municipality of Athens in 1924 to Abyssinia Square after the significant donation given by Ethiopia to the Greek refugees of the Asia Minor Catastrophe, and the over a century establishment of diplomatic relations.

The President of the Greek Community Association of Addis Ababa, reported on actions and claims of the Ethiopian Ministry of Education, which attempted to convert the English section of the Greek Community Schools owned by the Greek Community Association of AA, into a Charitable Endowment. A form that means the transfer of ownership of the school buildings through the Endowment to the Ethiopian State and dispossession of the Community's property. For the operation of the English section, the Greek Community Association of AA has established a new organization provided by the legislation for establishing an INTERNATIONAL SCHOOL from the 2023-24 school year and requested permission, which was not granted. He stressed that we are not a Community that wants to run to court but a Community that operates respecting Ethiopian laws.

He referred to the fact of the appointment of an Interim Administration by designs of the Ministry of Education, without any discussions or consultations, for the management of the English section of the school. The Interim Administration has exceeded its mandate by prohibiting the Board members of the Community to have access to the premises of the Community, issuing orders for the removal of residents from the houses that the community had provided them, etc. Still in excess of its authority, it is involved in purely community matters such as its social policy on indigent people, the management of the Greek St. Frumentius Church, the Cemetery, etc. Lastly they interfere in the Greek Section of the Schools that operate under the Greek Ministry of Education.

He pointed out that in May, the country's auditing mechanisms have taken the accounting documents of the Community for audit. No findings have been announced and the Bank accounts of both the Community and the personal accounts of the members of the Board of Directors of the Community have been frozen, despite the fact that the current Board, it is only one year in office, and since the beginning it met with this situation of interference.

He informed the Ambassador that the ownership of the Community Schools is not the same as the other schools where land was allocated for building. The Greek Community Schools were built on land which was purchased by the Greek community from the donations and sponsorships of its members.

The 2nd Vice President pointed that the Greek Community Association of AA has the full support of A.G.E., since A.G.E. represents the vast majority of the Community members living in Ethiopia at the time of the great exodus, who created and sustained the Community property, and that were forced to leave by the Derg Regime in 1975-76.

The Treasurer, Mr. Panas Theodoros, informed about the Marathon Road Museum and the request of the Municipality of Marathon to enrich the museum with exhibits from Ethiopian marathon runners. He also mentioned the cooperation of the A.G.E. with the "Pelargos" Association, which are families who have adopted children from Ethiopia, to teach Ethiopian culture to these children. From the bilingual books of "Pelargos” a part goes to support the literacy of young people in Ethiopia.

The Ambassador's statement was:

The long-standing relations between the two peoples have been strong and we must continue to deepen them. Relations that go back for hundreds of years.

The issue of the School will be resolved at the political and diplomatic level and she stressed that it is not the intention of the Ethiopian Government to take over the Community property. She regretted the turn the matter had taken.

On the issue of the monument in Abyssinia Square, she said that it is a very important initiative because that will show to future generations the relations between the two peoples. The initiative should be raised to a higher level, with the participation of the Ethiopian Ministry of Tourism and Culture, and when the unveiling ceremony is held, the two Prime Ministers should be invited to be present. She said that they have a wish that the monument should be jointly designed and reflect the long-standing relationship between the two peoples and asked to see the proposal of A.G.E.

She pointed out that they are planning some event for Abebe Bikila in Athens in October, of which they will inform A.G.E. in due time.

Regarding the marathon road museum, the Embassy's Second Secretary said that he would support the effort and took the initiative to find exhibits.

On the part of A.G.E. thanks were expressed for the time the Ambassador took to inform the Association and invited her on her next visit to be received at the A.G.E. offices for a briefing and then to have a dinner.

The whole discussion took place in an extremely friendly and family-like environment and all agreed to continue the constructive channel of communication that has started.

On August 25, a meeting took place between the President of A.G.E. Dr. Alexandros Grous, who came urgently and met with the Ambassador of Ethiopia.

============///==========

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...