Sunday, November 26, 2023

በውግዘት ውስጥ ላሉት፣አሁንም በድፍረት ለሚሄዱት ለትግራይ የቀድሞ ጳጳሳት አልቅሱላቸው።


  •  አክሱም ጽዮን በክርስትና ታሪክ ለሁለት ሺህ ዓመታት ያህል ያላየችውን የድፍረት ስራ በቅዱስ ሲኖዶስ በተወገዙት የትግራይ አባቶች እያየች ነው።
  • የእነርሱን አካሄድ እየተመለከተ ዝም ብሎ የሚገለገለው የትግራይ ምዕመን፣ የእዚህ ዓይነት አካሄድ ከአባቶቻችን አልተማርንም ተዉ! ማለት ይገባዋል።

እራሳቸውን ከቅዱስ ሲኖዶስ ለይተው፣ክርስትናን በመንደር ለመመተር የሚሞክሩት የትግራይ አባቶች ከቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት እና ስልጣነ ክህነት መያዝ በኋላም አባ ሰረቀን ጵጵስና ሾመናል ብለዋል። ይህ የድፍረት ስራ አክሱም ጽዮን በክርስትና ታሪክ  ለሁለት ሺህ ዓመታት ያህል ያላየችውን የድፍረት ስራ በትግራይ አባቶች እያየች ነው።

ይህ በትግራይ ያሉ አባቶች እያደረጉት ላለው አዕምሮውን የሳተ ሰው ስራ ምንም ሃተታ አያስፈልገውም።ድርጊቱ ስንት የበቁ አባቶች ዘግተው ቀን ከሌሊት ለዓለም የሚጸልዩ አባቶች ባሉባት የትግራይ ክልል እና በአክሱም ጽዮን ፊት የተፈጸመ ድፍረት ነው።ጥፋት በበለጠ ጥፋት አይስተካከልም።በውግዘት ውስጥ ላሉት፣አሁንም በድፍረት ለሚሄዱት ለትግራይ የቀድሞ ጳጳሳት አልቅሱላቸው።አሁን ለአባቶች የሚያስፈልጋቸው ለቅሶ ነው።ከልቦናቸው አይደሉም።ከልቦናው የሆነ አባት ቅዱስ ፓትርያሪክ በብዙ ድካም ከደጁ ሲመጣ የቤተክርስቲያን ደጅ ዘግቶ አይሸሸግም፣ቡራኬ ሊቀበል እየተጣደፈ ሄዶ ጉልበት ስሞ ይባረካል።

አሁን የትግራይ አባቶች ከቀልባቸው አይደሉም።ምን እያደረጉ እንደሆነ፣ምን እየሰሩ እንደሆነ ከአዕምሯቸው ጋር ስላልሆኑ አያውቁትም። አሁን የሚያስፈልጋቸው የሚያደርጉትን አያውቁምና የሚያለቅስላቸው፣ ወደ ቀልባቸው መልሳቸው ብሎ የሚያነባላቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል። የእነርሱን አካሄድ እየተመለከተ ዝም ብሎ የሚመለከተው የትግራይ ምዕመንስ? ቢያንስ የእዚህ ዓይነት አካሄድ ከአባቶቻችን አልተማርንም አይልም? በመንደር ተሰባስቦ ከቅዱስ ሲኖዶስ አንድነት ወጥቶ እንደፈለጉ በመሄድ የሚሰጥ ስልጣነ ክህነትን የትግራይ ምዕመናን ከአባቶቻችን አልተማርነውም።ከየት አመጣችሁት ብሎ አይጠይቅም? 



No comments:

''ሙዝ አትብላ! ጦጣዎች ከጫካ ሊመጡ ይችላሉ።'' ዓይነቱ የጀዋር ጊዜው ያለፈበት ትንተና በኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ላይ።

ቀይ ባሕር ዛሬ በዩቱብ አገኘን ብላችሁ በኢትዮጵያ የባሕር በር ጉዳይ ላይ የምትሳለቁ የዘመናችን ባንዳዎች ግዴላችሁም ጊዜ እና ትውልድ ይፈርዳል! እናንተን ብቻ ሳይሆን ልጆቻችሁም ''አባታቸው በዩቱብ ኢትዮጵያ ...