ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, July 24, 2020

ቱርክ፣ ኢስታምቡል የምትገኘው ጥንታዊቷ ሃጊያ ሶፍያ ካቴድራል ከሙዜምነት ወደ መስጊድነት መቀየሩ ውጥረት ፈጥሯል።ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ የጁማ ስግደት ተሰግዶባታል።

ቱርክ፣ ኢስታምቡል የምትገኘው ጥንታዊቷ ሃጊያ ሶፍያ ካቴድራል 

>> ቱርክ ቦታውን ወደ መስጊድ ከቀየረች በኃላ የመጥፊያዋ ዘመን ይጀምራል የሚል ትንቢት እንዳለ በሕዝቧ መሃል የሚናገሩ አሉ።

በቱርክ፣ዋና ከተማ ኢስታምቡል በ6ኛው ክ/ዘመን በቤዛንታይን ስርወ መንግስት ማለትም ከ532 እስከ 537 እኤአ የተገነባች ቤተክርስቲያን ነች።ቤተክርስያኗ በውበቷም ሆነ በሕንፃ ጥበቧ ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈች እና ቱርክ ከመመስረቷ በፊት ቀድማ የተገኘች እና ነቢዩ መሐመድ ከመወለዳቸው በፊት በቱርክም የክርስትና ማዕከል አሻራ ማሳያ ሆና ኖራለች።

ቤተክርስቲያኗ ከዘመነ ሰማዕታት ማብቃት በኃላ በታላቁ ንጉስ ቆስጠንጥኖስ (ደመራ ደምራ የክርስቶስን እውነተኛ መስቀል ያገኘችው የንግሥት ዕሌኒ ልጅ) የገነባት ቤተክርስቲያን ነች።ቤተክርስቲያኗ የኦቶማን ቱርክ ወረራ  በ1453 ዓም እስክትወረር ድረስ በቤተ ክርስቲያንነት አገልግላለች።በክርስቲያኑ ዓለም በትልቅነቱ ከሚጠቀሱት ካቴድራሎች ውስጥ ቀዳሚ መሆኗ የሚነገርላት እና በዩኔስኮም በቅርስነት ተመዝግቦ የሚገኘው ካቴድራል በ1935 ዓም በቱርክ ምንግሥት ውሳኔ መሰረት እና መንግስት የ ''ሴኩላር'' መርህ የሚያከብር መሆኑ በማወጁ  ቤተክርስቲያኗ ወደ ሙዜምነት ተቀይራ ከኖረች ከ85 ዓመታት በኃላ ዛሬ ሐምሌ 17/2012 ዓም (ጁላይ 24/2020 ዓም) የቱርክ መንግስት ወደ መስጊድነት ቀይሮት የመጀመርያው የጁማ ስግደት ተደርጎባታል።

የቱርክ መንግስት ዛሬ ቤተክርስቲያኗን ወደ መስጊድነት ሲቀይር የቱርክ  መስራች አባት ሙስጠፋ ከማል አታቱርካ  (Mustafa Kemal Ataturk) በ1934 ዓም የደነገገውን በፍርድ ቤት ሽሮ ነው ጁማ ያሰገደበት።በቱርክ ለረጅም ጊዜ  ቱርክ መልሳ ቤተክርስቲያኑን ወደ መስጊድነት ከቀየረች የመጥፍያዋ ጊዜ መጀመርያ ነው የሚል ንግርት እንዳለ በሕዝቡ መሃል ሲነገር ነው የኖረው።የቱርክ መስራች አባት ሙስጠፋ ከማል ቤተክርስቲያኑ ወደ መስጊድ መቀየሩን ቀርቶ በሙዜምነት እንዲቀየር ሲያደርጉ ይህንኑ ንግርት ሰምተው ለመሆኑ ወይንም ላለመሆኑ የታወቀ ጉዳይ የለም።

ቱርክ በ1923 ዓም እኤአ 1.5 ሚልዮን የሚሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ከሀገር እንዲባረሩ ከተደረጉ በኃላ የቀሩት 150 ሺህ የሚሆኑ ክርስቲያኖች በ1955 ዓም እኤአ በተነሳው ፀረ-ክርስቲያን እንቅስቃሴ እንደገና ከሀገር በግፍ ተባረዋል።ዛሬ በመላዋ ቱርክ ያሉት ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ከ40 ሺህ አይበልጥም።ሃጊያ ሶፍያ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በተመለከተ የእንግሊዝኛ ዶክመንተሪ ፊልም ከእዚህ በፊት ጉዳያችን ላይ የወጣ ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

በዛሬው የመጀመርያ የጁማ ስግደት በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ 500 ሰዎች ብቻ የተፈቀደላቸው እና የሰገዱ ሲሆን።የቱርክ መንግስትን ውሳኔ የራሷ የቱርክ ዜጎችም የተቃወሙት እንዳሉ ነው የተሰማው።የቱርክ መንግስት ድርጊትም በዓለም አቀፍ ደረጃም ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።ጉዳዩ በተለይ ከግሪክ እና ሩስያ ኦርቶዶክስ አባቶች ከፍ ያለ ተቃውሞ ያስከተለ ሲሆን የግሪክ አቴንስ ሊቀጳጳስ ሌሮንሞስ የዛሬውን ቀን የሃዘን ቀን በማለት ጠርተውታል።ሊቀጳጳሱ በተጨማሪም ዓለም በጅኦ-ፖለቲካ እና ጅኦ-ስትራቴጂ ስር ተደብቆ ጉዳዩን ችላ ማለቱ አሳዛኝ ነው በማለት ለ''ግሪክ ሲቲ ታይምስ'' ገልጠዋል።

በሶፍያ ካቴድራል ዛሬ የጁማ ስግደት ሲደረግ (Photo =CNN)

በመጨረሻም ዛሬ የቱርክ መንግስት ወደ መስጊድነት ቀይሮ ጁማ እንዲሰገድባት ያደረጋት ሃጊያ ሶፍያ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የውስጥ መልክ የሚያሳይ ፊልም ከእዚህ በታች ይመልከቱ።






No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...