ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, December 10, 2020

ለአንድ ወር የሚቆይ በሁሉም የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በቀጥታ የሚተላለፍ፣ሁሉም ቤተ ዕምነቶች የሚሳተፉበት የጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር ስለ ሶስት ምክንያት ያስፈልጋል።

 

ባለፈው ዓመት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እንደጀመረ መላው ዓለም በተጨነቀበት ጊዜ በኢትዮጵያም ከፍተኛ መረበሽ ይታይ ነበር።በወቅቱ ጉዳያችን ቤተ ዕምነቶች በወረርሽኙ ከተዘጉ የመንግስት ሚድያዎች የቀጥታ የጸሎት እና ትምህርት መርሃ ግብር አስፈላጊነት ላይ ፅፋ ነበር።የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ ሁሉም ቤተ ዕምነቶች የቴሌቭዥን የአየር ጊዜ አግኝተው መርሃ ግብሩ በሚገባ ተከናውኖ ነበር።በእዚህም ህዝቡ ከአምላኩ ጋር የተገናኘበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ዕምነቱን የዘነጋውም ጭምር ወደ ቀልቡ እንዲመለስ አድርጎ አልፏል።በእዚህ ጸሎት ጭምር ነው ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ ብዙ የተያዘ ሰው ቢኖርም ነገር ግን  ሕይወት እስክያገድ ድረስ የማይደርስ ደረጃ ደርሶ ይሄው ክትባቱ መገኘቱ የተሰማበት ዘመን ደርሰናል።

አሁን ባለንበት ጊዜም ይሄው ተመሳሳይ አገልግሎት ሕዝብ ማግኘት ያለበት ጊዜ ነው። ለእዚህም ሶስት ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል። እነርሱም።

1) ክፉ ሲሰማ የሰነበተ አዕምሮ እንዲረጋጋ እና የስነ ልቦና ፈውስ እንዲያገኝ 

ሕዝብ በትግራይ ሲደረግ በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ ስለ ማይካድራ የዘር ፍጅት፣በህወሓት የፅንፍ ኃይል በወታደሮች ላይ ስለተፈፀመ አሰቃቂ ስቃይ፣ሲሰማ የከረመ ሕዝብ ነው ያለው።ከድርጊቱ አሰቃቂነት፣ከክህደቱ ግዝፈት እና ሌሎችም አንፃር የብዙ ሰው ልቦና አዝኗል።ስለሆነም ይህ የጸሎት መርሐ ግብር መኖሩ ሕዝብ ያፅናናል፣ተስፋ ያለመልማል፣ሕዝብ ለሕዝብ ያቀራርባል፣በሕዝብ ውስጥ ያለ የቁጣ ስሜት ያበርዳል።

2) ምስጋና ስለሚያስፈልግ 

ምስጋናው ሀ) ኢትዮጵያን ሊያፈርስ ጫፍ ከደረሰ አደጋ ሀገሪቱን መታደግ በመቻሉ ምስጋና ስለሚያስፈልግ፣

            ለ )የኮቪድ ወረርሽኝ በተፈራው መጠን ባለመሆኑ ምስጋና  ስለሚያስፈልግ እና 

            ሐ) ኢትዮጵያ ዓለም ሁሉ ጥርስ ነክሶባት የዓባይ ግድብን የመሙላት የመጀመርያ ደረጃ በሰላም በመሳካቱ የሚሉት ተጠቃሽ ምክንያቶች ይሆናሉ።

3)   ስለመጪው ሁለት ወሳኝ ጉዳዮች ለመፀለይ።መጪዎቹ ሁለት ሃገራዊ ወሳኝ ጉዳዮች አንዱ  የአባይ ግድብ ቀሪ የመሙላት ተግባር ማከናወን ሃገራዊ ምርጫ የሚሉት ይጠቀሳሉ። 

ስለሆነም የመንግስት ሚድያዎች የአየር ሰዓት ለሁሉም ቤተ ዕምነቶች ሰጥተው፣ባለፈው የታዩት ችግሮች አርመው ለአንድ ወር የሚቆይ የፀሎት እና ትምህርት የቀጥታ ስርጭት መፈቀዱ የህዝብ አዕምሮ ከማነቃቃቱ በላይ ትልቅ ሀገራዊ መረጋጋት እና በረከት ያወርዳል።
====================
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ የሚችሉበት አዲስ ቴክኖሎጂ ጉዳያችን ማስተዋወቅ ጀምራለች።
ማሳሰቢያ ለጥቂት ቀናት የሚቆይ 50%ጭማሪ ጉርሻ አለዎት። ይህ ማለት እርስዎ የ100 ብር ካርድ ቢልኩ ተቀባዩ 150 ብር ካርድ ያገኛል።
የ200 ብር ካርድ ከላኩ ተቀባይ ወዳጅዎ ወይንም ቤተሰብ 300 ብር ካርድ ያገኛል እንዲህ እያለ ይቀጥላል።ይህ ጉርሻ ለጥቂት ቀናት የሚቆይ ስለሆነ በዕድሉ ይጠቀሙ 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...