ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, December 2, 2020

ማሳሰቢያ ለማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች በሙሉ!



>> ትዕግስት፣አስተዋይነት እና ንቃት! ይፈለጋል።
>> ሶስት ዓይነት ወገኖችን የማኅበራዊ ሚድያን ለማተራመስ እንደሚሰሩ በቀጣይ ቀናት ጠብቁ።
=================
በሀገር ውስጥ የሚገኙ የማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችም ሆኑ በአውሮፓ፣አሜሪካ እና በተለይ መካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ከምንጊዜውም በላይ ትዕግስት፣አስተዋይነት እና ንቃት! ሊኖራቸው ይገባል።ይሄውም በኢትዮጵያ ካለው ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ለውጦች እና ሰሞናዊ ሁኔታዎች እየተከተለ የማኅበራዊ ሚድያውንም አንዱ ሕዝብ የማወኪያ መንገድ እንዳይሆን ጥንቃቄ ከወዲሁ ማድረጉ ተገቢ ነው። 

ስለሆነም በቀጣይ ጊዜዎች ውስጥ ሶስት  ዓይነት ወገኖች የበዛ የዘረኝነት ንግግሮች የሚለቁ ሊኖሩ ይችላሉ። እነርሱም- 

1) በሰሞኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ ስሜት ውስጥ የገቡ -

የሕግ ማስከበሩ ሂደት ውጤት የሚፈጥረው ስሜታዊ ሁኔታዎች ይኖራሉ።እነኝህን ስሜታዊ ሁኔታዎች በጊዜ እስኪሰክኑ ማሳለፍ ያስፈልጋል።በሂደት ነገሮች በአንድ ጊዜ ግልብጥ ሲሉ የሚፈጠሩ ስሜቶች የሚፈሩት ጉዳይ አለመሆኑን ወይንም ይልቁንም የተሻለ ሁኔታ መኖሩን ሲረዱ የቀደመውን ስህተት ያርማሉ።

2) የራሳቸው ወገን በዘረኝነት አልነሳ ያላቸው ሌላውን በመተንኮስ ለመቀስቀስ የሚፈልጉ -

እነኝህ ወገኖች የበዛ የዘረኝነት ቪድዮዎች የሚለቁበት ዋና ዓላማቸው የሚሰድቡት አካል ከእዚህ የበለጠ የዘረኝነት ቀስቃሽ ቪድዮ እንዲለቅ ለመቀስቀስ  እና በውጤቱም የራሳቸውን ጎሳ አበሳጭተው 'ይሄው እነእንቶኔ እንዲህ እያሉህ ነው' ብለው  መልሰው ለማነሳሳት ነው።ስለሆነም ከፍተኛ ትዕግስት፣አስተዋይነት እና ንቃት ያስፈልጋል።እነኝህ ለረጅም ጊዜ በእዚሁ ተግባራቸው ተሰማርተው መገኘታቸውን ካወቅን በፍጥነት ባሉበት ሀገር  ላለው የፀጥታ አካል ማሳወቅ ያስፈልጋል።ምክንያቱም እነኝህ በጊዜያዊ ስሜት ወይንም ካለማወቅ ሳይሆን ስራዬ ብለው እየሰሩ ስለሆነ ለሕዝብ አደገኞች ናቸው።

3) አማርኛ፣ኦሮምኛ ወይንም ትግርኛ እና ሌሎች ሀገርኛ መግባብያዎች ተናጋሪ ባዕዳን 

በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ብዙ ሰው በአማርኛ፣ኦሮምኛ ወይንም ትግርኛ ወይንም ሌሎች ሀገርኛ መግባቢያ በመፃፉ ብቻ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወይንም ኢትዮጵያዊ ነው ብሎ የማመን ችግር አለ።በአሁኑ ጊዜ አንድ ሀገር ለማተራመስ እንደ ማኅበራዊ ሚድያ አመቺ የሆነ ቀላል ግን ትልቅ ትርምስ የሚፈጥር ጉዳይ የለም።ስለሆነም ኢትዮጵያን የማይፈልጉ እና በውስጥ ሀገር ለማተራመስ የሚፈልገውን አካል ለመርዳት የሚያስቡ ባዕዳን በከፍተኛ በጀት የሚንቀሳቀሱበት እና የሚሰሩበት ጉዳይ የማኅበራዊ ሚድያ ነው።ስለሆነም እጅግ የከፉ ከፋፋይ የዘርኝነት መርዞች የሚረጩት፣ሃሳቡ የሚመነጨው ኢትዮጵያን በሚገባ ባጠኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች ሁሉ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።

በመሆኑም የማኅበራዊ ሚድያው የኢንተርኔት አገልግሎት ቆሞባቸው የነበሩ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሲለቀቁ  የሚኖሩትን ሁኔታዎች በመረዳት የሚከተሉትን ሶስት ተግባራት በመተግበር ሕዝብን ማረጋጋት ያስፈልጋል።እነርሱም -

1) የዘረኝነት መልዕክቶችን ለሌላው ባለማካፈል፣

2) ለረጅም ጊዜ በእዚህ እኩይ ተግባር የተሰማሩትን ለሕግ አስከባሪ አካላት በማቅረብ እና 

3) የሕዝቡን የእርስ በርስ መቀራረቦች የሚያሳዩ ቪድዮዎች፣ዜናዎች እና የኪነ ጥበብ ትዕይንቶችን በማካፈል ተግባር ላይ ማትኮር ይገባል።

ባጠቃላይ የማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች እነኝህን ሁኔታዎች ከግንዛቤ አስገብተው እራሳቸውን፣ቤተሰባቸውን እና ማኅበረሰባቸውን መጠበቅ ያስፈልጋቸዋል።


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...