ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, August 6, 2020

ከእንቁጣጣሽ በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግስት በአንድነት 7 ጉዳዮችን ካሳኩ ለኢትዮጵያ ቀጣይ እርምጃ መንገድ ጠራጊ ነው


የኢትዮጵያ ጉዳይ የመንግስት ብቻ ኃላፊነት ወይንም የሕዝብ ብቻ ጉዳይ አይደለም።ሁለቱ ተናበው እና ተቀናጅተው መስራት አለባቸው።ስለሆነም ከእንቁጣጣሽ በፊት ኢትዮጵያ 7 ጉዳዮችን ሕዝብ እና መንግስት በአንድነት ካሳኩ ለኢትዮጵያ አንድ እርምጃ ነው ብዬ አስባለሁ። 

1) የብሔር ዘውግ ፖለቲካ ለፅንፈኛ አክራሪ እስልምና መጋቢ መሆኑን ማቆም አለበት።ይህ በተለየ መልኩ በኦሮምያ ይታይ እንጂ በሁሉም ክልሎች በተለያየ መጠን አለ።በኦሮምኛ ተናጋሪ ክልል በተለይ በቄሮ ስም የሚንቀሳቀስ አደረጃጀትም ሆነ ስብስብ በፅንፈኛ አክራሪ እስልምና የተጠለፈ መሆኑን በግልጥ መነገር ብቻ ሳይሆን የጥላቻው ዋና አቀጣጣይ መሆኑ መታወጅ እና ወደ ማስተካከል ሥራ መሄድ፣ የክልሉ አመራር የአፈፃፀም አቅሙ ዝቅተኛ በመሆኑ መስተካከል የሚገባው የአስተዳደር አካል በቶሎ መቀየር አለበት።

2) በኢትዮጵያ ከገጠር እስከ ከተማ ሁሉም በየአካባቢው ማኅበረሰቡ እራሱን ከማናቸውም የቡድን ጥቃቶች ለመከላከል አዳዲስ አደረጃጀቶችን መፍጠር አለበት።የጋራ ችግር በጋራ ጥረት ስለሚፈታ።ለእዚህ በቅርቡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ያሳየው የጋራ የመከላከል ሥራ ተጠቃሽ ነው።እዚህ ላይ ሕዝብ እራሱ የአካባቢ ጥበቃ መርጦ እንዲያደራጅ መንግስት የመነሻ ሃሳብ እና መተዳደርያ ደንብ ሊያወጣለት ይችላል።ሕዝብ ጠባቂውን ሲመርጥ ማንን እንደሚመርጥ ያውቃል።አደረጃጀቱ ብሔራዊ ስያሜም ያስፈልገዋል።ደርግ አብዮት ጠባቂ፣ኢህአዴግ ሰላም እና መረጋጋት እንዳለ የአሁኑ የለውጥ ኃይልም ለአደረጃጀቱ አዲስ ስያሜ ያስፈልገዋል።

3) በትግራይ ህወሓት አሁን ያሉት አመራሮች በህወሓት ስምም ሆነ አልሆነ ለአዲስ እና የለውጥ ወጣቶች አስረክበው የክልሉ ሕዝብ ከዓማራም ሆነ ከሌላው ሕዝብ ጋር ሲያቃቅሩ የነበሩ ጉዳዮች በቶሎ በዕርቅ እና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መፍታት መቻል አለባቸው። አሁንም ህዝብን ከህዝብ እያጣሉ ያሉት የህወሓት አመራሮች ናቸው።ህወሓት ከምር አሁን ያሉትን መሪዎች በወጣት እና ዘመናዊ አስተሳሰብ በያዙ ወጣቶች መተካት አለበት።

4) አዲስ አበባ የአዲስ አበባን ስነ ልቦና፣ዓለም አቀፍ ማዕከልነት እና ማኅበራዊ መስተጋብር ሁሉ ያገናዘበ ግን ደግሞ እጅግ  ከሁሉም የኢትዮጵያ ሰራዊት በዋናነት ግን ከተሜ የሆነ እና የከተማን ስነልቦና የሚያውቅ ዘመናዊ የሆነ  ልዩ የወታደራዊ-ፖሊስ (ወፖ) በቶሎ ሊኖራት ይገባል።

5) ፈድራሊዝምን የሚያከብር ነገር ግን የጎሳ ፖለቲካን የሚያኮስስ ግልጥ ዘመቻ ህዝብን ማዕከል አድርጎ መከፈት አለበት።ዘመቻው የጎሳ ፖለቲካን እስከመቅበር ግብ ሊያደርግ ይገባል።ዘመቻው ከመገናኛ ብዙሃን እስከ የትምህርት ካሪኩለም ድረስ መዝለቅ አለበት።አሁን ከልብ የመጀመርያው ጊዜ ነው።

6) የህዝቡን ስነ ልቦና፣አብሮነት፣ተስፋ እና ፍቅር የሚያጎለብቱ ልዩ ልዩ መርሃግብሮች መቅረፅ እና ወደ ሥራ መግባት።እዚህ ላይ በሁሉም ክልልሎች የሚጀመሩ የስፖርት ጨወታዎች፣ሕዝብን ወደ አንድ መድረክ እንዲሳብ የሚያደርጉ የጋራ የኪነጥበብ ስራዎች እና መንፈሳዊ አገልግሎቶች ሁሉ በሚገባ ተዘጋጅተው የህዝቡን ስነ ልቦና ከፍ ማድረግ አለባቸው።

7) የኢትዮጵያ ራድዮ እና ቴሌቭዥን የዜና፣የመርሃግብር ይዘት እና የትኩረት አቅጣጫ ለውጥ ማድረግ።
አሁን ያሉት የመንግስት ሚድያዎች የዜና ትኩረት፣የመርሃግብር ይዘት እና የትኩረት አቅጣጫ በገጠርም ሆነ በከተማ ከሚኖረው ሕዝብ ጋር የተሰናሰለ አይደለም።ሃሳቡን በአጭሩ ለመግለጥ፣አሁን ባለንበት ዘመን አደጉ በተባሉ ሀገሮችም የሚታዩ አቀራረቦች አሉ።የመጀመርያው አቀራረብ ለምሳሌ የአንድ ቤተሰብ ውሎ እንዳለ ሳይቀነስ እና ሳይጨመር ማቅረብ።ጧት ሲነሱ፣ልጆች ፊታቸውን ሲታጠቡ፣ሲያወሩ፣ወዘተ እውነተኛው የህዝቡ ስሜት ምንም ያልተጨመረበት ንግግሮች ውስጥ ይነበባሉ።ፍቅር፣ማኅበራዊ ችግሮች፣የመጪው ትውልድ ስሜት ሁሉ በእንዲህ ዓይነት ያልተቀባቡ ግን እንደወረደ በሚተላለፉ ዝግጅቶች ይታወቃል።ያንን ተመልክቶ መተንተኑን ለሕዝቡ ተዉለት።ይህ ምሳሌ ነው።ሌሎቹ ይዘቶች እና ዜናዎች ላይ የገጠሩ ሕዝብ እንዲሰማው ሆኖ ነው የሚቀርበው? ሁሉ መፈተሽ አለበት።የብዙ ችግሮች ውጤት የሚድያዎች የረጅም ጊዜ የተበላሸ አቀራረብ ውጤትም ጭምር ነው።

ሰባቱም ተግባሮች  ከእንቁጣጣሽ በፊት ስራቸው ከግማሽ በላይ መሄድ ይችላል።
==============/////================
ከታሪክ ማኅደር ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ የእንግሊዟን ንግስት ኤልሳቤጥ ለመጎብኘት ሄደው ያጌጡት በኦሮሞ ፈረሰኛ ጎፈሬ ነበር።

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...