Thursday, July 3, 2014

''ይህ ልብ የሚሰብር ዜና ነው በምንም ዓይነት አንገት የሚሰብር ግን አይደለም።በእዚህ አንገቱን የሚሰብረውን ሰው ያክል አንዳርጋቸው የሚፀየፈው ሰው የለም።አንዳርጋቸውን እኔ አውቀዋለሁ።ወያኔዎች እሱን በመያዛችን እናገኛለን የሚሉት ነገር ካለ ምንም ነገር አያገኙም።አንዳርጋቸው ትግሉን አንድ ምዕራፍ አሻግሮት ጨርሷል።አመራር ማብቃት ያለበትን ወጣቶችን አብቅቷል።አሁን ሂድ ጨርሰናል ተብሎ ለንደን መኖር ጀምሯል።ከአሁን በኃላ ብንወድቅም እየታገልን ነው የምንሞተው ብንሞትም እየገደልን ነው የምንሞተው።አሁን ጌሙ ተቀይሯል። ዛሬ ብዙ ሰዎች ሲያለቅሱ ሰምቻለሁ ግን አንዳርጋቸውን የምትወዱት ከሆነ አንዳርጋቸው የታገለለትን ዓላማ ነው መውደድ ያለባችሁ አንዳርጋቸውን አይደለም።አንዳርጋቸው ለቅሶ አይደለም የሚፈልገው አሁን አንዳርጋቸው የጀመረውን ትግል ዳር የሚያደርሱ ታጋዮች ነው የሚፈልገው።'' ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ዛሬ የተናገሩት (ቪድዮ)



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:

''ሙዝ አትብላ! ጦጣዎች ከጫካ ሊመጡ ይችላሉ።'' ዓይነቱ የጀዋር ጊዜው ያለፈበት ትንተና በኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ላይ።

ቀይ ባሕር ዛሬ በዩቱብ አገኘን ብላችሁ በኢትዮጵያ የባሕር በር ጉዳይ ላይ የምትሳለቁ የዘመናችን ባንዳዎች ግዴላችሁም ጊዜ እና ትውልድ ይፈርዳል! እናንተን ብቻ ሳይሆን ልጆቻችሁም ''አባታቸው በዩቱብ ኢትዮጵያ ...