Saturday, September 22, 2012

የ ኢትዮጵያን መጪ ዘመን የሚያመላክቱ ያለፉት የ 24 ሰዓታት ክስተቶች

ትናንት መስከረም 11 እና ዛሬ መስከረም 12/2005 ዓም በ ሀገራችን የ ፖለቲካ መድረክ ላይ መጪውን ዘመን የሚያመላክቱ ሶስት ሁኔታዎች ታይተዋል። ነገን በደንብ የሚያመላክቱ ኢትዮጵያውያን በውል ልንመለከተው የሚገባም ይመስለኛል።ኢህ አዲ ግ ወደቀደመው መዝሙሩ ከ አቶ መለስ ሞት በኋላ ሙሉ በሙሉ መመለሱን፣ ለለውጥ ዝግጁ አለመሆኑን በደንብ አረጋግጧል።በነገራችን ላይ አቶ ሃይለማርያም '' በመተካካት የ ኢህአዲግ ባህል መሰረት ወደ ስልጣን መጡ'' የሚለው ፈፅሞ ሐሰት ነው።መተካካት የሚባለው አቶ መለስ በ ፈቃዳቸው ስልጣን ለቀው ቢሆን ነበር እንጂ በ ሞት ሲለዩ በቦታቸው ሌላ ሰው ማስቀመጥ መተካካት አይባልም።
መጪውን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች  

መጪውን አመላካች 1 :-  ''አሁንም አጨብጭቡ!''
መስከረም 11/2004 ዓም  (Sep.21/2012)  አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በ ኢህአዲግ ምክርቤት ለማፀደቅ አቶ አባ ዱላ ምክርቤቱን እንዲያፀድቅ ሲጠይቁ ዝምታ ሰፈነ ቀጠሉና አባ ዱላ እንዴት እንደሚጨበጨብ ለማሳየት እጃቸውን እንደማጨብጨብ ሲያደርጉ የ ምክርቤቱ አባላት ማጨብጨብ ጀመሩ።
መጪውን አመላካች 2 - ''ጉድጓድ እስኪገባ?''
''መተካካት ማለት አዲሱን መሪ  በ ሩቅ  ሆኖ መታዘብ ማለት አደለም----- በሕይወት እስካለን ጉድጓድ እስኪገባ ድረስ ድጋፍ መስጠት አለብን---- የትም አንሄድም።----ህዝቡ እስካለ ድረስ አዲሱ አመራር ወለም ዘለም የሚልበት ዕድል አይኖረውም'' አቶ ስዩም መስፍን መስከረም 12/2005 ዓም  (Sep.22.2012) ለ ኢ ቴ ቪ  ከሰጡት መግለጫ።
መጪውን አመላካች 3 - ''ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ------!!!''
''ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ'' በማለት ከ 20 ጊዜ በላይ የጠራው የ ህዋሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ መስከረም 12/2005 (Sep.22.2012) ዓም በ ኢ ቴ ቪ ያስነበበው መግለጫ። በመጨረሻ እንዲህ አለ:-
''በተግባር የተፈተነው የድርጅታችን መስመሮች  ጓድ መለስ እንዳለው በድርጅታችን መቃብር ላይ ካልሆነ በቀር  በማንኛውም መንገድ ለ ድርድር እንደማይቀርብ ደግሞ ደጋግሞ ያረጋግጣል''
አሁንም አሳዛኝ ''ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ'' ነገር ገባን። ኢህአዲግ እራሱን ለማረም አልቻለም። ሁሉ ነገር እንደነበረ ይቀጥላል፣ ፖለቲካዊም፣ማህበራዊም ምጣኔ ሃብታዊም  ሽግርግር የለም።በ ኢህአዲግ  በ ክልል እና በ ቋንቋ የተከፋፈለ ትውልድ ነው የምንወርሰው? ይች ነች በ ኢህአዲግ  ቅኝት ውስጥ የምትኖረው ኢትዮጵያ?
 







 

3 comments:

Anonymous said...

mikerew mikerew kalsema mekera ymkerew new weyane.

Anonymous said...

እራስ የሚያም ነገር ነው። አሁንስ በዛ ቤተክርስቲያንን የዘረፈው መንግስት ብሎ ብሎ በቀደም እለት በ አቦይ ስብሃት በኩል ''ኦርቶዶክስ ስልጣን ባለመያዙ ተደስተናል'' ተባልን። ይህን ክላሲካል ስሰማ ውስጤ ደማ። ለ እራሴም ለሃገሬም አለቀስኩ። እመብርሃን አንቺ አጽናኚን።ጎረቤቶቸም እኩል ቁጭ ብለው አብረውኝ አለቀሱ።ቀጥለን ለምን አለቀስን? ብለን የቀረበውን ቡና ሳንጠጣ ተነጋገርን።የሚገርም ቅዳሜ አሳለፍኩ።መብታችን በ እጃችን ነው የሁላችንም ቃል ነበር።የ ዛሬን ቅዳሜ አልረሳትም።ክላሲካሏም ከ ውስጤ ተቀበረች። ይህን አስተያየት እንድጽፍ ያዘዙኝ አብሮ አደግ ጎረቤቶቸ ናቸው።

Anonymous said...

WEYNE HAGERE
MEQELEJA HONSH???
ENGA AHUN SEW ENBALALEN? WSHETAMOCH NEN.HAGEREEEEEEEEEEEE

OOOOOO!!! LBEL?