Saturday, July 4, 2020

አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች በሰላማዊው ሕዝብ ባደረሱት ጥቃት የ166 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን መንግስት ገለጠ።ከአስመራ ሲገባ በአቦይ ስብሐት የምሳ ግብዣ የተደረገለት ኦነግ ሸኔ በዓማራ ክልል ላይ የሞከረው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

በእዚህ ፅሁፍ ስር-   
  • በሐረር የተፈፀመ አንድ የግፍ ጥቃት የከተማው አምቡላንስ ባለመምጣቱ ከፈረንሳይ በተደወለ ስልክ ህይወቱ የተረፈበትን ታሪክ እና 
  • ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ በኦሮምያ የንፁሃንን ደም የሚያፈሱትን የመከረችበት ቪድዮ ያገኛሉ።

ባሳለፍነው ሳምንት መጀመርያ ላይ በተወዳጁ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ በግፍ ከተፈፀመው ግድያ ተከትሎ በኦፌኮ አባላት በጀዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ እንዲሁም በኦኤምኤን ቅስቀሳ በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮምያ ክልል እና በአዲስ አበባ የፀጥታ ችግር መፈጠሩ እና በመቀጠልም ጀዋር እና በቀለ ገርባን፣1084 ሰዎች መታሰራቸው እና እስካሁን የ166 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን ኮማንደር ግርማ ገላን የኦሮምያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሰጡት ቃል ገልጠዋል።እንደ ኮማንደሩ ገልጣ 10ሩ ሰላማዊ ሰዎች በአዲስ አበባ የሞቱ ሲሆን፣145ቱ ደግሞ በተለያዩ የኦሮምያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ የፅንፈኞች ጥቃት ሳብያ ህይወታቸውን ያጡ መሆናቸው እና 11 ከፀጥታ ኃይሉ ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጧል።

በሰሞኑ ክስተት በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት በርካታ መረጃዎች ስላልወጡ እንጂ በሐረር፣ዝዋይ፣ሻሸመኔ፣ሞጆ፣ምዕራብ ሸዋ እና አርሲ  ውስጥ ምንም ዓይነት ፖለቲካ የማያውቁ ከሁለት ትውልድ በላይ የኖሩበት ከተማ በግፍ የተገደሉት ቁጥር ብዙ እንደሆነ ነው የሚነገረው ። ለምሳሌ የእዚሁ ዜና አዘጋጅ በሐረር የተፈፀመው ግፍ እንደምሳሌ ያቀርባል።በእዚህ በያዝነው ሳምንት ውስጥ በሐረር አራተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ኮንደሚንየም በግል ስራው የሚተዳደረው የቤተሰብ ኃላፊ ላይ የደረሰው ግፍ ጉዳዩን በሚገባ ከሚያውቀው ሰው ሰምቷል።ግለሰቡ በእዚሁ በሐረር ከተማ አራተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያለው ኮንደሚንየም ነዋሪ ነው ።ግለሰቡ ከአዲስ አበባ ሊጠይቁት የመጡትን ዘመዶቹ ጋር ቤቱ ተቀምጦ እያወራ ነበር። ባለፈው ሮብ በድንገት ሁለተኛ ፎቅ የሚገኘው ቤቱ መስኮቱን ሰብረው እቤት ውስጥ ያሉትን ሰዎች ከባለቤቱ ጨምሮ በግፍ ይቀጠቅጧቸዋል።በመሃል ስልክ ወደ አምቡላንስ እና ወደ ፖሊስ  ቢደውሉ፣ የሚደርስ የለም።በመሃል ፈረንሳይ ሀገር የምትኖር እህቱ ደውላ አደጋ ላይ መሆናቸውን ሰምታ አዲስ አበባ እና ሌላ ቦታ የሚኖሩ ለምታውቃቸው ደውላ በብዙ ስልክ አምቡላንስ እንደደረሰለት ሰምተናል።አሁን ባለው ሁኔታ አንዳንድ የኦሮምያ ፖሊስ አባላት እና ኃላፊዎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እያዩ እንዳላዩ የሚያዩ እንዳሉ እየተነገረ በመሆኑ የእዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈፅሙትን መንግስት ተከታትሎ ለሕግ ማቅረብ አለበት። 

ይህ በእንዲህ እያለ ከሁለት ዓመት በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በአቦይ ስብሐት የምሳ ግብዣ የተደረገለት የኦነግ ሸኔ ቡድን ወደ ዓማራ ክልል በባቲ ከተማ በመግባት በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ሊፈፅም የነበረው ጥቃት በመከላከያ እና በዓማራ ክልል ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የዓማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 27/2012 ዓም ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ገልጠዋል። በእዚሁ መግለጫቸው ላይ አቶ ተመስገን እንዳብራሩት የሽብር ቡድኑ የአዲስ አበባው ጥፋት ቅጣይ መሆኑን እና የቡድኑ መሪ ጨምሮ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን እና የቀረዑት ከሙሉ ትጥቃቸው ጋር መያዛቸውን ነው የገለጡት።በመጨረሻም አቶ ተመስገን መንግስት በቀጣይ የሸረሪት ድሩ ላይ ብቻ ሳይሆን በሸረሪቱ ላይ አትኩሮ እንደሚሰራ  ነው የገለጡት።

በመጨረሻም ሰሞኑን በውጭ የሚኖሩ የህወሓት፣ኦነግ ሸኔ እና የጀዋር ደጋፊዎች በአንድነት የተለያዩ የማኅበራዊ ሚድያ ገፆች እየከፈቱ የተለያዩ የጥላቻ ቪድዮዎች እየለቀቁ ሲሆን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ለመንግሥታቱ የጥላቻ ንግግሮች የሚዘሩትን እየጠቆሙ እንደሆነ ነው የተነገረው።ጉዳዩን በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችም በቀጥታ ላሉበት መንግስት የጥላቻ ንግግር የሚዘሩትን ከመጥፎ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማመልከት ይገባቸዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም አዲስ አበባ ያሉትን ኤምባሲዎች በጉዳዩ ዙርያ ቢያነጋግር እና ጉዳዩን ቢከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ በዘረኝነት የጥላቻ ንግግር የሚያልቀውን ሕዝብ ለመታደግ እንደሚጠቅም ማሰብ ተገቢ ነው።

ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ በኦሮምያ የንፁሃንን ደም የሚያፈሱትን የመከረችበት ቪድዮ 

 


Friday, July 3, 2020

በሕወሓት እና በግብፅ መንደር ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ የሚመራው የለውጥ ኃይል በእዚህ ሳምንት በከፍተኛ ደረጃ ወደፊት ተስፈንጥሯል ማለት ይቻላል።ዓርብ ሰኔ 26፣2012 ዓም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፀጥታ እና የፍትህ አካላት ያሉበትን ኮሚቴ ሰብስበው ባደረጉት ውይይት ላይ ሰሞኑን እየተደረገ ያለው ጥፋት ቀደም ብሎ በደህንነት መስርያቤት ተመስርቶ የነበረው የ''ኢኤንኤን'' ቴሌቭዥን ከሁለት ዓመት በፊት የሚያሳየውን የስፖርት ጨዋታ አቁሞ በኦሮሞ እና አማራ መሃል ጠብ እንዳለ ለማስመሰል የነዛው ፕሮፓጋንዳ ቅጥያ ነው ያሉ ሲሆን፣ አንድ ጊዜ ዓቢይ ታፈነ ሌላ ጊዜ ታከል ታፈነ እያሉ የሚያወሩ ከንቱ ምኞታቸውን ነው የሚነግሩን ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልፅግና ፓርቲን እና አሁን ያለውን አመራር አስመልክተው ሲናገሩ ባለፉት ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ አሁን ያለነው የብልፅግና አመራር የእዚህን ያህል የጋራ አመለካከት ኖሮን አያውቅም ያሉ ሲሆን መስከረም 30 መንግስት የለም ሲሉ የነበሩ ለመስከረም 30 ያቀዱትን አሁን ለማፍጠን የተገደዱበት ምክንያት ባለን መረጃ መሰረት ባንዳዎቹ ከግድቡ ጋር በተያያዘ አጉራሾቻቸው ለእኛ አሁን ካልሆነ ምን ይሰራልናል ስላሏቸው  የእነርሱን ፍላጎት ለማርካት ያደረጉት መሆኑን አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ በሰሞኑ የመንግስት ጠንካራ እርምጃዎች ሳብያ በህወሓት መንደር እና በካይሮ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል።በተለይ በአዲስ አበባ በትናንትናው ዕለት ዓርብ ሰኔ 26/2012 ዓም ፖሊስ የጀዋር መሐመድን እና የበቀለ ገርባን ቤት ጨምሮ ሌሎች ስፍራዎች ባደረገው ፍተሻ ከፍተኛ ሰነዶች እንደያዘ ነው የተሰማው።በእዚህ መሰረት ከድርጊቱ ጋር  አላቸው የተባሉ መረጃዎች ከህወሓት ጋር እና ከአንዳንድ የግብፅ ንግድ ድርጅቶች ጋር መያያዛቸው ያልተጠበቁ መረጃዎች መንግስት እጅ እንዲወድቁ ማድረጉ ተሰምቷል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በዓርብ ዕለት ማብራርያቸው ላይም ቀድሞ አሸባሪ ይል የነበረው ነው ዛሬ አሸባሪ ሲለው ከነበረው ጋር የገጠመው በማለት የጠቀሱት ይህንኑ የሚስጥር ዕቅድ በተመለከተ ጥቆማ የሚሰጥ ነው።ሃጫሉን በቁሙ ሲያራክሱት የነበሩት ናቸው ዛሬ ለእርሱ የሚቆረቆሩ መስለው ከእኛ በላይ ያዘኑ መስለው የቀረቡት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሁን ሀሳባቸው ሁሉ ጨንግፏል ብለዋል።

ግብፅ የዓባይን ድርድር አስመልክታ ይዛው የነበረው ስልት በሰሞኑ የመንግስት የውስጥ በጥባጮችን በድንገት በመቆጣጠሩ እና ሌላው ቀርቶ ያሏቸውን የውስጥ ደጋፊዎች ለማግኘት እንዳይችሉ የኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ መዘጋት ለካይሮ የስልት መቃወስ ገጥሟታል። በመሆኑም የመረጃ መስመራቸው ሁሉ ጎርፍ እንደበላው አፈር በፍጥነት እንደተሸረሸረባቸው ነው የሚሰማው። በተመሳሳይ መንገድ በህወሓት መንደርም የሆነው ይሄው ነው።ህወሓት ዛሬ  ቢጨንቃት ምሽት ላይ መያዣ መጨበጫ የጠፋው መግለጫ አውጥታለች። መግለጫው በራሱ የሚያሳየው ጉዳይ ቢኖር ግራ የተጋባ ሰው ቃላትን ሰብስቦ በአንድ ጆንያ ያጨቀው  እንጂ መሰረታዊ የመግለጫው መልዕክት በራሱ መግለጫውን ላወጣው አካልም ግልጥ አይደለም።
አሁን መንግስት ትኩረቱ በህወሓት ቀንደኛ ተጠያቂ ባለስልጣናት ላይ አነጣጥሯል።የመቀሌ ሕዝብም ከምሽት ጀምሮ እንቅስቃሴው ቀንሷል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወታደራዊ ደንብ ልብስ ለብሰው መግለጫ መስጠታቸው በራሱ ለህወሓት መልዕክት ማስተላለፋቸው መሆኑን የተረዳው የመቀሌ ሕዝብ ቁጥሩ ቀላል እንዳልሆነ የሚናገሩ አሉ። 

በመጨረሻም ሕዝቡ ህወሓት ሰልችታዋለች።ህወሓት ተወግዳ በነፃነት ከጎንደር እስከ ሞያሌ፣ ከአስመራ እስከ ምፅዋ ተንቀሳቅሶ እና ነግዶ የሚኖርበት ሕይወት ናፍቆታል።ስለሆነም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነፃ እንዲያወጣው በጉጉት እየጠበቀ ነው።በእርግጥ በውጭ ሀገር ያሉ እንደ መቀሌ እና አዲግራት ሕዝብ ውሃ ያልጠማቸው በማኅበራዊ ሚድያ ህዝቡ ከህወሓት ጋር እንደሆነ ጧት ማታ እያወሩ ነው።እነርሱ ይዘውት የወጡትን የህዝቡን ዳቦ መብያ ገንዘብ እየተምነሸነሹ በሕዝቡ ላብ እና ደም የሚቀልዱ ናቸው።ለሁሉም ግን ኢንተርኔት ከመቀሌ ነፃ መሆን በፊት ላይከፈት ይችላል።   

የደቡብ ኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ስለ ዓባይ ያዜሙት ድንቅ ኢትዮጵያዊ ዜማ ቪድዮ ይመልከቱ 





Thursday, July 2, 2020

ሰው ከእንስሳ የሚለየው ማሰብ በመቻሉ ነው - የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ወንድም ሐብታሙ ሁንዴሳ ከወንድሙ ቀብር በኃላ ለቪኦኤ ዛሬ ከሰጠው ቃል (ሙሉውን ቪድዮ ይመልከቱ)

''ስለቀብሩ መጠየቅ ያለበት ቤተሰብ ነው። ሬሳ እንዳይቀበር ፀብ መፍጠር እና ሌላ ሰው እንዲሞት ማድረግ ይሄ ማሰብ አይመስለኝም።ሰው ከእንስሳ የሚለየው በማሰቡ ነው።ማሰብ ደግሞ ትልቅ ነገር ነው።ነገሮችን በስሜት ከመነዳት ወጣቱ እንዲያስብ የሚል መልዕክት አስተላልፋለሁ።''
ሐብታሙ ሁንዴሳ
Video source= VOA Amharic Service July 2,2020

Wednesday, July 1, 2020

ሰበር ዜና - ጀዋር መሐመድ፣በቀለ ገርባ እና ግብረ አበሮቹ በሰኞ ዕለቱ ግድያ ብቻ ሳይሆን ከእዚህ በፊት ባደረጉት ቅስቀሳ እና በጥቅምት ወር ለሞቱት 97 ሰዎች ወንጀል ሁሉ እንደሚከሰሱ የፌድራል ፖሊስ አስታወቀ

>> ከአሁን በኃላ ለሕግ ቀርበው በፍትህ እንጂ በሽምግልና የሚፈታ ምንም ነገር የለም - የፌድራል ፖሊስ 

የፌደራል ፖሊስ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኃላፊው በኩል በሰጠው መግለጫ የጀዋር መሐመድ ቡድን በአስከሬን ነጠቃ ብቻ አይደለም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ብሏል ፖሊስ በማብራርያው።ግለሰቦቹ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችን በመግደል በአዲስ አበባ ላይ የሰኔ 15ቱ ዓይነት እልቂት ለመፈፀም ቀደም ብለው አቅደው እንደነበር ነው ከምርመራው ሂደት የተረዳነው እና እየወጡ ያሉት መረጃዎች ያለው የፖሊስ መግለጫ፣በእነ ጀዋር ላይ የሚደረገው ክስ በእዚህ ሳምንት ባደረጉት የመግደል ሙከራ ብቻ ሳይሆን ከእዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሲቀሰቅሱ የነበሩበት ሂደት እና በጥቅምት ወር ላይ ባደረጉት ቅስቅሳ ለጠፋው የ97 ሰው ሞት ጭምር ጉዳዩ ተመርምሮ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተሰጠው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።

የፖሊስ ኮሚሽነሩ መግለጫ በተለይ የእነጀዋርን ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ ከአሁን በኃላ በሽምግልና ወይንም በሌላ መንገድ የሚታይ ምንም ዓይነት ዕድል አለመኖሩን እና ጉዳዩ በአስቸኩአይ አዋጅ ውስጥ ብንሆንም ለሕግ እና ስርዓት መከበር ምርመራው በሚገባ ተፈፅሞ ለፍርድ ይቀርባሉ ብለዋል።የምርመራውን ውጤትም በእየጊዜው ለሕዝብ እንደሚገለጥ ነው የፖሊስ ኮሚሽነሩ ያብራሩት።
 

"ደወል" በገጣሚት ረድኤት ተረፈ 

ከጦብያ ግጥምን በጃዝ የተወሰደ  

ግጥሙ ከላይ ከተፃፈው ዜና ጋር አይገናኝም 

 
 

Tuesday, June 30, 2020

ሰበር ዜና -የሎሬንት ፀጋዬ ገብረመድህን ቤተሰብ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴን አስከሬን ከቤተሰቦቻቸው ለመንጠቅ የሞከረው ጀዋር እና የድርጊቱ ፈፃሚዎች 35 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።


ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ 

(ጉዳያችን ዜና)

በጀዋር እና ግብረአበሮቹ ተግባር በርካታ የአምቦ፣የኦሮምያ እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ አበሳጭቷል። 

ከእናቱ ወ/ሮ ጉደቱ ሆራ እና ከአባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ 135 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው በአምቦ ከተማ የተወለደው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴ ትናንት ሰኔ 23/2012 ዓም በአዲስ አበባ ገላን ኮንደሚንየም አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች መኪናው ውስጥ እያለ በተተኮሰ ጥይት በሚያሳዝን መልኩ ህይወቱ አልፏል።የድምፃዊው ሕይወት በእንዲህ ዓይነት መልኩ መቀጠፉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ አሳዝኗል።ጉዳያችንም በድምፃዊ ሃጫሉ ሞት ላዘኑ ቤተሰቦቹ መፅናናትን ለሀጫሉም ዕረፍተ ነፍስን ትመኛለች።ድምፃዊ ሃጫሉ በኢትዮጵያ የስነ ፅሁፍ ታሪክ ትልቅ አሻራ ያስቀመጡትየአምቦው ተወላጅ  እና የሀገር ወዳዱ ሎሬንት ፀጋዬ ገብረመድህን ቤተሰቦች ጋር በአያቱ በኩል እንደሚገናኝ ከቤተሰቡ መረዳቱን አርቲስቱ በአንድ ወቅት በሰጠው መግለጫ ላይ ገልጦ እንደነበር ጉዳያችን ታስታውሳለች።

ይህ በእንዲህ እያለ ዛሬ ሰኔ 23/2012 ዓም የሃጫሉ ሁንዴሳን አስከሬን ቤተሰቦቹ ይዘው ወደ አምቦ በበርካታ ሕዝብ ታጅበው እየሄዱ ሳለ የቀድሞው የኦሮምያ ኔትወርክ ሚድያ ሥራ አስኪያጅ እና የአሁኑ የኦሮሞ ፈድራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ከጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን አስከሬኑን ከቤተሰቦቹ ለመንጠቅ ሙከራ ማድረጋቸው እና በምላሹም ከፌድራል ፖሊስ ጋር ግጭት መፈጠሩን ለማወቅ ተችሏል። በኢትዮጵያ ባሕል መሰረት አንድ ሰው ከእዚህ ዓለም በሞት ሲለይ አይደለም በሀገር ውስጥ ሆኖ በውጪ ሀገርም ቢኖር  አቅሙ እንደፈቀደ በትውልድ ቦታው መቀበር የነበረ ልማድ እና ባሕል ነው።የድምፃዊ ሃጫሉ  ቤተሰቦችም ይህንኑ ለማድረግ ወደ አምቦ መንገድ እንደጀመሩ ነው ጀዋር እና ግብረአበሮቹ አስከሬኑን ነጥቀው በመኪና በመጫን ህዝቡ የአስከሬን ዝርፍያ ያለውን ተግባር የፈፀሙት።

በእዚሁ የአስከሬን ነጠቃ ሙከራ ሳብያ በተከተሉ ሶስት ፍንዳታዎች መሰማታቸውን እና ቁጥራቸው እስካሁን ያልተገለጠ ኢትዮጵያውያን መጎዳታቸው ተሰምቷል።ከሞቱት ውስጥ ያፈነዱትን ጨምሮ ጉዳት ማድረሱ ነው የተገለጠው።ይህንኑ ተከትሎ የድምፃዊ ሃጫሉ አስከሬን ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ መገደዱን እና በኃላ በኤሊኮፍተር ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል።ይህ በእንዲህ እያለ መንግስት ድምፃዊው ከተገደለበት ሰዓት ጀምሮ ማን እንደፈፀመው ሳይገለጥ የእርስ በርስ ግጭት እና ጠብ የሚፈጥር ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረው የኦሮምያ ሚድያ ኔትወርክ በፌድራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።በሌላ በኩል ከጀዋር ጋር አቶ በቀለ ገርባም በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተሰማ ሲሆን በተለይ አቶ ጀዋርን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው ተግባር ላይ የአቶ ጀዋር ጠባቂዎች በሙሉ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረገ ሲሆን በሂደቱ ላይ አንድ ፖሊስ ህይወቱን ማጣቱ ነው የተሰማው።

በነገራችን ላይ ድምፃዊ ሃጫሉ በተለያዩ ጊዜ በሰጣቸው መግለጫዎች የብዙዎችን ትኩረት የሳበ አርቲስት ነው።ከእነኝህ መግለጫዎቹ ውስጥ - ''ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፣አይደለም የቴዲ አፍሮን የማሊንም ሙዚቃ እሰማለሁ፣''በማለት ከሚድያ ለተነሱለት ጥያቄዎች የመለሳቸውን ምላሾች አሁን ድረስ የምያስታውሱለት ብዙዎች ናቸው።በአንድ ወቅት ድምፃዊው፣ የጀዋርን እና በቀለ ገርባን አና አንዳንድ የኦሮሞ ዘውግ ፖለቲከኞች ከህወሓት ጋር የሚያደርጉትን መሞዳሞድ በግልጥ የወቀሰበት ጊዜም ነበር።ሌላ ጊዜ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ላይ በአንድ ወቅት ''ኦሮሞ አይደለም'' የሚል የሐሰት ዘመቻ ለከፈቱትም የሰጠው ምላሽ ''ዓቢይን አውቀዋለሁ ከሁላችንም ያልተለየ ኦሮሞ ነው።ዓቢይ ሀገር እየመራ ነው።ዛሬ በእርሱ ላይ የሚደረግ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነገ ሌላ የኦሮሞ ሰው ስልጣን ላይ ቢመጣም የሚቀር አይደለም።ስለሆነም ማናቸውም በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ላይ የሚደረገውን የስም ማጥፋት ዘመቻ አንቀበልም።'' ማለቱ ይታወሳል።

የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ለአምስት ዓመታት በቀድሞው የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት ታስሮ የነበረው ድምፃዊው ሃጫሉ የሚሰማውን ፊት ለፊት በመግለጥ ይታወቃል።በ36 ዓመቱ ሕይወቱን ያጣው ድምፃዊ ሃጫሉ ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።ለሀጫሉ ቤተሰብ መፅናናትን፣ለእርሱም እረፍተ ነፍስ ይስጥልን።




 


Monday, June 29, 2020

ሰበር ዜና - በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት በዛሬው የዓባይ ጉዳይ ስብሰባ ላይ የአሜሪካ ተጠሪ አምባሳደር ኬሊ ክራፍት ያደረጉት ሙሉ ንግግር ጉዳያችን አግኝታለች።ሙሉውን ያንብቡ። Breaking News - US Ambassador to UN, Kelly Craft's speech on the security council meeting of GERD, June 29/2020

''The United States takes note of the recent efforts of the African Union to facilitate additional discussions among the three countries on the GERD. We acknowledge the efforts by South African President Ramaphosa to bring this issue before the African Union bureau.'

Ambassador Kelly Craft Permanent Representative U.S. Mission to the United Nations

Ambassador Kelly Craft

===================
Ambassador Kelly Craft

Permanent Representative
U.S. Mission to the United Nations
New York, New York
June 29, 2020

AS DELIVERED

Thank you, Mr. President. Thank you for your efforts over the past several days to accommodate this important issue before the Security Council. Under-Secretary-General DiCarlo, we appreciate your insightful remarks.

Through our engagement as a facilitator and observer of the negotiations on an agreement for the filling and operation of GERD over the last several months, the United States understands and appreciates the importance of the Nile River to the histories and futures of Egypt, Ethiopia, and Sudan.

We have seen firsthand how the Nile is deeply intertwined with the national identities of Egypt, Ethiopia, and Sudan and how its future is of paramount importance to the livelihoods and the well-being of their peoples. I know firsthand, as President Trump has prioritized the GERD within our Cabinet.

The GERD poses a unique opportunity for this part of Africa, where precipitation droughts, desertification, and economic underdevelopment have befallen generations of people. An agreement on the GERD has the potential to transform a region that is home to over 250 million people, expanding economic opportunities through transboundary cooperation and regional integration. Increased food security, improved energy access, and expanded agriculture projects are just a few of the transformational benefits that the GERD can afford the region.

The considerable work by Egypt, Ethiopia, and Sudan over the last several months shows it is possible to reach a balanced and equitable agreement that takes into account the interests of the three countries if there is a commitment among all to do so. We commend the Government of Sudan and Prime Minister Hamdok’s administration for ongoing efforts to encourage this process and bring the parties together, including through hosting talks earlier this month.

The United States takes note of the recent efforts of the African Union to facilitate additional discussions among the three countries on the GERD. We acknowledge the efforts by South African President Ramaphosa to bring this issue before the African Union bureau.

We recognize that this issue is before the Council because time is short and the window to achieving such an agreement may be rapidly closing. We encourage all countries to build on their substantial progress in prior negotiations and the compromises that led to that progress, and further call on all countries to refrain from making any statements or taking any actions that would undermine the good will necessary to achieve an agreement.

We strongly believe that with constructive dialogue and cooperation a solution is within reach, and we reaffirm our commitment to remain engaged with the three countries until they conclude a final agreement.

We look forward to receiving further reports on this very important issue. Thank you.

የስምዖን ጉዳይ ተገቢው ምርመራ እና ፍትሕ ይፈልጋል

 ወጣት ስምዖን ደስታ (ፎቶ ኤንአርኮ)

(ጉዳያችን ሪፖርት)

ስምዖን ደስታ ይባላል።በኦስሎ፣ኖርዌይ ነዋሪ ነው።ስምዖን በስነ ምግባሩም፣በትምህርቱ እና ከሰዎች ጋር ባለው መግባባት ሁሉ የሚያውቁት ብቻ ሳይሆን በአንድ ቀን የተዋወቁት ሁሉ የሚወዱት ነው።በኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት አባል እና በሚታዘዘው አገልግሎት ሁሉ  በማገልገል በምሳሌነት የሚጠቀስ ቅን ወጣት ነው።

ይህ ወጣት ባሳለፍነው ወር ማለትም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ግንቦት 17/2020 ዓም የኖርዌይ ብሔራዊ በዓል ቀን የሚከበርበት ዕለት እንደመሆኑ እርሱም የበዓሉን ዝግጅት ከቅርብ ባልንጀሮቹ ጋር ለማክበር በኦስሎ የከተማ አውቶብስ  እየሄደ ነበር። በመጨርሻም ''ልሳከር'' የአውቶብስ ጣብያ (የመውረጃ ቦታው) ሲደርስ እንደማንኛውም ተሳፋሪ ከአውቶብሱ ሲወጣ የገጠመው እጅግ አስደንጋጭ ጉዳይ ነበር። ስምዖን ለኖርዌይ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (ኤንአርኮ) እንደ አውሮፓውያ አቆጣጠር ሰኔ  24/2020 ዓም እንደገለጠው እና ጋዜጠኛ አኔት ሁብሰን እንደዘገበችው -

'' ከአውቶብሱ እንደወረድኩ አንድ ሰው ወደ እኔ እየተጠጋ ፀያፍ ስድቦችን ሰደበኝ፣ከሰደበኝ ውስጥ አንተ የውጭ ሰው ነህ ወደ መጣህበት ተመለስ ! እና ሌሎች ይገኙበታል።በመቀጠል እጄን፣ክንዴን እና በመቀጠል ጥርሶቼ ላይ መላልሶ መታኝ'' ማለቱን ጠቅሳለች።

ስምዖን የእዚህ ዓይነት ጥቃት በአደባባይ ሰው እየተመለከተ በማያውቀው ሰው ከተፈፀመበት በኃላ ደም እየፈሰሰው እና አንድ ጥርሱን እንዲያጣ ተደርጎ እራሱን ለመከላከል ያደረገው ጥረትም ሳይሳካ ከወረደበት የከተማ አውቶብስ ማረፍያ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ተገዷል።ድርጊቱ የዘረኝነት ጥቃት ለመሆኑ ስምዖንም፣የኤንአርኮ ዘጋቢም ሆነ ጉዳዩን መመርመር የጀመረው የኖርዌይ  ፖሊስ ሁሉም በጋራ ያመኑበት ጉዳይ ነው።

ወንጀሉ የኖርዌይ ፖሊስ የመዘገበበት ክፍል (የወንጀሉ ''ካታጎሪ'') ''በቆዳ ቀለም እና ማንነት ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግር እና ጥቃት'' በሚል ርዕስ ስር መሆኑን በእዚሁ በኤንአርኮ ዘገባ በተገለጠው መሰረት ለማወቅ ተችሏል።የኖርዌይ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት የወንጀል ምርመራ ክፍል ''አክቲንግ'' ኃላፊ አስትሪድ ቡርገ፣ የኖርዌይ ፖሊስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኖርዌይ የእዚህ ዓይነቱ የዘረኝነት ጥቃቶች ላይ ትኩረት እንደሰጠ እና በማኅበረሰቡም ውስጥ የበለጠ ትኩረት እያገኘ እንደመጣ ለኤንአርኮ እንደገለጡለት ዜናው በተጨማሪ ያብራራል።

የኖርዌይ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት የወንጀል ምርመራ ክፍል ''አክቲንግ'' ኃላፊ አስትሪድ ቡርገ (ፎቶ ሸትል ግሩድ)

ለማጠቃለል የእዚህ ዘገባ ጸሐፊም ስምዖንን እንደሚያውቀው፣ ወጣቱ ፈፅሞ ከማንም ጋር ግጭት የመፍጠር ስብዕና ያለው ወጣት አይደለም።ወጣቱ በክርስትና ሃይማኖት የታነፀ እና እጅግ የሰከነ ስብዕና ያለው ወጣት ነው።በመሆኑም በስምዖን ላይ የእዚህ ዓይነት ጥቃት ፈፅሞ ሊፈፀምበት የሚገባ አይደለም።በስምዖን ላይ ብቻ አይደለም፣ድርጊቱ በማንም ላይ ሊፈፀም የማይገባ ድርጊት ነው።በመሆኑም ፖሊስ ተገቢ ምርመራ አድርጎ በወጣቱ ላይ የዘረኛ ጥቃት የፈፀመው ወንጀለኛ እና ተባባሪዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲያደረግ የሁሉም ፅኑ ፍላጎት ነው።


በጠ/ሚ/ዐቢይና ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ላይ በውሸት ወሬ የዘመቱት ''አፈ-ጊንጦች'' በቴዲ አፍሮ ዘፈን ሊሸሸጉ ሲሞክሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየሳቀባቸው ነው።

ጠ/ሚ/ዐቢይ አሕመድ እና ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ክብረት በታላቁ የዓባይ ግድብ ምርቃት ቀን። ======== ጉዳያችን ምጥን ======== አፈ ጊንጥነቱ እና የውርደት ካባው ''አፈ ጊንጥነት'' የሚለውን ...