Sunday, November 13, 2016

Tension between TPLF led, Ethiopia and Egypt is increasing; A couple of Egyptian citizens residing in Addis Ababa are arrested.

Taha Mansour 

According to sources from Addis Ababa a number of Egyptians were arrested by Tigray Peoples Libration Front (TPLF) led-government security personnel.  Ethiopian Weekly news paper, Capital on Nov.7,2016  issue, confirmed as a number of Egyptians are under Ethiopian security forces since October 31. 

The well known hotel, Addis Ababa Radisson Blue Hotel Executive Assistant Manager Taha Mansour was one of the arrested Egyptian citizen on Monday, October 31,2016.Taha has been working at the Radisson Blu since November 2012. That is after he moved from Radisson Blu Resort El Quseir, in Egypt. On the same day another Egyptian from his office was captured.The organisation name and individual´s name is not yet disclosed. 

State television of Ethiopia made a number of documentary films accusing Egypt for assistance Ethiopian opposition forces. While Egyptian officials repeatedly denied for Ethiopian Government accuses. It is known that Ethiopia is under state of emergency to crash protesters against TPLF brutal government.According to articles of state of emergency declared 6 weeks back, main highways from the capital take to southern, northern, western and eastern part of the country are under the title of ´´red line´´ meaning no one is allowed to approach them with out the information of the command post. 
  

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Monday, November 7, 2016

የኢትዮጵያ የወቅቱ የተቃውሞው የፖለቲካ ሜዳ ተስፋ አስቆራጭ አይደለም።ይልቁንም በብዙ ተስፋ የተሞላ ነው። (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)


  • የሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች እና ስብስቦች ፍላጎት ምንድነው? ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ አንድ ነው። 
  • የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ተስፋ ሰጪ እና ወደፊት ሲሄድ እንጂ ወደ ኃላ እየሄደ አለመሆኑን መገንዘብ ይገባል።
  • በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥም በሁሉም ወገን የሚታዩ ፅንፈኞች ይኖራሉ።
ኢትዮጵያን አንዳንዶች በአንዳንድ መድረኮች ላይ በተነገሩ ንግግሮች ወይንም የተንሸዋረረ የግለሰቦች የፖለቲካ እና ታሪካዊ ትንተና አንፃር እየተመለከቱ ተስፋ አስቆራጭ ደረጃ እንደደረሰች የሚገምቱ አሉ።ይህ ግን የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው።ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት የፖለቲካ ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ አይደለም። ተስፋ አስቆራጭ አድርጎ የሚያቀርበው ስልጣኑን የሙጭኝ ብሎ ሕዝብ እየገደለ እና እያሰረ የሚገኘው ሕወሓት ነው።ይህ ማለት ግን ከሁሉም ወገን ስልጡን አካሄድ መሄድ አይጠበቀም ማለት አይደለም።

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ሶስት  ቀናት ውስጥ በባህር ማዶ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ክንውኖችን በአጭሩ በማሳታወስ የወቅቱን የፖለቲካ ሁኔታ የተራራቀ የመሰለን ግን በአንድ መስመር የሚሄዱበት በርካታ እድሎች መኖራቸውን በቀላሉ ማሳየት ይቻላል።እያንዳንዱ ክስተቶች የእራሳቸው ተቃራኒ ሃሳቦች ተነስተውባቸዋል።

የመጀመርያው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ የተሰኘው በአርበኞች ግንቦት 7፣የአፋር ፓርቲ፣ሲዳማ ንቅናቄ እና ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የተመሰረተው ንቅናቄ ነው።ንቅናቄው እንደመግለጫው በርካታ ስራዎች የሚቀሩት መሆኑን ቢገልጥም በኢትዮጵያዊነት ስር መንቀሳቀስ ወሳኝ መሆኑን ገልጧል።የእዚህን ንቅናቄ የሚተቹት በአማራውም ሆነ ኦሮሞ ብሔርተኝነት ስም የሚገኙ ናቸው።የአማራው ብሔርተኝነት በተለይ እራሱ በአግባቡ አለመወከሉን ይገልፅና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ውስጥ የተወከሉት ግለሰቦች በ1980ዎቹ ውስጥ በአርሲ እና ሐረር ጨምሮ ለተፈፀሙት ግድያዎች ተሳትፎ አላቸው ይላሉ። በአንፃሩ በኦሮሞ ማሕበረሰብ በኩል የእነ አቶ ሌንጮ እና ዶ/ር ዲማ ከአንድነት ኃይል ጋር ንቅናቄ አባል መሆናቸው እንደ ስህተት ይቆትሩባቸዋል።እዚህ ላይ ኦነግ የሚለውን እንቅስቃሴ የጀመሩት ውስጥ እኔ ዶ/ር ዲማ መሆናቸውን ሁሉ ዘንግተው ከማን ጋር መሆን እንዳለባቸው ሊመክሯቸው ይሞክራሉ።ይህ ሁሉ ወቀሳ ግን የተለያዩ አስተሳሰብ ጥጎች ናቸው እንጂ ክፉ ክስተቶች አይደሉም። ዋናው ኢትዮጵያዊ አጀንዳ እስካልተጣለ ድረስ ሊስተካከል የሚችል ቀላል የሂደት ጥያቄ ነው።

ሁለተኛው የእዚህ ሳምንት መጨረሻ ክስተት የኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ከዶ/ር ፀጋዬ አራርሳ እና ኢታና ጋር በተደረገ ውይይት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር በቅርብ የተመሰረተች መሆኗን ከአንድ ሰዓት በላይ በረዘመ ቃለ መጠይቅ ላይ ሲነገር ተሰምቷል።ሌላው ቀርቶ የሚለበሰው ´´የሀገር ልብስ ሳይቀር የዐማራ ባህል ተፅኖ ነው´´ የሚል አገላለጥ ተሰምቷል።በተለይ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በቅርብ የመጣ ነው የሚለው አነጋገር የሚያጣቅሰው ማስረጃ ሳይኖር በደፈናው አቢሲንያ ትባል ነበር ሲባል ተሰምቷል።ሌላው ቢቀር የኢትዮጵያ ነገስታት ከጥንት ጀምሮ የተፃፃፉት ደብዳቤ፣በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት የተፃፈው ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ሁሉ ገደል የከተተ ስንኩል አቀራርብ ነበር።

ሶስተኛው ክስተት በትናንትናው ማለትም በጥቅምት 27፣2009 ዓም በሲያትል የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አዳራሽ የተጠራው እና ምሁራን፣የታሪክ ሰዎች፣የሃይማኖት አባቶች እና አክትቪስቶች የተገኙበት የዐማራ ማኅበረሰብ የጋራ ግብረ ኃይል የተጠራ ስብሰባ ነበር። 

በስብስባው ላይ የምጣኔ ሐብቱ ባለሙያ ዶ/ር አክሎግ እና ድምፃዊ ሻምበል በላይነህን ጨምሮ በርካቶች ታድመውበታል።በስብሰባው መጨረሻ ላይ የጋራ ምክር ቤት በመመስረት ተፈፅሟል።
ከእዚህ በተጨማሪ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በአማካሪነት እንዲሰሩ ጥቆማ ቀርቧል።ጉባኤው ከሞላ ጎደል የዐማራው ማኅበረሰብ በሕወሓት ስርዓት ውስጥ ዘርን ያማከለ ጥቃት መድረሱ፣ጥቃቱ ከሌሎች ፅንፈኛ አካላትም መሰንዘሩ፣ ኢትዮጵያን እና እምነቷን ለማጥፋት የዐማራው ማኅበረሰብ ኢላማ መሆኑ እና እነኝህን ችግሮች ለመፍታት የዐማራው መደራጀት አስፈላጊ መሆኑ ተደጋግሞ ተወስቷል።

ከላይ የተመለከትናቸው ክንውኖች በሙሉ እንቅስቃሴን፣መፍትሄ ፍለጋን እና አለመተኛትን የሚያሳዩ እንጂ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተስፋ አስቆራጭ መሆኑን አያሳይም።አሁን በስልጣን ላይ ላለው ስርዓት ግን በእየዘርፉ እና በአይነት የጠመዱበት የመሳርያ አይነቶችን ያሳያል።ከብሄር ስብስብ እስከ ኢትዮጵያዊነት መገለጫነት በእየመልኩ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚስማሙበት አንዱ እና ዋናው ነጥብ የሕወሓት መንግስት ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ እንዳለበት ነው። በሌላ በኩል ከላይ የሚታዩት የፖለቲካ አቀማመጦች መልክ ለመስጠት ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ስብስቦች በሙሉ እውነትኛ ችግሮችን እየነቀሱ እና በእርሱ ላይ ብቻ እያተኮሩ መፍትሄ መስጠት እና ወደ አንድ መድረክ መምጣት እንዳለባቸው አመላካች ጊዜም ነው ወቅቱ።ከሁሉም ግን በተለይ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የሚሰጡ ሃሳቦች ከስድብ እና አጉራ ዘለል ንግግሮች እንዲጠሩ እና በጨዋነት ላይ የተመሰረቱ ቃላትን መጠቀም የግድ ይላል።ማንም የፈለገውን አይነት ሃሳብ ይኑረው ማክበር እና ሃሳብን በጥሩ ቃላት መግለፅ መልመድ ተገቢ ነው።

ከእዚህ በተረፈ ግን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ተስፋ ሰጪ እና ወደፊት ሲሄድ እንጂ ወደ ኃላ እየሄደ አለመሆኑን መገንዘብ ይገባል።ምናልባት ኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነች ብለው የሚናገሩት ወደ ኃላ እየነዱን እንደሆነ እናስብ ይሆናል። እውነታው ግን በተቃራኒው ነው።ምክንያቱም የእዚህ አይነቱ አባባል በእራሱ  ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያነቃ እና ፅንፍ የያዙት ኢትዮጵያን የሚያጥላሉበት ደረጃ የት ያህል እንደሆነ ያነቃል፣ያዘጋጃል።

በመጨረሻም የሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች እና ስብስቦች ፍላጎት ምንድነው? ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ አንድ ነው። እርሱም በመጪዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ዋስትና ማግኘት የሚል ነው። የኦሮሞ ማኅበረሰብም ሆነ የዐማራ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሌላው ሁሉ በነገዋ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ በዳይ ሌላው ተበዳይ እንዳይሆን ዋስትና ይፈልጋሉ።ይህንን ዋስትና እንዴት አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል? ዋናው እና ቁልፉ የፖለቲካ ኃይሎች ሊመልሱት የሚገባ ቁልፍ ጥያቄ ነው።ይህንን ማስተማመኛ ዋስትና ቢኖርም የማይቀረው ግን የፅንፈኞች ጫፍ የያዘ ሃሳብ እስከመቼውም የማይቀር የፖለቲካ እንክርዳድ ነው።እንክርዳድ እንዳይኖር ማድረግ አይቻልም ዋናውን ስንዴ ሳይጎዱ መንቀል ግን ይቻላል።ለመንቀል ግን ትግስት እና ጥበብ ይፈልጋል።በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥም በሁሉም ወገን የሚታዩ ፅንፈኞች ይኖራሉ።ሆኖም ግን ሃሳባቸውን እንደ ሃሳብ እየሰሙ እና ተገቢ ከስድብ የራቀ ምላሽ መስጠት ከእዚህ ባለፈ ግን በኃይል ሃሳባቸውን ለመጫን ሲሞክሩ እንደ እየአመጣጣቸው በሕዝብ ምላሽ እንዲሰጥ ህዝብን ማንቃት ተገቢ ነው።ኢትዮጵያ አሁን የተጫናትን የሕወሓት አገዛዝ ማስወገድ ከቻለች መጪው ብሩህ ተስፋ እንደሆነ ቅንጣት ታህል መጠራጠር አይገባም።
==============================================
አንዳንዴ የጋራ ዕሴቶቻችን ላይ አለማተኮር ለምሳሌ ኪነ ጥበብ ልዩነታችን የበዛ ያስመስለዋል።ኦሮሞው ቢናገር፣ ዐማራው ቢደራጅ፣ሱማሌው ቢቃወም፣ ደቡብ ቢወቅስ  መርሳት የሌለብን ሁሉም ያገር ልጅ መሆኑን ለትውልዱ ደጋግሞ መንገር ተገቢ ነው።የጋራ የሆኑ ዕሴቶችን እያነሳን መኮርኮር የኅብረታችን መገለጫ ነው።ለሕዝብ ተስፋን ማሳየት ለዲሞክራሲ መብቱ የሚያደርገውን ትግል ሁሉ ያጠነክረዋል።

ድምፃዊት ፍሬ ሕይወት ስለሺ
  ´´ዘመድ ያገሬ ልጅ´´
ያገሬ ልጅ  (ሰሜን ያለው፣ደቡብ ያለው፣ ሱማሌ ያለው፣ወለጋ ያለው) 
አብሮ አደጌ እንዴት ነህ ቃናዬ .....


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Saturday, November 5, 2016

የሕግ ምሁሩ የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የቦርድ አባል ፕሮፌሰር ዓለም አንተ ገብረ ስላሴ አማራ፣ኦሮሞ እያሉ ከመደራጀት በመልክዓምድር መደራጀት ለኢትዮጵያ እንዴት እንደሚበጅ በምክንያት ያስረዳሉ።ያዳምጧቸው።

ማሳሰቢያ
======= 
ከጉዳያችን ውጭ የሚመጡ ነገር ግን በጉዳያችን በኩል የሚተላለፉ መልዕክቶች፣ዜናዎች እና ሃሳቦች  የጉዳያችንን ሃሳብ የግድ ያንፀባርቃሉ ማለት አይደለም።ሆኖም ግን የሚነሱ ሃሳቦች ለሕዝብ መድረስ እና ሕዝብ እንዲወያይበት ማድረግ ተገቢ ነው ከሚል እሳቤ መሆኑ መታወቅ አለበት። ሃሳቦችን በቶሎ ወደ ፊት እያመጡ እየተቋጩ ካልመጡ እየተመላለሱ የሕዝብን ሃሳብ ይበትናሉ።ተወደዱም ተጠሉም ሃሳቦቹ ሕዝብ መሃል የምንገዋለሉ ሃሳቦች ናቸው።መልክ አስይዞ ቅርፅ መስጠት እና ወደ በጎው መንገድ መምራት የመገናኛ ብዙሃን እና የምሁራን ሚና መሆን ነበረበት።

ምንጭ= ሕብር ራድዮ 




ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Friday, November 4, 2016

የዐማራ ሕዝብ አንድነት ግብረ ኃይል እሁድ ጥቅምት 27፣2009 ዓም በሲያትል አሜሪካ ስብሰባ ጠርቷል ስብሰባው ለኢትዮጵያ የወቅቱ ፖለቲካ ምን ይዞ ይመጣል?


ጉዳያችን/ Gudayachn 
ጥቅምት 26፣2009 ዓም 
================
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ወዴት እየሄደ እንደሆነ ለማወቅ በሚቻልበት ደረጃ አይደለም።በሀገር ቤት በተለይ በዐማራ እና ኦሮሞው ክፍል ለመናገር የሚዘገንን ግድያ፣ስቃይ እና ሰቆቃ በሕወሓት ወታደሮች እየተፈፀመ ነው።ይህ የኢንተርኔት እና ስልክ መስመሮችን በመዝጋት የሚፈፀመው ግድያ እና እስር በተለይ በዐማራ በኩል ከሕዝቡ እየተሰጠ ያለው ምላሽ ወደ በረሃ ወርዶ ከመፋለም እስከ እጅ በእጅ ትንቅንቅ ድረስ ሕዝቡ እየተፋለመ ነው።በእዚሁ ሳምንት መጀመርያ ላይ የባህር ዳር ነዋሪ ወጣቶች በስርዓቱ ባለስልጣናት መኖርያ ሰፈር እና በማዘጋጃ ቤት ቢሮ ላይ የፈፀሙት የቦንብ ጥቃት አንዱ የትንቅንቁ መገለጫ ሆኖአል።በሰሜን ጎንደርም መጠነ ሰፊ ጦርነት እየተካሄደ ነው።የገበሬውን መሳርያ ለመንጠቅ የዘመተው የሕወሓት ሰራዊት በሄደበት የገበሬው የጥይት አረር እያረገፈው መሆኑን የሚገልጡ ዜናዎች እየወጡ ነው። 

ይህ በእንዲህ እያለ ነው በመጪው እሁድ ጥቅምት 27፣2009 ዓም  ´´የዐማራ ሕዝብ አንድነት ግብረ ኃይል´´በሲያትል አሜሪካ ስብሰባ ጠርቷል።ይህ ስብሰባ በተለይ በዐማራ ዙርያ የተሰባሰቡ ድርጅቶች፣ሲቪክ ማኅበራት፣አክትቪስቶች እና ምሁራንን ሁሉ የሚያሳትፍ እንደሚሆን ተገልጧል።በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ብቻ እንደሚያሸበርቅ የሚጠበቀው ይህ ስብሰባ በዐማራው ማኅበረሰብ ዙርያ የተሰባሰቡ ሁሉ በግልፅ እና በጋራ የሚገናኙበት የመጀመርያ መድረክ ይሆናል።

ስብሰባው የሚደረግበት ዋና ምክንያት እና አጀንዳዎች ምን ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።በተለያየ መልኩ የተደራጁ አደረጃጀቶች ግን አንድ አይነት የኅብረት መድረክ እንደሚፈጥሩ ይታሰባል።በስብሰባው ላይ የጎንደር ኅብረት፣ሞረሽ ወገኔ እና ቤተ ዐማራን እንደሚጨምር የተገለጠው ስብሰባ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

ባብዛኛው ወጣቶች የሚንቀሳቀሱበት የዐማራ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ሲቪክ ማኅበራት እና አክትቪስቶች በተለያዩ መድረኮች ሲገልጡ እንደሚሰማው የሁሉም መድረሻ ግብ ወያኔን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን በዐማራ ማኅበረሰብ ላይ ከእዚህ በፊት በዘር ጥላቻ ላይ ብቻ ተመስርተው ግድያ የፈፀሙ እና ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የሚጠሉትን ሁሉ እንደሚፋለሙ ያሳስባሉ።በመጪው የእሁድ ስብሰባ ላይም እነኝህ ስሜቶች እንደሚንፀባረቁ ይጠበቃል።በዐማራ ማኅበረሰብ መደራጀት አለበት? ወይንስ የለበትም? የሚለው ክርክር በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ይሰሙ የነበሩት ክርክሮች አሁን አሁን አይሰሙም።ከጥቂት ወራት በፊት በእዚህ ዙርያ የሚነሱት ክርክሮች የእየራሳቸውን ነጥቦች ሲያነሱ ይሰማ ነበር።



የዐማራ ማኅበረሰብ መደራጀት አለበት የሚሉት ወገኖች ሁለት ምክንያቶች ያነሳሉ እነርሱም የማኅበረሰቡ  ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በሕወሓት የደረሰበት ዘርን ያማከለ ጥቃት እና በሌሎች የስርዓቱ አጋሮች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያደረሱትን ጥቃት በአብነት ይጠቅሳሉ። ከእዚህ በተጨማሪም በመጪው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስልጣን ላይ ዐማራውን ያገለለ የስልጣን ሽግግር ፈፅሞ የማይታሰብ መሆኑን አሁንም አበክረው ይመክራሉ።

የጥቅምት 27ቱ የሲያትል፣አሜሪካው ስብሰባ ባንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከላይ የተነሱትን ነጥቦች ዙርያ የሚንፀባረቁበት መድረክ እንደሚሆን ይታሰባል።የማኅበረሰቡ ትግል እስከምን ድረስ ይሄዳል? በኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ላይስ የሚኖረው ተፅኖ ምን አይነት ይሆናል? የሚፈጠረው መድረክ እራሱን ወደ ፖለቲካ ኃይል  ይቀይራል? ወይንስ ስብስብ ሆኖ ይቀጥላል? እና ሌሎች ጥያቄዎች ይነሳሉ።ከእዚሁ ጋር በተያያዘ ግን የማኅበረሰቡን የፖለቲካ አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው። 

በሌላ በኩል ሳይነሳ የማይታለፈው ጉዳይ የማኅበረሰቡ ስብስቦች ላይ የሚነሱ አከራካሪ ጉዳዮች መኖራቸው ነው።ከእነዚህ ውስጥ ፍፁም ጫፍ የያዘ እና ማኅበረሰቡ ´´የእራሱ መንግስት ይኑረው´´ የሚለው ሃሳብ ድረስ ይሄዳል።የእዚህ አይነቶቹ ሃሳቦች እንደ መከራከርያ የሚያነሱት በአሁኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አክራሪ እና ፅንፍ ካልተያዘ ´´በተቃራኒ´´ በኩል ያለውን ፅንፍ መመከት አይቻልም የሚል እሳቤ ይንፀባርቃል።ሆኖም ግን ይህ አስተሳሰብ በብዙዎች ዘንድ የእራሱ የሆነ ተቃርኖ ገጥሞታል። 

በሌላ በኩል ደግሞ የእዚህ አይነቱ የሃሳብ ክርክር ክስተት የአንድ ተቋም ጤነኛ ባህሪ መሆኑን የሚገልፁ አሉ። መከራከር፣የሃሳብ ፍትግያ እና ግጭቶች አስፈላጊ እና ወደ አንድ  ነጥብ የሚመሩ ተፈጥሯዊ የአንድ ተቋም የመመስረት ወይንም የመለወጥ የምልክት ሂደቶች ናቸው። እነኝህ ሂደቶች በመጪው እሁድ አይነት የፊት ለፊት ስብሰባዎች መፍትሄ እንዲያገኙ ይረዳል። 

በመጨረሻም የሲያትሉ ስብሰባ በቸልታ እንዳይታይ ያሚያደርገው አንዱ እና አይነተኛ ምክንያት በሺህ የሚቆጠር የዐማራው ማኅበረሰብ ብረት አንስቶ ከሕወሓት አምባገነን ስርዓት ጋር እየተፋለመ መሆኑ ነው።ስብሰባው ግን ከወጣት እስከ አዛውንት እና የሃይማኖት መሪዎች ሁሉ የሚገኙበት እና ከማኅበረሰቡ ጉዳይ እስከ ኢትዮጵያዊነት ሃገራዊ ጉዳይ እንደሚወሱበት ይጠበቃል። 


ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Wednesday, November 2, 2016

ጥቅምት 23 የታሪካችን አካል (ቪድዮ)

ዛሬ ጥቅምት 23 ነው።እስካሁን አንድም ሐውልት ያልቆመላቸው ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ የነገሱት የዛሬ 86 ዓመት ጥቅምት 23/1923 ዓም በአሁኑ አራዳ (ፒያሳ) የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ነበር።ሃውልት ብቻ አይደለም በስማቸው የተሰየመውን ከዩንቨርሲቲ እስከ የካቲት 12 ሆስፒታል ስም እየደለዝን የእራሳችንን ታሪክ ለመፃፍ የሞከርን ጉደኞች አሁንም እኛው ነን።
ይህም የታሪካችን አካል ነው።

ንግስት መነን የመጀመርያ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት መስራች፣የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል እና በኢየሩሳሌም ያሉ ገዳማት ያደርጉት አስተዋፅኦ ሁሉ የሚጠቀስ ታሪክ ነበራቸው።ከሁሉም የኢትዮጵያ ሴቶችን ንግስት መነን እኩልነትን ለማጠናከር የለፉ ነበሩ።ስለ ዓለም የሴቶች እኩልነት እናወራለን እንጂ የእኛዎቹን ፈላስፋዎች ማድነቅ አልፈጠረብንም።አንድ ቀን ይህንን ሁሉ ምስቅልቅል የሚያስተካክል እና ወደ እራሳችን ሀብት የሚመለከት ትውልድ ይነሳል።እስከዛው ድረስ ግን ለማያውቀው  ጠብታ ተጠራቅሞ ጋን ይሞላል እና እንዲህ የጠብታ ያህል እንነግራለን።



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

በዐማራ ፖለቲካ ዙርያ የሚታየኝ እውነት እና ስጋት (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)




ጉዳያችን /Gudayachn 
ጥቅምት 23/2009 ዓም 
====================
አንድን ነገር ፈርተነው ዝም ካልን አላዋቂ እንዲመራን መንገድ መክፈት ነው።ይህንን ጉዳይ የማነሳው አዲስ የውይይት ርዕስ ለመክፈት አይደለም።በፌስ ቡክ ላይ አንድ ግለሰብ ስለፃፈ/ስለፃፈች ወይንም ሶስት እና አራት ሰዎች ሃሳባቸውን ስላሰፈሩ ሃሳቡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይንም እንወክለዋለን ያሉት ሕዝብ ሃሳብ ነው ለማለትም አይደለም። ሃሳቦች ግን ከመጀመርያው ካልተነሱ ጊዜ በወሰዱ ቁጥር እየጠጠሩ እና ንግግሮች ሁሉ ሕግ ሆነው ሳይታወቅ ይቀራሉ።

ፖለቲካ መነሻ እና ግብ ከሌለው መውጫው ጭንቅ ነው። ፖለቲካ አስፍቶ የማየት አዕምሮ ላይ ካላረፈ አንድ ሰው ላይ ወጥታ  አጠገቧ ያለውን አንድ ቅንጣት ፀጉር ትልቅ ዛፍ አድርጋ አይታ ደን ውስጥ ነኝ ብላ እንደምታስብ ቅማልም በጠበበ መረጃ ላይ መመስረትን  ያመጣል። ፖለቲካ ልምድ እና ሙያም ይፈልጋል።ፖለቲካ በፍፁም ፍቅር እና የሰውን ልጅ ሁሉ የመውደድ ፀጋ ሳይታደሉ የሚገቡበት አይደለም።የሰውን ልጅ ሁሉ ሳይወዱ የሚገቡበት ፖለቲካ በአለማችን ላይ እንደተመለከትነው መጨረሻ ላይ የእራስን ጎሳ ወደማምለክ ይቀየርና ግቡ ´´ፋሽዝም እና ናዚዝም´´ ይሆናል። ስለዚህ ጥንቃቄ ይፈልጋል።

እውነታው  
=======
የዐማራ  ማኅበረሰብ ለሕወሐት ´እንደጠላት ተቆጥሮ በግልፅ እና በስውር ላለፉት 25 ዓመታት በተለየ መልኩ ተጠቅቷል።በሕወሓት ማኔፌሥቶ ውስጥ እንደተገለፀው በገዢ መደብነት ተጠቅሶ ቁጥር አንድ ጠላት ተብሏል።ላለፉት 25 ዓመታትም በሺህ የሚቆጠሩ በዐማራነታቸው ብቻ እና ብቻ ተጠቅሶ ተገድለዋል፣ከቤታቸው ተባረዋል፣በርካታ ስውር ጥቃቶች ተፈፅመዋል።እነኝህን ትውልድ፣ታሪክ እና እግዚአብሔር በጊዜው የሚፈርዱት ይሆናል።ይህ ማለት በሌላው ብሔር ላይ አልደረሰም ማለት አይደለም።በተለይ በዐማራው ላይ የተደረገው ግን ማኅበረሰቡን የስልጣን ስጋት ነው በሚል ብቻ ሳይሆን ከሰይጣናዊ ፍፁም ጥላቻ የተፈፀመ መሆኑ ነው።በሌላው ላይ የተፈፀመው  አንድ፣የተፈጥሮ ሃብቱን ለመቆጣጠር አልያም ለመብቱ በተነሳበት ወቅት ስልጣንን ለመጠበቅ በሚል ሕወሓት የወሰዳቸው እርምጃዎች ናቸው። በዐማራው ላይ የተወሰደው ግን ከእዚህ በተለየ ስልታዊነት ላይ የተመሰረተ ከፖለቲካ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ዘርፎች ሁሉ የማስወገድ እና በመጨረሻም ወደ ማጥፋት የዞረ ተግባር ነው። ይህ በርካታ ማስረጃዎች ያሉት ያለፉት 25 ዓመታት እውነታ ነው።

ስጋት 
====
ከላይ የተጠቀሰው እውነታ በርካቶች ስለ ማኅበረሰቡ መብት፣ነፃነት (በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ነፃነት) እና እኩልነት ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።ይህ ክስተቱ ያመጣው ሂደት ነው።ይህ ማለት ግን ብሶት በእራሱ ፖለቲካ አይሆንም።ብሶት ቁጭት እና የንዴት ማብረጃ ብሎ ያገኘውን ዕቃ ሁሉ የመወርወር ክፉ አባዜ ያስከትላል። ስለሆነም በዐማራ ማኅበረሰብ ዙርያ የሚነሱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች መልሶ እራሱን ዐማራውን የሚያስከፋ እንዳይሆን ጥንቃቄ ይፈልጋል።የዐማራ ማኅበረሰብን ስነ ልቦና፣ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሞራል ልዕልናን ከግንዛቤ ያላስገባ ፖለቲካ መጨረሻ ላይ ፈረንጆቹ እንደሚሉት ወደ እራስ መተኮስ (fire back) ያስከትላል።ይህንን ለማለት ያስገደደኝ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ አንድ ሰሞን በርካታ ተከታይ ስላገኙ ብቻ እራሳቸው የፖለቲካ ፕሮግራም አውጪ ቀጥለው ወክለነዋል ስለሚሉት ሕዝብ የወደፊት እጣ ለመወሰን የሚዳዱ ደፋሮች ስመለከት ነው።

ስለ ዐማራ ማኅበረሰብ እውነቱን የሚናገሩ በደሉ ስልታዊ መሆኑን በማስረጃ የሚያቀርቡ እና ይህ ለነገዋ ኢትዮጵያ አደጋ መሆኑን የሚያሳስቡ ሁሉ ክብር ይገባቸዋል።ይህንን በደልም አንስተው ቆርጠው ለመታገል የወሰኑም እውነተኞች እና ስለ ፍቅር የሚያደርጉት እንደሆነ የታመነ ነው።ከእዚህ አልፈው ይህንን ስሜት እየኮረኮሩ ስለ ዐማራ ነፃ መንግስት ለመስበክ የሚፈልጉ ግን ´´ሰከን በሉ´´ ማለት ተገቢ ነው። ፖለቲካ የዕቃ ዕቃ ጫወታ አይደለም።ፖለቲካ ሰፊ ልቦና እና አሁንም ልድገመው  በደልን ውጦ ሌላውን በፍፁም ፍቅር መውደድ ይፈልጋል።

የዐማራ ማኅበረሰብ የእረጅም ጊዜ የፖለቲካ ተሞክሮ አለው።ኢትዮጵያን ብሎ የሚኖረው ስለተመቸው እና ስላልተመቸው አይደለም።የዛሬ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን መደህየት የነገ እንዳልሆነ ያምናል። ያጣነው መልካም መንግስት ነው።ይህንን ደግሞ በበደላችንን እያሰማን ወደ እኩል ኢትዮጵያ የሚወስደንን መንገድ እንከታለለን እንጂ በማኅበራዊ ሚድያ የሚመራን ሕዝብ አይደለንም።በእርግጠኝነት የእዚህ አይነቱ የዐማራ መንግስት የምትል አጀንዳ ማራገብ አንድ ወያኔ በውጭ ባለው ማኅበረሰብ ዘንድ ሌላ አጀንዳ ለመፍጠር ያሰባት ነች። አልያም አዲስ ነገር የፈጠሩ መስሏቸው ወይንም ጊዚያዊ የፖለቲካ አጀንዳ በማንሳት ጥሩ ስልት የፈጠሩ የመሰላቸው የሚያነሱት ነው።

ባጠቃላይ ግን ያኛውም ተባለ ይሄኛው ቁም ነገሩ የዐማራ ማኅበረሰብን ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሞራል ልዕልና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ያለውን ቁርኝት የዐማራ መንግስት በሚል የፌስ ቡክ አጀንዳ አትጉዱት።በእርግጥ ይህ ሃሳብ በእራሱ ለመውቀስ ገና ነው ሊባል ይችላል።የእኛ ችግር ይህ ነው።ነገሮችን ከወዲሁ በእንጭጩ ሃሳቡ ካልተቀጨ ነገ የሚናገር የለም።እያየን ማለፍ መቼም ባህላችን ሆኗል።ስለዚህ ነው በደሉን አብረን እንጩህ፣ለነገዋ ኢትዮጵያ አብረን እንስራ ነገር ግን አጀንዳውን ወደተለየ መንገድ የሚወስዱትን ´´ሰከን በሉ´´ እንበል የምንለው።



ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...