ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, August 5, 2021

የኢትዮጵያ እናቶች እና ድንግል ማርያም ምስጢረኞች ናቸው።በምስጢር ያወራሉ፣በምስጢር ስለ ኢትዮጵያ ይመክራሉ።



ሐመረ ኖህ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት 

- ባለፈው ሰሞን ብዙ ታውቃለች የምላት አንዲት እህት የኢትዮጵያ ሰራዊት በ21 መቀሌ ገብቶ በ21 ወጣ የሚል ፅፋ ልክ ድንግል ማርያም የህወሓትን ደም አፍሳሽ ወንጀለኛ ሰራዊት የምትደግፍ አድርጋ በውስጠ ወይራ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ስትፅፍ አይቼ፣አዬ! የራስን ክፋት ቅዱሳን እንዲያግዙ የመመኘት የዘመኑ ድፍረት! ብዬ ገርሞኝ ነው የሰነበተው።

የኢትዮጵያ እናቶች በምስጢር የሚያማክሯት እናት አለቻቸው።ጎረቤት ቢያስከፋቸው፣መንግስት ቢበድላቸው፣የቤቱ ጣጣ ከገበያው አልጣጣም  ብሏቸው ልጆቻቸው እንዳይራቡ ሲሰጉ፣ሀገር ላይ ረሃብ እና ጦርነት ሲመጣ ወደ የምስጢር እናታቸው ድንግል ማርያም ስዕል ጠጋ ብለው ያወሯታል። 

================
ኢትዮጵያ ተአምር የሆነች ሀገር ነች።ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በስካንድንቭያን ሀገሮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የኢትዮጵያን ጉዳይ ሲያነሱ '' ልጆቼ አይምሰላችሁ።እኔ በሕይወቴ ሁሉ የተረዳሁት ሃገሩን እንዲሁ የሚጠብቀው የእግዚአብሔር መንፈስ አለ።ይህ መንፈስ ማዕበል ሲመጣ እንዴት አድርጎ እንደሚያጠፋ፣ሃገሩን እንደነበረ መልሶ ስገጣጥም ነው የሚታየው። ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት ልዩ መንፈስ አላት'' ይላሉ።ከሰማንያ ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት አባት ይህንን የሚሉበትን ምክንያት ሲያስረዱ ዝም ብለው ሳይሆን ከልጅነታቸው በኢትዮጵያ ላይ የተመለከቱትን እያንዳንዱን ክስተት እያስታወሱ ነው።

 ከ1933 ዓም እስከ 1982 ዓም የኖሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በቀድሞ አጠራር የሸዋ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኢትዮጵያን ሲገልፁ '' የእግዚአብሔር የምስጢር ሀገር'' ብለው ነው።እግዚአብሔር በዓለም እንዲቀመጡ ያልተዋቸው፣ዓለም የተዋቸውን ውድ የአምላክነቱ መገለጫ የአምልኮ ስርዓቶች የምስጢር ኪሱ የሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ አስቅምጧል።ዓለም የሌለው ያሬዳዊ ዜማ፣ታቦተ ፅዮን፣ግማደ መስቀሉ እና ገና ጊዜያቸው ደርሶ ያልወጡ ምስጢራት ሁሉ በኢትዮጵያ አሉ።በአስር ዓመታት የጵጵስና አገልግሎታቸው ብዙ ፍሬ ያፈሩት አቡነ ጎርጎርዮስ ዕብራይስጥ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና አረብኛ ቋንቋዎችን የሚችሉ ሲሆን የወታደራዊው መንግስት ከመውደቁ አንድ ዓመት ቀደም ብለው ብፁዕነታቸው ሚያዚያ 23/1982 ዓ.ም፣ ሻሸመኔ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያስተማሩት ትምህርት ላይ የኢትዮጵያውያንን አንድነት ሲናገሩ ''ምንም ብትሉ ምንም ብትሉ ይሄ ሕዝብ አንድ ነው'' ብለዋል።በወቅቱ ኢትዮጵያ ገና በህወሓት የጎሳ ክልል ሳትከለል እና የጎሳ እሳት ሳይጣድባት ነበር ይህንን የተናገሩት።

ከላይ የአረጋዊውን እና አሁንም በሕይወት ያሉትን አቡነ ኤልያስን እና በአካለ ሥጋ የተለዩን አቡነ ጎርጎርዮስ (ቡራኬያቸው ይደርብንና) ከተናገሩት መነሻ ላድርግ እንጂ የዛሬ ማጠንጠኛ ሃሳቤ የኢትዮጵያ እናቶች እና ድንግል ማርያም በምስጢር ከድንግል ማርያም ጋር እንዴት እንደሚያወሩ ለማውሳት ነው። ነገ ነሐሴ 1/2013 ዓም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሰረት ከሰባቱ የአዋጅ አፅዋማት ውስጥ የሚመደበው የፍልሰታ ፆም ነው።ይህ ፆም በኢትዮጵያውያን የሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ከህፃን እስከ አዋቂ የምፆመው፣አብያተ ክርስቲያናት በምእመናን የሚሞሉበት፣ካሕናት ሌሊት በሰዓታት፣ቀን በቅዳሴ እና የአንደምታ ትርጉም የሚያገለግሉበት ነው።ወሩ ክረምት እንደመሆኑ ሕፃናቱም ሆኑ ወጣቶች የትምህርት ጊዜያቸው ስላልሆነ ወደ አብያተ ክርስቲያናት ለመሄድ አመቺ ጊዜ ነው።

የዘንድሮው የፍልሰታ ፆም ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ፈተና እንዲቀል የሚጸልዩበት ልዩ ዓመት ነው።''ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖልም ቢሆን እንወርዳለን'' እያለ የሚደነፋ ባላጋራ ተነስቶባታል።ልጆቿን በጎሳ ከፋፍለው እያናከሱ ''የበቀል እጃችሁን አንሱ''  የሚል ግልጥ መልዕክት ከህወሓት አመራሮች ተሰጥቶባታል።ጦርነት በሀገሪቱ ሰሜን እየተደረገ ነው።በእዚሁ ጦርነት በህወሓት የአማራ እና የአፋር ሕዝብ ላይ በተከፈተው ጦርነት ከ200 ሺህ በላይ ሕዝብ ተፈናቅሏል።በትግራይም ላለፉት 9 ወራት በመቶ ሺዎች ለረሃብ በአስር ሺዎች ለመፈናቀል በአስር ሺዎች ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል።በእዚህ ሁሉ መሃል ግን የእናቶች ለቅሶ እና ጭንቀት አለ።

የኢትዮጵያ እናቶች በምስጢር የሚያማክሯት እናት አለቻቸው።ጎረቤት ቢያስከፋቸው፣መንግስት ቢበድላቸው፣የቤቱ ጣጣ ከገበያው አልጣጣም  ብሏቸው ልጆቻቸው እንዳይራቡ ሲሰጉ፣ሀገር ላይ ረሃብ እና ጦርነት ሲመጣ ወደ የምስጢር እናታቸው ድንግል ማርያም ስዕል ጠጋ ብለው ያወሯታል። ወደ ድንግል ማርያም ስዕል (ስዕለ አድህኖ) ሲጠጉ ልጇን ክርስቶስን አብረው ያገኙታል።እናትና ልጁን የሚነግሯቸው በእምነት ነው።እንደ ዘመኑ ጥቅስ ተቃሽ፣ቁጥር እና ምዕራፍ ሳይሆን በሕይወታቸው ከአምላክ እናት ጋር በምስጢር በማውራት ምን እንደሚገኝ በሕይወታቸው ሁሉ ያውቁታል።ብዙ መከራ በቤታቸው እየጨረፈ ሲጠጋ እንዴት በምስጢር ከድንግል ማርያም ጋር አውርተው እንዳለፈ የሚጠቅሱት አፍ የሚያስይዙ ታሪኮች አሏቸው።ብዙውን አይናገሩትም።እንደነሱ ምስጢሩን ለሚያውቁ እናቶች ካገኙ አብረው ያወጉታል።በሀገር የመጣ ፈተና እንዴት በጸሎት እንደሚያልፍ፣ኢትዮጵያን የነካ እንዴት በፀሎታቸው የውሃ ላይ ኩበት እንደሚያደርጉት ያውቃሉ።ብዙ አያወሩም።ፈተና ሲመጣ አይርበተበቱም።ብቻ መጣሁ ብለው ወደ የመኝታ  ክፍላቸው ወይንም ወደ አቅራቢያቸው ወዳለው ቤተክርስቲያን ሄደው ''የጭንቅ አማላጇ፣የአምላክ እናት'' ብለው ከልጅሽ ከወዳጅሽ አማልጅን ብለው በለቅሶ ይጠሯታል።በወንጌሉም በሰርግ ቤት ወይኑ ሲያልቅ መላ በይን ብለው ወደ ድንግል ማርያም ቀርበው የምልጃ ፍሬ ካዩት በላይ እነርሱ ብዙ የሚተርኩት እውነተኛ ታሪኮች አሏቸው።

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ እናቶች ማዶ ከትግራይ ወዲህ ከቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ሆነው ''ቅድስት ሆይ ልምኝልን'' እያሉ የሚማፀኑበት ጊዜ ነው። ድንግል ማርያም የማንንም ፖለቲካ አታይም።ኢትዮጵያን ለመበተን እስከ ሲኦል እወርዳለሁ ብሎ በድፍረት በተናገረው ግን ትደሰታለች ማለት አይደለም።ባለፈው ሰሞን ብዙ ታውቃለች የምላት የኢትዮጵያ ሰራዊት በ21 መቀሌ ገብቶ በ21 ወጣ የሚል ፅፋ ልክ ድንግል ማርያም የህወሓትን ደም አፍሳሽ ወንጀለኛ ሰራዊት የምትደግፍ አድርጋ በውስጠ ወይራ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ስትፅፍ አይቼ፣አዬ! የራስን ክፋት ቅዱሳን እንዲያግዙ የመመኘት የዘመኑ ድፍረት! ብዬ ገርሞኝ ነው የሰነበተው።የምድር የዘር አንቡላችንን እኛው ጋር እንደቀረፋ ይቀመጥ እንጂ በኃጢአት ለላሸቀ ከሰይጣን ለከፋ ክፋታችን ቅዱሳንን እንዲያግዙን  የማድረግ ድፍረታችንን ይቅር ይበለን።የኢትዮጵያ እናቶች እንዲህ አይደሉም።እነርሱ ክፉ ላደረገ ክፉ አታድርግ የሚል ብሂላቸው ሁሌም መመርያቸው ነው።ይህ ማለት ግን የግፍ ፅዋ የሚቀበሉበት የውሃ ልክ የለም ማለት አይደለም።እንደ ጣይቱ በሀገራቸው እና በሕዝብ ላይ የመጣን ከፊት የሚመሩበት ጊዜ አለ።የግፍ ፅዋው ሞልቶ ሲተርፍ።

ከእዚህ ሁሉ በፊት ግን ወደ ምስጢረኛዋ ድንግል ማርያም ቀርበው ስለሀገር፣ስለልጆቻቸው እና ስለ መንደራቸው ሁሉ እያለቀሱ ከልጅሽ አማልጅን ብለው መፀለያቸው ይቀድማል። ፀሎታቸው ደግሞ መሬት ወድቆ አያውቅም።ኢትዮጵያን እዚህ ያደረሳት የእናቶቻችን ፀሎትም ነው።ጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ  የኢትዮጵያ እናቶች ፀሎት ነው የሚጠብቀኝ ሲሉ ዝም ብለው አይደለም።በክርስትናም ሆነ በእስልምና ያሉ እናቶች እንዴት እንደየየሚያመልኩት አምላክ እንደሚፀልዩ ስለሚያውቁ ነው።ዘንድሮም በፆመ ፍልሰታ በትግራይ ያለች እናትም በጎንደር እና ጎጃም፣ገሞጎፋ እና ከፋ፣ሐረር እና ጅጅጋም ያለች እናት ስለ ኢትዮጵያ ስለልጆቿ እና ስለ ሁሉም ወደ የምስጢር ወዳጇ ድንግል ማርያም ጠጋ ብላ በሃዘን ፀሎቷን ታደርሳለች። በእዚህ የትግራይ እናት ከጅጅጋው፣የግምበላዋ እና ከደብረብርሃን፣የአምቦዋ ከጎንደር በፀሎት በእንባ ትገናኛለች።የእናቶቻችን ፀሎት ጎርፍ ነው።ኢትዮጵያን የሚጠላ ''ኢትዮጵያን ለመበተን እስከ ሲኦል እደርሳለሁ'' እያለ የደነፋውን ጎርፍ አድርጎ ይወስዳል።ድንግል ማርያምም የኢትዮጵያ ነገር አይሆንላትም እና ለምልጃ ከልጇ ፊት ትቆማለች።ስትቆም ደግሞ ፍርድ ከዙፋኑ ይወጣል። በእዚህ እናምናለን።

የኢትዮጵያ እናቶች እና ድንግል ማርያም ምስጢረኞች ናቸው።በምስጢር ያወራሉ፣ስለ ኢትዮጵያ ይመክራሉ።
ከፆሙ በረከት ይክፈለን! የኢትዮጵያን ጠላቶች ከእግሮቿ በታች ይጣልላት!
========================///===========

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...