ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, June 28, 2021

ምዕራፍ አንድ አበቃ!




ጉዳያችን ገፅም ሆነ የፌስቡክ ገፄ ምዕራፍ አንድ ጨርሰዋል።ላለፉት 9 ዓመታት የጉዳያችን ገፅም ሆነ ፌስቡኬ በምዕራፍ አንድ ስር ነበሩ።በእነኝህ ዓመታት ባብዛኛው የሀገር ጉዳይ እና  የሀገር ፖለቲካ አይመለከተኝም የሚለውን  በማንቃት፣በመጎትጎት ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች እንዲሁም  መጉላት የሚገባቸው ዜናዎች ላይ እያተኮሩ መዘገብ ላይ ነበር የጉዳያችን ገፅም ሆነ የፌስቡክ ገፄ ያተኮረው።በእነኝህ ዓመታት ውስጥ ብዙ የማይባልለት ማኅበራዊው፣ንግድ እና ምጣኔ ሀብት አልፎ አልፎ ቢነሱም ብዙ  የሃገራዊ ፖለቲካ ጉዳይ ያህል አልተነሱም።

ስለዚህ ፌስቡኬም ሆነ ጉዳያችን ምዕራፍ አንድ ከመጨረሳቸው ጋር ብዙ የሚያጣድፍ የእየቀን ሥራዎች እና መረጃዎች መለጠፍ ላይኖርባቸው እንደሚችል እያሰላሰልኩ ነው። እንደ ምዕራፍ አንድ በሀገር ውስጥ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ በጣም ተጭኖ መፃፍ ላያስፈልገኝ ይችላል ነገር ግን  ምዕራፍ ሁለት ላይ ንግድ፣ምጣኔ ሀብት እና ማኅበራዊ ላይ ማትኮር እንደሚገባኝ እያሰላሰልኩ ነው። ምዕራፍ አንድን እዚህ ላይ የመግታት አስፈላጊነት ምክንያቶቼ አራት ናቸው  -

1) አሁን ኢትዮጵያ በሚድያ አፈና ውስጥ አይደለችም በርካታ የግል ቴሌቭዥኖች እና ዩቱበሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በነፃነት እየተናገሩ በመሆኑ የመረጃ እጥረት አሁን የለም።በእርግጥ መጉላት ያለበትን የመምረጥ እና የ''ኮንቴንት'' ችግር እንዳለ አሁንም ይታወቀኛል።ሆኖም ግን የመረጃ ችግር አለመኖሩ መረጃዎችን እንደ ምዕራፍ አንድ ተከታትሎ መለጠፍ ላያጣድፍ ይችላል።

2) ኢትዮጵያ ምርጫ አካሂዳ ባብዛኛው አጠናቃለች።81 ነጥብ 5 % የእንደራሰዎች ምክር ቤት  ሰኔ 14/2012 ዓም መርጣለች።ቀሪው የሱማሌ እና ሐረር በመጪው ጳጉሜን 1 ስትመርጥ ደግሞ 93% ይሸፈናል።ቀሪው 38 ወንበሮች የሚይዘው የትግራይ ክልል ሲቀላቀል 100% ይሸፈናል።ይህ ምርጫ በዓይነቱም ሆነ በሂደቱ አንፃራዊ በሆነ መልኩ የተለየ እንደነበር የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስክርነቱን ሰጥቷል።ይህ ለጉዳያችን ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም የምዕራፍ አንድ ፍፃሜ ነው።ስለሆነም አሁን አዲስ የአክትቪዝም ሥራ በተለይ በሰላማዊ ትግል ዙርያ ብዙም አስፈላጊ አይደለም ብዬ አምናለሁ።

3) ሕዝብ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎችን መንግስት በቶሎ የመመለስ ባሕል በማሳየቱ እና ይህንኑም ያዳበረ መንግስት ከመስከረም በኃላ እንደሚመጣ በማመን እና
 
4) አስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ጥያቄዎች ላይ አሁን ያለው መንግስት እየሰራበት ስለሆነ የሚሉት ናቸው። 

በምዕራፍ አንድ ላይ በቻልኩት መረጃዎች ለሕዝብ እንዲደርሱ ያደረኩት ትንሽ ጥረት በአንድም በሌላም እንደተደመጠ፣ከከፍተኛ ኃላፊዎች እስከ ታች ያለው ሕዝብ የደረሰው ሰው ላይ የራሱ ተፅዕኖ እንደፈጠረ በብዙ መንገዶች አረጋግጫለሁ።ከህገር ቤት ኢርቄ ልሰራ የሚገባኝን ግዴታ በትንሽ ጠብታ ያህል እንደሞከርኩ በማሰብ  እና እንደ አንድ ማኅበራዊ ነፃ አገልግሎት በመውሰድ በጣም ተደስቼበታለሁ።

ምዕራፍ አንድ እዚህ ላይ ያበቃል።ስለሁሉም እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።   

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...