Thursday, February 6, 2014

እባክህ ክፈለኝ ያስተማርኩበትን (አጭር ግጥም የኢትዮጵያን ገበሬ ለተሳደቡት የኢህአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣን)



አንጀቴን አስሬ ፣
ከእኔ ይቅር ብዬ አንተን አስተምሬ፣

ዛሬ ያወቀ መስሎት…. ''ባዶ እግር'' ነህ አለኝ፣
  ትስቅብኝ ጀመር ጫማ ስለሌለኝ፣

ባለጫማ መሆን  መቼ ጠፋኝ እኔ፣
መልበስ መሽቀርቀሩ አንተን አደንቁሬ።

ላስተምርህ ብዬ እንጂ ነገ እንድትሻገር፣
መስሎኝ----እኔ መራቆቴ ላንተ ልሆን ማገር።

ግና ምን ያደርጋል አንተም አልተማርክም፣
    ማስተዋል ነስቶሃል ከእኔ አልተሻልክም።

እናም ---እኔ ባዶ ሆኘ ያለበስኩበትን፣
            እባክህ  ክፈለኝ ያስተማርኩበትን።

ጉዳያችን
ጥር 30/2006
ምሽት ኦስሎ፣ኖርዌይ

No comments:

የክፍለዘመናችን የኢትዮጵያ የስልጣኔ ማማ መለኪያ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ጉባዔ ነገ በአዲስ አበባ ይከፈታል። ህልውናችን፣መጪው ስልጣኔያችን፣ሰላማችን እና ዕድገታችን በእዚህ ጉባዔ ውጤትና ሒደት ይወሰናል።

Foto : Fana digital  የቻልን በሀሳብ እና በጸሎት፣ ያልገባን እና የተምታታብን ደግሞ እኪገባን በዝምታ በመቆየት ኢትዮጵያን እናግዛት። ========= ጉዳያችን ልዩ ========= ኢትዮጵያ ሐምሌ 8፣2018 ዓም...