Saturday, June 30, 2018

ሰበር ዜና በጋምቤላ ክልል ሜጢ ከተማ እና ዙርያዋ በአማራ ተወላጆች ላይ እልቂት ሊፈፀም ነው መንግስት እንዲደርስ እየተጣሩ ነው (ጉዳያችን ልዩ ዜና Gudayachn Exclusive News)



ጋምቤላ ክልል
ጉዳያችን ልዩ ዜና (Gudayachn Exclusive Breaking News) 
ሰኔ 23፣2010 ዓም (ጁን 30፣2018 ዓም)

  • አሁን ያንዣበበው የሞት አደጋ እንዲቀረፍ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ለሚጠይቀው ሕዝብ መንግስት በሰዓታት ውስጥ እንዲደርስለት ተማፅኖ እየቀረበ ነው።
  • በአካባቢው ያሉ በኢንቨስተርነት የቡና እርሻዎችን የተቆጣጠሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች በአማራ እና መዥንገር መሃል ጠብ በመዝራት ነዋሪዎች እየከሰሷቸው ነው።
  • ለልዩ ልዩ ሥራ የሄዱ የትግራይ ተወላጆች በኢንቬስተር ስም ወደ ስፍራው የመጡ የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች ከተግባራቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።
  • የቀድሞ ታጋዮች ከአማራ ተወላጆች ተደብቀው የመዥንገር ተወላጆችን ጠርተው ያደረጉት ምስጢራዊ ስብሰባ ተደርሶበታል።

ሰላማዊው ክልል እንዴት ታመሰ?

የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከሃያ ሰባት አመታት በፊት ሰላማዊ ብቻ ሳይሆን ደርግ በ1977 ዓም በሀገራችን በተከሰተው ድርቅ ሳብያ ከወሎ እና ትግራይ ሰፋሪዎች በማምጣት ያሰፍርበት የነበረ ቦታ ነው።ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ግን አካባቢው በጎሳ ፖለቲካ ሆን ተብሎ እንዲታመስ በህወሓት እና ኢህአዴግ ተፈርዶበታል።ጉዳዩ መልኩን ቀይሮ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ግጭት መነሻ እንዲሆን ያደረገው አንዱ እና አይነተኛ ምክንያት የቡና አምራች አካባቢዎችን ለመቆጣጠር የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች መሬት በመውሰድ እና በመንጠቅ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የኖሩ የአማራ ተወላጆችን ለዘመናት አብረው ከኖሩት ከመጀንገር እና ሸኮ ብሔር ጋር ግጭት እንዲፈጠር ሆን ተብለው መሰራታቸው ይታወሳል።በእዚህም ሳብያ እስከ አለፈው ዓመት ድረስ ሶስት ያህል አሰቃቂ ግጭቶች ተፈጥረዋል።በሁሉም ግጭቶች ላይ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ የህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በባህላዊ መልክ የታረቀውን ማኅበረሰብ ሁሉ መልሰው ወደግጭት እንደመሩት ከቦታው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ለጉዳያችን ከታማኝ ምንጭ የደረሳት ዛሬ ያኮበኮበው የሞት አደጋ

ሰሞኑን  በእሊባቦር፣ሜጢ ከተማ በኢንቨስተርነት ስም የመጡ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች (ባብዛኛው ነዋሪውን የአማራ የቡና እርሻ ከመዠንገር ጋር እያጋጩ የነጠቁት ናቸው) ሚስጥራዊ ስብሰባ ከመዥንገር ጋር መደረጉ የተሰማው ስብሰባው እንዳለቀ ነበር።ቀደም ብሎ እነኝሁ ኢንቨስተር ተብዬ የቀድሞ ታጋዮች በቦቴ ነዳጅ ጫኝ መኪና ውስጥ እየደበቁ  ክላሽ እንዲታጠቅ ያደረጉት የመዥንገር ተወላጅ ስብሰባው ላይ የተነገረው ''አማራ ሊወረው እንደሆነ፣በያዘው መሳርያ እንዲፈጀው'' የሚል ማሳሰብያ እንደነበር ከስብሰባው የወጡ መረጃዎች ለአማራ ተወላጆች ይደርሳል።ይሄንኑ እኩይ ተግባር ከአማራው ጋር አብረው በጉርብትና እና ተባብረው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም በሃዘን ይሰማሉ።ጉዳይ የአማራ ተወላጆች ጋር እንደደረሰ በሁሉም በኩል የትጥቅ ዝግጅት ተደረገ።ልብ በሉ በእዚህ ሁሉ መሃል በግጭቱ የሚያተርፉ የመሰላቸው በኢንቨስተርነት የመጡ የቀድሞ ታጋይ የህወሓት አባላት ናቸው።

ከእዚህ በፊት በቦታው ላይ በርካታ የአማራ የቡና እርሻ ባለይዞታዎችን ምንም  በማያውቁት ጉዳይ ግንቦት 7 ወዘተ እያሉ እስከ ቂልንጦ ድረስ ያሳሰሯቸው ግለሰቦች የቡና እርሻቸውን ተነጥቀው ባዶ እጃቸውን እንደቀሩ ዜናው ያብራራል።ሰሞኑን ይህ ውጥረት ከመፈጠሩ በፊት የተከሰተው ጉዳይ ቢኖር እነኝህ በግፍ የታሰሩ የአማራ እና በግጭት አሉበት ተብለው የታሰሩ የመዥንገር ብሔር ተወላጆች በዶ/ር አብይ የምህረት አዋጅ ብዙዎች እየተፈቱ ግፍ ወደ ተሰራባቸው አካባቢዎች መመለሳቸው ነበር።የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ይህንን ግጭት ያቀናበሩትም ከሰሩት ግፍ ስጋት እና የለውጥ ሂደቱን እንዲያደናቅፉ ከተሰጣቸው መመርያ አንፃር እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ወደ ስብሰባው ጉዳይ እንመለስ እና በእዚህ ሳምንት የተደረገው ምስጢራዊ ስብሰባ በኢንቨስተር ስም ባሉት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች እና በመዥንገር መሃል የተደረገው ሚስጥር ከወጣ በኃላ እና በቦቴ እየተደበቀ ለመዥንገር መሳርያ ከታደለ በኃላ ዛሬ ቅዳሜ ጦርነቱ ሊከፈት ቀጠሮ ተይዞ እያለ የመከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ኃይል ቀድሞ ሜጢ ከተማ ገቡ።ዛሬ የነበረው የቅዳሜ ገበያም ሳይደረግ ህዝቡ እንደጠፋጠጠ እንደሚገኝ እና ሌሊትም ውጥረቱ እንዳለ ለጉዳያችን ከታማኝ ምንጭ የደረሰው ልዩ ዜና ያብራራል።

መፍትሄው

ከላይ በጥቂቱ ለመግለጥ እንደተሞከረው የአካባቢው ግጭት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መልክ ከመያዝ አልፎ በሰሞኑ በሀገራችን ያለው የለውጥ ማዕበል ያላስደሰታቸው ወገኖች ደም እንደ ጎርፍ የሚፈስበት አንዱ የጥፋት ግንባር ለማድረግ አሰፍስፈዋል።ስለሆነም መግስት የሚከተሉትን ተግባራት በአፋጣኝ መውሰድ አለበት። እነርሱም : -
1ኛ) የደረሰው የመከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ኃይል ቶሎ ለቆ እንዳይሄድ እና ለረጅም ጊዜ በከተማዋ እና በአካባቢው እንዲቆይ እንዲደረግ፣
2ኛ) በአካባቢው ግጭት የሚፈጥሩት በኢንቨስተር ስም የመጡ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች እና በስልጣን ላይ ያሉ የአካባቢው ባለስልጣናት  ውስጥ በግጭቱ ላይ እጃቸው ያለበት በቶሎ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እና
3ኛ) በአማራ፣በመዥንገር እና ሸኮ ሽማግሌዎች መሃል የሚያጋጩትን ባልጨመረ መልኩ ልዩ ውይይት እንዲደረግ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ጥቅምን ባማከለ መልክ እንዲፈቱ ሆኖ በባህላዊ እርቅ እንዲፈፀም ላለፈውም የካሳ ክፍያ እንዲፈፀም ማድረግ ይገባል።
ለማጠቃለል ግን አሁን ያንዣበበው የሞት አደጋ እንዲቀረፍ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ለሚጠይቀው ሕዝብ መንግስት በሰዓታት ውስጥ እንዲደርስለት ተማፅኖ እየቀረበ ነው።



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

ኑ! ክፉውን ዘመን ኢትዮጵያ ጥላ ውስጥ ሆኖ ያሳለፈውን ክቡሩ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስን እናክብር! (ቪድዮዎች)

ጉዳያችን/ Gudayachn
ሰኔ 23/2010 ዓም (ጁን 30/2018 ዓም)
ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ 

ኢትዮጵያውያን እባካችሁ ፀሐዬ ዮሐንስን አግኑንልን።ፀሐዬ ኢትዮጵያን እንዳለ የኖረ የኢትዮጵያ ልጅ።
ክብር ዘመን ለማይቀይረው የኢትዮጵያ ልጅ ለድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ።
እናመሰግንሃለን! እንወድሃለን! ፀሐዬ ዮሐንስ።
ከእዚህ በታች የፀሐዬ ዮሐንስ ኢትዮጵያን ያገነነባቸው ቪድዮዎች ይመልከቱ።
ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ ሩቅ አይደለም ቅርብ ነው ደሞ አይቀርም መድረሱ 
ያ!ገናናው ያ!ገናናው ስሟ ዳግም መመለሱ 

ትኑርልን ከነክብሯ ኢትዮጵያ የእኛ ናት 

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Tuesday, June 26, 2018

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሁለት ወደ አንድ ሲኖዶስ እንድትመለስ በቀጣይ ቀናት ውስጥ ምእመናን ማድረግ እና አለማድረግ ያሉባቸው ጉዳዮች

ጉዳያችን/ Gudayachn
ሰኔ 20/2010 ዓም (ጁን 27/2018 ዓም)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ተከፍሎ፣በመንበራቸው የነበሩት ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ እና ሊቃነ ጳጳሳት ከሀገረ ስብከታቸው ተሰደው በውጭ ሀገር እየኖሩ እንደሆነ ይታወቃል።የቅዱስ ሲኖዶስ በሀገር ቤት እና በውጭ መኖር የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት ብቻ ሳይሆን የተፈታተነው፣የምእመናንን መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ግንኙነት በእጅጉ ጎድቶታል።ምዕመናን በተለያየ ፍረጃ ሳብያ እርስ በርስ ተቃቅረዋል።በተለይ ይህ ሁኔታ ፖለቲካዊ ቃና እየተሰጠው በርካቶች በሌሉበት ፖለቲካ እየተፈረጁ ከቤተሰባቸው ጭምር ስነ ልቦናዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገር ውስጥ እና ውጭ በሚል መከፈል የቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን ብቻ ሳይሆኑ አጠቃላይ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጤናማ ግንኙነትን አዛብቶ ቆይቷል።ለእዚህም አንዱ ማሳያ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከውጭ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያላትን ግንኙነት አዛብቶ ቆይቷል።ለምሳሌ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን እና በአውሮፓ እና አሜሪካ የሚገኙ የበርካታ ሀገሮች አብያተ ክርስቲያናት ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ከውጭ ወይንስ ከሀገር ውስጥ ሲኖዶስ ጋር መሆን አለበት? የሚለው ጥያቄ አንፃር ከፍተኛ ውዝግብ ሲፈጠር ቆይቷል። በእዚህም ሳብያ ጉዳዩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ግንኙነት አንፃር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በነበራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት አንፃርም የእራሱን የሆነ ጥላ እንዳጠላ የሚታወቅ ነው።ከእዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ በኃላ በቅርቡ ምናልባትም በሳምንታት ውስጥ በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለእርቅ እንደሚገናኙ መሰማቱ ይታወቃል።በእዚህ የእርቅ ሂደት ላይ የምእመናን ሚና ምን መሆን አለበት? የሚለው ጥያቄ መመለስ አስፈላጊ ነው።

ምእመናን ማድረግ የሌለባቸው 
  • በአባቶች እና በሊቃውንት ጉባኤ መታየት የሚገባቸው የሥርዓት (ቀኖና) ሂደቶች ላይ አባቶችን ተክቶ ሃሳብ በመስጠት ሌላ ንትርክ አለመፍጠር፣
  • የቅዱስ ሲኖዶስ በሁለት መከፈል ሂደት ላይ ዛሬ እያነሱ (ቢያንስ የእርቅ ሂደቱ እስኪያልቅ ድረስ) የታሪክ ንትርክ አለመፍጠር፣
  • በውጭም ሆነ በሀገር ቤት የሚገኙ አባቶችን የአንዳቸውንም እያነሱ የመደገፍ እና የማጥላላት ፅሁፎች አለመፃፍ እና 
  • ማናቸውም ልዩነቶችን የሚያሳዩ ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ንግግር፣ፅሁፍ እና አገላለጦችን ፈፅሞ ከመጠቀም መቆጠብ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ምእመናን ማድረግ የሚገባቸው  
  • አባቶች በምንም አይነት መልኩ የአሁኑን የእርቅ ዕድል እንዳያልፍ እንዲያደርጉ ደጋግሞ ማሳሰብ፣
  • የእርቅ ሂደቱ እንዲሳካ እና ምንም አይነት ከእርቅ ያለፈ ጉዳይ ምእመናን መስማት እንደማይፈልጉ አበክረው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለብፁዓን አባቶች በቃል፣በፅሁፍ እና ፔቲሽን በማዘጋጀት ጭምር ማሳሰብ እና 
  • ለእርቅ ሂደቱ የሚያስፈልገውን የሞራል እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት ምእመናን እንዲያግዙ የተከፈቱ የፌስ ቡክ ገፅ እና የፔትሽን ማስፈንጠርያዎች ለእርቁ በጎ እሳቤ ይዘው በተነሱ ምእመናን ተከፍተው ሥራ ላይ ውለዋል።ምእመናን ይህንኑ አውቀው የፌስ ቡክ ገፁን ''ላይክ'' በማለት እና ፔቲሺኑን በመፈረም እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን እያስተላለፉ ይገኛሉ።በእዚህም መሰረት  
የተከፈተው የፈስ ቡክ ገፅ ማስፈንጠርያ ለመክፈት የፌስ ቡክ ገፅ የሚለውን በመጫን መክፈት ሲችሉ፣ የፐቲሽኑ ማስፈንጠርያ ለመክፈት ደግሞ ፔትሽን የሚለውን በመጫን መክፈት ይቻላል።  

ባጠቃላይ ይህ ወቅት ወሳኝ ተግባራት የሚከወንበት እና የሁሉም ትኩረት በቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነትና የአባቶች እርቅ ጉዳይ ከሁሉም በቀደመ መልኩ የምእመናን ተሳትፎ በእርቁ ሂደት ላይ የሚኖራቸው ድጋፍ መጎልበት እና አባቶች ከእርቅ ውጭ ምንም አይነት አማራጭ አለመኖሩን ደግሞ ማሳሰብ ባጠቃላይ ከሁሉም የሚጠበቅ የጋራ ተግባር ነው።
አበው ፀልዩ (የይልማ ኃይሉ) መዝሙር 



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Tuesday, June 19, 2018

ግዙፍ የድጋፍ ሰልፍ ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 ዓም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይደረጋል።የሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ይከታተሉ።

  • ሰልፉ በዘጠና ቀናት ውስጥ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ላከናወኑት እና ለርዕያቸው ያለውን ድጋፍ ሕዝብ ይገልጣል፣
  • ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ይሞገሳል፣ ይህንን የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ የሚሞክሩ እንዳያስቡት ሕዝብ ማስጠንቀቅያ ይሰጣል፣
  • ኢትዮጵያዊነት፣ፍቅር እና መደመር ይሞገሳል።

ኮሚቴው ዛሬ ሰኔ 12/2010 ዓም የሰጠው መግለጫ 




ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Monday, June 18, 2018

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ በምክርቤት ቀርበው የተናገሩት (ቪድዮ)

=======================
ጉዳያችን/Gudayachn
ሰኔ 11/2010 ዓም (ጁን 19/2018 ዓም) ዛሬ  
===============
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ሰኔ 11/2010 ዓም ፓርላማ ቀርበው የተናገሩት እና ያቀረቡት ሪፖርት።
ከስር የሚገኙት ቪድዮዎች  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተናገሯቸው ርዕሶች በሶስት የተለያዩ ቪድዮዎች የተከፈሉ ናቸው። እነርሱም : -
  • ቪድዮ 1 ስለ ባድማ፣ስለ ኤርትራ የተናገሩት (20 ደቂቃ) 
  • ቪድዮ 2 ስለ ሙስና፣ የፍትህ ስርዓቱ እና የአፍሪካ ቀንድ ዙርያ ስለሰፈሩ የባዕዳን ጦር ጉዳይ (13 ደቂቃ)
  • ቪድዮ 3 የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ሪፖርት እና ሙሉ በምክር ቤቱ የተነሱ ጥያቄዎች የመለሱበት ሙሉ ቪድዮ  
==============================
ቪድዮ 1 ስለ ባድማ፣ስለ ኤርትራ የተናገሩት (20 ደቂቃ)

ቪድዮ 2 ስለ ሙስና፣ የፍትህ ስርዓቱ እና የአፍሪካ ቀንድ ዙርያ ስለሰፈሩ የባዕዳን ጦር ጉዳይ (13 ደቂቃ)

ቪድዮ 3 የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ሪፖርት እና ሙሉ በምክር ቤቱ የተነሱ ጥያቄዎች የመለሱበት ሙሉ ቪድዮ



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Friday, June 15, 2018

ላለፉት 27 ዓመታት የሄድንበት የክልል ወሰን አቀማመጥ ጉዳይ ያስገኘውን ጥቅምና ጉዳት የሚመረምር ከሁሉም ወገን የተውጣጣ ጠንካራ ኮሚሽን ለመመስረት መታቀዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አስታወቁ (ቪድዮ)

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ዛሬ ምሽት ሰኔ 8/2010 ዓም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ ውስጥ አንዱን ከአንዱ የሚለይ ድንበር ሳይሆን ለአስተዳደራዊ ሥራ ብቻ ሲባል የተቀመጠ የአስተዳደር አከላለል መኖሩን አስታውቀው ላለፉት 27 ዓመታት የሄድንበት የክልል ወሰን አቀማመጥ ጉዳይ ያስገኘውን ጥቅምና ጉዳት የሚመረምር ከሁሉም ወገን የተውጣጣ ጠንካራ ኮሚሽን ለምመስረት መታቀዱን አስታውቀዋል። ሙሉ መልዕክቱን ከስር ከሚገኘው ቪድዮ ይመልከቱ።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com