ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Tuesday, February 17, 2015
Monday, February 16, 2015
የትናንቱ የ''አይ ኤስ ኤስ'' በግብፅ ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ አንፃር ምን ያመላክተናል? ኢትዮጵያን ከ''አይ ኤስ ኤስ'' እና ''ግልገሎቹ'' ለማዳን መፍትሄው ምንድነው? (የጉዳያችን ልዩ ማስታወሻ)ISS terrorist movement from Horn of Africa current political condition point of view and possible solution.
'አይ ኤስ ኤስ' ባለፈው ዓመት ያወጣው አዲሱ ካርታ
ትናንት የካቲት 8/2007 ዓም እኩለ ሌሊት ላይ ''ሮይተርስ'' በሊብያ በ''አይ ኤስ ኤስ'' (ISS) የታገቱት ሃያ አንድ የግብፅ ክርስቲያኖች በአሰቃቂ መንገድ መገደላቸውን፣የአገዳደሉንም ቪድዮ በአሸባሪው ድርጅት መለቀቁን እና የግብፅ ኮፕት ቤተ ክርስቲያንም ድርጊቱ መፈፀሙን ማረጋገጧን ጠቅሶ የዘገበው ዜና ብዙዎቻችንን አሳዝኗል።ይሄው በ ''ሜጫዊ''(ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ በሰይፍ የመቅላት አባዜ) አስተሳሰብ አራማጅነቱ የሚታወቀው ቡድን እንደ 'አሜባ' እራሱን እየለጠጠ ከኢራቅ እስከ ሶርያ ከሶርያ እስከ ሊብያ እየተስፋፋ ነው።አለማችን ለአሸባሪ ተግባሮች አዲስ ባትሆንም በእንዲህ አይነት ሕብረ-ብሔራዊ ባህሪ ያለው እና የመካከለኛው ምሥራቅን እና የምስራቅ አፍሪካን ማኅበራዊ እና መልካ-ምድራዊ አቀማመጥ የደም ጎርፍ በማፍሰስ ለመቀየር መነሳቱን በአደባባይ በማወጁ ቡድኑን ከሌሎች አሸባሪዎች ይለየዋል።
ቡድኑ ኢትዮጵያን እና ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ባካለለ መልኩ የሰሜን አፍሪካን እና የአውሮፓ ከፊልን ጨምሮ አዲስ ካርታ ማውጣቱን እና የሚታገለውም ከእዚህ አንፃር እንደሆነ በተዳጋጋሚ ይገልፃል።ይህንን አላማውን ለማሳካት በሀገሮች ውስጥ ያሉት ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታዎች ለእንቅስቃሴው ግብአትነት እንደሚጠቀምበት የታወቀ ነው።
ከእዚህ በተጨማሪ መገንዘብ ያለብን ቡድኑ ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን መሰረት ያደረገ ነው።አንደኛው እና ቀዳሚው ክርስቲያን የተባለ ሰው የሆነ ፍጥረትን መግደል ሲሆን በእዚሁ መስመር የግዛት ስፋቱን ማስፋፋት ነው።እነኝህን ተግባራት የሚፈፅመው ደግሞ የቀደሙ ታሪኮችን በሙሉ በመደምሰስ የእራሱን የ''ሜጫዊ'' ወይንም በሰይፍ የመቅላት አባዜ መመርያው ያደርጋል።የእዚህ አይነቱ አስተሳሰብ በግልገል ተከታዮቹ በሀገራችን የፖለቲካ መድረኮች በተለይ በባህር ማዶዎቹ ግልገሎች ላይ መንፀባረቁን ልብ ይሏል።
ከፍተኛ ውድመት ያደረሱት ሁለቱ የውጭ እስላማዊ ፅንፈኛ እንቅስቃሴዎች
ከኢትዮጵያ አንፃር የእዚህ አይነቱ ፅንፈኛ እንቅስቃሴ በሁለት ታሪካዊ ወቅቶች ጎልቶ ወጥቷል።የመጀመርያው በ16ኛው ክ/ዘመን ቱርክ ወደ አፍሪካ የባህር ዳርቻዎች ይዞታዋን ባጠናከረችበት ወቅትሲሆን ሁለተኛው የአረቡ ዓለም የነዳጅ ዘይት ካገኘበት ከ 1960ዎቹ ወዲህ ነው።በሁለቱም ወቅቶች ኢትዮጵያ ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳቶች ደርሰዋል።እዚህ ላይ ሁለቱም የታሪክ ክስተቶች መነሻ ያደረጉት የውስጥ ፖለቲካዊ ጉዳያችንን በማጦዝ መሆኑን መዘንጋት አይገባም።
ከሁለቱ የታሪክ ክስተቶች ውስጥ የመጀመርያው የቱርክ መንግስት ወደ አፍሪካ የባህር ዳርቻዎች ያሉት ይዞታዎቹን ያጠናከረበት ወቅት ስንመለከት ቱርክ ቀደም ብላ የደቡብ ምስራቃዊ እና ምስራቃዊ አፍሪካን በንግድ እና ህዝቦችን በግድ ወደ እስልምና በመቀየር ተግባር ብትታወቅም በኢትዮጵያ ግን እጇን ያስገባችበት ሂደት ከውስጥ የተነሳውን ቅራኔ በቀጥታ በመደገፍ መሆኑን እንመለከታለን። ይሄውም ከሀገራችን ምስራቃዊ ግዛት የተነሳው በታሪክ ''የግራኝ መሐመድ እንቅስቃሴ'' ቱርክ በወታደራዊ፣በቁሳቁስ እና በሞራል ድጋፍ በማድረግ ግንባር ቀደም ነበረች።በወቅቱ ኢትዮጵያ በታሪክ ከደረሰባት የጥፋት መዓት በላይ በቀዳሚነት ክርስቲያኖች ደማቸው እንደ ጎርፍ የወረደበት፣አብያተ ክርስቲያናት እና ቅርሶች የተቃጠሉበት፣'ማኅበራዊ ጀሃድ' የተፈፀመበት የጥፋት ዘመን ሆኖ አልፏል።በተለይ ከግራኝ መሐመድ ወረራ በኃላ ኢትዮጵያ በሰሜን ምፅዋ ተከትሎ እስከ ቀድሞዋ አፋር እና ኢሳ (የዛሬዋ ጅቡቲ) ድረስ ያለው ከአንድ ሺህ ኪሎሜትሮች በላይ የሆነው ግዛቷ በተለያዩ ለቱርክ ባደሩ ሱልጣኖች እና በቱርኮች በቀጥታ መጠቃት የተባባሰበት ወቅት ነበር።
ሁለተኛው በኢትዮጵያ ላይ ጉዳት ያደረሰ የፅንፈኛ የእስልምና እንቅስቃሴ ከ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እጁን የከተተው ኃይል ነው።በተለይ ይህንን ወቅት አደገኛ የሚያደረገው በቀጣዩ አስር አመታት ውስጥ የአረቡ ዓለም በነዳጅ ሀብት የተንበሸበሸበት ወቅት ከመሆኑ አንፃር በሀገራት ላይ ተፅኖ የመፍጠር አቅሙ በእጅጉ በማደጉ ነበር።በእዚህ ወቅት ነበር የኤርትራ በፌድሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ በተባበሩት መንግሥታት መፅደቁ እና ያንን ተከትሎ በኤርትራ ሕዝብ እንደራሴዎች ከፍተኛ ጉትጎታ ፌድሬሽኑ መፍረሱ (''የኤርትራ ጉዳይ'' አምባሳደር ዘውዴ ረታ The Eritrean Affair (1941-1963) by Ambassador Zewde Retta) ኤርትራ ከጥንትም አብራ ከነበረችው ኢትዮጵያ ጋር መሃዷን ተከትሎ ''ጀብሃ'' በአረብ ሃገራቱ ከፍተኛ የገንዘብ፣የቁሳቁስ እና የሰው ኃይል ድጋፍ ተመሰረተ።በቀጣዮቹ ጊዜያት ''ሻብያ'' ጀብሃን ካባረረ በኃላም ሆነ ''ህወሓት'' እና ''ሻብያ'' በጥምር ከደርግ ጋር ባደረጉት ውግያ የመካከለኛው ምስራቅ አረብ ሃገራት እርዳታ አልተለያቸውም።እዚህ ላይ እርዳታዎቹ ዋና አላማቸው ኤርትራን አረባዊ ሀገር ማድረግ እና ኢትዮጵያን በሂደት በእዚሁ ተፅኖ ስር እንድትወድቅ ማድረግ ነው።
እዚህ ላይ የደርግ አምባገነን ስርዓት ለሕዝብ ተቃውሞ በቂ ምክንያት አልነበረም ለማለት ባልደፍርም ማጉላት የምፈልገው ጉዳይ ግን በማናቸውም የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የአረብ ሃገራቱ ዘሎ መግባት በተለይ ኢትዮጵያ የውስጥ ቅራኔዋን እንዳትፈታ የራሱን ጥላ አጥልቷል።እዚህ ላይ አቶ ኢሳያስ የኤርትራን ጥያቄ በመገንጠል ደረጃ ማስቀመጥ ከአረብ ሃገራት ለሚገኝ እርዳታ ቅድመ ሁኔታ እንደነበር ብዙዎች ይስማሙበታል።እዚህ ላይ የቀድሞ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ እና የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ ገብረ መድህን አርአያ በጦርነቱ ወቅት ከኢራቁ ሳዳም ሁሴን እና ከሊብያው ጋዳፊ አይሮፕላን ሙሉ መሳርያ እና ቁሳቁስ ይሰጣቸው እንደነበር ኢሳት ቴሌቭዥን ቀርበው መናገራቸውን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።
ሆኖም ግን ያለፉት ሃያ አመታት ያሳዩን ጉዳይ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተለያይተው መኖር የማይችሉ ይልቁንም ጉዳዩን የቅኝ ግዛት ግንኙነት ነበራቸው የሚለው ተረታ ተረት ዘመን በሄደ ቁጥር ሐሰትነቱ ፍንትው ብሎ እየታየ መሆኑን ነው።ለእዚህም ይመስላል አቶ ኢሳያስ ሰሞኑ በኢሳት ቴሌቭዥን ''የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጉዳይን እንዴት ይመለከቱታል?'' ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጉዳዩን ''ወደ አንዳንድ የታሪክ መፋለሶች'' (historical distortion) ደረጃ ለማውረድ የተገደዱት።ለእዚህም ምክንያቶቹ አንድም ካለፈው ታሪክ ከመማር አልያም አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ህብረት እና አንድነት ብቻ የሚያድነው መሆኑን ከመረዳት ይሆናል።
ከ''አይ ኤስ ኤስ'' እና ግልገሎቹ ኢትዮጵያን ለማዳን መፍትሄው ምንድነው?
አሁን ያለው ወቅት ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ከመረብ ማዶ ያሉ የኤርትራ ምድር ህዝቦች አዲስ የፖለቲካ ራዕይ መመልከት ያለባቸው ወሳኝ ወቅት ነው።በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጎሳ ፖለቲካ ለዓለም አቀፍ ፅንፈኛ እንቅስቃሴ ምቹ የሆነ እና ኢትዮጵያን እንደሀገር ለማስቀጠል ፈፅሞ ፍላጎት እንደሌለው በተለያዩ ድርጊቶቹ ያረጋገጠ ነው።
የህወሓት የፖለቲካ መመርያ፣ጎሳዊ የምጣኔ ሀብት አደረጃጀቱ እና በታሪክ ላይ ያለው የተፋለሰ አስተያየት ሁሉ አሁን በሕይወት ካለነው ዜጎች ብቻ ሳይሆን ከመጪው እና ካለፉት ጋር ሁሉ የተቃረነ ነው።ይህ ሁኔታ ደግሞ ተወደደም ተጠላ ኢትዮጵያን ወደ አንድ አይነት ውስጣዊ ቅራኔ መምራቱ ሳይታለም የተፈታ ነው።ሆኖም ግን ቅራኔው በሕዝብ እና እራሱን በተደጋጋሚ ጊዜ እንዲያርም ዕድል የተሰጠው ህወሓት መካከል መሆኑን መዘንጋት አይገባም።ኢትዮጵያን ለማዳን እና እንደ ''አይ ኤስ ኤስ'' እና ግልገሎቹ ለመታደግ አይነት አደጋ ለመታደግ የህዝብ አንድነት፣ኢትዮጵያዊ መንግስት እና ራዕይ ያለው መሪ የፖለቲካ መዋቅር እጅግ ያስፈልጋል።አሁንም ይህንን በህወሓት ስር ባለች ኢትዮጵያ ውስጥ ፈፅሞ አይታሰብም።ለእዚህ ነው ''ኢትዮጵያ በፍጥነት ዲሞክራስያዊት ሀገር መሆኗ ለእራሷ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ብሎም ለመላው አፍሪካ ወሳኝ ነው'' ሲል ለአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ግብዓት የተዘጋጀ ጥናታዊ ፊልም አበክሮ ያሳሰበው።
ባጭሩ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ከመረብ ማዶ ያሉ ኢትዮጵያውያንም በዓለም አቀፉ የፅንፈኛ እንቅስቃሴ ታልቅ አደጋ ላይ ናቸው።ይህንን አደጋ ለመከላከል የቤት ስራው የሚጀምረው ከውስጥ ነው።መጀመርያ ውስጣችን ያለው የጎሰኛ ስርዓት ከእነ አሰራሩ ሙሉ በሙሉ መነቀስ አለበት።ቀጥሎ ኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ፖለቲካዊ፣ማጣኔ ሃብታዊ እና ማህበራዊ ቦታዋ በአግባቡ የሚያስጠብቅላት መንግስት ያስፈልጋታል።ይህንንም ከመረብ ማዶ ያሉትም በአግባቡ ሊገነዘቡት እና ላለፉት 40 ዓመታት በአንዳንድ አረብ ሃገራት የታለሉትባቸውን መንገዶች በሙሉ በውል ሊያጠኑት ይገባል።በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች እና አቶ ኢሳያስ መካከል ያለው መናበብም አስፈላጊ ያምያደርገው ከእዚህ ሁሉ አንፃር ነው።ጉዳዩ ከስልታዊ ግንኙነት በዘለለ ታሪካዊ እውነታን ያገናዘበ መሆን እንደሚገባውም የሚሰመርበት ለእዚህ ነው።የምዕራቡ ዓለም በቀዳሚነት የፅንፈኛ እንቅስቃሴ አደጋ የመሆን ዕድል ኢትዮጵያ እንዳላት ይገነዘባል።ለእዚህም ህወሓት ከሕዝቡ ጋር የተጣላ መንግስት ከመሆኑ አንፃር ኢትዮጵያን አይደለም እራሱንም መከላከል የማይችልበት ወቅት እሩቅ አይደለም።ስለዚህ የአንድነት ኃይሎች መጠናከር ብቸኛ መንገድ መሆኑ ከፍተኛ ግንዛቤ ተወስዶበታል።በመሆኑም የአይ ኤስ ኤስን አደጋ ስንመለከት መጀመርያ የቤታችንን ጉዳይ በፍጥነት ማስተካከል እንዳለብን ግንዛቤ እንዳይጎለን።ጉዳዩ ሁሉ ከጊዜ ጋር ነውና።
ጉዳያችን GUDAYACHN
የካቲት 9/2005 ዓም (February 16/2015)
Friday, February 13, 2015
ኢትዮጵያ በ40 ሚልዮን ብር ለ''ህወሓት'' በዓል ትከሰክሳለች ዩጋንዳ ለዝነኛው ዩንቨርስቲዋ ''ማካራሬ ዩንቨርስቲ'' በ50 ሚልዮን ዶላር በአፍሪካ ልዩ የሆነ ዘመናዊ መፃህፍት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ትጥላለች።
በዩጋንዳ ማካረሬ ዩንቨርሲቲ አዲስ የሚገነባው መፃህፍት ቤት
አንዲት ሀገር ዛሬ እድገት ላይ ነች የሚባለው በእያንዳንዱ ሰው ላይ ከሚሰራው የልማት ሥራ በተጨማሪ በትክክለኛ የእድገት ፖሊሲ ላይ መሆኗ ከሁሉ በላይ አንገብጋቢው ጥያቄ ነው።ቀጣይነት ያለው ልማት ሲነሳ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ጀምሮ ትክክለኛ ሁለንተናዊ የዕድገት መስመር መከተል ይህ መስመርም በሕዝቡ ዘንድ በቂ ግንዛቤ እና ተስፋ የፈነጠቀ መሆን ይገባዋል።ከእዚህ ውጭ እንደ ኢህአዲግ/ህወሓት እኔ አውቅልሃለሁ የጎሳ ፖለቲካ ግን ውጤቱ ውድቀትን ማስከተል ብቻ ሆኗል።ስርዓቱ በተለይ ልማትን በተመለከተ ተግባር ሁሉ የታይታ፣ምርጫን ታሳቢ ያደረገ እና ጎሳዊ አድሏዊነት ስለሚንፀባረቅበት ውጤታማ አለመሆን ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ አደገኛ መስመሮችን ለነገዋ ኢትዮጵያ እየዘረጋ መሄዱ ነው ክፋቱ።
ይህ ብቻ አይደለም በትምህርት ዕድል በኢትዮጵያ ስም የነፃ ትምህርት ዕድል ያገገኙ ''የሜጫ'' አስተሳሰብ አራማጆች እነርሱ በነፃ የትምህርት ዕድል ሲያገኙ ሀገር ቤት ላለው ወገናችን (ቆመንለታል ለሚሉት ጎሳ) ግን ''የጡት ሃውልት'' በ20 ሚልዮን ብር መገንባቱን እንደ ትልቅ ስኬት ሲነግሩን የነበሩቱ የባህር ማዶ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆችን እኩይ አስተሳሰብ ሳይጠቅሱ ማለፍ ተገቢ አይደለም።
ዕውቀት ላይ የተመሰረተ የልማት መስመር የሚከተሉ ሀገሮች ሁል ጊዜ ቅድምያ የሚሰጡት ለትምህርት ነው።ትምህርት ላይ በጥራት እና በብዛት መዋለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ ሃገራት ለምሳሌ ህንድ፣ሲንጋፖር እና ቻይናን ብንመለከት የልማት ደረጃቸው በአንድ ትውልድ ብቻ ተመንጥቆ ሲሄድ እናየዋለን።
ኢትዮጵያ በትምህርት መስክ ከፍተኛ የጥራት ማሽቆልቆል ያሳየች፣በዋና ከተማዋ አንፃር 'ምንም የለም' ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ ህዝቧ መፃህፍት ቤት መጠቀም ያልቻለበት፣የትምህርት ፖሊሲው በጎሳ ፖለቲካ እንዲጠረነፍ የተደረገባት ሀገር ነች።ለእዚህም ነው አንድ መፃህፍት ቤት ከመክፈት ይልቅ 20 ሚልዮን ብር አውጥቶ ከመቶ ዓመት በፊት ላልተደረገ በሬ ወለደ ታሪክ ሃውልት እንዲሰራ የሚወስኑ ባለስልጣናት ያሉባት ሀገር የሆነችው።ለእዚህም ነው አዲስ አበባ ከ 4 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ይዛ የማንበብያ መፃህፍት ቤት የሌላት ከተማ ሆና የቀረችው።ለእዚህም ነው ወጣቶቿ በእየሽሻ ቤት እና ጫት ቤት እንዲውሉ እንጂ የሚያነቡት መፅሐፍ እንዲኖራቸው የማይደረጉት።ለእዚህም ነው ጋዜጠኞች፣ደራስያን እና ሳይንቲስቶቿን ከሀገር እየተባረሩ የህወሓትን በዓል ለማክበር 40 ሚልዮን የሚሆን የሀገር ሀብት እንዲጠፋ የሚደረገው።
ዩጋንዳ ከምትኮራበት እና የሀገሪቱ ''አይከን'' ተብሎ የሚጠቀሰው ተቋሟ ውስጥ ''ማካረሬ ዩንቨርሲቲ'' አንዱ እና ተጠቃሽ ነው።ዩንቨርስቲው ''የአፍሪካ ኦክስፎርድ'' የሚል ስያሜ ይሰጠው እንደነበር እና ዛሬም ትምህርት በጥራት ከሚሰጥባቸው አፍሪካዊ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።ሰሞኑን ዩንቨርስቲው አዲስ ፕሮጀክት ይዞ ብቅ ብሏል።በ50 ሚልዮን ዶላር አዲስ መፃህፍት ቤት መገንባት።በመሰረት መጣሉ ላይ ቀደም ብለው ከዩንቨርስቲው የተመረቁት እና የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ምዋይ ኪባኪ ስም ይሰየማል።ዩንቨርስቲው ለአፍሪካዊ ምሁር ዋጋ ሰጥቶ መሰየሙ የሚያስመሰግነው ነው።ከእዚህ በታች የዩንቨርስቲው ቻንስለር ፕሮፌሰር ሞንዶ ካጎንየራ ጉዳዩን አስመልክተው የተናገሩትን ቪድዮ ይመልከቱ።
አዎን! ኢትዮጵያ በአምባገነን ይልቁንም በጎሳ ላይ በተመሰረተ ስርዓት እየማቀቀች ነው።ሰሞኑን እንደተዘገበው ከፍተኛ የሀገሪቱ የፖሊሲ ቀራጮች የትምህርት ደረጃቸው ካልታወቀ እና አንዳንዱም በገንዘብ ኃይል ባገኙት ዲግሪ ሀገሪቱን እየመሩ መሆናቸው ተሰምቷል።እርግጥ ነው ትምህርትን በእዚህ አይነት የሚያውቅ ባለስልጣን መፃህፍት ቤቶችን እንዲወድ አይጠበቅበትም።ለእርሱ እድገት 40 ሚልዮን ብር እያወጡ የህወሓት በዓል ማክበር ይሆናል።ዩጋንዳውያን ግን ለሀገር የሚያስቡ ባለስልጣናት እውቀት ላይ የተመሰረቱ ባለሙያዎች አሏት እና በ50 ሚልዮን ዶላር መፃህፍት ቤት ይገነባሉ።የኢትዮጵያን ትንሣኤ ያሳየን።
Video from NTV Uganda youtube
News Source - NTV Uganda
Makerere to construct $50M Mwai Kibaki library
The building is estimated to cost 50 million US dollars. Of this amount, $40 million is projected for the presidential Library and the remaining 10 million is for the establishment of a Mwai Kibaki endowed chair in Economics.
Makerere University will construct a 30-storey presidential library, named after Kenya’s former president Mwai Kibaki.The building is estimated to cost 50 million US dollars. Of this amount, $40 million is projected for the presidential Library and the remaining 10 million is for the establishment of a Mwai Kibaki endowed chair in Economics.
The library and endowment are named after Mwai Kibaki in commeration the fact that he was the first student of Makerere University to get a first class degree in economics.The announcement was made by the Chancellor of Makerere, Mondo Kagonyera. Kibaki is expected to launch this project on Friday at Makerere University.
The library and endowment are named after Mwai Kibaki in commeration the fact that he was the first student of Makerere University to get a first class degree in economics.The announcement was made by the Chancellor of Makerere, Mondo Kagonyera. Kibaki is expected to launch this project on Friday at Makerere University.
የካቲት 6/2007 ዓም (ፌብሯሪ 13/2015)
Tuesday, February 10, 2015
Zone 9 Bloggers case, Presented to the United Nations Working Group on Arbitrary Detention
Six Zone 9 bloggers collective members and three other independent journalists are in detention since last April 2014. Accusation of Ethiopian government which suspected them in working with human rights organisations was changed to terrorism after 23 days of interrogation. After three months on interrogation detention , all of them including one more blogger in absentia were charged of terrorism at the end of July 2014. The case is still on its Pre- trial stage which was more focused on the format and the substance of the charges. With in the last nine months they were taken to court nineteen times and their constitutionally given rights has been continuously violated since their arrest.
EHRP (Ethiopian Human Rights Project) and Freedom Now ( DC based Human Rights advocacy organisation) takes the case to the united nation working group on arbitrary detention. This petition against the Ethiopian Government was presented to the working group on January 26th , 2015. The petition shows the rights violations they have faced during detention and legal analysis why their arrest was arbitrary.
Source - Ethiopian Human Rights Project
http://ehrp.org
Below is the link of the full petition.
http://ehrp.org/wp-content/uploads/2015/02/UNWGAD-Petition-Zone-9-Ethiopia-1.26.15_4-updated.pdf
ጉዳያችን GUDAYACHN
February 10/2015
Wednesday, February 4, 2015
Thursday, January 29, 2015
BREAKING NEWS - PEACEFUL POLITICAL ENVIRONMENT IN ETHIOPIA IS ABOUT TO END! (ጉዳያችን GUDAYACHN)
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
January 29, 2015
===============================================
The press conference held at Addis Ababa Hilton Hotel by Pro-TPLF (Tigray People Libration Front) Electoral board chairman Prof.Merga, states as it has suspended two prominent strong opposition parties in Ethiopia.These are ''Unity party'' (Unity) and ''All Ethiopian Unity party'' (AUP). The press conference also emphasis as acknowledgement which was given by the electoral board to Unity and AUP to operate legally with in the nation was taken by force and ''granted'' to the regime's 'Poppets' parties'.These two TPLF-duplicated parties will get green light to operate with an identical name of the suspended ones.
It is quite clear that the two TPLF-poppets parties, introduced by Electoral board, do not have even formal office, council and even members are not yet disclosed. Many believe TPLF is creating its own 'loyal party' in the name of the prominent one.It was another surprise, when the electoral board chair person confirms the major pre-condition to continue as opposition party is ''to be loyal'' to his Pro-TPLF board.
''Ethiopian Unity party'' (Unity) and ''All Ethiopian Unity party'' (AUP) were legally operating in all part of the nation with in strong controversy with TPLF cadres. Both parties were expecting to participant with the coming May 'stress-full' election.It is recalled that they were also active participant in 2005 controversial election that TPLF was beaten seriously by the peoples voice. The year 2005 is still non forgettable year by many Ethiopians that over 200 citizens were killed by the regime's fully armed soldiers and security men under the command post of the late Meles Zenawi. Independent bodies raised the number of massacres to over 250 innocent people.
The ''Blue party'' (ሰማያዊ ፓርቲ), the youngest but challenging the regime party may also host the same act from TPLF. Last month the party chairman and many of council members were beaten and send to prison during their peace-full demonstration in the capital demanding ''transparent election process'' on the coming May,2015.
At the result of such Un-lawful act of the regime, there is high tension in all part of the country. The two prominent parties response following to the decision is not yet known. ESAT, Ethiopian Satellite Television based on Washington DC announces on its social media page it will have detail report in this evening's broadcasting service.
There is strong believe as peaceful political environment in Ethiopia is about to end.It is about weeks that armed opposition parties Ginbot 7 Freedom and Justice movement and Ethiopian Patriotic Front (EPF) based on vast Eritrean deserts are united and created one front called ''Arbegnoch-Ginbot7 for Unity and Democracy Movement” (አርበኞች-ግንቦት7 የአንድነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ)
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
January 29/2015
(Tir 21/2007 EC)
Subscribe to:
Posts (Atom)
-
በቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ፣ ስዊድን (ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አርኪኦሎጂ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና በሉንድ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት...
-
አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን =============== ጉዳያችን /Gudayachn =============== ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵ...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...



