Tuesday, December 31, 2013

ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ'' ኒዎርክ ታይምስ '' ጋዜጣ (ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው


ጉዳያችን ጡመራ ታህሳስ 22/2006 ዓም
ዳግማዊ አፄ ምንሊክ ፎቶ 

ኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ  መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።

አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ ከማድረግ አልፈው እስከ ኬንያ፣ሱዳን እና ሱማልያ ግዛት ድረስ ዘልቀው ገብተው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ነፃ ያወጣሉ የሚል ስጋት የነበረባቸው  እና በወቅቱ በእነኚሁ የጎረቤት ሃገራት  ላይ የጥቅም ፍላጎት የነበራቸው የአውሮፓ ሃገራት በብርቱ ተፈታትነዋቸው ነበር።በመሆኑም አዲስ የድንበር ውል ከኢትዮጵያ ጋር የመፈራረም ፍላጎት ከእንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ኢጣልያ በኩል ጥያቄ መነጻቱን የወቅቱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።

ዛሬ ዛሬ በምንሊክ ላይ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ቀድሞ አፄ ምንሊክ የቅኝ ግዛት ጥማታቸውን በገቱባቸው እና ቂም በያዙ ፀሐፊዎች የተፃፉ ናቸው ብለው ከሚነግሩን አስገራሚ ''የታሪክ'' ፅሁፎች ውስጥ ''በምኒሊክ ዘመን እስከ አስር ሚልዮን ኦሮሞዎች አለቁ'' የሚል ፅሁፍ በአንዳንድ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ተለቀው ሲነበቡ መመልከት  አስገራሚ የሰሞኑ ክስተት ነው።በፖለቲካው አለም በቂ ርዕዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የጠፋባቸው አንዳንድ ወገኖች ''ትርፋማ'' ብለው ያሰቡት የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን መካከል መዝራት እና ከመቶ አመት በፊት  የሆነውን የታሪክ ክስተት የአሁኑን ትውልድ በመውቀስ ትኩረት ለማግኘት ሲታትሩ መመልከት የዘመኑ አስቂኝ ተውኔት ነው።ዳግማዊ ምንሊክ ገና ብዙ የሚጠና ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ወታደራዊ ክህሎት ባለቤት ለመሆናቸው በወቅቱ ከወጡት የዓለማችን ድንቅ ጋዜጦች አንዱ የ ኒውዮርክ ታይምስን እትም መመልከት ይበቃል።

ከእዚህ በታች በሚገኘው የኒውዮርክ ታይምስ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛትን 7,000,000 (ሰባት ሚልዮን) መሆኑን ያስቀምጣል። እዚህ ላይ አንዳንድ እራሳቸውን የታሪክ ምሁራን ነን በሚል ባልተጨበጠ ይልቁንም በምኒሊክ የቅኝ ግዛት ህልማቸው ከተደናቀፈባቸው ቂመኛ ፀሐፊዎች አነበብን የሚሉት እና የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ያማለሉ መስሏቸው  ''ምንሊክ 10 ሚልዮን ኦሮሞ ገደሉ'' እያሉ ኢትዮጵያ ከነበራት የህዝብ ብዛት (7 ሚልዮን) በላይ  ቁጥር ሲጠሩ እፍረት አልተሰማቸውም።

''ማን ያውራ የነበረ'' እንዲሉ የኒውዮርክ ታይምስ  ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ ጋዜጣው አዲስ አበባ በነበረ  በልዩ ዘጋቢው አማካይነት ስለንጉሡ እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ፅፎ ነበር።ጋዜጣው  አፄ ምንሊክ እና አስተዳደራቸውን ከገለፀበት አረፍተ ነገር  ውስጥ እነኝህ ይጠቀሳሉ  -

 - ኢትዮጵያን ወደ ህገመንግስታዊ የንጉሥ አስተዳደር ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን፣

 - የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 7 ሚልዮን መሆኑን፣

 - አፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ጦርነት የነበረው የአፄ ዮሐንስ ተተኪ  እሳቸው መሆናቸውን ካልተቀበሉት ጋር ብቻ እንደ ነበር፣

 - የአውሮፓውያንን ስልጣኔ ወደሀገራቸው ለማምጣት የባርያ ንግድን ከመዋጋታቸውም በላይ ነፃ ትምህርት ዕድል ዜጎች እንዲያገኙ መሰረት መጣላቸውን፣

 - ምንሊክ እራሱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰው መሆናቸውን። ከችሎታዎቻቸው መካከል  ዲፕሎማት፣የፋይናንስ ባለሙያ እና  ወታደር የሚሉት እንደሚጠቀሱ እና

 - እንደ ዲፕሎማት እና ወታደር የጣልያንን ወረራ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉበት ጥበብ መሆኑን፣

 የሚሉ ይገኙበታል።የጋዜጣውን ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።

 የኒውዮርክ ታይምስ  ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

Published: November 7, 1909 Copyright © The New York Times

http://query.nytimes.com/mem/archive-free/pdf res=F50A12F63A5A15738DDDAE0894D9415B898CF1D3 



Friday, December 27, 2013

'' ሆድ ያባውን ንግግር ያወጣዋል''- የጀዋር መሐመድ እና መሰሎቹ ፅንፈኛ 'ሜጫዊ' አስተሳሰብ አላማው ህዝብን ማፋጀት ነው!

('ሜጫ' የሚለውን ቃል ከጀዋር ንግግር አገባብ መረዳት እንደሚቻለው ካራ፣ጎራዴ ለማለት ተጠቅሞበታል)
 በአሜሪካዋ ሚኒሶታ ግዛት ሁለቱ ''አክቲቪስት'' ጀዋር መሐመድ እና ሃጂ ነጂብ መሐመድ ያደረጉት ንግግር አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በመጪው ግዚያት  የሚገጥሟትን ተግዳሮቶች የሚያመላክትም ጭምር ነው። የጀዋር መሐመድ ''ሙስሊም  ያልሆነውን'' እንደርሱ አገላለፅ እርሱ በተወለደበት አካባቢ ''በሜጫ አንገቱን እንደሚቀላ'' የተናገረበት እና ሃጅ ነጂብ መሐመድም በተራቸው ''ከኦሮሞ ተወላጅ ባብዛኛው (ከ80% በላይ) ሙስሊም ነው .....በኢትዮጵያም እንዲሁ ከ ሃምሳ ሚልዮን በላይ ነን.....'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሁለቱም የሜኖሰታ ተናጋሪዎች ከእዚህ ቀደም በሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ እየደረሰ ያሉትን መንግስታዊ የአስተዳደር በደሎች ለማስተጋባት ''ድምፃችን ይሰማ'' በሚሉ መድረኮችም ሆኑ ሌሎች መድረኮች በማስተጋባት መታወቃቸው ብዙ ግን አስፈላጊ ጥያቄዎች እንዲነሱ በር ከፍቷል።

በሀገራችን ካለው የፖለቲካ፣የሃይማኖት፣ወዘተ በደሎች አንፃር የእስልምና ወንድሞቻችን የሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች በትክክለኛ በኢትዮጵያ አንድነት፣ነፃነት እና ዲሞክራሲ በሚያምኑ ወገኖች አማካይነት ሲነሳ እና ሲመራ ማየት የሁሉም ሀገር ወዳድ ወገን ፍላጎት ነው።ከእዚህ በዘለለ ግን ጉዳዩ የአክራሪነት እና የፅንፈኝነት ስሜት በያዙ ወገኖች እሳት ዳር እንደሚጫወት ሕፃን ያሻቸውን ሲያደርጉ መመልከት ደግሞ ተገቢ አይደለም።

ጉዳያችን ጡመራ ባለፈው አመት ጥቅምት 2004 ዓም ላይ ''የሙስሊሙ ጉዳይ'' በሚለው ርዕስ ስር እንቅስቃሴው ወዴት ሊያመራ ይችላል? በሚል ከእዚህ በታች ያለውን ሁለት ስጋቶች አስቀምጣ ነበር።

''ጉዳያችን ጡመራ'' ቀ 27 ወራት በፊት (ጥቅምት/2004 ዓም) የነበራት ስጋት

  • ''የ ሙስሊም ፅንፈኛ ቡድን'' የ ሙስሊሙን ጥያቄ  የመሪነት ሚና ለመያዝ ቀና ማለት 
አልፎ አልፎ ብቅ ሲል የነበረው በ ሙስሊሙ ሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሰው ''የ ሙስሊም ፅንፈኛ ቡድን'' ከ ቢጫ ቀጥሎ ይወሰዳል ለተባለው እርምጃ የመሪነት ሚናውን ለመያዝ ቀና ቀና ማለቱ አይቀርም።በ ኢትዮጵያ ከ ቅርብ አመታት ወዲህ በ ጅማ፣ሐረር፣እልባቦር እርሲ ወዘተ እነኝህ ፅንፈኛ ቡድኖች በ አብያተ ክርስትያናት እና ምእመናን ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ እንደነበር ይታወሳል።በመሆኑም  የ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን የማይወክሉ ግን ለ እራሳቸውም እንግዳ ትምህርት ይዘው የመጡባቸው  ክፍሎች የ እዚህ አይነቱን  ቀይ ካርድ መምጣት ''ሰርግ እና ምላሽ '' አርገው እንደሚመለከቱት ሳይታለም የተፈታ ነው። እዚህ ላይ በ ነሐሴ ወር ላይ የ ''አልሸባብ'' ሰዎች ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ በ ከፍተኛ ደረጃ የታጠቁ ቡድኖች  በሞያሌ ከተማ ላይ ያደረጉት ጥቃት አይዘነጋም።
  •  በ አፍሪካ ቀንድ ለዘመናት ችግር ሲፈጥር የነበረው አለም አቀፍ አክራሪ እስልምና መነቃቃት ይጀምራል።
  
 አፍሪካ ቀንድ ለዘመናት ችግር ሲፈጥር የነበረው አለም አቀፍ አክራሪ እስልምና በመነቃቃት  ኢትዮጵያውያን  ፅንፈኝነት አስተሳሰብ ያላቸውንሙስሊሞች  መንግስት ስልጣን ጥያቄ እንዲያነሱ እና ኢትዮጵያ ''እስላማዊ መንግስት'' እንዲኖራት ወደሚል ግብ እንዲሄዱ ይህን ካደረጉ ብቻ  ጎናቸውእንደሚቆም ግፊቱን ሊያደርግ ይችላል። ይህንን ደግሞ ብዙ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አይደግፉትም።  እዚህም ነው ጥያቂያቸውን ጥንቃቄ እና  ሰላማዊ መንገድ ብቻ  ማቅረብ ብዙውን ሕዝብ ያስደመሙት።  እዚህ በተጨማሪ  አለም አቀፍ ፅንፈኛ  እስልምና እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ቦታ ካገኘ ሁለት መሰረታዊ ክስተቶች  ሀገራችን ላይ ሊያመጣ ይችላል። እነርሱም አንድ  ሃያላኑ መንግሥታት ጣልቃ ገብነት ቢያንስ  ቁሳቁስእና  ቴክኒክ እርዳታ ነገሩን ማወሳሰብ እና ሁለተኛው  እስልምና ውጭ በሆነው ኢትዮጵያዊ ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መክተቱ የሚሉት ይጠቀሳሉ።'' (ጉዳያችን ጡመራ ጥቅምት/2004 ዓም http://gudayachn.blogspot.no/2012/10/blog-post_5.html ) 

ዛሬ ጀዋርም ሆነ ሃጅ ነጂብ መሐመድ እያመላከቱን ያሉት ይህንኑ ነው።የዲሞክራሲ ጥያቄን በድምር የመመለስ አባዜ ማለትም ችግሩ የብሔር እገሌን ችግር መፍታት፣የሃይማኖት እገሌን ችግር መፍታታ፣ ወዘተ የሚሉ የአምባገነንነትን መጫኛ ፈረስ ማዘጋጀት የተበላ ዕቁብ ከመሆን አያልፍም።ጀዋርም ሆኑ ሃጅ ነጂብ መሐመድ በመኖሶታው መድረክ ሊነግሩን የፈለጉት ''ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ'' መሰል ላለፉት ሃያ አንድ አመት ስንሰማው የነበረውን ''ኢትዮጵያን በብሄር ከፋፍሎ አላማን ማሳካት'' የሚለውን ያፈጀ መዝሙር መሰል ማላዘን ነው።እነርሱ የጨመሩበት ነገር ቢኖር ''በኦሮሞ ስም የታሸ አዲስ እስልምና'' ያለ መሆኑን ለመናገር ደፋርነት ማሳየታቸው ነው። ይህ ሂደት በእራሱ በወንድማማችነት የኖረውን የእስልምናውን ሃይማኖት የሚጣረስ እና በሃይማኖቱ ብሔር ብቻ ሳይሆን የሀገር ድንበር የማይገድበውን በአለማችን ካሉት ታላልቅ አምነቶች አንዱ -እስልምናን እንደነርሱ አገላለፅ ''በኦሮሞነት'' ስር መሸበብ ነው።

በመሰረቱ የኢትዮጵያ የእውነተኛ ዲሞክራሲ ጥያቄ በግለሰቦች ''ሜጫዊ'' ''ቁረጠው!ፍለጠው!'' ንግግር እና ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወር በተጠቀበት መርዛማ ንግግር ብሄርን ከብሄር አልያም የሃይማኖት ተከታይን ከሃይማኖት ተከታይ በማበላለጥ አይሰናከልም። በብሄር እና በሃይማኖት ለመከፋፈል የቆሙ የመኖራቸውን ያህል ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለእምነቶች መከባበር የቆሙ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያ እንዳላት መዘንጋት አይገባም።የጀዋር መሐመድ እና የሃጅ ነጂብ መሐመድ ንግግር ግን የመብት፣የዲሞክራሲ እና የአንድነት ትግሉን ጠልፎ ወደ አለተፈለገ አቅጣጫ የመግፋት የግል ስሜታቸውን ከመግለፅ ባለፈ የሚያመጣው አዲስ ነገር አይኖርም። ይልቁን ''ሆድ ያባውን ንግግር ያወጣዋል'' የሚል ስያሜ መስጠት ግን የሁለቱን ንግግሮች በበቂም ባይሆን በመጠኑ የሚገልፀው ይመለኛል።
 በመጨረሻም የጀዋር መሐመድ እና የሀጂ ነጂብ መሐመድን ንግግር ይመልከቱ።




ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Thursday, December 26, 2013

ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው። የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ውል ዝርዝር ጉዳይ ከሕዝብ ሊደበቅ አይገባም።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሁለት ሳምንት በፊት በሱዳን ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።በእዚህ ጉብኝት ላይ አቶ ኃይለማርያም ''እጅግ ለም የሆነ  የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ተስማምተዋል አሁን የቀረው ችካል ማስቀመጥ ነው'' የሚል ዜና በኢሳት ሲዘገብ ቀናት ነጉደዋል።ትናንት ታህሳስ 16/2006 ኢሳት በአለም አቀፍ ራድዮ ስርጭቱ ላይ የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ የሚከታተሉ  'የኢትዮጵያ ድንበር ኮሚቴ' የተሰኘ ኮሚቴ አባላትን በቃለ መጠይቅ አቅርቦ ነበር።እንደ ኮሚቴው ገለፃ ከሆነ አሁን ''የኢትዮጵያ መንግስት ለሱዳን  ለመስጠት መስማማቱ የሚነገረው መሬት ከቀድሞ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ያለ አሁንም  ገበሬዎች የሚገኙበት እና ባዶው ቦታን ጨምሮ በትንሹ ካለምንም ማጋነን 15 ሚልዮን ሕዝብ አስፍሮ መመገብ የሚችል ቦታ ነው።15 ሚልዮን ልብ በሉ! 

በሕዝብ ስም የሚደረግ ማንኛውም ውል ከህዝብ ሊደበቅ አይገባውም።ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው።ይህ ደም ደግሞ ለዘመናት የኢትዮጵያ አባቶች እና እናቶች ያፈሰሱት ደም ነው።ማንም መንግስት በሕዝብ ደም ሊደራደርም ሆነ ድንበር ሊሰጥ አይችልም።ለአንድ 'ኩርማ' መሬት 'ለባድሜ' በሺዎች ላረገፈ ጦርነት ክተት ያወጀ  መንግስት 15 ሚልዮን ሕዝብ የሚያሰፍር መሬት ለሱዳን ለመስጠት መነሳቱ በቁም እየተሸጥን ለመሆኑ ማሳያ ነው። በትዊተር በብዛት የሚታዩት ባለስልጣናት ከሌላው ዜና ይልቅ የእዚህ አይነቱን ቅድምያ ሊሰጡት በተገባ ነበር።ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው።
ፊልሙ  መጨረሻ ላይ ሲናገር የምትመለከቱት የስርዓቱ አቀንቃኝ ይመስላል።በጋራ ''አሸባሪዎችን ይዋጋሉ'' የሚለው ጌቶቹ መሬቱን ሸጠው እንደጨረሱ በገደምዳሜ እየነገረን ነው።በመጀመርያ እንደዚህ አይነት አካባቢ አገር ጎብኚ ሲመጣ  እንዲያስተናግድ የሚፈቀድለት የስርዓቱ  ሹም ነው።በመሆኑም በጋራ ድንበር እየጠበቁ ነው ይለናል።አገር ጎብኝዋ ግን ''እህ!'' በማለት ውሸቱን ማወቅ መቻሏን ትገልፃለች። 



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Wednesday, December 25, 2013

ከትዝታዬ


ከትዝታዬ የሚሉ በጣም አጫጭር ጽሁፎች አልፎ አልፎ ጣል ለማድረግ ማሰቤን ልግለጽና ለዛሬ ይህችን ላካፍላችሁ። በደርግ መውደቅያ ዘመን አካባቢ አዲስ አበባን የምናውቃት በታክሲ ውስጥ፣በትምህርት ቤት፡ መምህራን፣ ካፌ ቤት፣ሰራተኞች ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር  በነጻነት (ሌላውን ነጻነት ትተን) በትግርኛ፣ኦሮምኛ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ይናገሩ ነበር።

ከሚኒባሱ ጋቢና የተቀመጠ ሰው ከኋላ ለተቀመጠ ወዳጁ በትግርኛ ድምጹን ከፍ አድርጎ ያወራ ነበር።በአውቶቡስ ውስጥም ኦሮምኛ ሆነ ጉራጊኛ ህዝቡ ካለ አንዳች መሳቀቅ ይናገር ነበር። ሁሉም ተከባብሮ ይኖር ነበር።ሌላ ቋንቋ ለመናገሩ አንዳች መሳቀቅ አይሰማውም።

ዘመኑ በደንብ ትዝ ይለኛል 'ጋሽ ተስፋ ጽዮን' የሚባሉ የሳይንስ መምህር ትምህርት ቤታችን ውስጥ ቮሊቮል መጫወት ይወዱ ነበር።ሲጫወቱ በትግሪኛ እያውሩ ነበር ኳሱን የሚሰርቡት... ጋሽ መገርሳ የእስፖርት አስተማሪያችንን አልረሳቸውም ኦሮምኛ የሚችሉ ልጆች ጋር በኦሮምኛ ይቆጧቸው ነበር፣ ኮሜርስ ስገባ ጎይቶም የሚባል በጣም የማዝንለት ጓደኛ ነበረኝ።ጎይቶም የአክሱም ልጅ ነው።አባቱ በህወሃት እስር ቤት መሆኑን ከእናቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መምጣቱን ይነግረን ነበር።ጎይቶም ትግሪኛ ሲናገር ባይገባንም ጓደግኞቹ የተለየ ንግግ ር የተናገረ ያክል አይሰማንም።እርሱም ደስ ብሎት አውርቶ ቀጥሎ ወደ እኛ ዞሮ አማርኛ ያወራናል... አዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ ሬጅስትራር ክፍል ስንሄድ ኦሮምኛ የሚናገሩ ሰራተኞች ብዙ ነበሩ።ይህ ቢሮ ውስጥ ነው የማወራው። ማንም ቅር አይለውም።ልዩነትም የለውም።

... መከላከያ ፊት ለፊት ያለው ትልቁ ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ለስራ ልምምድ ስላክ ብዙ አለቆች የእረጅም ጊዜ የስራ ልምድ ያላቸው የተከበሩ አባቶች የሚባሉ የትግራይና የኤርትራ ተወላጆች ነበሩ።በሻይ ሰኣት ሁሉም ዘና ብለው በትግሪኛ ያወራሉ ይጫወታሉ።ሁላችንም 'ጋሼ እትዬ' ብለን የታዘዝነውን እንሰራ ነበር... ብላቴ ስንሄድ ብዙ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች በየቋንቋቸው ይናገሩ ነበር።
ይህ ውበት ዛሬ ኢትዮዽያ የራቃት ይመስለኛል። ህዝቡን ጎሰኞች ስለ ጎሳ ብዙ በማውራት አሳቀቁት። ዛሬ ስለ ጎሳ አብዝቶ የሚያወራው መንግስት ከመጣ ወዲህ ወገኔ ተሳቀቀ።ነቀምት ሲገባ አማርኛ መናገር፣ጉራጊኛ ማውራት ተሳቀቀ።አዲስ አበባ ሲገባ ከ አራዳ ቋንቋ ሌላ ማውራት የሚያሳቅቀው ሆነ። የጎሳን ነገር  መንግስት ቤተ መንግስት አስገብቶ እንደፈለገው አብኩቶ ህዝቡን አሳቀቀው።ህዝቡ የእራሱ የሆነ የመከባበር ዘይቤው ጠፋው።ዘረኞች ፋታ አገኙ።ህዝቡን ናኙበት።ዛሬ በነጻነት ድምጹን ከፍ አድርጎ የሚያወራው አዲስ አበባ ላይ  በስደት ላይ የሚገኙ ሱማሌዎች ብቻ ሆኑ።እነርሱ ታክሲ ውስጥም ጮክ ብለው ያወራሉ።ሌላው አፈረ።ይህች ነች የብሔር ብሄረሰብ መብት? ሕዝብ መከፋፈል ለስልጣን ጥበቃ።

ታህሳስ 16/2013 ዓም 


በጠ/ሚ/ዐቢይና ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ላይ በውሸት ወሬ የዘመቱት ''አፈ-ጊንጦች'' በቴዲ አፍሮ ዘፈን ሊሸሸጉ ሲሞክሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየሳቀባቸው ነው።

ጠ/ሚ/ዐቢይ አሕመድ እና ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ክብረት በታላቁ የዓባይ ግድብ ምርቃት ቀን። ======== ጉዳያችን ምጥን ======== አፈ ጊንጥነቱ እና የውርደት ካባው ''አፈ ጊንጥነት'' የሚለውን ...