Thursday, April 18, 2013

'' እስረኛ እንኳን እየበላ ነው የሚቀጣው'' የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመለከተ ዕይታ

በቀል ሃይማኖታዊ መሰረት የለውም

  •  '' እስረኛ እንኳን እየበላ ነው የሚቀጣው ......ፈርኦንም ሕዝቡን በምግብ አልቀጣም ......ለመለመን ከኮሌጁ ግቢ ውጭ ስለተከለከልን ከውስጥ ሆነን በአጥር ስር ነው የምንለምነው '' የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች 

  • ''ምግብማ እግዚአብሔርስ እስራኤላውያንን መቼ በምግብ ቀጣ እየመገበ ነው.....'' አቡነ ህዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ፀሐፊ

  • ''ጉዳዩ እርስዎን ይመለከታል ተብዬ ነው ወደ እርስዎ የደወልኩት'' የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ መሳይ ለአባ ሰረቀ በአማርኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ
  • ''አይ ውል ፋይንድ አውት'' አባ ሰረቀ በአማርኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ በእንግሊዝኛ ሲመልሱ 

የ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የአስተዳደር እና የመምህራን ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባነሱት ጥያቄ ኮሌጁ በማን እንደተዘጋ አልታወቀም።ይህ ማለት በኮሌጁ አስተዳደር አይደለም ለማለት ባይቻልም ተማሪዎቹ ለቀው እንዲወጡ የተደረገበት ማስታወቂያ ፊርማ እና ስም የሌለው ግን የኮሌጁ ማህተም ብቻ ያለበት መሆኑ ተነግሯል። በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በብዙ ሌሎች ተቋማት ውስጥ እርምጃዎች ሲወሰዱ የሚመለከተው አስተዳደር ሽባ ሆኖ የማይታዩ እጆች ግን ሲያሽከረክሩት ማየት የተለመደ ነው። በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅም የሚስተዋለው ይሄው ነው።አቡነ ህዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ፀሐፊ ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የማያውቁ ሆነው መቅረባቸው ከሁሉም ደግሞ 
''ጉዳዩን የሚመለከተው ቦርዱ ነው ቦርዱ ስብሰባም ላይ ትናንት ተገኝቻለሁ'' ብለው ''ውሳኔውን ግን አልነገሩኝም '' ማለት  አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ቤተክህነቱን ከሚመለከታቸው በላይ አለቆች እንዳሉባት የሚያመላክት ነው።

የኮሌጁ የኃላ ታሪክ

በ 1942 ዓም እኤአ በ ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ የተመሰረተው የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በታህሳስ 1961 ዓም እኤአ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስር ሆኖ አገልግሎቱን እንዲሰጥ ተደረገ።ሆኖም ግን የንጉሡ ዘመን በደርግ ስርዓት ሲተካ ኮሌጁ የመዘጋት ዕድል ገጠመው። ይሄውም በ 1970 ዓም እንደሀገራችን ዘመን አቆጣጠር ኮሌጁ ሲዘጋ በወቅቱ የነበሩት ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እንዲዛወሩ እና የኮሌጁ ህንፃ ለአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሳይንስ ፋክልቲ እንዲሰጥ ተደረገ። የደርግ መንግስት ወድቆ ኢህአዲግ ስልጣን እንደያዘ አቡነ ጳውሎስ መንበረ ጵጵስናውን ያዙ።አቡነ ጳውሎስ ካደረጉት ነገር አንዱ የኮሌጁ እንደገና የማስከፈት ሂደትን ''ኮሌጁ ለቤተክርስቲያኒቱ ይመለስ'' የሚል የድጋፍ መጠየቅያ  ፊርማ  አሰባስቦ መንግስት ኮሌጁን እንዲመልስ መጠየቅ እና ማስመለስ ነበር።

ኮሌጁ ከተመለሰ ወዲህ በቀን እና በማታ መርሃግብር በዲግሪ እና በዲፕሎማ ደረጃ ብዙ ተማሪዎችን አስመርቆ አውጥቷል። ስለቤተክርስቲያን አስተምሮ የጠለቀ እውቀት ያላቸው በኮሌጁ የትምህርት ሂደትም ሆነ ይዘት 'ኦርቶዶክሳዊ እና ኢትዮጵያዊ ይዘት ይኑረው' የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ቆይቷል።ለእዚህም መነሻ የሚያደርጉት ከኮሌጁ የተመረቁ ጥቂት ምሩቃን ከቤተክርስቲያን አስተምሮ ውጭ  የሚስያስተምሩበትን ሁኔታ እና ቀድመው በቤተክርስቲያኒቱ መሰረተ እምነት የማያምኑ ከኮሌጁ ለመመረቅ እና የቤተክርስቲያንን መድረክ ለማግኘት የገቡበትን ሂደት በምሳሌነት ይጠቅሳሉ።ይህንን ችግር ለመፍታት ቤተክርስቲያን ባብዛኛው በእርሷ የውስጥ አስተዳደራዊ ጉዳዮች በመክረሟ እና ሊቃውንቷም ቢናገሩም የመደመጥ ዕድል ስላላገኙ ጉዳዩ በአንዳንድ ማህበራት የማሳሰቢያ መልክት ማለፍ አልቻለም።

አፍሪካን ባዳረስን ነበር

አሁን የተነሳውን በተማሪዎች እና በኮሌጁ መሃከል ያለውን አለመግባባት ምክንያት እንግዲህ ከላይ ስለኮለጁ የኃላ ታሪክን ከግንዛቤ ማስገባት ቢገባም የቤተክርስቲያን አስተዳደር የመታገት ቀጣይ ሂደት ግን ማሳያ መንገድ ከመሆን አያልፍም።ኢትዮጵያ ብዙ የመስርያ እና ወደላቀ ደረጃ የመድረሻዋን መንገድ የሚዘጉባት የታሪክ አጋጣሚዎች ታይተዋል። ለምሳሌ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን በጥራት አገልግሎቱን መስጠት ቢችል ዛሬ ቢያንስ በ አስር የአፍሪካ ከተሞች ቅርንጫፍ ኮሌጆችን ወይንም ከእዝያ በላይ በተለያዩ የአፍሪካ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ በትብብር ስልጠና የመስጠት ደረጃ በደረስን ነበር። እዚህ ላይ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያንን መጥቀስ ተገቢ ነው። የግብፅ ቤተክርስቲያን አማኞች በቁጥር ጥቂት ሆነው እና በእስላም አክራሪዎች ብዙ በደል ቢደርስባቸውም የሀገራቸውን ምጣኔ ሀብት ጉልህ ተሳታፊ ከመሆን አልፈው ገዳማት እና ኮለጆቻቸውን በባህር ማዶ መስረተዋል።


ወደ እኛ ጉዳይ ስንመጣ ግን ከተመሰረተ ከ ስልሳ አመት በላይ የሆነው ኮሌጅ ዛሬ ተማሪዎቹ አባሮ ለማኝ እያደረገ ነው። የችግሮቹን ምንጮች ስንመለከት ግን ከሁለት በኩል ይመነጫሉ።አንዱ ከእራሷ ከቤተክርስትያን አስተዳደራዊ ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው ከመንግስታቶቻችን(ከደርግ እና ከኢህአዲግ)ይመነጫሉ። ጉዳዩን ግልፅ ለማድረግ ኮሌጁ ከእድገቱ የተገታበት አንዱ ምክንያት ለ 17 አመታት በደርግ መንግስት መዘጋቱ ሲሆን ከተከፈተ በኃላም በአግባቡ እና በስርአት ለማስተዳደር እና ኦርቶዶክሳዊ እና ኢትዮጵያዊ ቃናውን ሳይለቅ ብቁ መንፈሳዊ እና በዘመናዊ ትምህርት የበሰለ ምሩቅ ለማውጣት ሁለት ችግሮች ተጋርጠውበት ቆይተዋል።አንዱ በሀገሪቱ የመናገርም ሆነ ሃሳብን የመግለፅ መብት መታፈንን እንደ መልካም አጋጣሚ የወሰዱ የቤተክህነት ''የመንግስት እንባ ጠባቂ ነን'' ባዮች ችግሩን ስያድበሰብሱት ከመክረማቸውም በላይ ከኮሌጁ የሚወጡ አንዳንድ ምሩቃንን የሃይማኖት አስተምሮ መሰረታዊ ችግር እንዳለባቸው እያወቁ የእነርሱን ስሜት እስከተጋሩ ድረስ በፀጋ መቀበላቸው ሲሆን በሌላ በኩል በቤተክህነት የሰፈነው ሙስና በአንድ ላይ የቤተክርስቲያንቱን ልዩ ልዩ አካላት ሲያዳክሙ ኮለጁንም አብረው መደቆሳቸው የሚለው ተጠቃሽ ነው። በተለይ  የቤተክህነት ''የመንግስት እንባ ጠባቂ ነን'' ባዮች የቤተክርስትያንቱን ሊቃውንት ከመግፋት አልፈው በሀገርውስጥ ምንም የመናገር መብት እንዳይኖራቸው መድረክ በመከልከል እና ገፋ ስል ደግሞ በተለያየ የፖለቲካ ስም በመለጠፍ ከሀገር እንዲሰደዱ ያደርጉት ድርጊት ለኮለጁ መጠናከር አይነተኛ አስተዋፅኦ ያደርጉ የነበሩ ሊቃውንትን አሳጥቷል።

ለመብት ከመነሳት ያለፈ ምን ምላሽ ይኖረዋል?

ለማጠቃለል የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ችግር ከላይ የተነሱት የኮሌጁ የገጠሙት ሃይማኖታዊ የትምህርት ስርዓት የማስፈን እና የመቅረፅ ችግር እንዳለ ሆኖ አጠቃላይ ችግሩ ግን ሀገራችን ያለችበት የአፈና ስርዓት ውጤት ነው።አፈና ባይኖር ዜጎች የተሰማቸውን የመናገር፣ ሃሳባቸውን የመግለፅ እና ችግራቸውን ካለፍርሃት በአንድ አዳራሽ ተሰብስበው እውነቱን በመነጋገር በተፈታ ነበር። የቤተክህነት የመንግስት እንባ ጠባቂ ነን ባዮችም እንዲህ እነሱ የወሰዱት እርምጃ ሁሉ ከመንግስት አንፃር ሁሌ ትክክል ነው እየተባለ  የሰሩት ሙስና እና አላግባብ መበልፀግ ቤተክርስቲያንን እየቀበረ ባልሄደ ነበር። በመሆኑም በጥቃቅን ክስተቶች ከማተኮር አጠቃላይ ሃገራዊ ችግራችንን መፍታት የጥቃቅን ችግሮችን የመፍታት ፋይዳውን ማሰብ ጠቃሚ ይመስለኛል።ሕግ ሰዎች በምግብ እንዲቀጡ አያዝም።ይህንን የፈፀሙም ሆነ ያስፈፀሙ ከሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን ከሰብአዊነት አንፃርም ወንጀል እንደሆነ ይኖራል።ምግብ ከልካዮቹም ወቃሽ ከሳሽ የሌለባቸው የሆኑት ''ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ከውጭ ታሳድራለች'' እንዲል የግል የመበቀል ስሜታቸውን እና ፈላጭ ቆራችነታቸውን የማሳያ መንገድ ሲያደርጉ ለመብት ከመነሳት ያለፈ ምን ምላሽ ይኖረዋል?
 
ለግንዛቤ እንዲረዳን የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ከሀገር ቤት አልፈው በውጭ ሃገራት ሁሉ የመንፈሳዊ ኮለጆቻቸውን እየመሰረቱ ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል ከድህረ-ገፅ ያገኘሁት በአውስትራሊያ የሚገኘው ፖፕ ሺኖዳ ሶስተኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ የትምህርት አይነቶቹን ዝርዝር ብቻ መጥቀስ ብዙ ነገር የሚያሳይ ነው። 
ይቆየን 
ጌታቸው 
ኦስሎ

Coptic Orthodox Theological College, Sydney Australia
Pope Shenouda III Coptic Orthodox
TheologicalCollege
SYDNEY, AUSTRALIA
 
 Source- http://www.coptictheology.com/diploma.php 

Monday, April 15, 2013

''አቤት በሉን''...''ለምን ልጣት ለምን ትዘን፣ ሆናኝ ጎኔ ለኔ በዚች አለም።''

ከእዚህ በታች የምታገኙት ግጥም እና ዘፈን ከያንያኑ ለሴት ልጅ መብት የደረሱት እና ያቀነቀኑት ነው። ነገር ግን ሀገር በሴት(እናት)  ትመሰላለች እና ለእናት ሀገር ብለው ቢሰሙት የማይሆንበት ምን ምክንያት አለ? 

አቤት !አቤት በሉን አቤት ስሙን ፣
መልክት አለን እዚህ ቤት ፣
አቤት በሉኝ አቤት መልክት አለኝ እዚህ ቤት። 
አቤት በሉን አቤት መልክት አለን እኛ ስለኛ።
----------እንዳንለያይ እንዳንለያይ አደራ።

እንውጣ ነቃ ብለን፣

እናስብ እንችላለን።

የናቁት አንድቀን ያደርጋል እራቁት፣

ንገሩት ለእዛ ሰው ምከሩና አንቁት።

ያክብረኝ ላክብረው መናናቁም ይቅር፣

መቸም የትም ቢሆን ያሸንፋል ፍቅር።

ለምን ልጣት ለምን ትዘን፣

ሆናኝ ጎኔ ለኔ በዚች አለም፣

የኛ ፡ የሁላችንም ድምጽ (ኢትዮ ገርልስ ግሩፕ እና ሃይሌ ሩት)

አጥታ ሰው ከጎኗ አቅሟም አንሷት፣

ላያት አልፈልግም ከፍቷት ብሷት፣

እንግዲህ ቻልኝ እሷን ልደግፋት፣

እንዳላየሁ ሆኘ ስንቴ አለፍኳት፣

ግን አሁን ይብቃኝ ልቁም ጎኗ፣

አለም ካለርሷ ሙሉ አትሆንምና።

ለምን ልጣት ለምን ትዘን፣

ሆናኝ ጎኔ ለኔ በዚች አለም።

ተነስተናል ቆርጠናል፣

ይሄው መጥተናል ።

ይበቃናል የድሮ፣ 

ተነስተናል ዘንድሮ። 
ተነስተናል ድሮ ተንቀናል፣

ባሳለፍነው ሰዎች ከፍቶናል 

ተነስተናል ዛሬ ቆርጠናል፣

ፍቅር ጥበብ ተስፋን ይዘናል፣

ተደፍረናል ድሮ ተንቀናል፣

ባሳለፍነው ሰዎች ከፍቶናል


Sunday, April 14, 2013

ይህ ጉዳያችን ካልሆነ ምን ጉዳያችን ሊሆን ይችላል? ኢትዮጵያ መሬት ባከራየቻቸውም ሆነ ከሸጠችላቸው ኩባንያዎች ሃገራት ጋር ክርክር ቢነሳ ጉዳዩ የሚታየው በ አለም አቀፍ ገላጋይ ፍርድ ቤት ነው

ኢጣልያ በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል በ ኤርትራ ለመጀመርያ ጊዜ ቦታ ማግኘት የጀመረችው በ አሰብ ግዛት ሩባርቲኖ በተባለ የመርከብ ኩባንያ አማካይነት ከ አንድ ሱልጣን   በ 1869 ዓም በገዛችው ትንሽ መሬት መሆኑ ይታወቃል። እንግዲህ ሃገራችንን ከ አንድ መቶ አመታት በላይ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ የቀጠለ ፖለቲካዊም ሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ችግር እየፈጠረ መሆኑ ይታወቃል። 

አፕሪል 14/2013 ዓም በኢሳት ቴሌቭዥን በቀረበው ''የእሁድ ወግ'' የውይይት መርሃግብር ላይ አቶ ዳንኤል ጥላሁን በካናዳ ቶሮንቶ የህግ ባለሙያ ስለ መሬት ለውጭ ባለ ሃብቶች መሸጡ ጉዳይ ያነሱት ሃሳብ ሚዛን የሚደፋ እና ብዙ ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው አይመስለኝም። ቀድሞ ስለመሬት ማከራየት ሳስብ ስጋት ይሆናል ብዬ የማስበው ወደፊት መሬት በኪራይ ወሳጅ ሃገራት ከኢትዮጵያ ጋር የጸብ ማንሻ ምክንያት ቢሆናቸውስ? የሚል ነበር። ይህንን ስጋቴን ግን በማስረጃ ለማስደገፍ አለመግባባቱ እስኪፈጠር መጠበቅ አለብኝ ማለት ነው? ብዬ ያሰብኩበት ጊዜ ነበር።ዛሬ አቶ ዳን ኤል ይህንን ስጋት አጠናክረውልኛል። 

የዛሬው የመሬት ኪራይም ሆነ ሽያጭ ነገ ከገዢውም ሆነ ከተከራዩ ሃገር ጋር እስከወታደራዊ ግጭት ድረስ የማድረስ እድል እንዳላቸው የሚያመላክት ሁኔታ መኖሩን ለመረዳት አቶ ዳንኤል በኢትዮጵያ እና በተከራይ የውጭ ኩባንያዎች መካከል የተደረጉትን ውሎች ባህሪ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል።

''የኢንቨስትመንት ኮንትራቶች ሲፈረሙ የኢንቨስትመንቱን መብቶች የሚያስጠብቁ ብዙ ነገሮች አሉ።''ባይላተራል ኢንቨስትመንት ፕሮተክሽን ትሪቲስ''  መንግስት  ከህንድ ከቻይና ከግብጽ ጋር ሁሉ ተፈራርሟል።በሌላ በኩል የ 1966ቱን የ ዋሽግተኑን ''ስቴት ኢንቨስተር ዲስፕዩት'' ይህ መንግስት ተፈራርሟል። እነኚህ ውሎች ምን ያመጣሉ? እነኚህ ሁሉ ነገሮች ሲደመሩ ስትል መሬታችንን በኮንትራት እየገዙ ያሉ ሰዎች መሬቱን ይይዙና የሚዳኙት ግን በ አለም አቀፍ ህግ ነው።በ አለም አቀፍ የግልግል ፍርድቤት ነው የሚዳኙት ከመንግስት ጋር ሙግት ቢገጥሙ በመሬቱ ዙርያ ማለት ነው።ይህንን ለማጠናከር ደግሞ ምን ታውጆላቸውል? ''ፕሮክላሜሽን ሰርቲ ሰቨን''የሚባል በ1996 በ አዋጅ ታውጆላቸዋል።ይህ ህግ ደግሞ ህዝቡን እያፈናቀሉ መሬቱን ከገዙ ባለሃብቶች ጋር ክርክር ቢነሳ ጉዳዩ በ አለም አቀፍ የግልግል ፍርድቤት እንዲታይ መንግስት ህግ አውጥቶላቸዋል።ይህ ሌላ አስገዳጅ ህግ ያግዘዋል የ 1958 ''ኒዎርክ ኮንቨንሽንን'' ፈርሟል።እነኚህን ነገሮች ዘርዝረህ ስትመለከታቸው አንድ ኢትዮጵያዊ ገበሬ በማንኛውም ጊዜ ሊነቀል የሚችል ነው።ምንም አይነት መብት የለውም።መሬታችንን የሚገዛው ባዕድ ግን ከእኛ በላይ መብት አለው።ይህንን መብቱን በ አለም አቀፍ ደረጃ ማስከበር የሚችል ነው።እየሆነ ያለው ነገር ዜግነታችንን ተቀምተናል።ከመቀሌ እስከ ሞያሌ ዜግነታችን ተገፏል።መሬት ላራሹ ተገቶ የቻይና ፊውዳሊዝም እየሰፈነ እኮ ነው።''ብለዋል።

የ አሰብ የቁራሽ መሬት ሽያጭ መዘዝ እስከ አሁን ድረስ የሃገራችን ችግር አንዱ ምንጭ እንደሆነ እንደቀጠለ ሁሉ የዛሬው የመንግስት የመሬት ኪራይ እና ሽያጭ ጉዳይ ካሁኑ እልባት ካላገኘ ብዙ ችግር ማስከተሉ እንደማይቀር አመላካች ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተደቀነ አደጋ ነው።። ይህ ጉዳያችን ካልሆነ ምን ጉዳያችን ሊሆን ይችላል?


አበቃሁ 

ጌታቸው 

ኦስሎ

                              ESAT Yehud weg 14 April 2013


Friday, April 12, 2013

Ethiopia Accused of Ethnic Cleansing Over Mass Amhara Evictions

written by Endalk
Source- Global Voices (http://globalvoicesonline.org) 
Thousands of ethnic Amharas in western Ethiopia are being expelled en masse from the country's Benishangul Gumuz region, where many have settled, in what some are condemning as a campaign of “ethnic cleansing“.
Ethiopia has been divided into nine ethnically based and politically autonomous regional states and two chartered cities since 1996. The Amhara people, reportedly including children, pregnant women, and the sickly, are being uprooted to a rural area of Ethiopia's Amhara region, which contains their historical homeland.
Human rights advocates say the deportation is illegal according to Ethiopian and international law. Ethiopian authorities have maintained that these claims are unsubstantiated, saying that they have been moving and resettling indigenous and local farmers in the name of villagization programs.
This isn't the first time Ethiopian officials have forced Amhara people to move to another region. A reported 22,000 Amharas were evicted from southern Ethiopia and their homes confiscated in 2012.
A report by Ethiopian Satellite Television in March 2013 and made available on YouTube [amh] quotes opposition party leaders condemning the eviction.

Many Ethiopians are opposed to the government policy of the rural population's mass eviction. An online petition, demanding the government stop the resettlement campaign, had 1,919 signatures at the time of this post's publication on April 11, 2013.
The petition page, which is addressed to Dr. Chaloka Beyani, the UN Special Rapporteur on the human rights of internally displaced persons, and many other Ethiopian government high officials, reads:
According to the information that I have, the eviction is poorly organized and is marred by several cases of human right violations. This petition is in protest of this eviction and is intended to get the plight of these voiceless Ethiopians to the attention of the Ethiopian government and international rights organizations. Please sign the petition and invite your friends to sign as well. This is the least we can do to show our solidarity with Ethiopians who are being victimized by a misguided and irresponsible policy.
Jawar Mohammed, a political analyst and blogger, theorized on his Facebook pag
Its my view that the mass eviction at this time has well calculated political agenda and is being hatched by the real power holders. By instigating attack on vulnerable Amharas who reside outside their regional state, the regime would like to stir ethnic victim-hood sentiment. This is meant to force Amhara political leaders to resort to open ethnic partisan advocacy, which would undermine their pan-Ethiopianist narrative. What does the regime benefit from this?
Since the 2005 election, the TPLF [Tigray People's Liberation Front, one of Ethiopia's political parties and the real dominant player in Ethiopia politics although the ruling party is Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front (EPRDF)] has been trying hard to transform its ethno-nationalist narrative to that of statist nationalism. That is it wants to justify its continuous rule by presenting itself as guardian of the Ethiopian state and its historical legacy. However, before it can achieve that, it has to displace the previous claimant–the Amhara elites. Hence such surgical attack on their ethnic brethren would eventually force Amhara elites to embrace ethno-nationalism and give up the throne of Ethiopian nationalism to the new claimant- Tigrean elites.
The sad thing is while the rulers experiment with all kind of dirty tricks to prolong their days in palace, innocent and poor farmers struggling to survive on a dollar a day income are pushed around. Making these farmers homeless at the time when people are barely surviving at their home due to the unbearably high cost of living is a heartless crime that sets a dangerous precedent, that must be condemned by everyone, in regardless of who we are or what political opinion we have.
Blogger Ephrem Eshete asked [amh] Ethiopians to strongly denounce the evictions:
 ሊወገዝ የሚገባው ተግባር መነሻው ምንም ይሁን ምን፣ የክልሉ ፓርቲ ከማንም ጋር ይስማማ አይስማማ በነዚህ ዜጎች ላይ የተደረገው ተገቢነት የሌለው ነገር ነው። የዜጎች በአገራቸው ውስጥ የመዘዋወር፣ የመኖር መብት እንዲህ በጥቂት የፓርቲ ሹመኞች መወሰኑ የሚያስጨንቅም የሚያስደነግጥም ምልክት
This action should strongly be denounced. The parties administering their respective regional states might have agreed on terms [for evictions] but it is wrong regardless of the reasons for the uprooting of these citizens of Ethiopia. It is alarming as well to know Ethiopian citizens’ rights to movement in their country is decided by political party officials.
Abraha Desta, an activist based in Tigray, Ethiopia identified [amh] three reasons for activists to support the Amhara people:
ሰዎች ከቀያቸው በሃይል (በግፍ በዘርሓረጋቸው እየተለዩ) ሲፈናቀሉ (ሲባረሩ) የከፋ የሰብኣዊ መብት ጥሰት ነው። ዜጎቻችን (ወገኖቻችን) ሲፈናቀሉ የሚደርሳቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና ስነልቦናዊ ቀውስ (Helplessness) መገመት ኣይከብድም። ሁሉም ኢትዮዽያ ሊተባበራቸው ይገባል፤ መንግስት ይህን ተግባሩ እንዲያቆም ተፅዕኖ ማድረግ ኣለብን።
እኛም እየተፈናቀሉ ካሉ ሰዎች ጎን መሰለፍ ያለብን ይመስለኛል። ምክንያቱም (1) ወገኖቻችን ናቸው። እኛ ኢትዮዽያውያን ያልደረስንላቸው ማን መጥቶ ይረዳቸዋል? (2) ዛሬ በኣማራ ተወላጆች እየተፈፀመ ያለው ግፍ (ኣሁንኑ ካልቆመ) ነገ በእያንዳንዳችን እንደሚፈፀም ማወቅ ይኖርብናል። (3) የማፈናቀል ተግባሩ የብሄር ፖለቲካ ችግር ኣባብሶ የጥላቻ ፖለቲካ ስር ሰዶ የኢትዮዽያ ሀገራችን ኣንድነት የሚፈታተን ይሆናል።
The following should be our reasons to stand by the sides of our fellow citizens: 1) The people are Ethiopians, so if we are not standing by their side who is going to support them? 2) If what happens to the Amharas does not stop here by now we should know that tomorrow it is going to happen to everyone. 3) These acts might inflame ethnic politics which might turn into hate politics that will jeopardize the integrity of Ethiopia.
However, Mesfin Negash warned [amh] that these acts should not be taken as acts of a certain ethnic group against another ethnic group but rather acts of people who don’t have any sense of decency:
የዛሬ አፈናቃዮች በብሔረሰብ ካባ ለመደበቅ ቢሞክሩም ሕግ ፊት የሚቀርቡበት ቀን እንደሚመጣ አምናለሁ። ተፈናቃዮዩቹ በሙሉ የአማራ ብሔር ተወላጆች ቢሆኑም አፈናቃዩ ወገን ግን የየትኛውም ብሔር ወኪል እንዳልሆነ እናስታውስ፤ አደራ። ግፈኞቹ፣ መዝባሪዎቹ፣ ወሮበሎቹ፣ ሆድ አደሮቹና ዘረኞቹ አፈናቃዮች ብሔራቸው “ነውር” ነው። ነውረኞች።
Today’s culprits of these mass evictions are trying to paint their acts and hide under ethnicity, but I believe a day shall come when these people will stand before a court of law. Though the evictees are Amharas, we should believe the perpetrators are not representatives of a certain ethnic group. Please be reminded that the ethnicity of wrong doers, looters and racists is indecency!
 Source- http://globalvoicesonline.org/2013/04/11/ethiopia-accused-of-ethnic-cleansing-over-mass-amhara-evictions/ 

Wednesday, April 10, 2013

ሕግ አለማወቅ በሕግ ከመጠየቅ የማያድን ከሆነ ሕግ እያወቀ ያጠፋውስ ላይ ቅጣቱ እንዴት አይከብድ?


ባለፈው ጊዜ በፈስቡክ ገፄ ላይ '' 'ሪፖርተር ጋዜጣ'  ስለ ቤንሻንጉል መፈናቀል አልስማም ይሆንን? ዜናው አዲስ አበባ አልደረሰ ይሆን?''እያልኩ ስጨነቅ  ሪፖርተር በዛሬው ሮብ ሚያዝያ 2/2005 እትሙ ቤንሻንጉል ተፈናቃዮችን ''በቃ ተዉት ኑ  ተብሏል'' የሚል መሰል ዜና  አስነብቧል።እኔ ደግሞ የእራት መብያዬ ሰአትን ግማሹን ለ ኢቲቪ ቀሪውን ለኢሣት አድርጌ መንግስት ስለጉዳዩ መግለጫ ይሰጣል ብዬ መጠበቄ ቆጨኝ።

ምክንያቱም  ኢቲቪም ፈርቶ ይሁን አፍሮ አይታወቅም ምንም አላለም።በ 1997 ዓም  ''ድምፄ ተነጠቀ'' ብሎ የአዲስ አበባ ሕዝብ ለተቃውሞ ሲወጣ መንግስት መጀመርያ ያደረገው ጉዳዩ ብሔራዊ ጉዳይ ላለማስመሰል ለፀጥታው ችግር (በከተማዋ ከንቲባ ደረጃ ያለ ችግር ይመስል) በየሰዓቱ  ዜና የሚያነቡት ኤፌም ራድዮኖች  አቶ አርከበን ብቻ እንዲጠይቁ ተደረጉ።ሰዓቱ እይረፈደ ሲመጣ መስርያቤቶች መዘጋታቸው ታወቀ። ከምሳ በኃላ ''ምነው እንትና'' አለ እና የፈድራል ፖሊስ መግለጫውን ገባበት።
አሁንም  ቤንሻንጉል ''ሂዱ! ውጡ!'' ብሎ በሺ የሚቆጠር ሕዝብ በስለት፣በጥይት ወዘተ እየተሳደደ፣ አራስ መንገድ ላይ እየወለደች፣ ሕፃናት ትምህርታቸውን ጥለው ከወላጆቻቸው ተለያይተው በየጫካው ውስጥ ሲንከራተቱ፣አብያተ ክርስታያናት ተዘግተው ካህናት ቁልፍ አምጡ ተብለው ሲደበደቡ እና ሲታሰሩ ያልሰማው መንግስት  ዛሬ ቤንሻንጉል ክልል ስም  ''ኑ ተብሏል''። ብሎ መናገሩ እና በመኪና እየጫነ በግድ መውሰድ መጀመሩ ተሰምቷል።አንዳንዶች ወዴት እንደሚወሰዱ ገና አልታወቀም እያሉ መሆኑ ሳይዘነጋ።ለነገሩ ዛሬ ተፈናቃዮቹ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ የነበረ መሆኑ እና የአለምአቀፍ የኢትዮጵያን ቁጣ ከመቼውም ጊዜ በላይ ማየሉ ሁኔታውን ቶሎ የማድበስበስ ሥራ ለመስራት መንግስት እንዲያስብ ሳያደርገው አልቀረም። ስለዚህም ''ሲፋጅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ'' የሚለውን አባባል  መንግስት ሥራ ላይ ለማዋል የተገደደ መስሏል።ይሄውም የህዝብ ሃሳብ በሌላ ነገር ሲጠመድ ሰይጣናዊ ሥራ መስራት ሕዝብ በአንድላይ ሲቆጣ ከነገር አለሙ መለስ ማለት።

በእጅም ሆነ በማንኪያ ይህ ሁሉ የመንግስት ተግባር  የሚያመለክተው አንድ እና አንድ ነገር ብቻ ነው።ኢትዮጵያ 'መከፋፈሏን' ያወቀ የተረዳ ግን ይህንን የሚያበረታታ መንግስት እንዳለን።ለእዚህም ከሰሞኑ ክስተት በተጨማሪ ያለፉት ሁለት ወራትን ሶስት ክስተቶች መመልከት ይቻላል።እነርሱም -
-ባለፈው በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የ ኦሮምኛ ተናጋሪ ተማሪዎች ''የኦሮሞ ተወላጅ በመሆናችን ብቻ ተቃዋሚ ናችሁ ተብለን ካለትራንስክሪፕት ተባረርን በየቶቦው ውስጥ ነው ይምንተኛው'' ማለታቸው ጆሮ ዳባ ልበሱ መባላቸው፣

- ጅጅጋ ዛሬ የሱማሌ ክፍል ነች ወይስ የኢትዮጵያ? እስኪባል ድረስ እስካሁን ከየት እንደመጡ በማይታወቁ የሚሊሻ ኃይል ስትተዳደር እና ማንኛውም አማርኛ ተናጋሪ ብቻ ሳይሆን የጉራግኛ ትግርኛ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሳይቀር እየተሳቀቀ የሚኖርባት መሆኗ እንድያውም የአማርኛ ተናጋሪዎች ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ የኖሩበትን የግል ቤት ካለምንም ካሳ መነጠቃቸው እና  

- ዜጋ በሀገሩ ላይ ለፋሺሽቱ ግራዝያኒ የተሰራውን ሃውልት መቃወም ኢህአዴግን መቃወም የሆነበት እና ህዝቡ በታክሲ ውስጥ ሳይቀር የግራዝያኒን ሃውልት ተቃውሞ መናገር የፈራበት ሁኔታ በቂ ማስረጃዎች ናቸው።

ለእዚህ ሁሉ ግን መልሱን ልብ አላለው ካልሆነ በስተቀር  ''ሪፖርተር ጋዜጣ'' እራሱ የመለሰው ይመስለኛል።በጋዜጣው ፀሐፊ ጌታሁን ወርቁ በ መጋቢት 29/2005 የተፃፈው ''

''ሕግን አለማወቅ ይቅርታ አያሰጥም'' በሚል አርዕስት ስር እንዲህ የሚል ይገኝበታል።

''ይህ አነጋገር (Maxim) በሕግ ሙያ ከተለመዱት መርሆች ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡ በሁሉም የሕግ ሥርዓት ውስጥ ለዘመናት ታውቆ የኖረ፣ የሚፈጸምም ነው፡፡ በሕግ ሙያ ከተለመዱ ጽንሰ ሐሳቦች ውስጥ በብዛት በኅበረተሰቡ ውስጥ የሚታወቅም መርህ ነው፡፡ ትርጉሙ ግልጽ ነው፡፡
አንድ ሰው ሕጉን ሳያውቅ በፈጸመው ጥሰት ተጠያቂነቱ አይቀርለትም፡፡ ጥፋት ያጠፋ ሰው ‹‹ሕጉን አላውቀውም›› ብሎ ሊከላከል አይችልም ማለት ነው፡፡ ጋሪ ስላፐር የተባለ እንግሊዛዊ የሕግ ባለሙያ፣ መርሁን ሲገልጽ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ሕግን አለማወቅ ይቅርታ አያሰጥም›› ማለት፣ ‹‹ለምሳሌ አንተ ከአንድ ሰው ጋር የነበረህን የውል ግዴታ ሳታከብር ስትቀር ወይም የመንጃ ፈቃድ ሳይኖርህ መኪና ስትነዳ፣ የሠራኸው ሥራ በሕግ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ባታውቅም ክስ ይመሠረትብሃል፤ በወንጀል ከሆነ ደግሞ በዓቃቤ ሕግ ትከሰሳለህ ማለት ነው፡፡›› በዚህ መርህ መሠረት በአገሪቱ የወጡትን ሕግጋት በሙሉ፣ ዜጎች ወይም በአገሪቱ የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ ያውቁታል ተብሎ ግምት ይወሰዳል፡፡ 
--------------ከዚህ በላይ በጽንሰ ሐሳብ ትንታኔው የተገለጸው ከሞላ ጎደል በአገራችንም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ሕጉ ማንኛውም ዜጋ/አገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ የኢትዮጵያን ሕግጋትን ያውቃል የሚል ግምት ይወስዳል፡፡ የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 3/1987 በአንቀጽ 3 ‹‹ማናቸውም የፌዴራል ወይም የክልል ሕግ አውጭ፣ አስፈጻሚ እና ተርጓሚ እንዲሁም ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል፣ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የሚወጣ ሕግን የመቀበል ግዴታ ይኖርበታል፤›› በማለት ሕግን ማወቅና መቀበል በግዴታ መልክ አስቀምጧል፡፡ ይህን የመቀበል ድንጋጌ በመተላለፍ ሕጉን አለማወቅም ሆነ አለመቀበል በማያውቀው/ባልተቀበለው ሰው ላይ ያለውን ተፈጻሚነት አያስቀረውም፡፡ ስለዚህ ማንኛውም በነጋሪት ጋዜጣ የወጣን ሕግ ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ያውቃል፣ ተቀብሎታል የሚል የሕግ ግምት መኖሩን ልብ ማለት ይገባል፡፡ 
ከዚህ ሌላ በፍትሐ ብሔርም ሆነ በወንጀል ‹‹ሕግን አለማወቅ ይቅርታ አያሰጥም›› የሚለው መርህ ተካትቶ እናገኛለን፡፡ መርሁ በፍትሐ ብሔር ሕጉ ‹‹ከውል ውጭ ኃላፊነት›› በሚለው ክፍል የሚገኝ ነው፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2035 ‹‹አንድ ሰው በሕግ ላይ በትክክል ተገልጾ የተመለከተውን ልዩ ድንጋጌ፣ ልዩ ደንብና፣ ሥርዓት የጣሰ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው›› በማለት በንዑስ ቁጥር አንድ ደንግጓል፡፡ በንዑስ ቁጥር ሁለት ደግሞ ‹‹ሕግን አለማወቅ ይቅርታ ሊያስገኝ አይችልም›› በማለት መርሁን ያለምንም ልዩ ሁኔታ ደንግጓል፡፡ '' ይላል።

አሁን ባለው የሀገሪቱ ሕግ ''ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ግለሰብ በፈቀደበት ቦታ የመኖር እና ሀብት የማፍራት ሙሉ መብት አለው'' ይላል።እናም በሀገራችን የዘር ፖለቲካ የሚያራምዱ ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ሃገርን ከጥፋት ህዝብን ከስደት ያድናል። ''ሲፋጅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ'' ግን ለሀገሪቱ ችግር መፍትሄ አይሆንም።ሕግ አለማወቅ በሕግ ከመጠየቅ የማያድን ከሆነ ሕግ እያወቀ ያጠፋውስ ላይ ቅጣቱ እንዴት አይከብድ?


አበቃሁ 

ጌታቸው በቀለ 


ኦስሎ

Monday, April 8, 2013

ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?

''ጎዳና ቤቴ'


ሰኔ 25/2012 እአአቆጣጠር  በቢቢሲ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ አንድ ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በአመት 5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ አሜሪካ  ብቻ እንደሚሄዱ  እና አሜሪካ ከዓለም ላይ በማደጎነት ከምትወስደው ሕፃናት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ከ አምስቱ አንዱ እንደሆኑይገልፃል።(http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474)
አዲስ አበባ ብቻ ዛሬ ከ አንድ መቶ ሺህ በላይ መግብያ ያጡ ''ጎዳና ቤቴ'' ብለው አንቅልፍ በጣላቸው ቦታ ክልውስ ብለው የሚተኙ ሕፃናት ይኖሩባታል።ይህ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ግዴለሽነት የመነጨ እንጂ ከድህነታችን ብቻ የሚመስለው ካለ ለመሳሳቱ እማኝ ላቅርብ። 

ሕፃናት አሳዳጊ የሚያጡት ባብዛኛው የርስበርስ ጦርነት ሲኖር ወይንም ሰላም በተናጋበት ጊዜ ነው።ኢትዮጵያ ግን ጎዳና የወጡት ሕፃናቶቿ የበዙት በአንፃሩም ቢሆን ጦርነቱ ከቆመ ጊዜ ጀምሮ ነው ለምን? 

በ 1969 ዓም በዚያድባሬ ሱማሌ ወረራ ሳቢያ ብዙ ሕፃናት አባት እናታቸውን አጡ።ሀገሪቱ በወቅቱ ገንዘብ የላትም።ምዕራባውያን ፊታቸውን አዙረውባት ነበር።ግን ሕፃናት ጎዳና አልተጣሉም ይልቁንም ኃላፊነት የተሰማቸው ኮለኔል መንግስቱ በ 16 ወራት ውስጥ የሕፃናት አምባ እንዲገነባ አድርገው በአንድ ጊዜ ከአምስት ሺህ ሕፃናት በላይ የሚይዝ ትልቅ የሕፃናት ማሳደግያ በአፍሪካ በግዙፍነቱ (በውቅቱ) እና በአቅሙ ቀዳሚ  ሆኖ ተገንብቷል። ኢህአዲግ መንግስት ከሆነበት ጊዜ  ጀምሮ ሲያዳክመው ቆይቶ በ 1990 ዓም ተዘጋ። ኢህአዲግ ወያኔ የነበረውን አስፋፍቶ ሕፃናትን ከጎዳና ኑሮ ከማዳን ይልቅ ሕፃናትን በማደጎነት እየሸጠ በአንድ ሕፃን በትንሹ 25ሺህ ዶላር መሰብሰብ እና ወደኪሱ  ማስገባቱን መረጠ።

ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?


ዛሬ ኮለኔል መንግስቱ እንደጀመሩት ቢቀጥል ኖሮ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሕፃናት በተማሩበት እና ከጎዳና ኑሮ በዳኑበት ነበር። ሃቁ ይህ ነው።አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ የተሰቀለው ቢል ቦርድ እና ኢቲቪ በአቶ መለስ የሞቱ ሰሞን ከዜና አንባቢው ጀርባ አቶ በለስ ጣታቸውን ወደ ሕፃናት ሲዘረጉ ያሳያል።ግን  እንዴት ነው አቶ መለስ የኢትዮጵያ ሕፃናት አባት የሚባሉት? በምን መስፈርት? ሕፃናቱን ጎዳና ወድቀው እሳቸው በሚያልፉበት መንገድ በወታደሮቻቸው ስለገፏቸው ነው?ወይንስ የሕፃናት አምባን ስለዘጉላቸው? ነው ወይንስ በአስር ሺዎች በማያውቁት ባእዳን እጅ እንዲያድጉ ስለሸጧቸው። 'መሸጥ' የሚለው ቃል ለቀረበው ዕቃ ወይም ሰው አልያም ሕፃናት ገንዘብ ከፍሎ ሕፃኑን መውሰድ የሚለውን ትርጉም እስከያዘ ድረስ መሸጥ ከሚለው ቃል የትሻለ ሊገኝ አይችልም።

ቅዳሜ ጧት 


ከአምስት አመት በፊት በ 2001ዓም አንድ ቅዳሜ ጧት ወደ ዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም 45 ሰዎችን አሳፍሮ አንድ መለስተኛ አውቶቡስ መመናንን ይዞ መንገድ ላይ ነበር።በመንገድ ላይ በእድሜ ጎልማሳ ካህን ስለገዳሙ ታሪክ ይናገራሉ።በአንክሮ በመገረም ነበር የምንሰማው።እውነተኛ ታሪኩ ይህ ነበር።

'' አቡነጎርጎርዮስ የዝዋይ ገዳም መስራች አንድቀን የመንፈስ ልጆቻቸውን እያስተማሩ ኮለኔል  መንግስቱ ከአዋሳ ሲመጡ ጎራ ይላሉ።ወደ ገዳሙ ውስጥ ሳይገቡ ገና አጥሩን ሲመለከቱ በረጅሙ ታጥሮ ይመለከቱ እና 'ይሄ መነኩሴ ይህን ይህል ቦታ አጥሮ አገሩ ታድያ ምን ተረፈ' ይሉ እና አንዱን ወታደር አቡነ ጎርጎርዮስን እንዲጠራቸው ይልኩታል። አቡነ ጎርጎርዮስ መልክቱ እንደደረሳቸው 'አሁን ትምህርት ላይ ነኝ ደግሞስ ፈላጊ ይመጣል እንጂ ተፈላጊ እንዴት ይሄዳል?' ብለህ ንገረው ብለው መልሰው ይልካሉ።ኮለኔል መንግስቱ እንዲህ አይነት ድፍረት በመስማታቸው ምንም ሳይሉ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ። በቀጣዩ ቀናት አቡነ ጎርጎርዮስ ኮለኔል መንግስቱን ቅሬታቸውን ለመንገር ይመጣሉ።ቅሬታቸው ሌላ ነበር።እንደገቡ አቡነ ጎርጎርዮስ በቁጣ ''ለመሆኑ ሕፃናት አምባ የምታሳድጋቸው ልጆች አምላካቸውን ካላወቁ አውሬ እንደሚሆኑ ታውቃለህ?'' ይሉታል ይደነግጣል። ''ምን ይደረግ?'' ይላቸዋል።''ለእኔ ፍቀድልኝ እኔ የማደርገውን አውቃለሁ '' ይሉታል። ከድጋፍ ደብዳቤ ጋር ይልካቸዋል።

አቡነ ጎርጎርዮስ በህፃናት አምባ ውስጥ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት አስይዘው በግቢው ውስጥ ለሕፃናቱ ቤተክርስቲያን ሰሩላቸው።ብዙ በስነምግባራቸው የታነፁ ሕፃናትን አፈሩ። በቀን በሚልዮን ብር ለጦርነት ታወጣ የነበረች ሀገር እንዲህ ልጆቿን ታሳድግ ነበር። ዛሬ የጎዳና ተዳዳሪ ሲበዛ መንግስት ኃላፊነት አይወስድም።ሕፃናቱን ለመሸጥ ግን ቢሮዎችን በየቦታው ባእዳን እንዲከፍቱ አርጎ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ አደረጋቸው። ቢቢሲ ከላይ በጠቀስኩት ቀን ላይ ባወጣው ዘገባ ላይ እንዲህ ይላል።
''International adoption is big business in Ethiopia and the country accounts for almost one in five international adoptions in the US, but how ethical is the process?'' http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474
''በኢትዮጵያ የማደጎ ሕፃናትን ወደውጭ መላክ የንግድ ሥራ ሆኗል።ይህም ወደአሜሪካ ከመላው አለም ከሚገቡት ውስጥ ከአምስቱ አንዱን እጅ ይይዛሉ።ነገር ግን ይህ እንዴት ሞራላዊ ሂደት ሊሆን ይችላል?'' በማለት ይጠይቃል። እውነት እንዴት ሞራላዊ ሂደት ሊሆን ይችላል?

ግን ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?
ይህንን በ ኮለኔል  መንግስቱ የተመሰረተውን ታሪካዊ የሕፃናት አምባ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፊልም ይመልከቱ እና ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት ስጠን በሉ።




Wach more videos on HITSANAT AMBA, click here below-
http://www.youtube.com/watch?v=66E-SVBAHVQ&list=FL5-Q4rqKJcqt17I0hTS4Nwg






አበቃሁ 
ጌታቸው 
ኦስሎ 

Friday, April 5, 2013

የኢትዮጵያ የተቃዋሚ አንድነት ኃይሎችን ወደ አንድ ግንባርነት የሚወስዷቸው ግን የዘነጓቸው ሶስቱ ኃይሎች



አሁን ያለንበት ጊዜ የ ኢትዮጵያ የትግል አቅጣጫ መቀየርያ (turning point) ላይ ያለን ይመስለኛል።ብዙ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አሉ።ሁሉም ግን የሳቷቸው ወይንም  ዋጋ ያልሰጧቸው ሶስት ኃይሎች ይታዩኛል። እነርሱም የዘውድ ምክር ቤት፣ የደርግ የሰራውትም ሆነ የምሁራን እምቅ ኃይል እና ወያኔን ትተው የወጡ ወደ አንድነት ትግሉ መቀላቀላቸውን ያወጁ የቀድሞ የወያኔ አባላት ናቸው።

 እነኝህ ኃይሎች ለዛሬዋም ሆነ ለነገዋ ኢትዮጵያ ላይ የሚኖራቸው አንደምታ ቀላል አይደለም።በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ታሪክ አካል በበጎም ሆነ በክፉ ሆነዋልና።በሌላ በኩል የተቃዋሚ የአንድነት ኃይሎች በአብዛኛው የተመሰረቱበት አላማ (በጣም ከጥቂቶቹ በስተቀር)  ባለፈ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ክስተት ላይ መነሻ ያደረጉ ናቸው። ታሪክን በመማርያነት መጠቀም ጥሩ ነው በዛሬ ትውልድ ላይ ግን ስላለፈው መፍረድ ሌላ ጉዳይ ነው።በየትኛውም የአለም ክፍል የሚገኝ ሀገር በታሪኩ አሳዛኝም  ሆነ አስደሳችም ኩነቶችን ያልፋል።ያንን ግን ለዛሬው ክስተት እንደ እንቅፋት አይመለከትም።ይልቁን በጋራ የምያስማሙት ነጥቦች ብቻ ይተኮርባቸውና እነርሱን አጉልቶ ለነገ ማቀድ ነው ዋጋ የሚሰጠው።
 በ ኢትዮጵያ አንድነት በሚያምኑ ወገኖች (በብሄር እና በጎጥ መከፋፈልን በማይደግፉ ወገኖች  ዘንድ ሁሉ) የሚያስማሙ ነገሮች  አሉ።

ይሄውም-
- የወያኔን ዘረኛ መንግስት መጣል፣
- የኢትዮጵያውያንን አንድነት የሚጠብቅ መንግስት ማምጣት፣
- የእያንዳንዱ ግለሰብ መብት በሕግ ጥላ ስር ዋስትና ያገኘ እንዲሆን ማረግ፣
- ለእዚህም ኢትዮጵያዊ የሆነ የህዝቡን አንድነት፣ሉዓላዊነት እና ክብር የሚያከብር ነፃ የሚድያ ተቋም መኖር፣ 
- ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያነት ማስቀጠል እና 
- ባላት የሰው እና የተፈጥሮ ሀብት ሀገሪቱን ማበልፀግ የሚሉት እና የመሳሰሉት  የሚጠቀሱ ናቸው።

በአንጻሩ ወያኔ ከስልጣኑ የሚገፋውን ማንኛውንም ኃይል የሚዋጋበት ብቸኛ መንገድ የዘር ፖለቲካ ማራመድ ነው። የዘር ፖለቲካ በ አሁኗ ኢትዮጵያ እጅግ አደገኛ ካርድ ከመሆኑም በላይ ወያኔ ከስልጣኑ በላይ የሚመለከተው ነገር ስለሌለ እንጂ ጦሱ እንደማይቀርለት ይረዳዋል ባይረዳውም አይቀርም።ነገር ግን ስለ ሶስት ምክንያቶች የዘር ፖለቲካን ያራግባል።እነርሱም-

1- የሚያሳምንበት ምንም አይነት የርዮት አለም መመርያ  ስለሌለው፣

2- ከ አፈጣጠሩ ዘረኛ ተፈጥሮ ስላለው እና በጥላቻ ስላደገ እና 

2- በውስጡ የተሰገሰጉ የኢትዮጵያ ጠላቶች እጅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስልጣኑን  ስለሚዘውሩትም ጭምር ነው።

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የአንድነት ኃይሎች አዲስ ራዕይ አስፈላጊነት


የፖለቲካ ድርጅቶች አዲስ ራእይ ይዘው መቅረብ የመቻል እና ትግሉን በዘለቄታ ለመምራት  መሰረታዊውን  የኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይን ትልቅ ራዕይ አድርገው ሊያነሱት የሚገባ ኃይል መሆኑን አሁንም መረዳት ተገቢ ነው። ይህንንማ ብዙ አመት ተቃዋሚዎች ሲናገሩት የኖሩት አይደለም እንዴ ? የሚል ጠያቂ ሊኖር እንደሚችል እገምታለሁ።ነገር ግን እኔ እንደምረዳው ከፕሮግራሙ ባለፈ የስልታዊ አፈፃፀም መሰረታዊ ችግር በአንድነት ኃሎች በኩል ይስተዋላል። 

ወያኔ በቀደሙ የታሪክ ሂደቶች ላይ ቀድሞ የሰራው ፕሮፓጋንዳ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ላይ በእራሱ የ ስነልቦና ችግር ፈጥሮባቸዋል። ለምሳሌ የተቃዋሚ የአንድነት ኃይሎች ስለ ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ እና ስለ ደርግ በኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ ስለነበራቸውን አስተሳሰብ እና ለአሁኑ ትውልድ ሊያስተምሩ የሚችሉ ተግባራት ላይ ማተኮራቸው የሚያስከፉት የህብረተሰብ ክፍል ይኖራል ብለው ስለሚያስቡ ባለፉ ታላላቅ ነገር ግን አሁን ሊያስማሙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ማውራት ያፍራሉ። በመሆኑም የወያኔን ግፍ እና አደጋ በማውራት(ማውራቱ ተገቢ ቢሆንም) ብዙ ገለፃቸውን ያጠፋሉ። ወያኔ ግን አሁን ከሚያደርገው ሥራ የበለጠ አደጋው ባለፈ የሀገሪቱ ታሪክ ላይ ያልተስማማ የባዕድ አስተሳሰብ ይዞ የመጣ ለኢትዮጵያ ህዝብም  እንግዳ ለሕዝቡ ባዳ የሆነ የታሪክ ቀረፃ ላይ መሆኑን ይዘነጉታል።

በመጀመርያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ጋር የማይስማማው አሁን ባለው የወያኔ አፋኝ ስርዓት ብቻ አደለም ወያኔ ኢትዮጵያን አፍርሶ በሚፈልገው ድቡሽት ፅንሰ ሃሳቡ ላይ ኢትዮጵያን ሊሰራት የሚታትር ''ደፋርም'' ስለሆነ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ የዛሬ ድልድይ እና መንገድ መሰራት ጉዳይ አይደለም። የተሰራውም ሆነ ወደፊት የሚሰራው ሥራ ሁሉ ለመጪው ትውልድ የመቆየቱ እና አስተማማኝ አብሮ የመኖር ዋስትናውን ነው ጉዳዬ ነው ፋይዳዬ ነው የሚለው።ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው። የዕለት ከዕለት ጉርሻውን እያመሰገነ የሚኖር እንስሳዊ ባህሪ ሰው ከፈጣሪው ገና አልታደለም(መታደል ባይሆንም)።

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ የመሆን እና የተቋማዊ ህብረት ብቻውን ኢትዮጵያን አይሰራትም።በታሪካዊ ሁነቶች ላይ የመነጋገር ባለፉ ስህተቶች መንቀስ እና ለሀገር አንድነት፣ለሕዝብ ልዕልና እና እድገት ለተሰሩ ስራዎች እና ለሰሩት  ግለሰቦች ዋጋ በመስጠት ግን የህዝብን አንድነት ማምጣት እና ወያኔን ባዶ ማስቀረት ይቻላል።

 የኢትዮጵያ የተቃዋሚ አንድነት ኃይሎች እንዴት ያስቡ?


በመጀመርያ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲም  ሆነ ለኢትዮጵያ እሰራለሁ የሀገሬ  ጉዳይ ያሳስበኛል ያለ ዜጋ በሙሉ  ሶስት ነገሮችን መመርያው ማድረግ አለበት።እነርሱም-

1ኛ/ የአርበኝነት(patriotic feeling) ስሜት ማስፈን

  
አርበኛ (patriotic) የሚለው ቃል ለጦር ሜዳ ውሎ የተሰጠ ብቻ አይደለም። ነገር ግን ለሀገራቸው ካለ አንዳች ዋጋ፣ዝና መፈለግ እና የግል ስሜትን ውጦ ለጋራ እና ለሀገር በነፃ የመስራት ክቡር ተግባር ነው።

ለሀገሩ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ግዴታው ስለሆነ ብቻ እንደሚያደርግ ማሰብ እና ነገ በምትኖረው ኢትዮጵያ የእያንዳንዱ ዜጋ በሕግ ጥላ ስር ዋስትና ማግኘትን፣የኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና አንድነት የመከበርን ፋይዳ እንጂ  ለግሉ ከነፃነት በኃላ ባገኘው የስራ መስክ ለመስራት እና በነፃነት ለመሞት ብቻ ማለም ማለት ነው። 

ነገ ኢትዮጵያ በተሻለ ደረጃ ስትሆን የአርበኛ ስሜት የተጋራ የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ዜጋ በጥረቱ ብቻ ለመስራት ዛሬ ላይ ሆኖ የወሰነ ሊሆን ይገባል። ብዙ ችግሮች በተለይ በ ፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል በሚሉ  ዘንድ የሚስተዋለው ነገ ዛሬ ላደረጉት ተግባር እንዲከፈል የመፈለግ እና ሁኔታዎችን የማመቻቸት ሂደቶች ናቸው። ይህ ሁሉንም ይመለከታል ባልልም ሆኖም ግን አንዳንዴ አከራካሪ ሆነው የሚቀርቡት ነጥቦች ለምሳሌ ''እኛ ከእዚህ አመት ጀምሮ ስንታገል፣እንዲህ አድርገን፣ይሄን ፈጥረን '' ወዘተ የሚሉ መግለጫዎች ከአሁኑ ትግል ጋር ተያያዥነት የሌላቸው ወደፊት ምናልባት አዲስ አበባ ሲገቡ ትልቅ ሙዜም ሰርተው ሊያስቀምጡት የሚገባውን ጉዳይ ከመሆን ባለፈ ዛሬ ከሌላው ጋር የመጋጫ ነጥብ አድርጎ ማቅረብ ከሞራል የወረደ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ምድር ያልተፈጠሩም ያስመስላል።በመሆኑም በመጀመርያ የአርበኝነት ስሜት (ዋጋ የማይጠየቅበት ሥራ) ማስፈን ተገቢ ነው።

2ኛ/ ኢትዮጵያን እንደሀገር በሚያስቀጥሉ ጉዳዮች ላይ መጀመርያ መስማማት።

ኢትዮጵያን የማዳን ሥራ ላይ የሚያስብ ድርጅትም ሆነ ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰብ ወይንም ቡድን በመሰራታዊው የ ኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ፣በሕዝቡ ህብረት፣በሕግ የበላይነት የሚያምን ወይንም ለማመን ዝግጁ ነኝ ካለ ማንኛውም አካል ጋር (ከድያብሎስ በስተቀር እርሱ ቃሉ ስለማይታመን) አብሮ ለ መስራት መዘጋጀት አለበት።
እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባን በ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ሜዳ ላይ ሶስት የታሪክ አካላት ወሳኝ ሆነው ላለፉት አንድ መቶ --/ . . . አመታት ዘልቀዋል። 
. የዘውድ ስርዓት፣ 
. የደርግ ስርዓት  እና 
. አሁን ስልጣን ላይ ያለው የወያኔ ስርዓት ናቸው። 

በሶስቱም ስርዓቶች ውስጥ ዛሬ የምንጮህለት የኢትዮጵያ አንድነት እና የ ዲሞክራሲ ሂደት የሚደግፉ ለትግሉ ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው ኃይሎች አሉ።ነገር ግን በተለያየ ጊዜ የተለያየ ስም ስለተሰጣቸው የሚሰማቸውም ሆነ ከፍተኛ ልምዳቸውን የሚጠቀም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ቡድን የለም። ይልቁን ካለፈ የታሪክ ሂደት ጋር የእራሱን ስም የሚያጎድፍ ስለሚመስለው እና በተለይ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ (በሁሉም ላይ የከፈተው የማጥላላት ዘመቻው) በከፊል ስለተሳካለት እነኚህን የታሪክ አካላት ዛሬ ድረስ የሚያፍሯቸው በዝተው ወያኔ ግን ለግሉ እንዲጠቀምባቸው ተትቶለታል።

በሶስት የታሪክ ሁነቶች የተፈጠሩት ኃይሎች የማቀናጀቱ ሥራ ወያኔን በ አጭር ጊዜ ያፍረከርከዋል

በኢትዮጵያ ሕዝብ አስተሳሰብም ሆነ የፖለቲካ መድረክ ላይ በሶስት የታሪክ ሁነቶች የተፈጠሩት ኃይሎች ማለትም የዘውድ መንግስት፣የደርግ ኃይል እና ከወያኔ ያፈነገጡ (የኢትዮጵያን አንድነት ዘግይተውም ቢሆን ያመኑ) ኃይሎችን የማቀናጀቱ ሥራ ወያኔን በ አጭር ጊዜ ያፍረከርከዋል። የኢትዮጵያንም ትንሣኤ ያመጣል።አሁን ማሰብ የሚገባው በፓርቲ እና በድርጅት ስሜት መሆን እንደማይገባው ነገር ግን በአርበኝነት (patriotic) ስሜት መሆን እንዳለበት ከላይ ለመግለፅ ሞክርያለሁ።የአርበኝነት ስሜት ሲባል ደግሞ በስሙ የተደራጁ ድርጅቶችን(እንደ አርበኞች ግንባርን) መጥቀሴ ሳይሆን የቃሉን ለሀገራዊ ፍቅር ካለአንዳች ዋጋ የሚስራ ሥራን ለመግለጫነት መጠቀሜን ልብ ይባልልኝ ። የአርበኝነት ስሜት መለክያዎቹ ኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያ ወዳጅ መሆን ብቻ ናቸው። አባቶቻችን ኢትዮጵያን የጠበቁት ደሞዝ ይከፈለኝ፣ዋጋ ይሰጠኝ፣ዝና ላትርፍበት ብለው ሳይሆን ካለዋጋ ከልብ በመነጨ ሃገራዊ ፍቅር ብቻ ነው። 
ለእዚህም ነው ከላይ የጠቀሱት ሶስቱ ኃይሉችን   ቢያንስ በሶስት ጉዳዮች ላይ የሚያስታርቁ ነጥቦች ላይ እስከተስማሙ ድረስ የኢትዮጵያን የማዳን ተግባር አካል አድርጎ የመስራት ሥራ አስፈላጊ የሚያደርገው። እነርሱም-

1/ በኢትዮጵያ ባለፈ በጎም ሆነ በጎ ያልሆኑ ታሪኮች፣

2/ በ ኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ላይ እና 

3/ ዜጎች በዘር እና በቋንቋ ሳይሆን በሰውነታቸው ብቻ በሕግ ጥላ የመጠ በቃቸው ሂደት የሚሉት ናቸው።

ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ

ይህ ማለት በዲሞክራስያዊ ዘውድ መንግስት የሚያምኑም ሆኑ በደርግ ስርዓት ውስጥ ለኢትዮጵያ አንድነት የታገሉ የጦር ሰራዊት፣ ምሁራን ወዘት እንዲሁም የወያኔን ስርዓት አላማ የተቃወሙ የቀድሞ የድርጅቱ አባላት ሁሉ ከላይ በተጠቀሱት ሶስት ነጥቦች እስካመኑ ድረስ ለአንድነት ትግሉ አስተዋፅኦ የማያደርጉበት ምንም ምክንያት የለም። ይህ ግን በአንድነት ኃይሎች አንፃር ያለፈ ታሪክን እየመዘዙ እንደወያኔ መውቀስ አቁመው አሁን አንገብጋቢው ጥያቄ ሀገር ን የማዳን ብቻ እና ብቻ መሆኑን ማመን ይገባቸዋል።በእዚህ ስሜት ሕዝቡን በሙሉ ለማግኘትም ሆነ ከጎሰኝነት የፀዳ በኢትዮጵያዊነት ርዕዮት ላይ የተመሰረተ ህብረት መፍጠር ይቻላል።
ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም 


የደርግ ከፍተኛ አባላት በፍርድ ቤት ውስጥ

''የኢትዮጵያ ችግር እግሩ ሀገርቤት ቢሆንም እራሱ ግን ከውጭ አለ'

እዚህ ላይ ''የኢትዮጵያ ችግር እግሩ ሀገርቤት ቢሆንም እራሱ ግን ከውጭ አለ'' የሚለውን አባባል ማጣጣል አይገባም።ከጉያችን የወጡ በዘር እና በሃይማኖት ለመከፋፈል ይታትሩ  እንጂ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በኢትዮጵያ ላይ ስትራተጃዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ብሎም እንደሀገር እንዳትቆም የሚተጉ ባእዳን ግለሰቦችም ሆኑ ሃገራት መኖራቸው ከእግዚአብሔር የተሰጠን ፀጋ ነው። ይህ ነው ባለፈ ታሪክ ኩነቶችን ትተን ኢትዮጵያን የማቆም ሥራ ላይ የማተኮር በደቂቃዎች የሚቆጠሩ ጊዜዎች እንዲኖሩን የሚያደርጉን።አዲሱ ትውልድም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ የምፈልገው ይህንን ነው።በ1997 ዓም  የቅንጅትን ህብረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉበሙሉ ደግፎ የቆመው ከላይ የተጠቀሱት ስጋቶች በኢትዮጵያ በር ላይ መቆማቸውን ጠንቅቆ ስለሚረዳ ነው።
ይህ ማለት በቆየ አስተሳሰብ ውስጥ ሆነው ከደርግ ጋር ልሰራ? ከቀድሙ የንጉሡ አስተሳሰብ ጋር ልሰራ? ወይንም ህዋሃትን ከመሰረቱት ከ እነ ገብረመድህን ጋር ልሰራ? እያሉ ለሚናገሩ  መልሱ  ኢትዮጵያን የማዳኛው ጊዜ ካለፈ በኃላ  ስሟን የሚጠሯት ሀገር እንደማይኖራቸው ለመንገር ምሁር መሆን አለመጠየቁን ነው።

ይህንን ሃገራዊ ህብረት ከድርጅታዊ ፍቅር በተለየ የአርበኘነት ስሜት(patriotic feeling) የተላበሰ ኃይል ለመፍጠር ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት እና ለ አመታት የያዙትን አሰራር የመፈተሽ ብሎም ስልትን የማስተካከል ሥራ ይጠይቃል።እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባን የአንድነት ኃይሎች ሁሉን ያቀፈ መሰረት ላይ ያለፉ ኩነቶችን ቢያነሱም ወያኔ ግን ከላይ ከተጠቀሱት ኃይላት ጋር በ ፖለቲካ አካልነት ሳያስገባ ግን  ከአጠገቡ ባለማራቅ እየተጠቀመባቸው ነው። ሚስጥሩ ያለውም እዚህ ላይ ነው።
ዶ/ር አረጋዊ በርሄ (የህወሓት መስራች ወያኔን በመቃወም በስደት የሚኖሩ)

ይሄውም የዲሞክራስያዊ  ዘውድ ተዋናዮች የንጉሳውያን ቤተሰቦችን በሀገርቤት አንዳንድ ንብረቶችን ለምሳሌ እንደ ዋቢሸበሌ ሆቴል፣ወዘተ በመመለስ እያባበለ ትንፋሻቸውን ያዳምጣል አልያም በአንዳንዶች ዘንድ ''ደጉ'' ተብሎ እንዲጠራ ይታትራል።የደርግ ባለስልጣናትን ደግሞ  ''በዘር ማጥፋት ወንጀል'' ከሰስኩ ብሎ ቆይቶ ግን ሁሉንም በሚባል ደረጃ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን ፈቷል።ይህ ብቻ አይደለም በ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ የቀድሞ ጦር መኮንንኖችን በአማካሪነት ተጠቅሞ መልሶ አባሯል። በሶስተኛ ደረጃ ከድርጅቱ አፈንግጠው የወጡትን እንደእነ ስዬ አብርሃ ያሉትን ከሀገር ወጥተው የበለጠ ችግር እንዳይፈጥሩ ከስሩ አድርጎ የማይሞት የማይሽር አይነት የተቃዋሚ ድርጅት እንዲመሰርቱ ፈቅዶ ሞታቸውን እየጠበቀ ነው። 
ባጠቃላይ ወያኔ እንዲህ እያደረገ ነው። የአንድነት ኃይሎች ግን የተለያየ ስም እየሰጡ የትግሉ አጋር አድርገው ወደ ሃገራዊ ህብረት ለመምጣት ቀድሞ የኢትዮጵያን ፖለቲካን በዘውድም፣በደርግም ሆነ በወያኔ ስር ሆነው የተረዱትን ልምድ መቀበል (ታሪክን ለታሪክ ሰዎች ትቶ) በአዲስ መንፈስ የመነሳት ጥያቄ ከፊት ለፊት ፈጦ  መጥቷል። 
ኦነግ በብዙ አመት ቆይታው ወደ ኢትዮጵያዊነት ስሜት መጥቶ ''ከኢትዮጵያ ጋር መደራደር እንፈልጋለን'' (ለ ሩህ መፅሄት 1984ዓም አቶ ሌንጮ የሰጡትን መግለጫ ያስተውሉ) ያሉት የድርጅቱ አንጋፋ መስራች አቶ ሌንጮ ''በኢትዮጵያዊነት ስር ሆነን የሁሉም ችግር ሲፈታ ነው የ እኛም ችግር የሚፈታው'' ባሉበት ዘመን የደርግ፣የዘውድ እና የቀድሞ የወያኔ ባለስልጣን መባባል ለቃሉ ይቅርታ እየጠየቅሁ ''የፖለቲካ ጅልነት'' ሆኖ ይሰማኛል። 

ለመደምደምያ

ዛሬ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄው ካለፈው ስህተት ተምሮ ባለፈው የታሪክ ስህተት ተፀፅቶ ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ከዘረኞች እና ሉዓላዊነቷን ከሚፈታተኗት ባዕዳን ማዳን ነው ፈታኙ ጥያቄ።ስለሆነም  ማንም ቢሆን ማን  ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያምም ሆኑ የቀድሞው ንጉስ ልጅ ልዑል ኤርምያስ አልያም  የቀድሞው የህወሓት መስራች አቶ ገብረመድህን አርአያ የትግሉ አካል ማድረግ ማክበር እና ወደ አርበኝነት(patriotic) ስሜት ውስጥ  መግባት ከፖለቲካ ድርጅቶችም፣ከተፅኖ ፈጣሪ  ግለሰቦችም ሆነ ከመገናኛ ብዙሃንም የሚጠበቅ ከመሆኑም በላይ መፈራራትን ትቶ ኢትዮጵያን የማንሳቱ ስራን በብልህነት እና በማስተዋል መከወን ያለበት ጊዜ ይመስለኛል። ይህም  ጊዜ የማይሰጠው አዲስ የአስተሳሰብ ለውጥ ውስጥ የመግቢያው የለውጥ ነጥብ (turning point) ላይ መሆናችንን ልብ ማለት ይገባል።የፖለቲካ አስገራሚ ክስተቱም ይህ ነው አይገናኙም የተባሉ ተገናኝተው አንድ ሆነው ለአንድ ግብ ሲሰሩ መመልከት በእኛ አልተጀመረም ያውም ኢትዮጵያን ያክል ሀገር ይዘን።በሉ የአንድነት ኃይሎች ታምር ሰርታችሁ አሳዩን።እየተበቅናችሁ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
አበቃሁ

ጌታቸው በቀለ 

ኦስሎ 

ኖርዌይ 

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...