Wednesday, December 19, 2012

ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴን የተመለከቱ 7ቱ ልዩ ጥናታዊ ፊልሞች



ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴን የተመለከቱ  7ቱ ልዩ ጥናታዊ ፊልሞች 
 part 1

 part 2
 part 3
 part 4
 part 5
 part 6
 part 7

Haile-selassie part 8

Tuesday, December 18, 2012

ESKINDIR NEGA-TYPICAL SYMBOL OF CURRENT ETHIOPIAN GENERATION

Eskindir Nega


Tomorrow- December 19/2012, Eskindir Nega will present to Ethiopian Court. The Government accused him as if he was terrorist. But the only act he did was to express his ideas. Eskindir had awarded  ‘’press freedom award’’ from PEN America. He is a typical symbol of the current Ethiopian generation that is  facing lack of freedom of expression. Today 16 members of European Union representatives have signed a petition and sent a requisition letter to Ethiopian Government to release Eskindir without any pre-condition.


New York Times on May 2,2012 states about Eskindir:-
''Mr.Eskindir Nega has stood by his writing and maintained his right to publish. His defiant stance in defense of human rights in Ethiopia earned him a prestigious press freedom award from PEN America in what the literary nonprofit organization said was both recognition of his past work and an attempt to pressure the Ethiopian government into halting its prosecution of journalists.''(http://www.nytimes.com/2012/05/03/world/africa/eskinder-nega-ethiopian-journalist-honored-by-pen.html?_r=0)
 PUBLIC FORUM: Carl Bernstein & Liev Schreiber on Eskinder Nega (see video)


WHO IS ESKINDIR NEGA? please open the link http://www.ethiopianreview.info/index/?p=2809

Monday, December 17, 2012

''ቡሃዚ ዛሬ ላንተ እናለቅሳለን ነገ ግን አንተን የገደሉህን እናስለቅሳቸዋለን''የ ቡሃዚ ሰማዕትነት ዛሬ ሁለተኛ አመቱ

መሐመድ ቡሃዚ በ ሰፈር ስሙ ''ባስቡሳ'' ይባላል።እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር መጋቢት 29፣1984 ''ሲዲ ቦስድ'' በተሰኘ ቦታ ቱንስያ ውስጥ ተወለደ።አባቱ በ ሊብያ ውስጥ በ ግንባታ ሥራ ተሰማርተው ይሰሩ ነበር። መሐመድ ቡሃዝ አባቱን በሞት ያጣው ገና በ ሶስት ዓመቱ ነበር።በልጅነቱ ያገኘውን ሥራ አየሰራ ቤተሰቡን መርዳት የጀመረው ግን  ገና በ አስር አመቱ ነበር። ነገር ግን ጥሮ ግሮ መስራቱ በ ሙስና ለተበከለች ሀገር ምኗም አይደል።ትምህርቱን አጠናቆም ሥራ ማግኘት አልቻለም። ጥቂቶች በ ስልጣን በ ሚባልጉባት እና የተቀማጠለ ሕይወት በሚመሩባት ሃገሩ ውስጥ ያለው ፍትህ-አልባ ስርዓት ተስፋ ቢያስቆርጠውም ቡሃዚ እጅና እግሩን አጣጥፎ አልተቀመጠም በመንገድ ዳር አነስተኛ ንግድ ለመስራት ደፋ ቀና ማለት ጀመረ።ታህሳስ 16፣2010 ሁለት መቶ ዶላር ተበድሮ የመንገድ ዳር ንግድ ለመነገድ ብድር ያገኘባት ቀን ነበረች።
በቀጣዩ ቀን ታህሳስ 17፣2010 ከ ጧቱ ሁለት ሰዓት ላይ በተበደረው ገንዘብ የገዛቸውን ሸቀጦች ይዞ ከ መንገድ ዳር መሸጥ ጀመረ። ስርዓቱ ግን አሁንም እረፍት አልሰጠውም ፖሊሶቹን ልኮ ቁም ስቅሉን አሳየው። ፖሊሶች የመስርያ ቦታውን እንዲያፈርስ ነገሩት። መንገር ብቻ አደለም በ ግፍ ዕቃዎቹን ወረወሩበት። ፖሊሶቹ ጉቦ ቢሰጣቸው እንደሚተዉት ቡሃዚ ይውቃል። ግን የሚሰጠው የለውም። አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ ወደከተማው አስተዳደር ሄዶ ''አቤት!'' አለ። ሰሚ አላገኘም። ፍትህ ካልሰጡት እራሱን እንደሚያቃጥል ነገራቸው። አልመሰላቸውም ሰማዕትነቱ ከ እነርሱ አልፎ የ ቱንስያን ቤተመንግስት እንደሚያርገፈግፍ ብሎም መላ ሰሜን አፍሪካን አልፎም የመንና ሶርያ እንደሚደርስ ማንም አልገመተም። ልክ የዛሬ ሁለት አመት ታህሳስ 17፣2010 እ ኤ አቆጣጠር ቡሃዚ በ ከተማው ምክርቤት ፊት ለፊት እራሱን በ አደባባይ አቃጠለ።

በቀብሩ ስነስርዓት ላይ ከአምስትሺህ በላይ ቱንስያውያን እያለቀሱ ቀበሩት ቀብሩ ላይ ግን ወጣቶቹ እንዲህ አሉ ''ቡሃዚዛሬ ላንተ እናለቅሳለን ነገ ግን አንተን የገደሉህን እናስለቅሳቸዋለን'' አሉ ። እንዳሉትም አልቀሩ ወጣቶቹ ተነሱ ፕሬዝዳንት ቤን አሊ ሀገር ጥለው እንዲሄዱ አደረጉ።ወላፈኑ ለልብያው ጋዳፊ፣ለግብፁ ሙባረክም ተረፈ።ዛሬ ቡሃዚ በመላው ዓለም ታስቧል።በተለይ በሰሜን አፍሪካ ''የሃገራትን ቅርፅ ''የቀየረ ተሰኝቷል። የ እኛው የኔ ሰው ገብሬም በተመሳሳይ መልክ በ ፍትህ እጦት እራሱን አቃጥሏል።''የኔ ሰው እንዲታሰብ እንደ ገርማሜ ንዋይ እና መንግስቱ ንዋይ አምታትን ይጠብቅ ይሆን?
 
መሐመድ ቡሃዚ
                                                              ወጣቶቹ ስለ ቱንስያው አብዮት ለ አልጀዚራ ሲናገሩ (ቪድዮ ) 







የኔ ሰው ገብሬ
መሃመድ ቡሃዚእራሱን ያቃጠለበት አደባባይ                                         
¨                                                                                                


  

Saturday, December 15, 2012

ኳታር በ ምስራቅ አፍሪካ ጉዳይ



አቶ ኢሳያስ ለድርድር ኳታርን ሸምግይኝ ማለታቸውን ''አዋተ''የተሰኘውን ድህረ ገፅ አስታውቋል። እርግጥ ነው አቶ ሃይለማርያም ባለፈው ለአልጀዚራ ሲናገሩ ''አቶ መለስ ከ ሃምሳ ጊዜ በላይ ጠይቀዋል እኔም አሁኑኑ አስመራ ሄጄ ለመደራደር እቻላለሁ'' ማለታቸው ይታወሳል። ለሰላም ለመነጋገር በኳታር በኩል ከመዞር እንደ እኔ እንደ እኔ በደብረ ዳሞ በኩል ተቀታጥሮ አንዳፍታ መወያየት ይቀል ነበር። ኳታር '' አልጀዚራ'' የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣብያ ማዕከል ብቻ ሳይሆን ባላት የ ተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ ሀብት በ 2009 ከተባበሩት አረብ እምሬት ቀጥላ በመካከለኛው ምስራቅ ካሉት ሃገራት ውስጥ በ ተባበሩት መንግሥታት የ '' ሰው ልማት ሰንጠረዥ'' (Human development Index) የሁለተኘትን ደረጃ ይዛለች።

''ትንሽ ሀገር ትልቅ ችግር?'' (small country but big problem)

የኳታርን በተለይ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ዘው ብላ መግባቷን ያዩ እና በ ሌሎች ሀገሮች ጉዳይ ላይ ደግሞ በዜና ማሰራቻዎቿ ማራገቧን የተመለከቱ የአካባቢው አጥኚዎች ''ትንሽ ሀገር ግን ትልቅ ችግር'' ብለው ይጠሯታል።የሀገሪቱ ያለፈ ታሪክ ላይ ትንሽ ስእል ለመስት:-

·  እ.አ.አ ከ 1783 እስከ 1868 ባህራኒ አስተዳደር ስር፣
·  እ.አ.አ ከ 1871 እስከ 1916 በ ኦቶማን ኢምፓየር ስር፣
·  እ.አ.አ ከ 1916 እስከ 1971 በ እንግሊዝ ስር ተዳድራለች።

ከሁለተኛው አለም ጦርነት መጠናቀቅ ተከትሎ ሀገሪቱ የ እንግሊዝ ቅኝ የነበሩ ሃገራት ነፃነታ ውን ሲያገኙ እንግሊዝም የ ፖለቲካ ስልጣን ለመስጠት የ ሶስት አመት ጊዜ አስቀምጣ ስለነበር ኳታርም በ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 1968ዓም ከ ባህሬን ጋር በ ፈድሬሽን እንድትዋሃድ አደረገቻት። በ መጨረሻ አሁንም በ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ መስከረም 3 ቀን 1971 ዓም ሙሉ ነፃነቷን አገኘች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በ አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የ ማደራደር አቅሟን ለማጎልበት ጥረት አድርግላች። በ ምዕራብ ሳሃራ ግጭት ፣ብ የመን ግጭት እና በ ፍልስተሞቹ ''ፋታህ'' እና ''ሐማስ'' ምካከል ለመሸምገል ሞክራለች።

የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ እና ኳታር

ኳታር በ አፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ መግባት የጀመረችው በ ደርግ ዘመነ መንግስት ነበር። ሻብያ በኢርትራ  ሲዋጋ ስንቅ እና ትጥቅ አቀባይ ከሆኑት ሃገራት ውስጥ ብቻ ሳይሆን  ቀንደኛ የ ድርጅቱን አባላት በማስጠለል እና የ መንቀሳቀሻ ፓስፖርት በመስጠትም ትታወቅ ነበር። ይሄው ግንኙነት ከ ደርግ መውደቅ ጋር የተሻሻለ መልክ የያዘ ቢመስልም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተከትሎ የመሻከሩ ደረጃ ብሶበት በ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2008 ዓም ተመልሶ የ ኢትዮጵያ እና የ ኳታር ዲፕሎማሲ ግንኙነት መልሶ ተቋረጠ። በ ቅርቡ ከ አቶ መለስ እረፍት ተከትሎ ባለፈው ጥቅምት 2012 ዓም ነው ኳታር የ ዲፕሎማሲ ግንኙነቷን ከ ኢትዮጵያ ጋር ያደሰችው።


ኳታር በ ሱዳን እና በ ኤርትራ መሃከል ያለውን በጫፍ ያለ የሚባልለትን ግንኙነት  በመያዝም ትታወቃለች። በሁለቱ መሬቶች መሃከል ያለውን የድንበር ችግር ለመግታት የድንበር ከተሞቹ ላይ የኢንዱስትሪ ማዕከል ልመስርትላችሁ ብሎ ከመጠየቅ ባለፈ በገንዘቧ የሁለቱን ሃገራት የሚያገናኝ የአስፋልት መንገድ ሰርታ ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ላይ የኳታር መሪ ኤሚር ሼክ ሐመድ አል ታኒ፣የ ሱዳኑ አልበሺር እና የ ኤርትራው ኢሳያስ በተገኙበት አስመርቃለች። በምረቃውም ላይ የ ሱዳኑ አልበሺር ኤርትራ በ እሳቸው ላይ የ ዓለም አቀፉ ፍርድቤት የ ቆረጠውን የ መያዥያ ሰነድ ወደጎን በማለት ያስተናገደቻቸው ሀገር መሆኗን ጠቅሰው ወደፊትም ነፃ የ ድንበር ክልል እንዲኖር እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ይህን ይበሉ እንጂ የ ሁለቱን መሬቶች ግጭት በ ኳታር የ ገንዘብ ኃይል እንዲገታ መደረጉን እና የ ጊዜ ቦንብ መሆኑን ግን ለማውሳት አልበሺርም ሆኑ ኢሳያስ አልደፈሩም።

የኳታር ኢሚር ፣አልበሽር እና ኢሳያስ ኳታር ያሰራችውን መንገድ ሲመርቁ


የኳታር የ ድርድር ጥያቄ ቀደም ብሎ የጠየቀ የነበረ ቢሆንም በ አቶ ኢሳያስ የግል በጎ ፈቅድ ብቻ የሚመራው የኤርትራ አስተዳደር በ አንድ በኩል የመለስን መሞት ተከትሎ የሚመጣውን ለውጥ ስተባብቅ በ ሌላ በኩል ደግሞ በ ኢትዮጵያ በኩል ጫፍ የያዙ የ ህዋሀት አመራሮች ሲጎትቱት የቆየ ጉዳይ ነበር። አሁን ግን ሁለቱም ለድርድር የሚቀርቡ ከሆነ ስለ ሚከተሉት ምክንያቶች ብቻ እንጂ ለውጤት ሁለቱም እንደማይተጉ ግን ለመረዳት ሊቅ መሆን አያስፈልግም። ለድርድር እንዲቅርቡ ያደረጋቸው ምክንያት የመጀመርያው በ ኤርትራ በኩል እና በ ኢትዮጵያ በኩል ያለው የውስጥ ቅራኔ ከፍተኛ ደረጃ ስለደረሰ እና ለ ቅራኔው አቅጣጫ ማስቀየርያ ትልቁ የሀገር ውስጣቸውንም ሆነ አካባብያዊ ብሎም አለምአቀፍ ፖለቲካን የማብረጃ ስልት አድርገው ስላዩት ብቻ ነው። ኤርትራ የ ኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች ስልጠና ከምስጠት አልፎ አስከ ማስታጠቅ ድረስ እየሰራች እንደሆነ አቶ መለስ ብዙ ጊዜ ተናግረዋል። ኢትዮጵያም ከፍተኛ ባለስልጣናቷ ሳይቀሩ የተገኙበት የ አቶ ኢሳያስ ተቃዋሚዎችን አለማቀፍ ስብሰባ ከማስተናገድ አልፋ ''በ አረብ ሳተላይት'' በኩል ''ሓዳሽ ኤርትራ'' የተሰኘ የ ቴሌቭዥን ፕሮግራም ከ ምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ ዘወትር ማስተላለፍዋ እና የ ኤርትራ ቴሌቭዥን የደበቃቸውን የሃገር ውስጥ ክስተቶች ይፋ መሆናቸው በ እረጅም ጊዜ ተፅኖ መፍጠሩ አልቀረም። ከሁሉም ግን ኤርትራ ከ ዓለም ሕብረተሰብ ከ ሚድያውም በመጥፋቷ ትንሽ ለ ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ አርስት መሆንም አስባ ይሆናል።የምሰመርበት ግን ሁለቱም ሃገራት ውስጣዊ ችግሮቻቸውን ማስታገሻ እና ማስቀየሻ የምትመዘዘውን የ ተለመደች ካርድ መምዘዛቸው ብቻ ነው።

ከሁሉም ግን አሳዛኙ ክስተት የሁለቱ ሃገራት ጉዳይ በ አቶ ሃይለማርያም እና አቶ ኢሳያስ እጅ ላይሆን የመቻሉ ጉዳይ ነው። ጉዳዩ እጅግ ግሎ ውይይት የሚደረግበት እና የሚወሰነው በ ድብቅ በር በ ሁለቱ የ ጦር አለቆች ዘንድ ነው። በ ሁለቱም የ ጦር ሰራዊት አዛዦች ዘንድ ከ ብሔራዊ እና ስትራተጃው አስተሳሰብ ይልቅ ክልላዊ እና የ ትውልድ ቦታ ቅድምያ ስለሚሰጠው እልህ እና ተደፈርኩ ባይነት የጎላበት ስሜት ብዙውን ጊዜ የ ፕሬዝዳንቱንም ሆነ የ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሚና ያኮስሰዋል። በመሆኑም ይህን የሚያውቁት አቶ ኢሳያስ ባለፈው ለ አልጀዚራ ቴሌቪዥን አቶ ሃይለማርያም የሰጡት '' አስመራም ቢሆን ሄጄ እደራደራለሁ '' የሚለው ንግግር በ ህዋሀት የጦር አበጋዞች ዘንድ ምን ያህል ንዴት እንደፈጠረ እና ይህ ልዩነት ደግሞ ''ኳታርን አደራድርኝ ብላትማ የትየለሌ ይደርሳል'' አሉና አቶ ኢሳያስ ይሄው ''ያለቅድመ ሁኔታ እንደራደር'' አሉ ተባለ። ''እውነትና ንጋት እያደር'' እንደሚባለው በ ሺህ የሚቆጠረው የ ኤርትራ ወጣት በሺ ከሚቆጠረው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ እና አህቱ ጋር በ የመን በሱዳን በ እግሩ እየሄደ ይንከራተታል። ለህዝባቸውም ሆነ ለ እራሳቸውም ያልሆኑት መሪዎች ግን አንዴ ከ ኳታር አንዴ ከ ዱባይ እያሉ በ ህዝቡ ይነግዳሉ።
                       ከ ኢትዮጵያም ሆነ ከ ኤርትራ ስደተኛው ሃገሩን ትቶ መሄዱን ቀጥሏል።