ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, October 23, 2017

ከሰሜን አውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ!


አሁን ለቤተ ክርስቲያናችን ህንፃ ኮሚቴ በደረሰው ኢሜይል እና ስልክ መሰረት ቀድመው ከነበሩት በተጨማሪ ሌሎች ተጫራቾች በመምጣታቸው እና እነርሱም ቤተ ክርስቲያኑን በእራሳቸው መሀንዲስ ለማስመርመር እስከ መጪው ማክሰኞ ድረስ ጊዜ ስለጠየቁ ጨረታው በአንድ ሳምንት ተገፍቷል:: ስለሆነም እባካችሁ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ንብረት ለማድረግ ለምናውቃቸው ሁሉ ነግረን በተሻለ አቅም እንድንቀርብ እንትጋ::እስካሁን ለለገሳችሁ እግዚአብሔር ዋጋችሁን አያስቀርባችሁ።



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቁስ አሐዱ አምላክ አሜን።
በመላው ዓለም ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ ጥሪ! 

ይህንን በመደገፍዎ ኢትዮጵያ ሃይማኖትን ፣ቅርስን እና ታሪክን በአውሮፓ ምድር እንድትተክል በመርዳት እራስዎን የሂደቱ አካል አደረጉ ማለት ነው። 
++++++++++++++++++++++++++++++
በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በ1900 ዓም የተገነባ እና ጥንታዊ ይዘቱን ሳይለቅ በ1990ዎቹ በሚገባ የታደሰ በ730 ካሬ ላይ የሰፈረ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ከፍተኛ ርብርብ ላይ ነች።ጨረታው በ72 ሰዓታት ውስጥ ይደረጋል።ለጨረታው የሕንፃ ኮሚቴ ካለው ገንዘብ እና የባንክ ብድር በተጨማሪ የተወሰነ ገንዘብ ያስፈልገዋል።ቅርሱ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ባለፈ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ አንደምታ አለው። ስለሆነም በመላው ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ይህንን ለጥቂት ሰዓታት የተከፈተ ጎ ፈንድ አካውንት የአቅማችሁን በመስጠት ከበረከቱ ተካፈሉ። ይህንን በመደገፍዎ ኢትዮጵያ ሃይማኖትን ፣ቅርስን እና ታሪክን በአውሮፓ ምድር እንድትተክል በመርዳት እራስዎን የሂደቱ አካል አደረጉ ማለት ነው።

በኖርዌይ ኦስሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ከበረከቱ ለመሳተፍም ሆነ የታሪኩ አካል ለመሆን ከስር የተለጠፈውን ተጭነው በ''ጎፈንድ'' አካውንት አስተዋፅኦ ያድርጉ።
እስካሁን ለለገሳችሁ እግዚአብሔር ዋጋችሁን አያስቀርባችሁ። ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ተጭነው የበኩልዎን ትንሽ ነው ሳይሉ ይለግሱ።






ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments: