Friday, August 11, 2017

በኢትዮጵያውያን ደም የተጨማለቀ የአሸንዳ በዓል ከፋሺስት ብሔራዊ መዝሙር እኩል ነው።ፋሺሽት ሕወሓት በቃን!የኢትዮጵያ ሕዝብ እያሰማ ያለው መፈክር።

ኢትዮጵያ ከሰሜን ተራሮች እስከ ደቡብ ምስራቅ ጅጅጋ፣ ከጋምቤላ አኮቦ እስከ አፋር አሳይታ የ26 ዓመታት የወያኔ አገዛዝ ያንገሸገሸው ሕዝብ ለነፃነቱ እየወደቀ እና እየተነሳ ነው።በያዝነው ሳምንት ብቻ በሐዋሳ የባጃጅ ትራንስፖርት ሥራ ማቆም አድማ ተጀምሮ እስከዛረዋ እለት ድረስ እንደቀጠለ ነው። ሰሜን ጎንደር ያሉ የንግድ ቦታዎች በሙሉ ተዘግተው አድማ ላይ ናቸው፣ ባህር ዳር 50 በላይ ነዋሪዎቿን በህወሓት ወታደሮች የተፈጁባት አንደኛ ዓመት ለማክበር በያዝነው ሳምንት የስራ ማቆም አድማ መትጣለች። እስካሁን ድረስ በርካታ የከተማዋ ነጋዴዎች እና ነዋሪዎች እየታሰሩ ነው።ፋሺሽት ወያኔ በቃኝ! ያሉ እና በንግድ እና ሥራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ ሌሎች ከተሞች ወልዲያ ፣ አምቦ፣ጎንደር፣በለሳ እና ሌሎች በርካታ ከተሞች ሲኖሩ ምስራቅ ሐረርጌ ባቢሌ ሱማሌ እና ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በመሬት ጉዳይ ስርዓቱ አጋጭቷቸው እርስ በርስ ውጊያ ላይ ናቸው።

አንዳንዶች ፋሺስት ሕወሓት ሲባል የተጋነነ ስድብ አድርገው የሚያስቡ አሉ። ሆኖም አሁን ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ካለው አንፃር ፋሺስት የሚለው አጠራር ለህወሓት ሲያንሰው እንጂ ከልኩ በላይ የተሰጠው ስም አይደለም።በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያውያን ላይ ሰራዊት አዝምቶ፣መሳርያ ወድሮ እና በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ታጅቦ ኢትዮጵያውያንን መጀመርያ ሀብታቸውን ቀጥሎ ሕይወታቸውን እየቀጠፈ የሚገኘው የህወሓት ቡድን ፋሽሽት የሚለው ቃል ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም።

ኢትዮጵያውያን በሲቃ መከራ ላይ በሚገኙበት በእዚህ ወቅት ስለ ሕወሓት እና ጀሌው ትንታኔ መስጠት ወይንም ፀሐይ የሞቀውን የሕወሓትን ግፉን መዘርዘር አንዳች ፋይዳ የለውም።ባጭሩ የህወሓት ፈድራሊዝም ተንኮታኩቷል።የወደቀ ነገር ትንታኔ አይፈልግም። ሕዝብ ለወያኔ አለመገዛቱ ያሳየበት አንዱ መንገድ ለወያኔ ግብር አልከፍልም በማለትም ነበር።ኢትዮጵያውያን እዚህ የመጨረሻ የትዕግስት እንጥፍጣፊ ደረጃ ለመድረስ በርካታ የመከራ ፅዋዎችን ተጎንጭተዋል።አሁን ግን ከእዚህ በላይ የመኖር እና አለመኖር ወሳኝ ጥያቄ ላይ የደረሰበት ሕዝብ ሕወሀትን  ከትከሻው ላይ ለማሽቀንጠር ወስኗል።ይህንን የኢትዮጵያ ሕዝብ ውሳኔ ለጊዜው በአፈሙዝ ተገድቦ የተያዘ ይምስለ እንጂ በከባድ አሻጥር እና ኢትዮጵያዊ ስሜት አመፁ እንደሚቀጥል እና በሌላ መልክ እንደሚከሰት በእርገጠኘንት መናገር  ይቻላል። ይህ ወቅት ኢትዮጵያን ከእነሙሉ ክብሯ ለማስጠበቅ የመነሳት ኃላፊነት የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነው።"ከሚቃወሙት ይልቅ ዝምተኞቹን እና ቸልተኞቹን እፈራለሁ" እንዲል በቸልታ ውስጥ ያለው በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ አሁን ላይ ቆሞ መመልከት ያለበት በርካታ ጉዳዮች አሉ። አሁን ሕዝብ ሁሉንም ጉዳዮች ተመልክቶ  በአንድነት የመቆም ግዴታ እንዳለበት እየተረዳ ነው።

መላዋን ኢትዮጵያ በደም እየነከረ ያለው የፋሽሽት ስርዓት በኢትዮጵያውያን ደም ከመነከሩ በላይ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ የምጣኔ ሀብት አቅም በበለጠ ለማቆርቆዝ እና የበለጠ ባርያ ለማድረግ በግብር ሰበብ ነጋዴውን ከንግድ ቦታው እየነቀለ የእኔ ለሚላቸው የጎሳ መሰሎቹ እና አድር ባይ ካድሬዎች ለመስጠት አዲስ ዘመቻ ላይ ነው።አንዳንዶች እንዴት ወያኔ በእዚህ በተወጠረበት ወቅት የንግድ ግብር ጉዳይ አንስቶ ሕዝብ እንዲነሳ ምክንያት ሆነ? ብለው ይጠይቃሉ። ለእዚህ ምክንያቶቹ ግን ሁለት ናቸው።አንደኛው ከውጭ የሚገባ እርዳታ እና ብድር ከመመናመኑ የተነሳ እና የውጭ ንግድ ገቢው ስለወረደ ቀሪ የበጀት ማሟያ ብቸኛ ምንጩ ቀረጥ ህዝቡ ላይ መጣል ሲሆን ሁለተኛው እና እግረመንገዱ ለማሳካት ያሰበው ከውጭ በተለይ ከአረብ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የምገቡቱ የጎሳው ሰዎች አነስተኛ እና መካከለኛ ንግድ እንዲሰሩ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ማፈናቀል የሚለው እንደ ቀዳሚ ተግባር ተደርጎ ተወስዷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማለትም ኢትዮጵያውያን ከገጠር እስከ ከተማ በሚታሰሩበት፣በሚገረፉበት  እና በሚገደሉባት ኢትዮጵያ አሸንዳ ሊዘፈንበት ሽር ጉድ ተይዟል።አስከሬን ላይ ቆሞ አሸንዳ የለም።በኢትዮጵያውያን ደም የተጨማለቀ የአሸንዳ በዓል ዘፈን ከፋሽሽቶች ብሔራዊ መዝሙር እኩል ይቆጠራል።ህዝብን አስለቅሶ ባሕሌን ተጋቱልኝ ማለት አይቻልም።ለሃያ ስድስት ዓመታት ሕዝብን ንቆ የቆመ ፋሽሽታዊ ስርዓት ጋር አብሮ ለመቀጠል የሚፈልግ እና እራሱን ከእውነት ጋር በተ ንጠፈጠፈች ሰዓትም ላይ ቢሆን  የሚለይ ካለ ሕዝብ አሁንም እጁን ዘርግቶ እየጠበቀ ነው።ሁኔታው ግን "ካፈርኩ አይመልሰኝ" ሆኗል።አይን አውጥቶ መግደል፣የንግድ መደብሮችን ማሸግ እና ቤተሰብ ተርቦ እንዲያድር ገፋ ስል ደግሞ ለጎዳና ሕይወት ተዳርገዋል።ባዕዳን ወራሪዎች ኢትዮጵያን ቢወሩ ሊያደርጉ የሚችሉት አሁን ወያኔ እያደርገ ያለውን ነው።ወያኔ ፋሽሽት እንጂ ኢትዮጵያዊ መንግስት አይደለም።ኢትዮጵያዊ መንግስት ወገኖቹ ወደ ባህር ሲጣሉ ጉዳዩን የሚያጣራ ልዑክ ቢያንስ ሰይሞ ይንቀሳቀሳል።አረመኔው ወያኔ ግን ትናንት በመላው ዓለም የተሰማው የ160 ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ሲሄዱ ሆን ተብሎ ከመርከብ ወደ ውሃ እንደወረወሩ መደረጋቸውን እንዳልሰማ አንዲት ዜናም ሳይሰራለት ይሄው አሁን 24ኛ ሰዓቱ አልቆ ወደ ሁለተኛ ቀን አልፈናል።ጉዳዩን ግን በመላው ዓለም ተናኝቷል። 

ፋሽሽት ወያኔ የኢትዮጵያ ወኪል ሆኖ መቀመጥ እንደማይችል ከአንድ መቶ ስልሳ በላይ ኢትዮጵያውያን እጅ እና እግራቸው እየታሰረ ወደ ባሕር ውስጥ መወርወራቸው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ከተነገረ 24 ሰዓት ቢያልፈውም የኢትዮጵያ ራድዮ እና ቴሌቭዥንም ሆነ ሕወሓት የሚመራው መንግስት አንዳች ነገር አልተናገረም።የትኛው መንግስት ነው ዜጎቹ ባህር ውስጥ ገብተው አንዳች የማይተነፍስ? በአሸንዳ ከሚውረገረገው ወያኔ በቀር።ሕዝብ አሁን መድረሻ ግቡን እያስቀመጠ ነው።ይሄውም በቅደም ተከተል ከወያኔ በኃላ ስለሚኖረው መንግስት ሕዝብ ይወያያል።ፋሺሽት ሕወሓት በቃን!የኢትዮጵያ ሕዝብ እያሰማ ያለው መፈክር ነው። ከእዚህ በኃላ የወያኔ የባርነት ቀንበር ውስጥ የሚገባ ኢትዮጵያዊ የለም።

ቪድዮ - ጎንደር ላይ የተደረገው ሕዝባዊ ሰልፍ በከፊል።ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Wednesday, August 9, 2017

የኢትዮጵያ አምላክ እንዲነሳ እንባ አዋጡ! (የጉዳያችን መልዕክት)

ኢትዮጵያ አምላክ አላት።የሁሉም አምላክ እንደሆነ ሁሉ በተለይ የኢትዮጵያ አምላክም መሆኑን የነገረን ደግሞ ከ40 ጊዜ በላይ በቅዱስ መፅሐፍ ስሟ እንዲጠራ ያደረጋት ሀገር ኢትዮያ ነች።ይህ ያለንበት ወቅት (ከነሐሴ 1 እስከ 16፣2009 ዓም) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሰረት ከሰባቱ ዋና የፆም ወቅቶች ውስጥ አንዱ ነው።ፆሙ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤ እና የእርገት ምስጢርን ለሐዋርያት በሁለት ዙር ሱባኤ  ከእግዚአብሔር ምስጢሩን የተገለጠላቸው ወቅት ነው።ኢትዮጵያ እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፊት ለፊት የሚነጋገሩ ምስጢረኞች ናቸው።ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴን ጨምሮ ከእሳቸው በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ  መሪዎች በእግዚአብሔር የሚያምኑ በድንግል ማርያም አማላጅነት የተጠቀሙ ነበሩ።አንዳንዶች እግዚአብሔርን በሚገባ ስለማያውቁት ወይንም ከስንፍና የተነሳ ስለድካማቸው መሸፈኛ እግዚአብሔርን ማመን የመሸነፍ እና የተስፋ መቁረጥ ምልክት ይመስላቸዋል።ጉዳዩ ግን በተቃራኒው ነው።አባቶቻችን እና እናቶቻችን ኢትዮጵያን ለትውልድ ሲያስተላልፉ መንገዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር አድርገው እንጂ በትዕቢት መንገድ ተጉዘው አልነበረም።

ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ይህ የፍልሰታ ፆምን የዓመት እረፍት ወስደው  ድሬዳዋ ኪዳነ ምሕረት አልያም መስቀል አደባባይ የሚገኘው ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን 15ቱንም ቀኖች እያስቀደሱ ያሳልፉ ነበር።በተለይ ድሬዳዋ በወረዱበት የፍልሰታ ፆም ወቅት እርሳቸውን በፍጥነት ለማግኘት የመጣ የውጭ ሀገር ልዑክ ድሬዳዋ መውረድ ነበረበት።ኢትዮጵያ የተሰጣት ፀጋ ይህ ነው።ከእግዚአብሔር ጋር መንገዱን ያላስተካከለ ቤተ መንግስቷ ውስጥ ቢገባ እንደታወከ ይኖራል።በደርግ ዘመንም ሆነ አሁን አራት ኪሎ የሆነውን እያየን ነው።

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ጊዜ አንድ ሱባኤ አይደለም በርካታ ሱባኤዎች ይፈልጋል።ሕዝብ በጎሳ በተከፋፈለ ችግር ነው።ከወዲህ በጎሳ የሚከፋፍል በመንግሥትነት ተሰይሞበት ያሰቃየዋል፣ ከማዶ በእየጎሳው የተደራጁ ድርጅቶች የነገ አንደነቱን ሊያጨልሙበት ሲሯሯጡ ይታያሉ።በእግዚአብሔር ዕርዳታ ሰው በጥረቱ የሚፈታው ጉዳይ አለ። ሰው ምንም ያህል ቢሮጥ በእግዚአብሔር ብቻ እና ብቻ የሚሰራ ሥራ አለ።ስለ ኢትዮጵያ ማንባት ጥቂት እንባ ማዋጣት ከእግዚአብሔር ጋር መንገዷን ያስተካክላል።ለዘመናት መላ ያጣችበትን የቤተ መንግስቷን ጉዳይ መልክ ያስይዘዋል።መልክ የምያስይስዘው ከሰማይ ወርዶ አይደለም።የሕዝብን ልብ ያፀናል፣ፍቅር ይሰጣል፣አሸናፊ ያደርገዋል።ይህ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ልብ አፅንቶ፣በአንድ አቁሞ፣የሚወደው መሪ አውጥቶ ኢትዮጵያን ለመጪው ክፍለ ዘመን ነፃነቷን፣አንድነቷን፣እምነቷን እና ብልፅግናዋን አምጥቶ ያሻግራታል።እግዚአብሔር በቸርነቱ፣ ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ የኢትዮጵያን ምስጢር እንድትፈታ ትንሽ ትንሽ እንባ እናዋጣ። እንደ እውነቱ ለመናገር ማናችንም ስለ እራሳችን እና ቤተሰባችን እንፀልይ ይሆናል።ጥያቄው  ከልብ ጊዜ ሰጥተን የኢትዮጵያ ጉዳይ ብለን እየፀለይን ነው ወይ? የሚለው ነው።ከሆነ መልካም።እርግጥ ነው ቀን ከሌሊት የሚፀልዩ በግልጥም በስውርም የሚኖሩ የእግዚአብሔር ወዳጅ ቅዱሳን የሚኖሩባት ነች ኢትዮጵያ። የእዚህ ማስታወሻ ዋና አላማ ግን ስለ ካህናቱ፣መነኮሳቱ ለማውራት አይደለም።ከእዛ በታች ስላለነው ምእመናን ሁሉ ነው።እስኪ የኢትዮያን ጉዳይ ፍታው ብለን ትንሽ ትንሽ እንባ እናውጣ። እግዚአብሔር በኢትዮጵያ እና በሕዝቧ ላይ የተነሱባትን ባያንበረክክ በእዚህ እንፈትነው።

ከስር ቪድዮ "ቅያሜው ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን" በዘማሪ ይልማ ኃይሉ (ያድምጡት)ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, August 7, 2017

መንግስት በእራሱ ለውጥ ማምጣት ካልቻለ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደገና አጠቃላይ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል ሲል የሰብዓዊ መብት ተመልካች ድርጅት (ሁማን ራይትስ ዋች) አስታወቀ።

የዓለም ሰብአዊ መብት ተመልካች ድርጅት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዛሬ በድረ-ገፁ ላይ የፃፈውን ከእዚህ በታች ይመልከቱ።
  • Government Should Use Reform, Not Force, to Avoid More Protests
  • ...Without  efforts and meaningful reform, it is just a matter of time before they start protesting again. 

August 7, 2017 4:10PM EDT
Ethiopia’s parliament has just lifted the country’s 10-month-long state of emergency. The government’s emergency powers brought mass detentions, politically motivated criminal charges, and numerous restrictions on people’s movement and communication. While the end is welcome news, thousands remain in detention without charge, none of the protesters’ underlying grievances have been addressed, and politically motivated trials of key opposition leaders, artists, journalists, and others continue.
In October 2016, at the beginning of the state of emergency, the government promised “deep reform” in response to the year-long protests that left over 1000 people dead. The reforms included tackling corruption, cabinet reshuffles, and a dialogue with what was left of opposition political parties. The government also pledged youth job creation and good governance. But these are not the fundamental issues that protesters raised during the hundreds of rallies between November 2015 and October 2016. The government has largely redefined protester grievances in its own terms, ignoring more fundamental demands to open up political space, allow dissent, and tolerate different perspectives that are critical in such a large and ethnically diverse country. It has also failed to conduct even a remotely credible investigation into security force abuses since the protests began.
Impunity for security forces remains a major concern. The Ethiopian Human Rights Commission’s two investigations into the protests and a recent speech by their chair – which both echoed the government’s misleading allegations of the extent of violence by protesters and its inaccurate portrayal of protester grievances – underscore longstanding concerns over the commission’s independence. Accountability matters – not only for corruption, but for security force abuses. Ethiopia’s repeated unwillingness to meaningfully investigate and hold its security forces to account is why Human Rights Watch and others have long argued that an international investigation is crucial.
Even though it was abusive and overly broad, Ethiopia’s state of emergency gave the government a window to address citizens’ grievances without the shadow of imminent protests. But the government missed that opportunity. Suppressing grievances through brutal force is more likely to provoke instability than to ensure Ethiopia’s long-term stability.
The government should release those arbitrarily detained or subject to politically motivated charges, including opposition politicians like Dr. Merera Gudina, Oromo Federalist Congress chairman. Many protesters, including those who were held in Ethiopia’s “rehabilitation camps” during the state of emergency, have told me that without such efforts and meaningful reform, it is just a matter of time before they start protesting again. 

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Sunday, August 6, 2017

ሃዘን ጎሳ የለውም።ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።አባታቸውን፣እናታቸውን ወይንም ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው ጋር አብረን እንዘን።

ጉዳያችን/Gudayachn 

ኢትዮጵያ ላለፉት አርባ ዓመታት የፖለቲካ ስልጣን  ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የመብት ጥያቄ ያነሱ ሁሉ በአደባባይ ሲገደሉ ኖረዋል።በህወሓት የሚመራው መንግስት ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የኢትዮጵያውያን እንባ አልቆመም።በተለይ ባለፉት 10 ወሮች ውስጥ በአስር ሺዎች ወደ እስር ቤት ሲጋዙ ብዙ መቶዎች (ቁጥሩ ከእዚህም እንደሚልቅ ይታመትናል) በአደባባይ በስርዓቱ ወታደሮች ተገድለዋል።በጎንደር፣ነቀምት፣አምቦ፣ባህርዳር፣አዲስ አበባ፣ኮንሶ፣ቴፒ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ቤተሰብ ሃዘን ላይ ነው።

ነገ ነሐሴ 1፣2009 ዓም በባህርዳር ከተማ ልክ የዛሬ ዓመት ባዶ እጃቸውን የመብት ጥያቄ ባነሱ ነዋሪዎች ላይ ጨካኞቹ የስርዓቱ ወታደሮች እና በጎሳ ስሜት እራሳቸውን  የተበተቡ ታጣቂዎች ከኮንደምንየም ቤቶች መስኮቶች ላይ ሁሉ በማድፈጥ በ60 ደቂቃዎች ውስጥ ከ50 ያላነሱ የከተማው ነዋሪዎች እንደቅጠል የረገፉበት ቀን ይታሰባል።በባህር ዳር ከተማ ሥራ የማቆም ጥሪ የተጠራ ሲሆን ጉዳዩ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊንም የሚመለከት ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው።
ሃዘን ጎሳ የለውም።ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።አባታቸውን፣እናታቸውን ወይንም ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው ጋር አብረን እንዘን።በኢትዮጵያ የትኛውም ክፍል በግፍ በአገዛዙ ሕይወታቸው የተቀጠፈውን ሰማዕታት እንዘክራቸው።

ቪድዮ:  በፕሮፌሰር አሽናፊ ከበደ “እረኛው” የተሰኘው በመሳርያ ብቻ የተቀናበረ ሙዚቃ። 
                

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, July 17, 2017

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአውሮፓ ለመጀመርያ ጊዜ ሲመተ ጵጵስና አካሄደች።የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የጵጵስና ማዕረግ ተሹመዋል።


ሲመተ ጵጵስና ከተከናወነ በኃላ (ፎቶ ጉዳያችን)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገሮች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ተወላጆች የምትሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።ይህ አገልግሎት በተለይ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለየ መልክ እና እጅግ ወሳኝ የሆነ ገፅታ አለው። ከሀገሩ በርቀት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማለት የመንፈሳዊ ሕይወታቸው መሪ ብቻ ሳትሆን የባህል፣ማንነት እና ስነልቦናዊ ፋይዳ ሁሉ የሚገለጥባት ልዩ አካሉ ነች።ከእዚህ ሁሉ የአገልግሎት ፋይዳ ጋር እንግዲህ የአገልጋይ ካህናት ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም።ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደ አንድ ቁልፍ ተቋም እና የምእመናንን ሕይወት በመንፈሳዊ እና ዓለማዊ ሕይወት ዙርያ የመምራት አቅም፣ አሻጋሪ ርዕይ እና ብቁ ትውልድ የማፍራት ሥራ ሁሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሚኖራት ብቃት ያላቸው አገልጋይ ካህናት ይወሰናል። 

ቤተ ክርስቲያኒቱ ካሏት መሰረታዊ ባህርያት ውስጥ አንድነት እና ሐዋርያዊ መሠረትነት ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በፈተና ላይ መውደቃቸው ይታወቃል።ለእዚህም ዋነኛ ምክንያቱ አሁን ስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት የነበሩትን ፓትርያርክ መርቆርዮስ ከሀገር እንዲወጡ ግፊት ካደረገ በኃላ ፓትርያርኩ በሕይወት እያሉ የአቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክነት መሰየም ነው።ችግሩ ከተፈጠረ በኃላም በውጭ እና በሀገር ቤት  ያሉ ብፁዓን አባቶች መካከል  ንግግር ተደርጎ ችግሩን ለመፍታት የተደረጉ ሙከራዎች  የሚፈለገውን ውጤት አላስገኙም።ለእዚህ በዋናነት የሚጠቀሰው ምክንያት ለአንድነቱ በጎ ፍቃድ ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ በታማኝነት ለመስራት ፈፅሞ ምልክትም ያላሳየው በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት  አንዱ እና ተጠቃሽ ነው። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሀገር በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ብፁዓን አባቶች አህጉረ ስብከቶቹ ከሚያስፈልጋቸው አገልጋይ ጳጳሳት አንፃር ተጨማሪ ጳጳሳትን ከቆሞሳት መካከል እየመረጡ ለጵጵስና ማዕረግ እያበቁ ይገኛሉ።ከአገልግሎቱ አንፃር የቆሞሳት ለጵጵስና ማዕረግ መብቃት ቤተ ክርስቲያን እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ እግዚአብሔር እንደፈቀደ የሚቀጥል መንፈሳዊ ተግባር ነው።የሁሉም ምእመናንም ሆነ የሁሉም ብፁዓን አባቶች ምኞት እና ፀሎት ግን አሁንም ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነቷን መልሳ የምታጠናክርበት ቀን እንዲቀርብ ነው። ይህ እስኪሆን ድረስ ግን በአባቶች መካከል የቀኖና እና ስርዓት ጉዳይ እንጂ የመሰረተ ሃይማኖት (ዶግማዊ)  ልዩነት ካለመኖሩ አንፃር ቤተ ክርስቲያን አሁን ያሉባትን ችግሮች የመፍታት አቅሟ አሁንም ትልቅ መሆኑን መረዳት ይቻልል።

በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭም ሆነ በሀገር ቤት የሚገኙ አባቶች በጋራ በመቆም አርአያነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች እየታዩ ናቸው። እነኝህ እንቅስቃሴዎችም በተሃድሶ ጉዳይ ላይ እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ናቸው።በያዝነው ዓመት ብቻ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ያሉ አባቶች በሲኖዶስ ስብሰባዎች ላይ በመግለጫ ደረጃ በጋራ ያስነበቡት ዓቢይ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሰረተ ዕምነት መፃረር ላይ የሚገኘው በተሃድሶ እንቅስቃሴ ላይ ያሳዩት ግልጥ መመሪያ ነው። በስደት የሚገኙ አባቶች በቅርቡ በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይም ሆነ ባሳለፍነው ሳምንት በስዊድን ፣ ስቶኮልም በተደረገው ሃያኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ ፍፃሜ ላይ በወጣ መግለጫ በተሃድሶ እንቅስቃሴ ላይ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት እራሳቸውን መጠበቅ እና ምእመናንን ማስተማር ተገቢ መሆኑን አፅኖት በመስጠት አሳስቧል። 

የመጀመርያው ሲመተ ጵጵስና በአውሮፓ 

ከላይ የተጠቀሱት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ነባራዊ እና ወቅታዊ ሁኔታ ለመንደርደርያነት ከቀረበ ባሳለፍነው ሳምንት ማለትም ሐምሌ 9፣2009 ዓም በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመርያ ጊዜ ሲመተ ጵጵስና ማካሄዷን ወደ ሚገልጠው ዜና እንለፍ።በጵጵስና የተሾሙት አባት የቀድሞ ስማቸው መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ ለገሰ ሲሆኑ የጵጵስና ስማቸው አቡነ ሕርያቆስ ተብለው በስደት የሚገኙት ብፁዓን አባቶች በተገኙበት ፀሎት ተሹመዋል።ከእሁዱ የሹመት መርሃግብር በፊት በ2008 ዓም አቡነ ሕርያቆስ የቀደመ አገልግሎት እና ለጵጵስና ማዕረግ ብቁ መሆናቸው በውጭ ለሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በአቡነ መርቆርዮስ ሰብሳቢነት ጉዳዩ  የቀረበ እና ብፁዓን አባቶችም ጉዳዩን መርምረው ለጵጵስና ከታጩት ስምንት አባቶች መካከል አንዱ መሆናቸው እና ከስምንቱ መካከል ስድስቱ ጥቅምት 23፣2009 ዓም በኦሀዮ መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን አባቶች ምልዓተ ጉባኤ ሲሾሙ በቪዛ ምክንያት በቦታው ተገኝተው መሾም ያልቻሉት አቡነ ሕርያቆስ (የቀድሞው መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ ለገሰ) ባሉበት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ  መልካም ፍቃድ እና ብፁዓን አባቶች ምርጫ ባሉበት እንዲሾሙ ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዓን አባቶችን ልኮ እንዲከናወን ምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፎ ነበር። በእዚሁም መሰረት ቋሚ ሲኖድስ የምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሰረት መጋቢት 5፣ 2009 ዓም ባደረገው ስብሰባ ሿሚ ሊቃነ ጳጳሳትን በመመደብ  ሹመቱ ሐምሌ 9፣2009 ዓም በብፁዕ አቡነ ኤልያስ መንበረ ጵጵስና በሚገኝበት በስቶኮልም ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን እንዲከናወን  በመጋቢት 20፣ 2009 ዓም ለሿሚ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለአቡነ ኤልያስ እና ስቶኮልም ለሚገኘው ደብረ ሰላም መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በፃፈው ደብዳቤ ማሳወቁን ለማወቅ ተችሏል። በመሆኑም አቡነ ሕርያቆስ መቀመጫቸውን በኦስሎ፣ኖርዌይ አድርገው የአቡነ ኤልያስ ልዩ ረዳት በመሆን ተሹመዋል።


አቡነ ሕርያቆስ ከጵጵስና ሹመት በኃላ ከዲያቆን ናትናኤል እና ዲያቆን ሳሙኤል ጋር 

አቡነ ሕርያቆስ  (ከጵጵስና በፊት በነበራቸው ስማቸው መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ) ማን ናቸው?

ልደት 

ጥቅምት 5፣1968 ዓም ከአባታቸው ከአቶ ለገሰ አዛናው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጥሩ ወርቅ ከበደ በኢትዮጵያ ስማዳ ወረዳ ተወለዱ።

ትምህርት 
እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በተወለዱበት በደብረ ቅዱሳን ዱቄ እየሱስ ከአባ ተፈራ ፀጋው ፊደለ ሐዋርያ፣ ውርድ ንባብና አምስቱ አዕማደ ምስጢርን ከአባ አሳየ ጎሹ በቃል ልዑል ሰምራ በዓታ፣ ዳዊት እና ቅዳሴ ከአባ ይሄይስ ካሳ በቅዱስ ወይራዬ ቅዱስ ገብርኤል ተምረዋል።ከእዚህ በተጨማሪ የሚከተሉትን ትምህርቶች በሚገባ አጠናቀዋል።እነርሱም -

1/ ዜማ 
ከየኔታ ይትባረክ እና ከየኔታ ኪነ ጥበብ ዓለማየሁ በአንጎት ማርያም ተምረዋል።

2/ ቅኔ 
በስማዳ ስመጥር ከሆነው ደብር ቃጨና ኢየሱስ ከየኔታ ዓለሙ፣ እንዲሁም ወደ ምስራቅ ጎጃም ተሻግረው በደጀን ጊዮርጊስ ከየኔታ ናቃቸው ዲበ ኩሉ ተምረዋል።

3/ አቋቋም 
በአጋጥ ሩፋኤል ከየኔታ ተመቸ እና በደብረ ኤልያስ ከየኔታ ወልደ ሚካኤል እና የክብረ በዓላትን እና መዝሙራትን አሰላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ከሊቀ ጉባኤ ጽጌ አክሊሉ ተምረዋል።

3/ ትርጓሜ
ውዳሴ ማርያም፣ ቅዳሴ ማርያም፣ኪዳን፣ትምህርተ ኅቡዓት እና ባሕረ  ሀሳብ የትርጓሜ መምህር ከነበሩት የኔታ ፍስሃ (አበባው) በመቱ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ተምረዋል።

4/ ኮርሶች 
- በመቱ ፈለገ ሕይወት የካህናት ማሰልጠኛ የሶስት ወራት ኮርስ ወስደዋል፣
- አዲስ አበባ በሚገኘው በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአንድ ዓመት ኮርስ ተከታትለዋል።

5/ ማስተርስ፣ ባችለር ዲግሪዎች  እና ዲፕሎማ 
ደቡብ አፍሪካ፣ ጆሃንስበርግ  በሚገኘው ወርልድ ሃርቨስት ቴዎሎጂ ኮሌጅ (World Harvest Theological College _ WHT)  የማስተርስ ዲግሪ በክርስቲያን አመራር (Christian leadership)፣ የባችለር ዲግሪ በነገረ መለኮት (Bachelor of Divinity) እና ዲፕሎማ በመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት( Diploma in biblical studies) ተምረው ተመርቀዋል።

6/ክህነት 
- በ1983 ዓም ዲቁና ከብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣
- በ1991 ዓም ምንኩስና እና ቁምስና ከአቡነ ፊሊጶስ መቱ፣ኤልባቦር ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል 

7/ አገልግሎት 
- ከመጋቢት 1989 እስከ የካቲት 1990 ዓም በኢልባቦር ሃገረ ስብከት እና በደሌ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመሪ ጌትነት፣
- ከ1990 እስከ 1993 ዓም ወደ ሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ከፍተኛ ኮሌጅ ለተጨማሪ ትምህርት እስከተላኩበት ድረስ የኢልባቦር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ አቡነ ቀሲስ በመሆን እና በመቱ የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል መንበረ ጵጵስና ረዳት መሪ ጌታ በመሆን አገልግለዋል።
- ከ2001 እስከ 2005 ዓም በአቡነ ኤልያስ መልካም ፍቃድ የዩጋንዳ መካነ ሰላም መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
- ከ2005 እስከ 2015 ዓም በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ፅርሐ አርያም ስላሴ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ሆነው ለአስር አመታት አገልግለዋል።
- ከ2007 ዓም ጀምሮ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው በጵጵስና እስከተሾሙበት ሐምሌ 9፣2009 ዓም ድረስ አስተዳዳሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በጵጵስና ማዕረግ ከተሾሙም በኃላ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነታቸው የሚቀጥሉ መሆናቸው ሲታወቅ በተጨማሪ የአቡነ ኤልያስ ልዩ ረዳት በመሆን ያገለግላሉ።

በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ እና በአቡነ መርቆርዮስ ፍቃድ መሰረት በአቡነ ሕርያቆስ ሲመተ ጵጵስና ላይ ስቶኮልም፣ ስዊድን መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ከአቡነ ኤልያስ ጋር  በተጨማሪ ተገኝተው ሹመቱን የፈፀሙት ብፁዓን አባቶች የሚከተሉት ናቸው። እነርሱም - 
1ኛ/ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የምዕራብ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ዋና ፀሐፊ፣

2ኛ/ አቡነ ዲሜጥሮስ የምስራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣

3ኛ/ አቡነ ቴዎፍሎስ የካሊፎርኒያ ሃገረ ስብከት ረዳት ሊቀጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣

4ኛ/ አቡነ ማርቆስ የዋሽንግተን ሲያትል እና የፖርትላንድ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።ፎቶ - በሃያኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ከብፁአን አባቶች ጋር አቡነ ኤልያስ ሲናገሩ

በመጨረሻም አቡነ ሕርያቆስ ከላይ ቀደም ብሎ ከተጠቀሱት ተግባራት በተጨማሪ በደቡብ አፍሪካ እስከ ክህነት ድረስ ያደረሷቸው ወጣቶችን በማስተማር አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል። በኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንም ማገልገል ከጀመሩ ገና ሁለተኛ አመታቸው ቢሆንም የአብነት ትምህርት መርሃ ግብር በመክፈት፣የቤተ ክርስቲያኗ የአገልግሎት መዋቅር እንዲሰፋ በማድረግ እና ሁሉንም ምእመናን በአባታዊ ፍቅር በማቅረብ እየሰጡት ካለው አገልግሎት በተጨማሪ የአብነት ትምህርት ዘወትር አርብ በአካል እየሰጡ ሲሆን የያይዝነውን ክረምት ሁለት ወሮች ደግሞ በእየቀኑ ለሶስት ሰዓታት እየተገኙ ትምህርት እየሰጡ ሲሆን በእዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥም አራት ዲያቆናትን ኦስሎ ላይ አፍርተዋል። ለአቡነ ሕርያቆስ እረጅም እድሜ እና መልካም የአገልግሎት ዘመን እንመኛለን።ጉምህርትዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Wednesday, July 12, 2017

በሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ሥራ፣ሕይወት እና አስተዋፅኦ ዙርያ ልዩ ውይይት

 ምንጭ : - አደባባይ (www.adebabay.com) ዩቱዩብ 
አወያይ : ዲ/ን ኤፍረም እሸቴ 
ተወያይ : መምህር ብርሃኑ አድማስ 
ማሳሰቢያ :-  የመጀመርያዎቹ  ጥቂት ሰኮንዶች ድምፁ ዘግይቶ ስለሚጀምር በትግስት ይጠብቁት
ክፍል አንድ
 ክፍል ሁለት 
 ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, June 29, 2017

የተቃወሰ መንግስት ምልክቱ እራሱን ወደ 'አናርኪዝም' ማሸጋገሩ ነው - የኢትዮጵያን የባንክ ኢንዱስትሪ ጉዳይ ይመለከታል


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 


ጉዳያችን/ Gudayachn
ሰኔ 23/2009 ዓም (ጁን 30/2017 ዓም)
++++++++++++++++++++
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ታሪክ የኢትዮጵያ ባንኮች ከሌሎች የአፍሪካ በተለይ ከሣሃራ በታች ካሉት ሀገሮች በተለየ ጥሩ ተአማኒነትን በሌላው ዓለም አትርፈዋል።ለምሳሌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደርግ ዘመን ማለትም ኢትዮጵያ ከቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ጋር ወዳጅ ሆና ሳለም ሳይቀር የምዕራብ ባንኮች በ"ሌተር ኦፍ ክረዲት" የላኪ እና የአስመጪ ሰነዶች ላይ በሚፈፀሙ ክፍያዎች ታማኝነቱ የተመሰከረለት ነው።ለምሳሌ የአሜሪካው "ሲቲ ባንክ" እና የእንግሊዙ "ስታንዳርድ ቻርተር" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰነዶች ላይ እምነታቸው ከፍ ያለ ነው።ለእዚህ ደግሞ ምክንያቱ የስርቆት አደጋዎች በብዛት የማይታዩበት፣ለቀረቡለት የክፍያ ሰነዶች በወቅቱ መክፈሉ እና ለእረጅም ጊዜ በባንኩ የዓለም አቀፍ ባንክ አገልግሎት ክፍል (International Banking Division) ላይ የሰሩት ኃላፊዎች የገነቡት ዓለም አቀፍ ስብዕናም ጭምር ነው።ይህ ማለት ታማኝነቱ በአንድ ጀንበር የተገንባ ሳይሆን የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ከቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ጊዜ ጀምሮ የገነባው ብቁ እና ታማኝ የሰው ኃይል ውጤትም ጭምር ነው። በእርግጥ ደርግ የሆነ ወቅት ላይ በሙያው በቂ ስልጠና የሌላቸውን አስገብቶ እንደነበር እና ይህም ለባንኩ የስራ ጥራት ላይ የእራሱን አስተዋፅኦ ማድረጉን የሚናገሩ አሉ። ይህም ሆኖ ግን በታማኝ የሰው ኃይል እና ስራን በማክበር አይታማም።

በእዚህ ፅሁፍ ማንሳት የፈለኩት ግን ይህንን አይደለም።ስለ የባንኮቻችን በቀውስ ላይ ያለው መንግስት አናርክዝም ወይንም ስርዓት አልበኝነት ሰላባ ስለመሆን ነው።በአሁኑ ጊዜ የግል ባንኮችን ጨምሮ 18 ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ።ይህ በራሱ ጥሩ ነገር ነው። ሆኖም ግን የባንክ ቁጥር መደርደሩ ሳይሆን አጠቃላይ የባንክ ኢንዱስትሪው ለኢንዱስትሪው ስነ-ምግባር እና የንግድ ሕግ ተገዢ ነው ወይ? የሚለው ጉዳይ ወሳኝ ነው።አንድ ባንክ ከሁሉም በላይ በገበያው ውስጥ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገር ተመሳሳይ የገንዘብ ድርጅቶች ዘንድም ታማኝ የሚያደርገው ለደንበኞቹ ያለው ዋጋ ነው።ደንበኞቹ ማለት ደግሞ ገንዘብ ያስቀመጡ እና የምበደሩ የሀገር ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ በውጭ ያሉ ባንኮች እራሳቸው ደንበኛ ባንኮች ይባላሉ።ይህ ማለት የውጭ ባንኮችም ደንበኞቻችን ናቸው ማለት ነው።ባንክ ባንክ ለመባል ትንሹ የሚጠበቅበት እና ለምንም ድርድር የማይቀርበው ጉዳይ ደንበኞች ያስቀመጡትን ገንዘብ በፈለጉ ጊዜ መክፈል መቻሉ ነው።ይህ የባንክ ሀ! ሁ! ነው።ይህንን ማድረግ ያልቻለ ባንክ ባንክ አይባልም።ይህ ሃገራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ግዴታ ነው። የብሔራዊ ባንክ ካሉበት ትልልቅ ሃገራዊ ምጣኔ ሃብታዊ ኃላፊነቶች ውስጥ ትንሹ እና ለድርድር የማይቀርበው የቁጥጥር ቀዳሚ ስራው ውስጥ የንግድ ባንኮች ደንበኞቻቸው ገንዘባቸውን ሲፈልጉ መልሰው  የመክፈል አቅም ሳይኖራቸው ተበዳሪ አገኘን ብለው  ያላቸውን ሁሉ አበድረው ደንበኞች ገንዘባቸውን እንዳያጡ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ ነው። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ታሪክ ውስጥ ጥያቄ ሆኖ አያውቅም። በእዚህ በአሁኑ ዘመን ግን አንድ ሰው በፈለገበት ሰዓት ባንክ ሄዶ ገንዘቡን ለማውጣት ሲፈልግ " ሲስተሙ ችግር አለበት ወይንም ዛሬ ሲስተም የለም" እየተባለ መመለስ የተለመደ ነው። ይህ አይነቱ መልስ በባንኮች ታሪክ በኢትዮጵያ ውስጥ በደርግም ሆነ በሃይለስላሴ ዘመን ተደረገ ሲባል አልሰማሁም።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 'ሲስተሙ አይሰራም' በሚል ምክንያት ደሞዝ ወደ ሂሳባቸው የገባ ሰራተኞች ደሞዛቸውን ሳይወስዱ ከሶስት ቀናት በላይ ይመላለሳሉ።የንግድ ውል ተዋውለው ገንዘቡን መክፈል የሚፈልጉ ነጋዴዎች ባንካቸው ገንዘቡን መክፈል ሳይችል ለሳምንት ልዘገዩ ይችላሉ አልያም ደንበኞች ያስቀመጡትን ገንዘብ ለማውጣት ለቀናት በእዚሁ ሲስተም በሚል ሰበብ ይመላለሳሉ። እዚህ ላይ ሲስተም ተብሎ የሚነገረው በኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ብቸኛ አቅራቢነት የሚሰጠው የኢንተርኔት አገልግሎት ነው።ቴሌን የሚመሩት የኮማንድ ፖስቱም አለቆች ናቸው እና እነርሱ ስለ ንግድ ሕግ፣ ስለ ባንኮች ለደንበኞቻቸው የገቡት ቃልም ሆነ የኢትዮጵያ ባንኮች ለዓለም አቀፍ ባንኮች የገቡት የንግድ ሰነዶች ጉዳይ ሁሉ በወሬ ይሆናል የሚያውቁት። 'ዛሬ ኢንተርነቱን ዝጋው አየሩ ጥሩ አደለም' ካሉ መዝጋት ነው።እዚህ ላይ የባንኮች ለክፍያቸው ታማኝ አለመሆን ያለውን ሌላውን ጣጣ ጉዳያቸው አይደለም። አናርክዝም ወይንም ስርዓት አለበኝነት ማለት ይህ ነው።በሕግ የማይመራ የተቃወሰ መንግስት። በውጪ እና ገቢ ንግዶች ዙርያ ያሉ ክፍያ የሚጠብቁ ዓለም አቀፍ የባንክ የክፍያ መጠየቂያ ሰነዶች ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልጉ እና የክፍያ ሂደቱም ከተባለለት ጊዜ ከፍ ወይም ዝቅ ሳይል መሆን እንዳለበት ይታወቃል። 

አንድ አስመጪ ወይንም ላኪ  እቃው ወደ ሚላክበት ሀገርም ሆነ እቃው ከሚመጣበት ሀገር ያሉ ባንኮች ገንዘባቸው እንዲከፈላቸው የሚፈልጉበት የጊዜ ገደብ በሌተር ኦፍ ክረዲቱ ላይ የተጠቀሰ እና ገዢ እና ሻጭ በገቡበት የውል ሰነድ መሰረት ነው። በሁለቱ ገዢ እና ሻጭ መካከል ከፍተኛ ታማኝ ተብለው የሚያቀባብሉት ደግሞ ኢትዮጵያ ያለው ባንክ እና ውጭ ሀገር ያለው ባንኮች ናቸው። ልብ በሉ። የኢትዮጵያ ቴሌ ሲስተም መዝጋት ስንት የክፍያ ሰነዶች ለቀናት እንዲቀመጡ እና የውጭ ሀገር ባንኮች በእዚህ ሳብያ ስንት ወለድ እንደጠየቁባቸው በእየባንኩ ቤት ያላችሁ መስክሩ።በእዚህ ሳብያ የሚደርሰው ኪሳራ የወለድ ብቻ አይደለም።ወለዱ ቢደመር ኢትዮጵያ በቴሌ እና የኮማንድ ፖስት አለቆቹ ሳብያ ምን ያህል እንደከሰረች መለስተኛ የዳሰሳ ጥናት ቢደረግ አስደንጋጭ እንደሚሆን ለማወቅ ሊቅ መሆን አይጠበቅም። ከእዚህ ሁሉ በላይ ያለው ኪሳራ ግን የኢትዮጵያን መልካም ስም እንዲጠበቅ አድረገው በዓለም አቀፍ ባንኮች ውስጥ ከሁሉም አፍሪካ ሀገሮች በተሻለ ታማኞች የተባሉት የኢትዮጵያ ባንኮችን ስም እንደሚያጎድፍ እና እየቆየም ወደ ጥቁር ዝርዝር መዝገብ እንደሚያስገባን ማወቅ አለብን። 

ለማጠቃለል እነ አባይ ፀሐዬ የቦርድ አባል ሆነው የመሩት የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የስርዓቱ "አናርክዝም" ወይንም ስርዓት አልበኝነት ሰለባ መሆኑ ሌላው የኢትዮጵያ የወቅቱ ህመም ነው።በየትም ሀገር አልፎ አልፎ የሲስተም መቆራረጥ ሊያጋጥም ይችላል። የኢትዮጵያ ግን ኢንተርኔት የሚዘጋው በተደጋጋሚ ያውም በኮማንድ ፖስቱ አለቆች መሆኑን ሲታሰብ እና እያመጣ ያለው ቀውስ ሲታይ የተቃወሰ መንግስት ምልክት መሆኑ በግልፅ አመላካች ነው።በንግዱ ሕግ እና ስነ-ምግባር መሰረት ቴሌ ለባንኮች አገልግሎቱን ሲሰጥ ውል ገብቷል።ባንኮች ደግሞ ለደንበኞቻቸው አገልግሎታቸውን ሲያቀርቡ ውል ገብተዋል።ቴሌ የገባው ውል አገልግሎቱን ሳያቆም ለማቅረብ ሲሆን ባንኮቹም በበኩላቸው ለሚሰጡት አገልግሎት ምንም አይነት መቆራረጥ ሳይኖር ለማገልገል ነው። ስለሆነም በእዚህ የንግድ ትስስር መሃል አንዱ ውሉን ባያሟላ ሌላው ለሚደርስበት ኪሳራ ተጠያቂ ነው።ኪሳራ የደረሰበትም በፍርድ ቤት ቀርቦ ከሶ ካሳ ማግኘት ይችላል። ይህ የአምባገነን መንግስት መኖር እና አለመኖር ጉዳይ አይደለም።በደርግ ዘመን በትክክል ይቻላል።በደርግ ዘመን የነበረው የመብራት ኃይል እና የውሃ ፍሳሽ አገልግሎቶች በእለተ እሁድ የሚሰጡት አገልግሎት የሚቆም ከሆነ ቀድመው ከሶስት ቀናት በፊት በራድዮ እና ቴሌቭዥን እንዲናገሩ የንግድ ውል ሕጉ ያዛቸዋል። ከደንበኛው ጋር ውል ሲገቡ አገልግሎቱን ላያቆሙ ካቆሙ ግን ቀድመው ሊያሳውቁ ነው። ይህ ቀላል የንግድ ውል ሕግ በተቃወሰው የሕውሓት መንግስት ውስጥ አይሰራም። መብራት እና ውሃ እንደሚቆም ሳይነገር ለቀናት መጥፋት የጅመረው በአናኪዝም ወይንም ስርዓት አለበኛው የሕወሓት መንግስት ነው እንጂ በደርግም ሆነ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ  ዘመን ማስታወቂያ ሳይነገር ውሃ እና መብራት አይቆምም።ምናልባት ከዋናው ጣቢያ ሳይሆን በመንገድ ላይ በደረሰ አደጋ አገልግሎቱ ካልቆመ ማለት ነው።በዘመነ ሕወሓት ግን ውሃ እና መብራት ለሳምንት ሲጠፋ ማስጠንቀቂያ የሚባል ነገር የለም። ይህንን ነው ስርዓት አልበኝነት ወይንም አናርክዝም የነገሰበት መንግስት የምለው። የዶ/ር ደብረፅዮን መስርያቤት ለባንኮች የሚሰጠውን የኢንተርኔት አገልግሎት በማቆሙ መክፈል ያለበት በሚልዮን ምናልባትም በብልዮን የሚቆጠር ብር አለበት።ባንኮችም ለደንበኞቻቸው መስጠት የሚገባቸውን አገልግሎት በወቅቱ ባለመስጠታቸው ደንበኞቻቸው በንግድ ስራቸው ላይ ለደረሰባቸው ኪሳራ በፍርድ ቤት ከሰው የመጠየቅ መብት አለባቸው።ይህንን ስናገር በዛሬዋ የተቃወሰ መንግስት ውስጥ ስለ ሕልም እንደማወራ እንደምትገምቱ አውቃለሁ።እንደዚህ አይነት ግምት ላይ እንድንደርስ ያደረገን ግን እራሱ አናርክዝም የሰፈነበት ስርዓት ነው። ቢያንስ ግን መሆን ያለበትን እያወቅን እየሆነ ባለው መናደድ ከቻልን ለነገ መስተካከል ያለበትን ከአሁኑ እያወቅን መጣን ማለት ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Tuesday, June 27, 2017

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም አለው! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የሕወሓት ሀገር ከፋፋይ ቀጣይ አጀንዳ አካል ነው (የጉዳያችን ማስታወሻ)

ጉዳያችን / Gudayacnhn
ሰኔ 21/2009 ዓም (ጁን 28፣2017)
++++++++++++++++++++
ዛሬ ሰኔ 20፣2009 ዓም የሕወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮምያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ የሚኖራት ጥቅም በሚል ርዕስ ውሳኔ ማሳለፉ እና የሕወሓት ኢህአዴግ  99% አሸነፍኩ ወዳለበት ምክር ቤት እንደሚመራ ተነግሯል። ጉዳዩ ልዩ መብት የሰጠ የመሰለው ካለ እርሱ ከ26 አመታት በኃላም ገና ፖለቲካ ሀ ሁ እያለ እንደሆነ መረዳት ያለበት ይመስለኛል።

1/ ልዩ ጥቅም የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?

ልዩ ጥቅም የሚለው አባባል በእራሱ የመከፋፈል አላማ ያነገበ አባባል ነው።አንድ ሰው ልዩ ጥቅም ለማግኘት ዋናው መሰረት ሊሆን የሚገባው በኢትዮጵያዊነቱ ነው እንጂ የታሪክ የበላይነት ወይንም የዘር መሰረቱ ወይንም የተለየ አነጋገር በመናገሩን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ ከሆነ መከፋፈል ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከኢትዮጵያ ምድር በመውጣቱ ነው።ከጃፓን ወይንም ብራዚል የመጣ ሰው የማይኖረው ልዩ ጥቅም ኢትዮጵያዊ ሊኖረው ይገባል።ይህ ማለት ኦሮሞው አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያዊነቱ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ አዲስ አበቤውም በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ኦሮሞው በመቀሌ ላይ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ የአክሱሙም ሰው በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የወለጋው ገበሬ በጎንደር ላይ ልዩ ጥቅም እንዳለው የራስ ዳሽን ገበሬም በነቀምት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ይህ ሁሉ ልዩ ጥቅም የሚመነጨው እንደ ህወሓት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በከፋፋይ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ሙሉ መብት ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ እና መሬት በሁሉም የኢትዮጵያ መሬት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የኦሮምያ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ የሚለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ  በእራሱ ከፋፋይ የሆነው  የስርዓቱ አጀንዳ ቀጣይ ምዕራፍ ነው።

2/ የውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሰጥ አገልግሎት አይደለም እንዴ?

 "የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት በአዲስ አበባ ዙርያ ላሉ የኦሮምያ ክልሎች ያካተተ ይሆናል" ይላል ከአዋጁ አካል ውስጥ አንዱ።አሁንም ውሃ የማግኘት ልዩ መብት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ነው።ይህ አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያዊነቱ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልሎች የውኃ አገልግሎት ላያገኙ ነበር? የውኃ ፍሳሽ አገልግሎት ለማግኘት የልዩ ጥቅም አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያውነታቸው የማግኘት መብት የላቸውም ነበር? ይህ በእራሱ ከፋፋይ አቀራረብ ነው።በአዲስ አበባ ዙርያ ያለ የኦሮሞ ሕዝብ ውሃ ለማግኘት ልዩ አዋጅ መጠበቅ ነው ያለበት ወይንስ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያገኘው መብት ነው መሆን ያለበት? ለአዲስ አበባ ውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ወጪ የሚሸፈነው  ቀረጥ  ከኦሮምያ የሚመጣ ገንዘብም ጭምር መሆኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያረሳሳን ነው ? እናስ የአዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ገና ለገና ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር አብሮ ይነሳብኛል ልከፋፍለው በሚል እሳቤ ውሃ በልዩ ጥቅም አዋጅ መሰረት ይዘረጋልሃል የሚል አዋጅ ረቂቅ አንድ ሐሙስ የቀረው እና የታመመ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካልሆነ ማን ያወጣዋል?   

3/ የጤና አገልግሎትስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?

በአዋጁ ረቂቅ ላይ "አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ በከተማዋ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙሪያ ያሉ የክልሉ ተወላጆችን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል" ይላል። የጤና አገልግሎት የኢትዮጵያዊነት ልዩ ጥቅም ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍልል ቢኖር የጤና አገልግሎት የማግኘት መብቱ ነው።በእዚህ ረቂቅ ላይ አዲስ አበባ እና ኦሮምያ የተለያዩ ሀገሮች ይመስል በአዲስ አበባ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙርያ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ታሳቢ ያደርጋል ሲል ዛሬ ተነስቶ ልዩ ጥቅም የሰጠ አስመስሎ ሕዝብ የመከፋፈል አላማ ለማሳካት ብቻ የተገለፀ ነው።

4/ የአዲስ አበባ ሕዝብ እና የኦሮምያን ሕዝብ ከህወሓት በበለጠ ይተዋወቃል  

በእዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአዲስ አበባ ስም በፊንፊኔ፣የከተማዋ አንዳንድ ቦታዎች እና አደባባዮች በኦሮምያ ታሪክ ይቀየራሉ የሚል ሃሳብ የያዙ አረፍተ ነገሮች እንዲሁም ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር የስራ መጠቀምያ ይሆናል ይላል።ኦሮምኛ የስራ መጠቀምያ መሆኑ አማርኛ እስካልገባው ድረስ ኦሮምያ የተወለደ ኢትዮጵያዊ በኦሮምኛ አገልግሎት ማግኘቱ ሙሉ መብቱ ነው።ዛሬ ህወሓት እንደ ልዩ ጥቅም አድርጎ ማቅረቡ ነው የማይመቸው። ይህ እንዴት ልዩ ሆኖ ይቀርባል? ኢትዮጵያዊ መብቱ በሚለው ስር የሚገባ ነው።አንድ የጋምቤላ ተወላጅ አዲስ አበባ መጥቶ አማርኛ ካልገባው በጋምቤላ አነጋገር አገልግሎት የማግኘት መብቱ ኢትዮጵያዊነቱ ያጎናፀፈው መብት ነው እንጂ ልዩ መብት ሊባል ያችልም። ሕወሓት ለመከፋፈል ስትፈልግ ልዩ መብት ብላ ትርክት መጀመሯ አስቂኝ ነው። የአዲስ አበባ ስያሜ መቀየር እና የከተማዋን ታሪካዊ ቦታ ከመቀየር አንፃር የተነሳው አገላለጥ በእራሱ የተደናበሩ ሰዎች ያወጡት ረቂቅ አዋጅ ነው። በመጀመርያ ደረጃ በአዲስ አበባ ውስጥ የተሰጡት ስሞችም ሆኑ የአዲስ አበባ የእራሷ ስያሜ እውን ታሪካዊ አመጣጥ የሌለው ባዶ ትርክት ከነበረ የታሪክ ሰዎች ይንገሩን እና እንመን።በሐሰት ታሪክ ግን የትም ሀገር ስም አይቀየርም። ይህንን ልሞክር የሚል ካለ የመስቀል አደባባይ እና የአብዮት አደባባይ ስያሜን ማስታወስ ነው።በሕልም እና በስሜት ሕዝብ ያጋጭልኛል ከሚል እሳቤ ብቻ ሕወሓት ይህንን ማሰቧን እራሱ የኦሮሞ ሕዝብ እና የአዲስ አበባ ነዋሪ ጠንቅቆ ይረዳል።

ባጠቃላይ ልዩ ጥቅም በሚል ቡልኮ የተሸፈነው የህወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ አዲስ አበባ እና ኦሮምያን የተለያዩ ሀገር በማስመስል የአዲስ አበባ እና ዙርያዋን ያሉት የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ግንኙነት ኢትዮጵያዊ የሆነ የጋራ እሴት ሳይሆን የጥቅም ግንኙነት ብቻ ያላቸው  አስመስሎ የማቅረብ ሙከራ ነው።መንግስት የተባለ አካል የመጀመርያ ስራው ዜጎቹን በእኩልነት የማስተዳደር፣ሕግ የማውጣት እና የማስፈፀም አቅሙን የማስመስከር  መሆን ይገባው ነበር።ከእዚህ ውጭ አንዱን አስነስቶ በእዚህ አካባቢ ልዩ ጥቅም አለህ።አንተኛው ግን በምትኖርበት ከተማ ከእርሱ ያነሰ ጥቅም ነው የምታገኘው የሚሉ አባባሎች በእራሳቸው ህዝብን ለመከፋፈል የሚደረጉ አጀንዳዎች የማስቀጠል ሥራ አካል ካልሆኑ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም። አዲስ አበባ እና ኦሮምኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል አትሞክሩ።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ሕዝብ የምታገለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እኩል ልዩ ጥቅም እንዲኖረው ነው።

ይህንን ፅሁፍ የምደመድመው አንድ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አክቲቪስት በተናገረው ንግግር ነው። አባበሉ አሁን ሕወሓት እየዳከረበት ካለው የመከፋፈል ከንቱ ሥራ ፍሬ እንደሌለው በሚገባ ያሳየ ነው። አክትቪስቱ ያለው እንዲህ ነበር
"ሕወሓት የኦሮሞ ማሕበረሰብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ያለውን ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር በመቶዎች በሚቆጠሩ  ዓመታት ውስጥ ያለፈ እና ጠንካራ የደም ትስስር መሆኑን ህወሓት በደንብ ያወቀው አይመስለኝም።እነርሱ ራቅ ካለ አካባቢ ስለመጡ የእዚህ አይነቱ ጠንካራ ግንኙነት ታሪክ በደንብ የገባቸው አልመሰለኝም።የኦሮሞ ሕብረተስብ አሁን ሕወሓት እለያይበታለሁ እያለ የሚያቀርባቸው አጀንዳዎችን የመለያያ አጀንዳዎች እንደማይሆኑ ጥንት በሰራቸው ስርዓቶች ካፈረሳቸው ቆይቷል።ሕወሓት ትልቅ የመረጃ ክፍተት ላይ እንዳለ መረዳት አለብን" ነበር ያለው። ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Thursday, June 22, 2017

ስምንት ሚልዮን ሕዝብ በረሃብ የሞት አፋፍ ላይ ባለበት ሁኔታ የጅቡቲ ወደብ በፀጥታ ምክንያት አገልግሎቱ የመታጎል አደጋ ተጋርጦበታል (ጉዳያችን ዜና)

ፍጥጫ - አቶ ኢሳያስ እና ኢስማኤል ኦመር ጉሌህ 

አቶ ጆን ግራም (Mr. John Graham) የሕፃናት አድን ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር በተጨነቀ ስሜት ውስጥ ሆነው ለፕሬስ ቲቪ ይህንን የተናገሩት የትናንትናዋ ጀንበር ሳትጠልቅ ነበር።ጆን ግራም እንዲህ ነበር ያሉት -

    " የሕይወት አድን የምግብ እርዳታው ሊቆም ይችላል። በአንድ ወር ውስጥ ያለው የምግብ ክምችት ያልቃል።ከዝያ ምን እንደሚሆን አሁን መገመት አንችልም " (ፕሬስ ቲቪ፣ ሰኔ 15፣2009ዓም )
"We're looking at the food pipeline actually breaking, so the food is running out in about a month's time," John Graham, country director for Save the Children, said, adding, “After that, we don't know what's going to happen." 
እንደ ቴሌቭዥን ጣቢያው የዛሬ ሰኔ 15፣2009 ዓም ዘገባ በሱማሌ ክልል ድርቁ በተባባሰበት አካባቢ በትንሹ ወደ ግማሽ ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ ቀየውን ትቶ ተሰዷል።የፕሬስ ቴሌቭዥን የኢትዮጵያ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ምትኩ ካሳን ጠቅሶ እንደዘገበው ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የለገሰው እርዳታ አነስተኛ መሆኑን ማማረራቸውን ይገልፃል።

በተባበሩት መንግስት የዓለም ምግብ ድርጅት (FAO) ገለጣ መሰረት ረሃብ ዋነኛ መሰረቱ ድርቅ ብቻ ሳይሆን የመንግሥታት መልካም ያልሆነ አስተዳደር ውጤት መሆኑን በማያሻማ መንገድ ይገልጣል። ከእዚህ በተጨማሪ ረሃብ የሚከተለው የፀጥታ መደፍረስ መሆኑን ይሄው የዓለም የምግብ ድርጅት ሲገልጥ  "በየትኛውም የዓለማችን ክፍል  ረሃብ የፀጥታ ስጋት ነው "  "Hunger anywhere threatens peace everywhere" (FAO Summit, June, 2002) ይላል። 

በኢትዮጵያ አሁን የተንሰራፋው አድሏዊ ስርዓት እና በዕውቀት ላይ ያልተመሰረተ ነገር ግን በሙስና እና ብልሹ አሰራር የተተበተበው የሕወሓት አገዛዝ ከሩብ ክ/ዘመን በኃላም የኢትዮጵያን የእርሻ ምርት አንዲት ስንዝር ሳያራምድ ይልቁንም የኢትዮጵያን ለም መሬት ለአረብ ቱጃር በመቸብቸብ ዛሬም የስምንት ሚልዮን ሕዝብ ርሃብተኛ የያዘች ሀገር ሆና ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ እርዳታው ዘገየ የምትል ሀገር ሆናለች።ይህ እንግዲህ አዲሱ የፈረንጆች 21ኛው ክፍለ ዘመን (ሚሊንየም) ከገባ ከ17 ዓመታት በኃላም መሆኑ ነው ህመሙ።


ከሁሉም የሚዘገንነው ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ራድዮ ድርቁን ከሚገመተው በላይ ደብቀውታል።ሕዝብ ተረባርቦ ወገኖቹን እንዳያድን መረጃው መደበቁ አሁንም በገሃድ እየታየ ነው።የበልግ ዝናብ በብዙ ቦታዎች ላይ በበቂ አለመገኘቱ እና በጎጃም የተነሳውን የአንበጣ መንጋ ትልቅ ስጋት ሆኖ እየታየ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ለመከላከል አሁንም  ምንም አለማድረጉ የህዝቡን ችግር አባብሶታል።የህዝብን መራብ መደበቅ በእራሱ ከሰብአዊ መብት ጥሰት በላይ በዓለም አቀፍ ሕግም የሚያስጠይቅ መሆን እንዳለበት በርካታ አካላት ሲያሳስቡ መቆየታቸው ይታወቃል።በላቲን አሜሪካ እና ሩቅ ምስራቅ አገሮች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ረሃብ የደበቁ መንግስታቶቻቸውን ለፍርድ ቤት እያቀረቡ ማስፈረዳቸው የሚታወቅ  ነው። 

በዓለም ምግብ ድርጅት ማብራርያ መሰረት የርሃብ ምክንያቶች በርካታ መሆናቸውን እና በዋናነት ግን ስድስት መሆናቸውን ይገልፃል። በቅድምያ ፅሁፉ በመግቢያነት የሚይስቀምጠው ነጥብ ''ዓለም ለ7 ቢልዮን የዓለማችን ሕዝብ በቂ ምርት ያመርታል'' በማለት ይጀምርና ስድስቱን በአንድ ሀገር ላይ ርሃብ የሚከሰትባቸውን ምክንያቶችን ይዘረዝራል። እነርሱም : - ድህነት (Poverty trap)፣በእርሻ ላይ በቂ መዋለ ንዋይ አለመመደብ ( Lack of investment in agriculture)፣ የአየር ንብረት ለውጥ 
( Climate and Weather)፣ ጦርነት እና የህዝብ ከስፍራው መፈናቀል (War and displacement)፣ ያልተረጋጋ የምግብ ገበያ ( Unstable Market)፣ የተረፈ ምግብ ብክነት ( Food Wastage)።

የኢትዮጵያን የአሁኑን የርሃብ ችግር የሚያባብሰው አንዱ ጉዳይ በአንድ ወር ውስጥ የመካከለኛው ምስራቅ ግለት ከጨመረ እና በጅቡቲ እና በኤርትራ መካከል ግጭት ከተነሳ የኢትዮጵያ ብቸኛ ወደብ ጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የእርዳታ እህል ብቻ ሳይሆን ነዳጅ ጨምሮ ምንም አይነት ሸቀጥ ላይገባ ይችላል።በሱዳን በኩል ይገባ የነበረው የነዳጅ ምርት በአሁኑ ጊዜ አካባቢው በአማፅያን ኃይሎች በመያዙ ሕወሓት የሱዳን መኪናዎችንም ጭምር መከላከል እንዳልቻለ ይታወቃል።በመጪው ሁለት የክረምት ወራት ደግሞ አማፅያኑ የበለጠ ቦታዎችን ለመያዝ አመቺ ሁኔታ ከወንዝ መሙላት እና ሳሮች ተራሮችን ከመሸፈናቸው አንፃር የሕወሓት ሰራዊት በአብዛኛው ይዞታዎቹን እንደሚያጣ መገመት ይችላል።ምክንያቱም በመካናይዝድ ጦር የተሻለ አቅም የሚኖረው ሕወሓት በክረምት ወራት መንቀሳቀስ ስለማይችል ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ ኤርትራ ሰሜናዊ ጅቡቲ የሚገኘውን ራስ ዱሜራ ተራራማ ቦታ ኳታር 400 የሚሆኑ ወታደሮቿን ማንሳቷን ተከትሎ መቆጣጠሯ የወቅቱ ሌላው አዲስ ክስተት ነው።ኳታር ስፍራውን የለቀቀችበት እለት ማለትም እኤአ ሰኔ 12 እና 13/2017 ዓም  ሲሆን ኤርትራ ስፍራውን የያዘችውም በተመሳሳይ ሁለት ቀናት መሆኑን የጅቡቲ መንግስት ገልጧል።ይህንኑም  ተከትሎ ቀጣዩ ግጭት ኢትዮጵያ የጅቡቲን ወደብ የመጠቀም አቅሟን በእጅጉ ሊፈታተን የሚችል ሁኔታ እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ማለት ኢትዮጵያ ለአፋጣኝ የምግብ ዕርዳታ ብቻ ሳይሆን የጦር መሳርያ ለማስገባትም የጅቡቲ ወደብ ማለት ብዙ ማለት መሆኑ የታወቀ ነው።

በሕውሃት አስተዳደር ወቅት ኢትዮጵያን ከአካባቢው ሀገሮች በስልታዊ የተፈላጊነቷን ደረጃ ዝቅ እንድትል ካደረጋት አንዱ እና ዋናው ጉዳይ የአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ኢትዮጵያ ካለ ወደብ መኖር እንደምትችል በመግለፅ ጉዳዩን ማድበስበሳቸው መሆኑ ይታወሳል። በእርግጥ እዚህ ላይ የሚነሳው ጉዳይ ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት መግባት ነበረባት ወይ? የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ ይታወቃል። ሆኖም ግን የአቶ መለስ ሕወሓት የወደብ ጉዳይን ወደተራዘመ የመደራደርያ አጀንዳነት ማቅረብ ሲችሉ እና አንዳንድ የአሜሪካ ባለስልጣናትም ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት የመሆኗ ዓለም አቀፍ ሕግ እንደሚፈቅድላት ይሄውም 90 ሚልዮን ሕዝብ በ20 ኪሜ ርቀት ካለወደብ ሊቀመጥ አይችልም የሚለው መከራከርያ ጎልቶ የወጣ ግዙፍ ሃሳብ ነበር።የወደብ ጉዳይ የሕወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ማማለያ ካርድ ከሆነ ሰንብቷል።ሕወሓት ውጥረት ውስጥ በሚሆንበት ወቅት የወደብ ጉዳይን እንደ ሰሞኑ ጀኔራል ፃድቃን "ኢትዮጵያ ወደብ ያስፈልጋታል" የሚል አረፍተ ነገር የመሰለ የወቅታዊ ካርድ መዘዛ አንዱ አካል ነው።የጅቡቲ ወደብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሳድ ኦማር ጉለህ 
M. SAAD OMAR GUELPH

ባጠቃላይ ሕወሓት የመዳከሙ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የበለጠ አደጋ ላይ የጣለ ቡድን ለመሆኑ አንዱ መገለጫ ሆኖ እየቀረበ ያለው ብቸኛ የኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ መስመር የሆነው የጅቡቲን ወደብ መከላከል የማይችል መሆኑን አስመስክሯል።የጅቡቲ ወደብ በአንድ መለስተኛ ሮኬት ተኩስ ጠቅላላ ወደቡ የመድን ሽፋን ዋስትና ሊያጣ እንደሚችል እና የዱባይ ኩባንያ በኮንትራት የሚያስተዳድረው የጅቡቲ ወደብ በማንኛውም ጊዜ በፀጥታ ችግር ሳቢያ አገልግሎቱ ሊቆም እንደሚችል አመላካች ነው። የሃያ ስድስት አመታት የሕወሓት አመራር ኢትዮጵያውያ ወደብ አልባ ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት ሀገር ጅቡቲም የምትጠቀምበትን ወደብ መከላከል የማትችል ሀገር ደረጃ አድርሷታል። ይህ የሕወሓት የስልጣን ጥማት እና እጅግ የጠበበ የጎሳ ፖለቲካ ይህንንም ተከትሎ የፍትህ እና ዲሞክራሲ ጥያቄ የሚጠይቁ ኢትዮጵያውያንን የመግደል፣ማሰር እና ማሰደድ ተግባር  ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ያማዳከም ደረጃው ከሚገመተው በላይ ነው።ለእዚህም ነው ኢትዮጵያን ለማዳን ሕወሓት ስልጣኑን መልቀቁ እና የሽግግር መንግስት መመስረት ብቸኛ ወቅታዊ ሃገራዊ ጥሪ ሆኖ የሚቀርበው።

ጉዳያችን GUDAYACHN

www.gudayachn.com


ማጣቀሻዎች 

- ፕሬስ ቲቪ http://217.218.67.231/Detail/2017/06/22/526188/Ethiopi-UN-Warder-Save-the-Children

- የዓለም ምግብ ድርጅት (ዜሮ ሀንገር)   http://www1.wfp.org/zero-hunger 

- የዓለም ምግብ ድርጅት 2002 ጉባኤ   http://www.fao.org/worldfoodsummit/msd/Y6808e.htm
-


Saturday, June 17, 2017

አገራዊ ንቅናቄው የአገራችንን የፖለቲካ ችግር የሚመጥን መፍትሄ ለመፈለግ ጠቃሚ ነው - ፕ/ብርሃኑ ነጋ።የኢትዮጵያ ጉዳይ ከልብ ያሳስበኛል - አቶ ሌንጮ ለታ


በፅሞና መመካከር - ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ሌንጮ ኦስሎ ጉባኤ (ፎቶ ጉዳያችን)


ጉዳያችን ሪፖርታዥ 
ሰኔ 10፣2009 ዓም 
==============
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ቅዳሜ ሰኔ 10፣2009 ዓም በኦስሎ፣ኖርዌይ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ጉባኤ ሁለት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ጋብዞ ጉባኤ አካሂዶ ነበር።ይሄው በኦስሎ የቀይ መስቀል ዋና መስርያ ቤት አዳራሽ የተካሄደው ጉባኤ ላይ ከ200 ሰው በላይ የታደመበት ነበር።በጉባኤው ላይ የተጋበዙት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ነበሩ።

የዝግጅቱን መክፈቻ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሰብሳቢ አቶ ይበልጣል ጋሹ በንግግር ከተከፈተ በኃላ  የመጀመርያ ተናጋሪ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ ነበሩ።
አቶ ሌንጮ "ተቀምጨ እንዳልናገር አጭር ነኝ" በሚል ቀልድ አዘል ንግግር ተሰብሳቢውን ፈገግ ካስደረጉ በኃላ የመተባበር አስፈላጊነት ላይ አፅኖት ሰጥተው ተናግረዋል።በመቀጠልም " በ1966 ዓም ንጉሱ ከስልጣን ሲወርዱ እርሳቸው ይወረዱ እንጂ መጪው ጊዜ የተሻለ እንደሆነ በጣም ተስፋ አድርገን ነበር። ካሉ በኃላ ሆኖም ግን ደርግ መጣ ብለዋል።

አቶ ሌንጮ አያይዘውም ደርግ ሲመጣ ከደርግ የባሰ ሊመጣ አይችልም ብለን ስናስብ የባሰ መጣ።ሆኖም ግን ማሰብ የሚገባን ደርግ ሲገድል በቀጥታ `የፍየል ወጠጤ` እያለ ነበር።ስለሆነም የገደለውን ቁጥር መገመት ይቻላል።የአሁኖቹ ግን በስውር ነው።በስውር ያሰሩት፣የገደሉት እና የሰወሩት ሕዝብ ቁጥር አሁን መናገር አንችልም። ምክንያቱም ሁሉን በድብቅ ነው የሚያደርጉት" ካሉ በኃላ ስለመጭዋ ኢትዮጵያ ማሰብ እንደሚገባ እና እርሳችውንም የሚያሳስባቸው ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።ለዚህም የሱማሌ፣ደቡብ ሱዳን ጉዳይ እያነሱ በሰፊው ለማብራራት ሞክረዋል። አቶ ሌንጮ ኢትዮጵያ እስካሁን እንደ ሀገር እንድትቆይ ካደረጋት ጉዳይ ውስጥ ቀዳሚው ያሉት የህዝቡ ጨዋነት መሆኑን ሲናገሩ እንዲህ አሉ - "ኢትዮጵያን እስካሁን ጠብቆ ያኖራት የህዝቧ ጨዋነት እንጂ የመሪዎቿ ብቃት አይደልም" ነበር ያሉት።በመቀጠልም አቶ ሌንጮ አሁን ያለው መንግስትም ሆነ ተቃዋሚዎች እንዲሁም ሕዝቡም ትኩረት የማይሰጠው ጉዳይ የህዝብ ቁጥር መጨመር እና እርሱን ተያይዞ የሚመጣው የአካባቢ ብክለት፣ የማህበራዊ ኑሮ መዳከም እና የህዝብ ኑሮ ማሽቆልቆል ዋነኞቹ ችግሮች ውስጥ እንደሚካተት አብራርተዋል።

ከጉባኤው ተሳታፊዎች በከፊል 


በመቀጠል ንግግር ያደርጉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ነበሩ።ፕሮፌሰሩ ንግግራቸውን የጀመሩት ሶስት ነገሮችን በቅድምያ ካላወቅን ነገን ለማወቅ ያስቸግረናል በሚል መነሻ ነጥቦች ነበር። እነርሱም : -

1/ አሁን የገጠመን ባላንጣ (የወያኔ ስርዓት) ብሔራዊ ጥቅም የሚባል ነገር የማያውቅ፣ ስርዓቱ ስልጣኑን የማያስጠብቅበት ሁኔታ ከተፈጠረ ሁሉ ነገር እንዲወድም የሚሰራ ስርዓት መሆኑን፣

2/ የሀገራችን ፖለቲካ  በብዙ ምክንያቶች ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ያለ መሆኑ እና 

3/ የህዝባችን የሞራል ደረጃ እየወረደ መምጣቱ የሚሉት መሆናቸውን አብራርተዋል።

ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች የአገር አድን ንቅናቄው መፍትሄ መሆኑን ለማመላከት ንቅናቄው እንዴት ችግሮች ይፈታሉ ብሎ እንደሚሰራ አብራርተዋል።

ለመሆኑ የአገር አድን ንቅናቄው ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች የሚሰጣቸው ስልታዊ ምንድን ናቸው? በሚል በጥያቄ ንግግራቸውን የቀጠሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ንቅናቄው በሚከተሉት ስልታዊ መንገድ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር የመፍታት አቅም እንዳለው አብራርተዋል።

1/ በሚደረጉ የንቅናቄው ውይይቶች መጥራት የሚጎዳላቸው የሃጋራችን የፖለቲካ ችግሮች እንዲጠሩ በማድረግ፣ 

2/ በውይይቱ ሂደት መስማማት።በሂደቱ ላይ ከተስማማን በውጤቱ ላይ መስማማት መጨረሻ የሚመጣ ጉዳይ ነው። አሁን የውይይቱ ሂደት ዲሞክራሲያዊ መሆኑ ላይ መስማማት እና ውጤቱን ደግሞ ሕዝብ እንዲወስን መተው ነው።

በዲሞክራሲ ሂደት ላይ ከተስማማን በሌሎች ጉዳዮች ላይ ልዩነት አይኖርም ማለት አይደለም።ለምሳሌ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ እና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ የግድ ላንስማማ እንችላለን። ሆኖም  ግን የቀሪ ልዩነታችን መፍቻ ዲሞክራሲያዊ አፈታትን ስለመረጥን ብዥታ አይኖርም  ማለት ነው።

ለጨረታ የቀረበው እና ከበርገን ከተማ የመጡ የጉባኤ ታዳሚዎች በ16 ሺህ የኖርዌይ ክሮነር የወሰዱት ስዕል 

ከእዚህ በተጨማሪ የጋራ ንቅናቄው ምን እያደረገ ነው? ለሚሉ ጥያቄዎች  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሲያስረዱ አገራዊ ንቅናቄው - 

ሀ) ዋና ጉዳዮች ላይ ማትኮር መቻሉ ፣

ለ) ሌሎች ድርጅቶችን እያሰባሰበ ወደ አንድ ነጥብ ማምጣት ላይ እየሰራ መሆኑ፣

ሐ) ድርጅቶችን ማቀፉ የትግሉን መልክአ ምድራዊ ሽፋን ማስፋቱ እና አገራዊ ቅርፅ መያዙ፣ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው። 

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት የንቅናቄው ተግባራት በምሳሌ ካስረዱ በኃላ የወያኔን ውድቀት ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ሶስት አበይት ጉዳዮችን ጠቅሰዋል። እነርሱም -

1ኛ) የጠራ መንገድ በትግሉ ሂደት መያዝ፣

2ኛ) መሬት የያዘ ትግል ማካሄድ እና 

3ኛ) ወያኔ ያዳከመብንን ሞራላዊ ልዕልና መልሰን መገንባት እና ማምጣት የሚሉ ናቸው።

ከላይ የተጠቀሱት ሶስት አበይት ጉዳዮች ውስጥ የሞራል ልዕልናችንን መልሰን መገንባት የእረጅም ጊዜ ስራችን መሆን ያለበት ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ግን በፍጥነት የሚሰሩ እና አሁን እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች መሆናቸውን አውስተዋል።

በእዚሁ ጉባኤ ላይ ከነበሩት የፕሮፌሰር ብርሃኑ እና አቶ ሌንጮ ንግግሮች በተጨማሪ የጥያቄ እና መልስ መርሃ ግብር ነበር።በጥያቄ ከተነሱት ውስጥ አሁን ያለነው ወጣቶች በወያኔ ዘመን ያደግን ስለሆነ ስለ ጎጥ እየሰማን ስላደግን ኢትዮጵያዊ ስሜታችን ሳይጎዳ ለመጠበቅ ምን ማድረግ ´አለብን? የሚል የነበረ ሲሆን አቶ ሌንጮ ሲመልሱ - 

"በኢትዮጵያ ታሪክ ማንም ንጉስ ከእዚህ ብሔር የመጣሁ ነኝ ብሎ አያውቅም።በኢትዮጵያም  ጨቋኝ  የሚባል ብሔር የለም።የጨቆነ ከአንድ ብሔር የወጣ ቡድን ቢሆን ይህ ቡድን ብሄሩን ይወክላል ማለት አለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።" ብለዋል።በመጨረሻም አቶ ሌንጮ " እኔ ኦሮሞም ኢትዮጵያዊም መሆን እፈልጋለሁ።" ብለዋል። በማስከተልም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያዊነት ከኢትዮጵያዊው ወጣት ትውልድ ውስጥ ወጥቷል የሚል ፈፅሞ ግምት እንደሌላቸው እና ለእዚህም በርካታ  ማስረጃዎች መኖራቸውን አብነት እየጠቀሱ አስረድተዋል።

በመጨረሻም በዋናነት የፕሮፌሰር ብርሃኑን እና አቶ ሌንጮ ለታን ንግግር፣ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች መመለስ፣የገቢ ማሰባሰቢያ ጨረታ የተካሄደበት ጉባኤ ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ እንግዶችን በክብር በመሸኘት ተፈፅሟል።ባጠቃላይ በእዚህ ጉባኤ ላይ የታየው ከፍተኛ ዲስፕሊን፣የሰዓት አጠቃቀም እና የመድረክ መስተንግዶ ሁሉ የተዋጣለት እና ደረጃውን የጠበቀ መሆን የጉባኤውን ተሳታፊዎችንም ሆነ እንግዶችን ያስደሰተ ተግባር ሆኖ አምሽቷል። 


ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Friday, June 16, 2017

ሰበር ዜና - አዲስ አበባ የሚለውን ስም እና የጎዳናዎቿን ስም ለመቀየር በሕወሓት የሚታዘዘው የኢህአዴግ ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባ ይቀመጣልሃያ አባላት እንደቀሩት የሚነገረው በሕወሓት የሚታዘዘው የኢህአዴግ ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 10፣2009 ዓም የአዲስ አበባን ስም ወደ ፊንፊኔ ለመቀየር፣የአዲስ አበባ ጎዳና ስሞችን በኦሮሞ ታሪክ ስሞች ለመቀየር፣የአዲስ አበባን የስራ ቋንቋ ኦሮምኛ ለማድረግ፣የኦሮምኛ ተናጋሪዎች አዲስ አበባ ላይ መሬት ካለ ሊዝ እንዲወስዱ ለመፍቀድ እና በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ሁሉም መስሪያ ቤቶች ሥራ አስኪያጆች በኦሮሞ ተወላጆች ለመቀየር በሚሉ የውሳኔ ሃሳብ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ለማወቅ ተችሏል። ዜናውን ከአስተማማኝ ምንጭ መገኘቱን የኢሳት ራድዮ እና ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በእየፊናቸው ሰኔ 9፣2009 ዓም ምሽት ገልጠዋል።

ሕወሓት አዲስ የመነታረኪያ አጀንዳ ለመሃል ሀገር ለመስጠት እና በዐማራ ክልል የተነሳበትን ብረት ያነሳ ሕዝባዊ ኃይል ለመዋጋት ያቀደ ይመስላል።አሁን በአዲስ አበባ ላይ ሊወሰድ ነው የተባለው እርምጃ ውሎ አድሮ እራሱ ሕወሓትን ጠልፎ እንደሚጥለው ለማወቅ ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ማሰብ አያስፈልግም።

ከእዚህ በታች አለምነህ ዋሴ ጉዳዩን አስመልክቶ የለቀቀውን ዜና ያዳምጡ።ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, June 12, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ለመጀመርያ ጊዜ አዲስ አበባ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ገለጠ

Patriotic-Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy attacks TPLF´s secret torching house and armament store in Addis Ababa 

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ለመጀመርያ ጊዜ አዲስ አበባ ከተማ  ውስጥ በሚገኝ የስርዓቱ የሚስጥር ማዕከል ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ።ጥቃቱ የተፈፀመው የቀድሞው ናዝሬት አውቶብስ ተራ አጠጋብ በሚገኝ የሕወሓት ድብቅ ማሰቃያ እና የመሳርያ ማከማቻ ላይ መሆኑን ይገልጣል።ይህ በአዲስ አበባ የድርጅቱ ሴል በኩል መፈፀሙ የተገለጠው ጥቃት የሚስጥር ማሰቃያ ቤቱንም ሆነ የመሳርያ ግምጃ ቤቱን ሙሉ በሙሉ እንዳወደመው እና ውድመቱ በቶሎ ሳይጠፋ መቆየቱን እና የአዲስ አበባ ህዝብም ለሰዓታት እንዲመለከተው መደርጉን ዜናው ያብራራል።

ድርጅቱ ለኢሳት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ዛሬ ሰኔ 5፣2009 ዓም በላከው ዜና ላይ መለቀቁን ለማወቅ ተችሏል።ከእዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ቦታዎች በስርዓቱ ወታደራዊ ኃይል ላይ ጥቃት መፈፀሙን እና ከስልሳ በላይ እስረኞችን ማስለቀቁን ገልጦ ነበር።ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሕወሓት በኩል የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች በፈቃዳቸው ወደ መንግስት እጃቸውን ሰጡ የሚል ዜናም የተለቀቀው ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ነበር።

በሌላ በኩል የመንግስት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ የሚለው ዜና ድርጅቱ ጥቃት የመፈፀሙ አፀፋ ፕሮፓጋንዳ ሆኖ መቅረቡ በትክክልም አንድ አይነት ግጭት መኖሩን አመላካች ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው።የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ላለፉት ሁለት የሳምንታት መጨረሻዎች በሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ በተዘጋጁ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ንግግር ማድረጋቸው ሲታወቅ በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ ሰኔ 10 ኦስሎ ኖርዌይ፣ ሰኔ 11 ደግሞ በስዊዘርላን ተመሳሳይ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ላይ እንደሚገኙ ከድርጅቱ የወጡ ዘገባዎች ጠቁመዋል።

ከእዚህ በታች አባይ ሚድያ ላይ የአዲስ አበባውን ጥቃት አስመልክቶ የወጣው ዜና ነው። 

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Tuesday, May 30, 2017

የኢትዮጵያ ሀገር አድን የጋራ ንቅናቄ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ እና መጪ የፖለቲካ ጉዳይ አንፃር (የጉዳያችን ዕይታ )


ጉዳያችን/ Gudayachn
ግንቦት 23፣2009 ዓም / May 31,2017 

መንደርደርያ ኢትዮጵያ በታሪካዊው ምርጫ ዋዜማ 

ወቅቱ ኢትዮጵያ አዲሱን ምዕመት ልትቀበል ሽር ጉድ እያለች የነበረበት ወቅት ነበር።በኢትዮጵያ በ1997 ዓም የተደረገው ምርጫ ውጤት በሕወሓት/ኢህአዴግ (የዚያን ጊዜው ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ሕዝብ በአደባባይ በግልፅ ከተካደ በኃላ የኢትዮጵያውያን ምሁራን ደት በአዲስ መልክ የተንቀሳቀሰበት ጊዜም ነበር።ከእዛን ጊዜ በፊት ለትምህርት ወደውጭ የሚሄዱ ወጣቶች ሁሉም ባይሆኑም የሀገሪቱ መንፈስ የምርጫ ንፋስ እየሸተተው እና ትውልዱም ከአሁን በኃላ በኢትዮጵያ ምድር ስልጣን በደም መፋሰስ ሳይሆን በሰላማዊ ምርጫ ሆን ነው የሚል ከፍ ያለ ሕልም ሁሉም ሰንቆ የነበረበትም ወቅት ሆኖ አልፏል።በተለይ በምርጫው ክርክር ወቅት ሁለት ነገሮች ገሃድ ሆኑ።አንድኛው ኢትዮጵያ ከሕወሓት/ ኢህአዴግ ውጭ እጅግ አቅም ያላቸው እና ሀገሪቱን በአጭር ጊዜ ወደተሻለ ደረጃ የማድረስ ርዕዩም ሆነ ልምዱ ያላቸው ምሁራን እንዳሉ በግልጥ ታየ። ሁለተኛው ሀገሪቱን የመራ ያለው ስርዓት ቀድሞ ሕዝብ ከሚያውቀው እና ከምገምተው በላይ ከአቅም በታች በሆኑ እንደ ወቅቱ አጠራር (ከአፍንጫ እንሰ ከንፈር ብቻ የሚያስቡ) ሰዎች የሞሉበት እንደሆነ ታወቀ።ብዙ ሰው አቶ በረከትን፣አቶ ስዩም መስፍንን እና ሌሎች የሕወሓት ባለስልጣኖች ቀድሞ ከሚያውቃቸው በታች እጅግ ዝቅ ያለ አቅም እንዳላቸው አወቀ። ማወቅ ዕዳ ነው እንደሚባለው ይህንን ማወቁ ቀድሞ ከነበረው የለውጥ ስሜት የበለጠ በናረ መልኩ ምርጫው ሃገርን የማዳን ራ አካል መሆኑን ሕዝብ አመነበት።ሃገርን የማዳን ሥራ የሚለው አስተሳሰብ በሕዝብ ዘንድ መስረፅ የጀመረው በቅርብ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በሁሉም ሕዝብ ዘንድ የተናኘው በእዚሁ በከሸፈው ምርጫ ወቅት ነበር። ይህ ትክክል አስተሳሰብ ነው።የተሳፈርክበት መኪና ሹፌር ከአቅም በታች መሆኑን ስትረዳ መክናውንም አንተንም ሲቀጥል እራሱ ሹፈሩንም ለማዳን መነሳት ተገቢ ነው።የኢትዮጵያ ህዝብም ያደረገው ይህንኑ ነው።የበለጠ ሲያውቅ የበለጠ ሃገሩን ለማዳን በሰላማዊ መንገድ ቆረጠ

ከ1997 ዓም ምርጫ ክሽፈት በኃላ የኢትዮጵያውያን ስደት 

አመታት በነጎዱ ቁጥር የኅብረተሰብ አስተሳሰብ፣አኗኗር እና የትግል መንገድ ሁሉ ይቀየራል።ከ1997 ዓም ወዲህ ኢትዮጵያ በበርካታ አሰቃቂ የፖለቲካ ምች ተመታለች። ከአዲሱ ሚሊንየም ማለትም ከ2000 አመተ ምህረት ወዲህ ብቻ  የዓለም ምሁራንን ፍልሰት ስታትስቲክስ ጠቅሶ የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ እንደዘገበው በምሁራን ፍልሰት በአፍሪካ ቀዳሚ ኢትዮጵያ መሆኗን እና በዓለም አቀፍ ደረጃም ቀላል ታ እንደሌላት መዘገቡን የእዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ ያስታውሳል።ባጭሩ በአሜሪካ፣አውሮፓ እንዲሁም አፍሪካ ሳይቀር ለትምህርት የተላኩ ወጣቶች ሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሳይመለሱ የቀሩት በተለየ መልኩ ከ1997ዓም ወዲህ ነው። ይህ ሁኔታ በደርግ የስልጣን ዘመን የነበረ ቢሆንም ደርግ በወደቀባቸው የመጀመርያ ዓመታት የመሻሻል አዝማምያ ታይቶ ነበር። 

በንጉሡ ዘመን የምሁራን ስደት ችግር ተብሎ የማይታሰብ እንደነበር እና ለትምህርት የሄዱ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ይልቁንም የምረቃ ጊዜ ሳይደርስ ወደ ሀገር ት እየመጡ የዲግሪ ሰርተፍኬታቸው ይላክላቸው እንደነበር ወቅቱን የሚያስታውሱ የሚናገሩት ጉዳይ ነው። በእንግሊዝኛ የሚታተመው "ኢትዮጵያን ሄራልድ" እኤአ 2015 ህዳር 10 ቀን " The Menace of Brain Drain On Ethiopia's Development" በሚል ርዕስ ሥር ባውጣው ዘገባ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ይገኛል።
 " Prior to 1974 revolution virtually all Ethiopians who attended university in the country remained at home and the vast majority of those who studied overseas returned to Ethiopia. According to one study, only one Ethiopian physician was working outside the country as recently as 1972. The brain drain has not always been a problem in Ethiopia.

" ከ1966 አብዮት በፊት በውጭ ሀገር ዩንቨርስቲዎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ከነበሩ ኢትዮጵያውያን ውስጥ ብዙዎቹ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ነበር።አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በ1964 ዓም ከኢትዮጵያ ውጭ ቀርቶ ለሌላ ሀገር ይሰራ የነበረ ኢትዮጵያዊ አንድ ሀኪም ብቻ ነበር።የምሁራን ፍልሰት በእራሱ ለኢትዮጵያ ችግር ተብሎ የሚወራ አልነበረም"

የኢትዮጵያውያን ስደት  በሕወሓት ዘመን እጅግ የከፋ እና ኢትዮጵያውያን በየትኛውም ዘመን ደርሶባቸው የማያውቅ መከራ ነው።ድንበር የለሽ ሀኪሞች ድርጅት (MSF) የኢትዮጵያውያን ስደት ርነት ወደሚደረግባት የመን ጭምር መሆኑ ምን ያህል አሰቃቂ ጉዳይ በሀገራቸው እንደገጠማቸው የሚያመላክት መሆኑን በገለጠበት እኤአ 2008 ዓም  ላይ ያቀረበው አመታዊ ሪፖርት ላይ በአንድ ወቅት ከደረሱት ስደተኞች ላይ በተወሰደ መረጃ ከስደተኞቹ ውስጥ 30% ቶች ሲሆኑ የቀሩት 70% ወንዶችን ምሮ ከሁለቱም ታዎች ውስጥ 54% የሚሆኑት በትዳር ይኖሮ የነበሩ እና ትዳራቸውን ትተው የተሰደዱ መሆናቸውን ይገልጣል። ይህ በገሃዱ አለምም የምናውቀው እውነታ ነው።በአረብ ሃገራት ተሰደው ከሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን እናቶች በትዳር ላይ እንደነበሩ እና ልጆቻቸውን እና ባለቤቶቻቸውን ትተው የተሰደዱበት ጉዳይ የከፋ የምጣኔ ሀብት መገለል ይህም የፖለቲካ ተፅኖ ውጤት እንደሆነ የታወቀ ነው።ባጭሩ ግን ስደት የሀገር መፍረስ ዳርዳርታ ነው።እዚህ ላይ ሀገር ማዳን የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ምን ያህል ጋ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን መረዳት አያስቸግርም።ጥያቄው ማን ነው ሃገርን የማዳን ኃላፊነት መውሰድ የሚገባው? የሚለው ነው።

የኢትዮጵያ አደገች ሮፓጋንዳ እና የስልጣን መጠበቅያ መሣርያነቱ 

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከአዲሱ ሚሊንየም (2000ዓም) ወዲህ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ብዙ ጉዳዮች እየተቀያየሩበት መጥተዋል።በሀገር ውስጥ በምርጫ ማጭበርበር እፍረት ያልተሰማው ሕወሓት አቶ መለስን ከፊት አስቀድሞ ኢትዮጵያ እያደገች ነው የሚል አዲስ ትርክት ይዞ ብቅ አለ።አቶ መለስ ልማታዊ መንግስት መርሆዎች የሚል ፅሁፍ ሲበትኑ አጫፋሪ ካድሬዎች በሚገባ እንዲያዳንቁ ከተላለፈ ሚስጥራዊ ትእዛዝ ጋር ነበር።የአቶ መለስ ዜናዊ ልማታዊ መንግስት አገላለፅ ግን ውስጠ ወይራ መሆኗን ይልቁንም የአንድ ጎሳ የበላይነትን ለማውጣት ውስጣዊ አጀንዳ የያዘ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው።ከላይ በሚታየው ገፅታው ግን የአቶ መለስ ዜናዊ ፅሁፍ የመንግስትን ሚና ሲገልፅ 
" Role of the government should be limited to the protection of individual and property rights, enforcement of contracts, and safeguarding competition among economic actors" 
" የመንግስት ሚና መሆን የሚገባው የግለሰብ መብትን  እና የንብረት መብትን ማስከበር እንዲሁም በምጣኔ ሃብቱ ውስጥ ለሚኖሩ የእርስ በርስ ውድድሮች ዋስትና መስጠት ነው" ይላል።ይህ አባባል ግን ከእውነታው እና በገሃዱ ዓለም አቶ መለስ እና አስተዳደራቸው ሲያደርግ ከነበረው ጋር ፈፅሞ የተቃረነ ነበር።በሕወሓት ዘመን መንግስት ለግለሰቦች ነፃነት እና ንብረት ዋስትና ሲሰጥም ሆነ ለጤናማ ውድድሮች ዋስትና  የሰጠው መቼ ነው? ሌላው ቀርቶ በከተማ ቦታ ይዞታ ላይም ሆነ በገጠር መሬት ላይ ኢትዮጵያውያን ካለምንም ዋስትና ከቦታቸው የተነቀሉት በሕወሓት ዘመን ነው።የአቶ መለስ ፅሁፍ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባሉ ምሁራን ይህንን ያህል የከበደ ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከልማት ጥናቶች የተገለበጠ መሆኑ ስለታወቀ ትኩረትን ከካድሬዎች ባለፈ አልሳበም። አቶ መለስ ግን በዙርያቸው ያሉትን የእራሳቸውን ተቀናቃኞች ለማጥቃት አዲስ ሃሳብ ይዘው የመጡ መስለው ታይተውበታል። 

ከእዚሁ ጋር ተያይዞ ሕወሓት እንደ ጊዜያዊ የአመፅ ማስታገሻ ክኒን የተጠቀመበት ኢትዮጵያ በሁለት ዲጅት እያደገች ነው የሚለውን አባባል ነው።ለእዚህም ከሙሰኛ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር በመሞዳሞድ ኢትዮጵያ አደገች የሚል ሪፖርት መዥጎድጎድ ጀመረ።ሆኖም ግን የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ባለሙያዎችም ሆኑ አቶ መለስ እና ስርዓታቸው አንዲት ሀገር በጠቅላላ ምርት ድምር በማስላት አደገች የሚለው መርህ በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) ሳይቀር ከተተወ እና ሀገሮች ማደጋቸው የሚለካው በተለያዩ መስፈርቶች ማለትም እያንዳንዱ ግለሰብ ካለው የትምህርት፣የጤና፣የገበያ፣የዲሞክራሲ እና ነፃነት ዕድል አንፃር መሆኑን ያውቃሉ።ሆኖም ግን በዓለም አቀፍ መድረክም እድገትን አስር የማይሞሉ የስርዓቱ ሰዎች በጠቀራመጡት  ሀብት አንፃር ሪፖርት እያቀረቡ ህዝቡ አደገ እያሉ ሲናገሩ ምንም አይነት እፍረት አላሳዩም። በእዚህ በቁጥር ማምታታት የአፍሪካ ሀገሮች "ከእጅ አይሻል ዶማ" እንዲሉ በእየቤታቸው እሳት ስላለ የኢትዮጵያ እድገት እያሉ መለፈፋቸው አልቀረም። እዚህ ላይ ኢትዮጵያ እድገት ፈፅሞ የላትም በ1983 ዓም በነበረችበት ቦታ ነች እያልኩ አይደለም።የከተሞች ማደግ፣የግንባታ መስፋፋት እና የመንገዶች መገንባት አዎንታዊ ነገር ግን በብዙ ብድር እንደተሰሩ ይታወቃል።ጥያቄው ግን ይህ ልማት ነው ወይንስ የቁጥር እድገት ነው? የሚለው ነው። ልማት እያንዳንዱ ሰው ሕይወትን የማሻሻል ኃይል አለው።የእድገት ቁጥር ግን የጥቂቶች ሀብታምነትን እና የብዙሃኑን የምጣኔ ሀብት ባርያ መሆንን ያሳያል። 

ኪኒን ጨምርልኝ    

የሕወሓት የራስ ምታት ክኒን ማለትም አድገናል የሚለው ፕሮፓጋንዳ ለጥቂት ጊዜ ጎማውን ለማሽከርከር ጠቀመው እንጂ ብዙም  አላራመደውም ይልቁንም 11% የምትለዋ ትርክት በእየሻይ ቤቱ መቀለጃ ሆነች።ከ1997 ዓም የምርጫ ክህደት በኃላ ሕወሓት ሕዝቡንም ሆነ ሚድያውን በሥራ የወጠረባቸው ጉዳዮች የመጀመርያው የሚሊንየም አከባበር ግርግር በመቀጠል የልማታዊ መንግስት ሃሳቦች ፕሮፓጋንዳ እና ኢትዮጵያ በሁለት ዲጅት አደገች የሚሉት ሁሉም ብዙ እርቀት አላስኬድ አሉ። የእዚህን ጊዜ አዲስ ሕዝብ የሚወጥር ጉዳይ ይዞ መምጣት ተፈለገ።የአባይ ግድብ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ግድብ ካርድ ተመዘዘ። ይህ የግድብ ሥራ ለኢትዮጵያ ያለው ጥቅም ምንም የለም ከሚል እሳቤ መነሳት አይቻልም።ጉዳዩ ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን ጀምሮ ብዙ ተብሎበታል።በንጉሱም ዘመን የተያዙ እቅዶች እንደነበሩ እና የግብፅ ደህንነቶች በብርቱ ጉዳዩን ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል። ስለሆነም ግድቡን በጭፍን ማጥላላት በጎ ሃሳብ አይደለም።እስካሁንም በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የእዚህ አይነት ሃሳብ ሲያንፀባርቅ አልታየም።የስርዓቱ ደጋፊዎች ግን ለፕሮፓጋንዳ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ያላለውን ሲናገሩ ግን ተሰምተዋል። የኢትዮጵያ ሌቭዥንም አስተጋብቶላቸዋል። የአባይ ግድብ ጉዳይ በሕወሓት በኩል ሲቀርብ ግን ታስቦበት እና ታልሞ ሳይሆን የመቆያ ክኒን ጨምርልኝ መልክ ነው።ሕዝብ የሚወጥር፣በተስፋ የሚያስፈነድቅ እና ሕወሓትን ጀግና የሚያስብል ሃሳብ ተደርጎ ተወሰደ።ለእዚህም ማስረጃው እቅዱ በአምስት ዓመቱ የልማት እቅድ ላይ የሌለ እና የበጀት ምንጩም የድሀውን ኢትዮጵያዊ ጎጆ የበለጠ የሚያሟጥጥ መሆኑ ነበር።በሌላ በኩል ሕወሓት የመጀመርያ የአባይ ቦንድ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዋሽንግተን ላይ ሲያዘጋጅ ጀምሮ ኢትዮጵያውያንን አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን በስብሰባው ለመሳተፍ ሲሄዱ ከበር ላይ እየመረጠ አስቀራቸው።በእዚህም የአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጉዳይ ሳይሆን የፖለቲካ መሳርያ መሆኑን በይፋ አወጀ።

በአባይ ግድብ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያን ምሁራንም ሆኑ የውጭ ባለሙያዎች የሚሰጡት ሁለት መሰረታዊ ሃሳቦች አሉ። በቅድምያ ግን ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውሃ ማመንጨት አቅም እንዳላት እና ይህንን መጠቀም እንዳለባት የሁሉም ስምምነት ነው።ምሁራኑ ግን የሚያነሱት ሁለት ነጥብ።አንደኛ ኢትዮጵያ በእርሻ ምርት እራሷን ሳትችል ይህንን ያህል ግዙፍ የሀገር ሀብት የሚበላ ፕሮጀክት ላይ ሙሉ ኃይሏን ማሳረፍ ሃገሩን ሊያፈርስ የሚችል አደገኛ ውሳኔ ነው የሚል ነው።ለእዚህም ማስረጃው ፕሮጀክቱ የመንግስትን ለልዩ ልዩ ወጪ መዋል የሚገባው ሀብት ከመውሰዱ በላይ እያንዳንዱ ምስኪን ኢትዮጵያዊም ከጉሮሮው እየነጠቀ እንዲያዋጣ ማድረጉ በእራሱ ድህነትን ማስፋፋት ነው የሚል ሲሆን። ሁለተኛው ደግሞ በአሁኑ ዘመን ግዙፍ ግድብ መገንባት በጥቂት አመታት ውስጥ ግድቡ በደለል ሲሞላ ግድቡን ለማፅዳት የሚጠይቀው ወጪ በእራሱ የግድቡን መስርያ ለማከል ይቃጣዋል የሚል ነው።ለእዚህም አማራጭ የሚያቀርቡት በአውሮፓም ሆነ ሌሎች ሃገራት እንደሚደረገው በርካታ አነስተኛ ግድቦችን ማብዛት እና ኤሌክትሪክ ማመንጨት ይቻላል።ይህም ከፀጥታ ጥበቃም ሆነ የመስኖ ስራን ከማስፋፋት አንፃር ብዙ ጥቅም አለው የሚለው ይጠቀሳል።

ከእዚህ በተለየ ግን የሕወሓት መንግስት በግድቡ ግንባታ ላይም ካለጨረታ የሰጠው የጣልያኑ ኩባንያ እና የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች በስራው ላይ ካለምንም ተቀናቃኝ መግባት የግንባታውን አላማ ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች በላይ አላማ እንዳለው የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው።ይህም ሆኖ ግን አሁን አሁን ስለ ግድቡ ጉዳይ መሰረት የተጣለበትን ዓመት ከማክበር ባለፈ ወሬው እየራቀ መምጣቱ የብዙ ኢትዮጵያውያን የሹክሹክታ ወሬ ሆኗል።  

ከሶስተኛው ክኒን በኃላ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ህወሓት ለማስታገሻነት የተጠቀመበት ነገር ግን ምንም ፍሬ ያልያዘለት የጥልቅ ተሃድሶ ጉዳይ ነበር።አቶ ኃይለማርያም ትልቅ ተሃድሶ፣ሙስና እያሉ ጫፍ መናገር ስጀምሩ በደረሰባቸው ከባድ የአንድ ወገን ምት አሁን ሙስና የምትል ቃል ከንግግራቸው አውጥተው እና ለገሃር ላይ የሚገኘው የፀረ ሙስና ሚሽን መስርያ ቤት ሲፈርስ እና በአርብቶ አደር መስርያ ቤት ሲገባ የመክሰስ መብቱም በፖሊስ ኮሚሽን ስር ሲወድቅ እያዩ ድምፃቸውን አጥፍተዋል።

የኪኒን ጋጋታ ያላስቆመው ሕዝብ ሆ! ብሎ ተነሳ 

ሕወሓት በእየዘመኑ ያወጣቻቸው የማስታገሻ ኪኖች አለምስራታቸው ብቻ ሳይሆን ህዝብን ዘላለም ማታለል አይቻልም እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእየአቅጣቸው በስርዓቱ ላይ ተነሳ።በባዮሎጂ ትምህርት አንድ ባክተርያ ለማጥፋት በተደጋጋሚ የምትሰጠው መድሃኒት ከእረጅም ጊዜ በኃላ ባክቴርያም ሊለምደው እና የመገዳደር አቅሙን ሊያጎለብትበት እንደሚችል ይገለጣል። የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር ማለትም የነፃነት፣የዲሞክራሲ፣የፍትህ እና የእኩል ተጠቃሚነት ችግሮች ሳይፈቱ ሕወሓት  እራሷን እና ደጋፊዎቿን ለመደለል ያቀረበችው ክኒን ሁሉ አልሰራ አለ። ሕዝብ በቃኝ ብሎ ተነሳ።በኦሮምያ፣በዐማራ፣ጋምቤላ፣አፋር፣ቤንሻንጉል ወዘተ አመፆች ተቀጣጠሉ። 

በመጀመርያ ደረጃ ሕወሓት አመፆቹን የአካባቢው የአስተዳደር ችግሮች እንጂ የብሔራዊ ጉዳይ አይደሉም በሚል ዝቅ ለማድረግ ብዙ ጥረት አደረገ።እውነታው ግን ይህ አልነበረም።አመፆቹ እያየሉ በአስር ዎች ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ብዙ ሺዎች እንደወጡ የቀሩበት ሕወሓት ላለፉት 26 ዓመታት ገጥሞት የማያውቀው የህዝብ የቆረጡ ድምፆች ነበሩ። በመጨረሻ ግን አመፁ እንደማይቻል ሲታወቅ አስቸይ ጊዜ አዋጅ በያዝነው 2009 ዓም መጀመርያ ላይ ታወጀ።ሕወሓት አዲስ የሞት ድግስ የያዘ ክኒን ይዛ ብቅ አለች።የኮማንድ ፖስት የሚባል  ክኒን። የኮማንድ ፖስት የተሰኘው ክኒን ግን እራሷን ህወሓትን ይዞ ወደ ሞት የሚያወርድ መሆኑን በደንብ አላወቀችውም ማለት አይቻልም።አማራጭ ስታጣ የተገኘውን ሁሉ መድሃኒት ነው ብሎ መውሰድ ተስፋ የቆረጠ ሰው ተግባር ነው።ሕወሓትም ተስፋ ቆረጠች።አዋጅ አወጀች።አዋጁ ስድስት ወር ላይ ያበቃል ተብሎ ህወሀትን ሊያሽላት ስላልቻለ አላዋቂ ሀኪሞች የሕውሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተሰበሰቡ እና እንደገና አራዘሙት።
  
የቅርቡ የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፖለቲካ ለውጦች  

የሕወሓት የሞት ድግስ የያዘው አዋጅ በእዚህ ዓመት ከመታወጁ ቀድም ባሉት ወራትም ሆነ ወዲህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ አዳዲስ የሚባሉ የቅርፅ እና የይዘት ለውጦች መታየት ጀምረዋል። በሀገር ውስጥ የሕወሓት ተጣማሪ እንደሆኑ የሚናገሩት ብአዴን እና ኦህዴድ ተፈረካክሰው የቀራቸው አንዳንድ ምልክቶች ናቸው።ሕወሓት ግን አሁንም እንደሚመቹ አድርጎ እንደገና ለመጠገን ሙከራ እያደረገ ነው።ያለፉት አይነት አሻንጉሊት አድርጎ ለመቅረፅ ግን ፈፅሞ የማይቻል ሆኗል።ምክንያቱም አመፆቹ የተነሱት ከታች ካለው ሕዝብ እስከ ማዕከላዊ አመራር ደረጃ ባሉት ሁሉ ስለሆነ ይህንን ሁሉ መጠገን በእራሱ ሕልም ሆኖ ቀርቷል። እዚህም ላይ ሕወሓት አንዳንድ መጠቀም የፈለጋቸው  አዳዲስ እና አስቂኝ ኪንኖች ብልጭ ብለዋል። ለምሳሌ የኦሮምያ የኢኮኖሚ አብዮት እና የዳሸን ቢራ ጉዳይ ይጠቀሳሉ።የኦሮምያ የኢኮኖሚ አብዮት ምንም አይነት የፖለቲካ ስልጣን የሌለውን ኦህዴድ በተስፋ ዳቦ መሬቱ እና በመሬቱ ላይ ያሉ መዋለ ንዋይ ሁሉ ያንተ ነው የሚል ቃላት እየተጠቀሙ የነበረውን ጥቂት ስራዎች ማወክ ከተያዘ ሰነባብቷል።በእዚህም ክልሉን የበለጠ ወደ ኃላ የመውሰድ እና በመጨረሻ ሕወሓት ሲረጋጋ ከአዲስ እቅድ ጋር ለመዋጥ መሆኑን የማይረዳ ሰው የፖለቲካ ሀሁ ገና ያልተገለጠለት ሰው ብቻ መሆን አለበት።

ሌላው በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ የታዩት አዳዲስ ክስተቶች ውስጥ በተለይ በውጭ ሃገራት መሰረታቸውን ያደረጉቱ ውስጥ የዐማራ የዘውግ ድርጅቶች መሰባሰብ እና የአርበኞች ግንቦት 7 ጥምረት ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው።የዐማራ የዘውግ ድርጅቶች በመጀመርያ መነሻ አመታት ላይ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስተው ነበር።በመጀመርያ ደረጃ የነበረው በሶሻል ሚድያ ላይ ከመብዛታቸው የተነሳ የጥያቄዎቹ ቅርፅ ብዙ ክርክሮች አስነስተው ነበር።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በዋሽንገተን ከተደረገው ዓለም አቀፍ የአማራ ጉባኤ ወዲህ የድርጅቶቹ መሰባሰብ በተወሰነ መልኩ እየታየ ነው። በተለይ የዐማራ የዘውግ ፖለቲካ የፅንፈኛ የዘውግ ፖለቲካን የማስፋፋት ዕድል ይፈጥራል ለሚሉ ሃሳቦች በእዚሁ በዋሽንግተኑ ጉባኤ ላይ ወረቀት ካቀረቡት ውስጥ የዳግማዊ መዐሕድ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ምስጋናው አንዱ ዓለም የዐማራው መደራጀት የፅንፈኛ ፖለቲካን የሚያከሽፍ መሆኑን ሲገልጡ : - 

የአማራው የአማራነት ጥያቄዎች ግን ይሄንን እንደልብ ሲፈነጭ የቆየ የአክራሪ ብሄረተኞች አደጋ ሚዛን በመስጠት ያረግበው ነበር። አማራው ራሱን ችሎ እንደ አንድ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሀይል ብቅ ማለት የእነዚህ አክራሪ ብሄረተኞች ህልውና መክሰም መንስኤ ነው። ለዛ ነው ብንዘገይም እንኳ አሁንም በቶሎ አማራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ይሄንን ሁሉ ለአርባ አመት የተዛባ ሚዛን ማስተካከል ታሪካዊ ግዴታችን የሆነበት ጊዜ ላይ ነን የምንለው" ብለዋል። 

በእርግጥ ይህ አባባል በእራሱ በርካታ የተቃርኖም ሆነ የሚደግፍ ሃሳቦች ሊንሸራሸሩበት ይችላሉ።ጉዳዩ ፖለቲካም ነው እና አንዳንድ ሁኔታዎች የሚያመጡት በጎም ሆነ በጎ ያልሆነ ተፅኖ ለመፈተሽ የጊዜ እና የአካባቢያዊ ለውጦችን በሚገባ መፈተሽ ይጠይቃል። 

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ አንድነት ጎራ ቀዳሚ ሚና የያዘው የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የእራሱ የሆነ ስልታዊ መንገዶች እየሄደ መሆኑን መመልከት ይቻላል።ድርጅቱ በመጀመርያ ከነበረበት ወደ ኤርትራ ለምን? የሚሉ ጥያቄዎች አልፎ አሁን ውጤቶችን የመለካት ደረጃ ላይ ደርሷል።በማኅበራዊ ሚድያ ላይ በጭፍን የሁሉንም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በመተቸት የማጥላላት ዘመቻ ላይ የተጠመዱቱን ትተን ለሀገር በመቆርቆር የአርበኞች ግንቦት 7 ከሚነሳበት ወቀሳ አንዱ ጥምረት በዛ የሚል ነው።

"ድርጅቶች በዙ እና ጥምረት በዛ"  የቀድሞ እና የዘንድሮ ወጎ

በቀደሙት አመታት ይሰሙ የነበሩ ድርጅቶች በዙ የሚሉ ድምፆች በአሁኑ ጊዜ ጥምረት በዛ የሚሉ ሆነው ማግኘት በራሱ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከማናቸውም አይነት ትችት እንደማይድን አንዱ ምስክር ነው።በተለይ የአንድነት ድርጅቶች ከብሄር ድርጅቶች ጋር መቀናጀት ለመፍጠራቸው መሰረቱ ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ በእራሱ የወቅቱ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ እና ጎልቶ እየወጣ ያለ ጥያቄ ነው።እዚህ ላይ ግን ድርጅቶች በዙ በተባለባት ሀገር ውስጥ ጥምረት መብዛቱ በእራሱ ችግር ሊሆን ይችላል ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።ስለሆነም ጥምረት መፈጠሩ በእራሱ በአደጋነት ሊፈረጅ አይገባም ማለት ነው። ከእዚህ ይልቅ የሚፈጠሩ ጥምረቶች ያላቸው በጎ እና በጎ ያልሆኑ ጎኖች ምንድናቸው? ብሎ መፈተሹ ተገቢ ነው።የኢትዮጵያ ሀገር አድን የጋራ ንቅናቄ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ እና መጪ የፖለቲካ ጉዳይ አንፃር መፈተሹ አስፈላጊ የሚሆነውም እዚህ ላይ ነው።

ፖለቲካ ከግለሰቦች ስብዕና በላይ የዘለለ ተልዕኮ አለው 

 በአርበኞች ግንቦት 7 እና የብሔር ድርጅቶች መካከል የተደረጉት የጥምረት መግለጫ ለመጀመርያ ጊዜ የተሰማው በ ጉሜ 3፣ 2007ዓም ምሽት ነበር።

በእዚህ ዜና ላይ በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ አራት በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ኃይሎች  የጋራ ንቅናቄ መመስረታቸው ተነግሮ ነበር።በእዚህም መሰረት 

1ኛ/ የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ

2ኛ/ የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣

3ኛ/ የአማራ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እ

4ኛ/ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅና

 በጋራ ለመስራት በመስማማት የኢትዮጵያ ሀገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን  መመስረታቸውን አስታውቀዋል። በእርግጥ የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት እና የአማራ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በጥምረቱ ላይ ለመቀናጀት የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉ መጠቀሱ እና ደት ላይ ነው መባሉ ይታወሳል። 

በቅርቡ በጥቅምት ወር 2009 ዓም  ጥምረት የተፈጠረበት መድረክ ደግሞ በአቶ ሌንጮ ለታ እና በምክትላቸው ዲማ ነገዎ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር፣ በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው አርበኞች ግንቦት 7፣ በዶ/ር ኮንቴ ሙሳ የሚመራው የአፋር ህዝብ ፓርቲና አቶ በቀለ ዋዩ የሚመራው የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተመሰረተው ነው።ይህ ጥምረት በኢትዮጵያ የመልክዓ ምድር ሽፋን አንፃር የተሻለ መሠባጠር የታየበት ሲሆን የሚነሱበት ሁለት ጥያቄዎች ግን አሁንም አሉ። እነርሱም ጥምረት የፈጠሩት ድርጅቶች በተለይ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በአሁኑ ወቅት ያለው ተሰሚነት ምን ያህል ነው የሚል እና የድርጅቱ መሪዎችም በ1984 ዓም አካባቢ በዐማራ ላይ በተነሱ ጭፍጨፋዎች እጃቸው አለ የሚሉ ናቸው።ሆኖም ግን ግለሰቦችን ከድርጅቶች ነጥሎ ማየት እና ግለሰቦቹ አጠፉ የሚባለውን ጥፋት በውጭ ሃገራት የመክሰስ መብት ያለው ኢትዮጵያዊ የተባለው ማስረጃ አሰባስቦ ከመጠየቅ ይልቅ በፖለቲካ መድረኩ ላይ መታየታቸው ብቻ ጥፋት እንደሆነ መገለፁ አስቸጋሪው ጉዳይ ነው።ከእዚህ በተለየ ደግሞ አሁንም ጥምረቱ ለምን ዐማራዊ ድርጅቶችን አላቀፈም የሚለው ጥያቄ ነው።ሆኖም ግን ጥምረቱ ለእነኝህ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቱ እንዳለ ሆኖ የድርጅቶች ጥምረት በእራሱ ለኢትዮጵያ መጪ የፖለቲካ ሁኔታ በእራሱ እንደ አደጋ ሊታይ ፈፅሞ አይችልም። ምክንያቱም ፖለቲካ ከግለሰቦች ስብዕና በላይ የሆነ ተልዕኮ ስላለው ነው።ግለሰቦች በግለሰቦች ይተካሉ። የፖለቲካ መስመሩ እና ዓላማው እንዲሁም ድርጅታዊ አቅም ግን የሚገነባው በአባላቱ እና በመላው ሕዝብ ፈቃደኝነት ነው።

ኢትዮጵያዊ ውል በአስተማማኝ መልኩ መልሶ ሳይታሰር ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ማውራት እንዴት ይቻላል?

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማንም በማኅበራዊ ሚድያ ውስጥ ገብቶ የሚተችበት አደገኛ ዕድል ፈጥሯል።አደገኛ ያልኩበት ምክንያት በሙያው በበሰሉ ሰዎች ሳይሆን በግብታዊነት እና ሻይ እና ቡና ሲጠጡ በሰሙት ውይይት ላይ ብቻ ተመርኩዘው ያንንም እንደ ትልቅ የእውቀት ምንጭ እየቆጠሩ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ድርጅቶች ሳይንሳዊ ባልሆነ መልክ የሚተቹ መብዛታቸው እና ሕዝብ ማሳሳታቸው እጅግ አደገኛ ክስተት ነው። በማናቸውም ጥምረት ላይም ሆነ አደረጃጀት ላይ ማንኛውም አይነት ጥይቄዎች፣አስተያየቶች እና ስጋቶች ሊገለጡ ይችላሉ። ጥምረት እና መተባበር ግን በእራሱ አደጋ ሊሆን ፈፅሞ አይችልም።

የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ በርካታ ተቺዎች የሚያነሱትን ያህል ለኢትዮጵያ አደጋ ነው ወይ? የአቅም፣የአፈፃፀም እና የታክቲክ ጉዳዮች ሊነሱ ይችላሉ።እነኝህ በሂደት እየጠሩ የሚሄዱ አበይት አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው።ጥምረት መፍጠር፣መወያየት፣በመጪው የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በሰለጠነ መልክ መደራደር ግን ለነገ የማይባሉ ዛሬ መጀመር ያለባቸው ቁልፍ ተግባራት ናቸው።የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ከኦሮሞ፣አፋር እና ሲዳማ ጋር ብቻ ሳይሆን በቅርቡ በጀርመን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት ከኦጋዴን ተቃዋሚ ኃይል ጋር የጋራ መግባብያ ሰነድ ተፈርሟል።ውጤታቸው አመርቂ ይሁንም አይሁን እነኝህ ተግባራት ለነገዋ ኢትዮጵያ ወሳኝ ተግባራት ተደርገው መወሰድ አለባቸው። 

ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚደገሱ የባዕዳንም ሆኑ የስልጣን ጥመኛው ስርዓት ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም የሚሆን እልቂት ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያዘጋጁ የታመነ ነው። ብልህ ፖለቲከኛ ደግሞ በዛሬ ላይ ብቻ ሳይሆን በነገ አደጋዎች ላይ ከአሁኑ እያነጣጠረ እና ችግሮችን የመፍታት ሥራ እየጀመረ መሄድ ዋና ተግባሩ ነው።ሕወሓት ከስልጣን ቢወርድም የኦጋዴን ጉዳይ ሆነ የአፋር ሁኔታ በተወሰነ ደረጃ ለመጪው የኢትዮጵያ ፀጥታም ሆነ ልማት ቀላል የማይባል መንገጫገጮችን ማስከተሉ ሳይታለም የተፈታ ነው። ስለሆነም ዛሬ ላይ በጋራ ርዕይ ላይ የተመሰረተ የኢትዮጵያዊነት ውል ላይ መነጋገር፣መተማመን እና ቢያንስ መስማማት ባይቻል ተቀራርቦ መነጋገር በእራሱ ለነገዋ ኢትዮጵያ ላይ አንድ ብሩህ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያዊ ውል በአስተማማኝ መልኩ መልሶ ሳይታሰር ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ማውራትስ እንዴት ይቻላል? ስለሆንም ሃገራዊ ንቅናቄውን በሚገባ መረዳት እና ዘግይተንም የምንመጣው ወደ እንደዚህ አይነቱ ንቅናቄ በመሆኑ ከአሁኑ መስተካከል የሚገባውን እያገዙ ጅምሩን ማበረታታት ከአንድ ንቁ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ተግባር ነው።ሃገራዊ ንቅናቄው በአሁኑም ሆነ በመጪው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሚከተሉት አዎንታዊ ተፅኖዎች መፍጠር ይቻላል። እነርሱም ; -

1/ ትልቅ ሃገራዊ ግንባር የመፍጠር አቅም ይኖረዋል፣

2/ በነገዋ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ በሂደት በሚመጣ ለውጥ ከብሄር አስተሳሰብ ወደ ሃገራዊ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ አደረጃጀት እንዲዳብር ይረዳል፣

3/ በነገዋ ኢትዮጵያ ላይ አዲስ የግጭት አጀንዳ ለመፍጠር ለሚፈልጉ ባእዳን መንገዱን ይዘጋል፣

4/ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህገ መንግስታዊ ስርዓትም ሆነ የሀብት እኩል ተጠቃሚነት የተረጋጋ ያደርጋል።

ባጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ ስንናገር ስለመላዋ ኢትዮጵያ መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለብን።መላዋ ኢትዮጵያ ደግሞ የተለያዩ አመለካከቶች፣የፖለቲካ ብስለቶች፣ ባህላዊ አመጣጦች እና ምጣኔ ሃብታዊ መሰረቶች አሏት። ይህንን ሁሉ አስተባብሮ ወደ አንድ ሀገር ጉዳይ ለማምጣት በእራሱ ጥበብ፣ትዕግስት እና ፅናት ይጠይቃሉ። 

ብዙዎቻችን የዘመኔ ሰዎች በፅሁፎች መካከል የአውሮፓውያን ምሁራን እና ታዋቂ ሰዎች የተናገሩት ንግግር የማድነቅ ሆኖም ግን የሀገራችን ሰዎች (ዓለም ያደነቃቸው) አባባሎች ብዙም ትኩረት አለመስጠት አባዜ ተጠናውቶናል።በመሆኑም ለእዚህ ፅሁፌ መደምደምያ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ ለሀገራቸው በሚሰሩት ሥራ ላይ ምን ያህል የአላዋቂዎች ወሬ ያውካቸው እንደነበር በገለፁበት አረፍተ ነገር  ላይ የተጠቀሰው አነጋገር  የኢትዮጵያን ሃገራዊ አንድነት ለማቆም እና ኢትዮጵያዊ ውል በአስተማማኝ መልኩ መልሶ ለማሰር መፅናት እንደሚገባ አመላካች ሆኖ ስላገኝሁት በእዚሁ ፅሁፌን ልደምድም። ንጉሡ በእራሳቸው እጅ በፃፉት "ሕይወቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ" በሚለው መፅሐፋቸው መግቢያ ላይ እንዲህ ነበር ይሉት : - 

      " የተበላሸውን ለማቅናት፣ያልተጀመረውም ሥራ እንዲጀመር ለማድረግና አዲሱን ስልጣኔ ለማግባት  እሳቤና ይልቁንም አሮጌውን ልማድ ለሚወደው ሕዝብ አጋዥ ስለነበረው በሁለት ብረት መካከል እንዳለ እንጨት አጣብቀውኝ የተቻለኝን እየሰራሁ ጊዜውን አሳለፍኩ።በመዝናናት ሰውነትን ደስ የሚያሰኝ ሥራ በመስራት የማሳልፈው ጊዜ ጥቂት ነበር።ከተጀመረው ከሀገሩ ውስጥ ሥራ ያቃናሁትና አዲስ የሰራሁት፣ከውጭ ሀገርም የስልጣኔ ሥራ በሀገር ውስጥ እንዲገባ ያደረግሁት በእየተራ ተፅፎ ይገኛል።በእዚህም ላይ የአዲሱ ስራችን መሰናክል የሚሆን በውስጥ ወይንም በውጭ ሰዎች የሚወራ አንዳንድ የውስጥ እና የውጭ ችግር በእየጊዜው ይደርስብን ነበር እና ሽብር እንዳይሆን እና የሰው ደም እንዳይፈስ በጎሳ መለያየትን እንዳይስከትል ስራውን ሁሉ በትግስት መስራት የሚያስፈልግ ሆነ
ሕይወቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ፣ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ፣1965።


ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com


ዋቢ ማጣቀሻዎች 
===============

- Development state, Meles Zenawi, 2012

- Ethiopian Herald, Nov.102015

- MSF Report, 2008

- Zehabesha, 2016

- ሕይወቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ ፣ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ፣1965 

GUDAYACHN BLOG started on August 28/2011 ኢሜይል አድራሻዎን በመሙላት ጽሁፎቹን መከታተል ይችላሉ/Follow by Email

በብዛት የተነበቡ/Popular Posts

ጉዳያችን በፌስ ቡክ ገፅ / GUDAYACHN ON FACE BOOK

https://www.facebook.com/gudayachn/?pnref=story