ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, December 23, 2016

ከአበበ ቢቂላ ቀጥሎ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሩጫ ነፍስ መዝራት ምክንያት የሆነው ምሩፅ ይፍጠር አረፈ።

The 1980s Ethiopian famous Athlete Miruts Yifter has died.
ኃይሌ ገብረ ስላሴ ወደ ሩጫው ዓለም እንዲገባ ምሩፅ ይፍጠር ምክንያት እንደሆነው ደጋግሞ ተናግሯል።ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክ ማሸነፉ የወቅቱ ድል ብቻ ሳይሆን ዛሬ ላሉን አትሌቶች ልባቸው ወደ አትሌቲክስ እንዲሸፍት ያደረገ አኩሪ የኢትዮጵያ አትሌት ነው። ኃይሌ ገብረ ስላሴ ምሩፅ ኦሎምፒክ ያሸነውን በዜና ስሰማ ውስጡ ለአትሌቲክስ ሩጫ መነሳቱን እና እንደ እርሱ በሆንኩ የሚል ምኞት እንዳደረበት በተለያየ ጊዜ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ገልጦ ነበር።
ምሩፅ ይፍጠር በተለይ በሞስኮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ካደረገ በኃላ ስሙ በመላው ኢትዮጵያ እና በዓለም ተናኝቶ ነበር። የሞስኮ ኦሎምፒክ አሸንፎ ሲመጣ ከአየር መንገድ ጀምሮ በግልፅ መኪና ሲገባ በሺህ የሚቆጠር የአዲስ አበባ ነዋሪ በሆታ እና በእልልታ ተቀብሎት ነበር።በወቅቱ ኮለኔል መንግስቱ ቤተ መንግስት ድረስ አስጠርተው ሽልማት አድርገውለታል። ምሩፅ በወቅቱ ከመንግስት ካገኘው ሽልማት ውስጥ የታርጋ ቁጥሯ 00001 የነበረ አዲስ መኪና እና በቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አጠገብ ዘመናዊ የመኖርያ ቪላ ነበሩ። 
ምሩፅ በህክምና ሲረዳ ከቆየ በኃላ ማረፉ ተነግሯል። የምሩፅ ይፍጠርን ነፍስ በገነት ያኑርልን።

ቪድዮ: ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክ 1980 እኤአቆጣጠር  1974 ዓም


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...