ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, October 7, 2016

ሕወሓትን በፍጥነት ከስልጣን ማስወገድ ማለት ኢትዮጵያን ከበለጠ የጎሳ ግጭት ማዳን ማለትነው

ጉዳያችን / Gudayachn
መስከረም 28/ 2009 ዓም
========================
በኢትዮጵያ የተነሳው ሕዝባዊ አመፅን ለማፈን ሕውሐት  ጎሳ ከጎሳ ማጋጨቱን ተያይዞታል።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በማዕከላዊ፣ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ክፍሎች የተነሱ የህዝብ አመፆችን ለማፈን በቀጥታ በሰራዊቱ ለመጨፍለቅ ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ በነዋሪዎች መካከል የሚያደርገውን የእርስ በርስ ማጋጨት ቀጥሎበታል።ከእዚህ በፊት በ1997 ዓም ምርጫ ወቅት አድርጎት እንደነበረው ሁሉ በዛሬው እለት ብቻ  በአርሲ ነገሌ መቂ፣ በሲዳማ ይርጋ ጨፌ እና ዲላ ላይ እርስ በርስ ሕዝቡ እንዲመታታ እየተደረገ ነው።ቀደም ብሎም በአዲስ አበባ ዙርያ ቡራዩ እና ወለቲ  ተመሳሳይ ግጭቶች በሕወሓት ካድሬዎች መሪነት ለመፍጠር ሙከራ መደረጉን እና ሕዝብ በፍጥነት እንዳወቀው ተሰምቷል።

ከእዚህ በፊት በዐማራ ክልል ቅማንትን ከአማራ ጋር፣ ኦሮሞን ከሱማሌ እና ዐማራ ጋር  በደቡብ ደግሞ ጌድዎን ከሲዳማ፣አማራ እና ጉራጌ ጋር እያጋጨ መሆኑ ተሰምቷል።ከእዚህ በተጨማሪ ሆን ተብሎ በሕወሓት ወኪሎች እሳት መለኮሳቸው የተረጋገጡ የጎንደር ገበያ እና የኮንሶ መኖርያ ቤቶችን መጥቀስ ይቻላል።ይልቁንም ጎንደር ላይ ተጨማሪ እሳት ለማያያዝ የተላከች ሴት በአደባባይ መያዝዋ ይታወሳል።በቅርቡም በአዲስ አበባ ዙርያ እና ደብረዘይት የደረሱ የእሳት ቃጠሎዎች ውስጥ የስርዓቱ አገልጋዮች የሆኑ ግለሰቦች ድርጅቶች ከሆኑት ውጭ ያሉት ላይ አሁንም የሕወሓት እጅ ሊኖርበት ይችላል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። 

በእየቦታው ሆን ተብሎ ለሚጫሩ የእርስ በርስ ግጭቶች ከመነሻው የጎሳ ፖለቲካ አውጆ ሕዝብ እያባላ የስልጣን ዘመኑን ለማርዘም የሚፈልገው ሕወሓት ከእዚህ በከፋ ደረጃም ማስፋፋቱ ስለማይቀር በቀጣይ ጊዜዎች የአካባቢ ሽማግሌዎች ሚና ቀላል አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
ስለሆነም የአካባቢ ሽማግሌዎች የእራሳቸውን መንገድ እየተጠቀሙ ሕዝቡን ማረጋጋት ይጠበቅባቸዋል።ሕወሓት ስልጣኑን ሲለቅ የእዚህ አይነት ግጭቶች ፈፅሞ አይኖሩም ምክንያቶቹም ሶስት ናቸው። እነርሱም - 

አንድ፣ የግጭቱ ጠንሳሽ እና አንዱን ´አጋር´ ሌላውን ´ጠላት´ እያለ የሚያበላልጠው ሕወሓት ስለሆነ። ሁለተኛ፣ከሕወሓት ውድቀት በኃላ የመገናኛ ብዙሃን  ስለማይታፈኑ የግጭት ችግር ያለባቸውን ቦታዎች ሁሉም ሕዝብ እንዲሰማ ስለሚደረግ እና ምክር በመገናኛ ብዙሃን ስለሚሰጥ እንዲሁም የወቅቱ መንግስት ማስጠንቀቅያ ግጭት በሚፈጥሩት ላይ እንዲደርስ ስለሚደረግ ሕግ በቀላሉ ማስከበር ስለሚቻል እና በሶስተኛ ደረጃ፣  የሕበረትሰቡ የጋራ እሴቶች እና አደረጃጀቶች እንዲሁም የሃይማኖት አካላት በነፃነት ሕዝቡን ለመምከርም ሆነ ለመገሰፅ ስለሚችሉ።ይህንን እንዲያደርጉም በነፃ ሚድያ ዕድል ስለሚያገኙ ሕዝብ አብሮ የመኖር እድሉ ትልቅ ነው። አሁን እነኝህ የሃይማኖት አካላት ሲናገሩ የአንዱ ወገን ደጋፊ ስለሚባሉ እና በሙሉ ልብ ለመናገር ስለማይችሉ ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ እንዳልሆኑ ይታወቃል።ይህንን ሆን ብሎ ያደረገው ገዢው ስርዓት ሕዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት ብሎ መሆኑ ይታወቃል።

ባጠቃላይ ሕወሓት ለስልጣን ማቆያ ´ነዳጅ´ ብሎ የሚያስበው የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርስ መከፋፈል ነው።ከመነሻውም ሕወሓት ኢትዮጵያን በክልል ሲከፋፍል ትክክለኛ ፈድራሊዝም ለማስፈን እንዳልሆነ ያለፉት 25 ዓመታት ምስክር ናቸው። ሕወሓት የብሔር ብሔረሰቦች መብት ሲል የነበረው ሁሉ ቀልድ እንደነበር እና የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች በታሪካቸው አይተውት ወደማያውቁት ግጭት የከተታቸው አሁንም ሕወሓት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስክር ነው።ህዝብን ከህዝብ የማጋጨቱ ሥራ ሕወሓት በምን ያህል  ደረጃ ይሳካለታል? የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ከፋፋይ ስርዓት ኢትዮጵያን በጎሳ ግጭት እያነደዳት ነው። ስለሆነም ሕወሓትን በፍጥነት ከስልጣን ማስወገድ ማለት ኢትዮጵያን ከበለጠ የጎሳ ግጭት  ማዳን  ማለትነው።




ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...