ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 5, 2016

በስደት የሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ ብፁአን አባቶች ከጳጉሜን 1 እስከ መስከረም 3 ድረስ ብሔራዊ የጸሎትና የሐዘን ቀን እንዲሆን አውጀዋል (የውሳኔውን ሙሉ ቃል ያንብቡ)



ብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያ  

ስመ አብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 

“አቤቱ ሕዝብህን አዋረዱ፣ ርስቱንም አስቼገሩ፣ ልቴቲቱና ድሃአደጉን ገደሉ ግዚአብሔር አያይም፣የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ።” /መዝ 935/ 

በመላው የአገራችን ኢትዮጵያ ክፍሎች የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ በቅድሚያ ተወልዳችሁ ባደጋችሁበት በአያት በቅድመ አያቶቻችሁ ርስት ላይ፥ በሰላምና በነጻነት እንዳትቀመጡ ፣ በጨካኞችና በነፍሰ ገዳዮች ተከባችሁ ለስደት የተዳረጋችሁ፣ ቆስላችሁ በሆስፒታልና በየመንገዱ ወድቃችሁ በስቃይ ላይ ለምትገኙ ልጆቻችን፣ታስራችሁ ያለፍትህ በጨካኞች እጅ የምትሰቃዩ ሁሉ፥ በመከራ ያሉትን የሚያጽናና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፍጹም ሰላምና ምሕረትን በእናንተ ላይ እንዲያበዛ ሎታችንን ሁሉ ወደሚሰማና ወደሚያይ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እናቀርባለን። ነፍሳችሁን ከገዳዮች ለማዳንና በእኩያን እጅ ላለመውደቅ፣ ወገኖቻችሁን ከፋሽስቱ የህወሐት ወራሪ ይል ለመታደግ ለምትባዝኑ ልጆቻችን ሁሉ፣ የኃያሉ እግዚአብሔር በቃና ምሕረት ከእናንተ ጋር ይሆን ንድ ልዑል እግዚአብሔርን እንማልዳለን! ፍትህንና ነፃነትን በመጠየቃችሁና ማንነታችን ይጠበቅልን በማለታችሁ ምክንያት፣ በቀያችሁ እንደ በግ በግፈኞች ለታረዳችሁ፣ በጨካኞች እጅ በከንቱ ደማችሁ ለፈሰሰው ልጆቻችን በሙሉ፣እግዚአብሔር አምላክ የሰማዕታትን ክብርና እረፍት እንዲያጎናጽፍልንና በግፍ
የፈሰሰውን ንጹህ ደማችሁን ይበቀልልን ዘንድ፣ በጥልቅ ሐዘን ውስጥ ሆነን ወደ እውነተኛው ፈራጅና ተበቃይ አምላካችን፣ በመሪር ለቅሶና በብዙ ሐዘን ውስጥ ሆነን እንጮሃለን።ለሟች ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው ህዝባችንም መፅናናት ይሰጥልን ዘንድ ቅዱስ እግዚአብሔርን እንለምናለን። በመላው አገራችን ላይ እየደረሰ ባለው እልቂት፥
የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት በሙሉ የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንገልጻለን።

ውድ ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን !

ይህን መግለጫ በምናስተላልፍበት በዚህ ሰዓት፣ የወያኔ ኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባስተላለፉት የዘር ፍጅት ትእዛዝ መሠረት፣ የጎንደርና የጎጃም ህዝብ በምላ በመንግስት ወታደሮች እየተጨፈጨፈ እንደሆነ፣ አካባቢውም የጦር ቀጣና እንደሆነ፣በቅሊንጦ እስርቤት የተሰሩ የህሊና እስረኞች ላይ ጥቃት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙሃን እየሰማን ነው። ሕዝባችን በገሩ እንደ ሰው በነጻነት የመኖር መብቱን ተነጥቆ በታጠቀ የመንግሥት ሠራዊት እየተገደለና እየተዋከበ በብዙ እንግልትና መከራ ላይ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ችለናል። በጎንደር እና በጎጃም ሕጻናትና እናቶች ሳይቀሩ በመሣሪያ እየተደበደቡና እየተገደሉ ነው። ዛሬ ሕዝባችን ተዋርዶ ፣ ድሆችና አቅመ ቢሶች በግፍ እየተገደሉ መንገድ ላይ በሚጣሉበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በብዙ የሚቆጠሩ ወጣቶች ታስረው ኢሰብአዊ የሆነ ግፍ እየተፈጸመባቸው ይገኛል። በሥልጣን ላይ የሚገኘው የሕወሐት ዘረኛ ቡድን ይህ የግፍ ድርጊቱን ዓለም እንዳያውቀው፣ ስልክና ኢንተርኔት የመሳሰሉ የመገናኛ ብዙሐን መንገዶችን በመዝጋት የጎጃምና የጎንደርን ሕዝብ አፍኖ በማሰቃየት ላይ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት በመምላ ሐገሪቱ የሚገኙት ሕዝቦች በጨካኞች አገዛዝ ቀንበር ሥር በመሆናቸው፣ከገዢው ጥቅመኞች በቀር ሰላምና ነጻነት የሚሰማቸው ጎች በአገራችን የሉም።

በአሁኑ ሰዓት ሕዝባችን የሚገደለው አብረን እንኑር፣ ነገር ግን ርስታችንን አትቀሙን ስላለ ነው፤ አሁን ሕዝባችን የሚገደለው በአንዲት ሃገር እንጂ በመከፋፈል አናምንም፣ አማራ ወይም ኦሮሞ ወይም ትግሬ ወዘተ እያላችሁ አትከፋፍሉን በማለቱ ነው። ሕዝባችንም ለዚህ ሁሉ መከራ የተዳረገው በገራችን ሕዝብ የመረጠውና ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ስለሌለ፣ ያለው መንግሥት ነኝ ባይ አካል በሕዝብ እኩልነትና በሃገር አንድነት የማያምን፣ ዘረኝነትና ሙሰኝነት የተጠናወተው ፍጹም አምባገነን ቡድን በመሆኑ ነው። በአሁኑ ወቅት በመላ ሃገሪቱ ይልቁንም በጎጃም፣ በጎንደርና፣ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የታወው ጦርነት ለገሩ አንድነት ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር ክቡር ዋጋ ሲከፍል የኖረውን ሕዝብ ዘርና ተተኪ ትውልድ ለማጥፋት ነው። የኢትዮጵያን ታሪክ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሣው፣ ይህ ዘረኛ መንግሥት ሕልሙን ለማሳካት የቻለውን ግፍ ቢፈጽምም አይሳካለትም፤በመሆኑም ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፥ ለገራችን ህልውናና ለሕዝባችን ደኅንነት መረጋገጥ ሲባል፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን የምትችሉትን ታደርጉ ዘንድ ከዚህ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል።  

1. ከጳጉሜ አንድ  ጀምሮ እስከ መስከረም ስት ድረስ ብሔራዊ የጸሎትና የሐዘን ቀን እንዲሆን ታውጆአል! 

መንግሥት አስተዳድረዋለሁ በሚለው ሕዝብ ላይ ጦርነት አውጆ፣ የንጹሐን ልጆቻችን ደም በምድራችን ላይ በግፈኞች በየዕለቱ እንደ ጎርፍ እየፈሰሰና አቅመ ደካማ አረጋውያንና ሕፃናት ረዳት አጥተው በጭንቅ እየዋተቱ ስለሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቤቱ ለዘመን መለወጫ እንደ ቀደሙት ዘመናት ሁሉ እርድ አርዶ፣ ድግስ ደግሶና፣ ተድላ ደስታ እንዳያደርግ በጥብቅ አዘናል። ጊዜው ብሔራዊ የሐዘን ጊዜ ስለሆነ፣ ሁሉም ሕዝብ ቢቻል በህብረት ካልተቻለ በግል በመሆን በጸሎትና በምሕላ ለአንድ ሱባኤ ያህል ወደ እግዚአብሔር እንዲጮህ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪውን ያቀርባል።

2. ለኢትዮጵያ የመከላከያና የጸጥታ እንዲሁም የጦር ሠራዊት አባላት በሙሉ! 

ግብር እየከፈለ፣ ደመወዝ እየሰጠ በሚያኖራችሁ፣ ከአብራኩ በአስገኛችሁ ሕዝብ ላይ ከመተኮስና የገዛ ቤተሰባችሁን ከመግደል የበለጠ ምድራዊ ወንል የለም። ይህ አድራጎት በምድርም በሰውና በህሊናችሁ ፣ በሰማይም በእግዚአብሔር ት ያስፈርድባችኋል። ሕዝባችሁን እየገደላችሁ ከምትሞቱ ከሕዝባችሁ ጎን ተሰልፋችሁ በክብር ብትሰዉ ሕያው ታሪክ ሠርታችሁ ታልፋላችሁ። ዛሬ ከህወሃት ጎን ተሰልፋችሁ የምትሞቱት ሞት ገር ነጻ ሊያወጣ ዘምቶ ከባእዳን ጋር ተዋግቶ በክብር ሞተ የሚያስብል አይደለም፤ የጎጃምን ፣ የጎንደርን፣ የኦሮሞን፣ የኮንሶን ህዝብ ሊያጠፋና ሊገል ዘምቶ ሞተ ነው የሚያስብለው፤ ወገኑን ሲገድል ሞተ መባል ትሻላችሁን? ወይስ ስለሕዝቡ መብት ሲታገል ሞተ መባል? ይህ ሥርዓትና መንግሥት ያልፋል፣ ይሻራል፤ታሪክ ግን ሁልጊዜም አሸናፊ ነውና እስከ ዓለም ፍጻሜ ይኖራል።ስለዚህ ለሕዝባችሁና ለወገናችሁ ክብር ስትሉ ለከፋፋዩና ነፍሰ ገዳዩ የሕወሃት አምባገነን ቡድን መሣሪያ እንዳትሆኑና በወገናችሁ ላይ እንዳትተኩሱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል። ከዚህ አባታዊ ምክራችን ተላልፎ ንፁሐን ወገኖቹን የሚገል፣ የሚያንገላታ፣ የሚያስርና፣ የሚደበድብ እንዲሁም ለዚህ ክፉ ቡድን ጥቆማ እየሰጠ የሚያሳስር ሁሉ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሥልጣነ ጥሮስ ወጳውሎስ አውግዞታል!ከህወትና ከቅጥረኛ ገዳዮች ጋር የሚተባብረውን ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ “ውጉዝ ከመ አርዮስ” ብላችሁ ከህብረታችሁ እንደትለዩት ቅዱስ ሲኖዶሱ በእግዚአብሔር ሰም ጥሪውን ያቀርባል።

3. የትግራይ ሕዝብ በአምባገነኖች ጥይት ከሚረግፈው የአማራና የኦሮሞ ወገኖቹ ጋር እንዲሰለፍ ጥሪ እናቀርባለን! 

የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ዘር ነው! የህወሃት አምባገነን መሪዎች ለስልጣናቸው ማራዘሚያ ሲሉ ብቻ ለትግራይ ህዝብ የቆሙ ለማስመሰል ያልሄዱበት መንገድ የለም።ክርስቲያኑ ሕዝብ ወገናችሁ ነው “አክሱም ከተማዬ ትግራይ ወንድሜ እኅቴ” ብሎ የሚያምን መሆኑን ያምታውቁት ነው፤ ለእናንተም ሁሉም አገራችሁ ነው፤ እንደ ልባችሁ የምትኖሩበት ንብረት የምታፈሩበት ክፉ ቀን የምታሳልፉበት በሥጋ በደም የተሳሰራችሁ ሕዝቦች ናቸሁ። አማራም ሆነ ኦሮሞ ጠላታችሁ አይደለም፤ ሆኖም አያውቅም፤ ጎንደርም ሆነ ጎጃም ወይም ወለጋ የጠላታችሁ ምድር አይደለም።ለትግራይ ህዝብ የሚያስብ ማንኛውም ሃይል ቢኖር ቅድሚያ የሚሰጠው ለትግራይ ህዝብ ወዳጅ ያበዛለታል እንጂ ወዳጆቹን ወደ ጠላትነት አይቀይርበትምነበር።ስለሆነም ህወሃት ለትግራይ ህዝብ ዙሪያውን በጠላት እንዲከበብ እያደረግ እንጂ በወዳጅ እንዲምበሸበሽ እያደረገ እንዳልሆነ ትላንት በትግራይ ህዝብ ስም ከኤርትራ ህዝብ ጋር ዛሬ ደግሞ ከአማራና ከኦሮሞ ህዝብ ጋር እያደረገ ያለውን ጦርነት ማስተዋል ያሻል። ዘመን ሰጠን ብለው ከአብራካችሁ የተከፈሉ ልጆቻችሁ አማራና ኦሮሞ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን በቀያቸው በነጻነት እንዳይኖሩና እንዲሳደዱ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ማየት አይገባችሁም፤ ተዉ ልትሉ ይገባል። በፈርኦን ዘመን እንደ ተደረገው ዛሬ በምድራችን ወንድ ልጅ እንዳይኖር እየተለቀመ ሲገደል ይኸው 25 ዓመት ሆነ። ይህ ሕዝብን አብሮ የሚያኖር አድራጎት አይደልም፤ በዚህ በደል ውስጥም መተባበር የለባችሁም። ቀን ያልፋል ዘመን ይለወጣልና ወደፊት ልጆቻችሁን የሚያስወቅስ ታሪክ ሲሠራ ዝም ብሎ ማየት የለባችሁም። ይልቁንም ቀን ከጣለው ሕዝባችሁ ጋር አብራችሁ ልትሰለፉ አብራችሁ ልትሞቱ ይገባል። የአንድነት መገለጫው ደስታውንም ዘኑንም አብሮ መካፈል ነውና።

በተለይም የትግራይ ተወላጅ ምሁራን ህወሐት የገባበትንና ለትውልድ የሚተርፍ መዘዝ በጭፍን ከመደገፍና በዝምታ ከማየት ወጥታችሁ በግልጽ ልትቃወሙና ይህን እኩይ ድርጊት ልታስቆሙ ይገባል። የትግራይን ህዝብ አስተባብራችሁ ያለምንም ማመንታት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ልትቆሙና ህወሃት በአማራና በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን የዘር ፍጅት እንድታወግዙና ራሳችሁን ከዚህ ክፉ ሥራ እንድትለዩ በኢትዮጵያ አምላክ፤ በኃያሉ እግዚአብሔር ስም ጥሪያችን ይድረሳችሁ።


4. የጎንደር፣ የጎጃምና፣ የኦሮሞ ህዝብ በአካባቢያችሁ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን ከምንጊዜውም በበለጠ መንገድ ትንከባከቡና ደህንነታቸውን ትጠብቁ ዘንድ አባታዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን! 

ሁሉም ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አርማው እንግዳ ተቀባይነቱ ነው። ይልቁንም ክርስቲያኑ ህዝባችን በዚህ ምግባሩ የሚወዳደረው እንደሌለ መላው ዓለም በሚገባ ያወቀዋል። ዛሬ ሕዝባችንን እየገደለ ያለው ቡድን መለያ ባህሪው፣ የተለያዩ እኩይ መንገዶችን በመጠቀም ህዝብን በህዝብ ላይ ወንድምን በወንድሙ ላይ እንዲነሳ በማድረግ በማጋጨት ነው። ለአለፉት 25 ዓመታት አማራውን ከኦሮሞው፥ ኦሮሞውን ከሌላው ብሔር ለማጣላት ያልሞከረው ዘዴ አልነበረም። ምንም እንኳ በመጠኑ የተሳካለት ቢመስልም በአርቆ አሳቢው የኢትዮጵያ ህዝብ ትዕግስትና ጨዋነት የተነሳ የህወሐት አላማ ሊከሽፍ ችሏል። በዚህ ሰአት የህወሃት የፍጅት ተንኮል ኢላማ የሆኑት የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ስለዚህ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በአካባቢያቸው የሚገኙትን የትግራይ ልጆች እንዲከባከባቸውና ደህንነታቸውንም ሆነ ንብረታቸውን ከህወሃት የእጅ አዙር ጥቃት ነቅቶ እንዲጠብቅና የሰይጣንን ራ እንዲያከሽፍበት ቅዱስ ሲኖዶሱ አደራ ይላል።

5. የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ሆኖ የዘር ፍጅት ከታወበት ወገኑ ጎን በጽናት እንዲሰለፍ ማሳሰብ!በሃገራችን የምትገኙ ወገኖቻችን ሆይ! የሚደርስባችሁ ግፍና ጭቆና ቅዱስ ሲኖዶስን እጅጉን ያሳዝነዋል፤ ሕመማችሁ ሁሉ ይሰማናል። 

ሞታችሁ ሁሉ እጅግ ያስለቅሰናል። ይህንን ከባድ የመከራ ቀን እግዚአብሔር እንዲያሳጥረው ቅድስት ቤተክርስቲያን በጸሎት እና በምልጃ ከእናንተ ጋር ናት። እግዚአብሔር ይህን ክፉ ዘመን ያሳልፈዋልና በርቱ፤ ስለ ነጻነቱ የሚሞት ሕዝብ ሁልጊዜ አሸነፊነውና አይዟችሁ በርቱ። ነጻነቱ የተነጠቀ ሕዝብ ሆኖ ከመኖር ስለነጻነት ታግሎ በክብር መሞት እንደሚሻል የቅዱሳት መጻህፍትም ሆነ የገራችን ታሪኮች ይነግሩናል። ክርስቶስ ዓለምን ያዳነው በሞቱ ነውና! የሕዝባችንም ሞትና መከራ በእግዚአብሔር ፊት እየታ ስለሆነ በግፈኞች የፈሰሰው ደማችሁ ኢትዮጵያን ነጻ እንዲሚያወጣት ቅዱስ ሲኖዶስ ያምናል። በዚህ ክፉ ጊዜ ሕዝብ በግፍ ሲጨፈጨፍ መሐል ሰፋሪ ሆኖ መመለከት፣ ከህሊናም ሆነ ከእግዚአብሔር ፍርድ አያድንም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት በመቆም እራሱንና ወገኑን ከጥፋት ለማዳን የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ጥቃት ከሚደርስበት ወገኑ ጎን በጽናት እንዲሰለፍ ሲኖዶሱ ጥሪውን ያቀርባል። 

በመጨረሻም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለሚመለከታቸው ሁሉ 

በሃገራችን በኢትዮጵያ ፍትህ በመጓደሉ፣ ሕዝባችን በተፈጥሮ ከእግዚአብሔር የተሰጠው መብቱ በመገፈፉ፣ ሕዝብን የሚለያይና አገር ገዳይ ዓላማን በሕግና በመመሪያ መልክ ቀርጾ ሕዝብን መለያየትና አገርን መበታተንን እንደ ለቲካ መሣሪያ አድርጎ የሚጠቀመው በሥልጣን ላይ ያለው አካል ሕዝባችን ለእልቂት፣ ለረብ፣ ለስደት አሳልፎ የሰጠ አካል በመሆኑ፣ ለሕዝቡ ክብር፣ አንድነት፣ መብትና፣ እኩልነት የማይሠራ በመሆኑ ማንም እንደ መንግሥት ሊቀበለው አይገባም። አንድ መንግሥት መንግሥት የሚሰኘው ለሁሉም ሕዝቦች መብት እና ነጻነት በእኩልነት ሁናችሁ በመነሣት አሁን በመሳሪያ ጊዜያዊ የአደራ መንግስት እንዲቋቋምና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሃገር ክብር እና አንድነት የሚያስብ ሕዝባዊ መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ እንዲፈጠር ሁሉም አገሩንና ወገኑን የሚወድ   ኢትይጵያዊ ሁሉ እንዲረባረብ ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሳዊ የአደራ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

´´ ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ´´


"ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር"



No comments: