ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, August 28, 2016

ህወሓት ምንም አዲስ መልዕክት የሌለው መግለጫ ዛሬ ሰጠ።ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው EPRDF press release is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years


የአማርኛ ፅሁፍ ከስር ይመልከቱ።
EPRDF press release of August 28,2016 is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years. It is  full of empty words. There is no single word of ´´excuse´´ for over 1000 Ethiopians killed in last seven months by the regime. The press release is expected to invite more people to protest  TPLF. Because it did´t even reason out the real situation of the country plus the possible solutions suppose to be proposed by this particular press release. In addition to that the press release, at the last statement conclusion, warns peaceful protestors and appreciate the regime´s security personnels. Such a kind of approaches of TPLF is very common for Ethiopians in the last 25 years. In short it is possible to say that this is another confirmation as dictators will make fast their last days by following poor minded advisers. The same is happening in TPLF. For your easy information about the press release, please read the below Amharic version of Gudayachn´s view and full press release of TPLF video at the end of article.

የኢትዮጵያ ሕዝብ እያገባደድነው ባለው የ2008 ዓም ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል በአዲስ መልክ ያቀጣጠለበት ዓመት ነው።በእዚህ ዓመት ብቻ እስካሁን ትክክለኛ ቁጥሩ ባይታወቅም በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች ብቻ በሰላማዊ ሰልፍ መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን በጥይት አረር ተገድለዋል። በአስር ሺዎች ወደ እስር ቤት ተግዘዋል።ሌሎች አስር ሺዎች ካሉበት ቀዬ ወደ ሌላ ቦታ ተሰደዋል።

ሕዝባዊ አመፁ እያየለ መጥቶ ይህ ፅሁፍ በምፃፍበት በእዚህ ቅፅበት በጎንደር እና ጎጃም ሕዝብ የህወሓት መዋቅር የሆኑ የአስተዳደር እርከኖችን አፍርሶ እራሱን በእራሱ ጊዝያዊ የአስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ እና መሪውን እየመረጠ መሆኑ እየተዘገበ ነው።በእዚህ ሁኔታ እያለ ነው እንግዲህ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከስብሰባ በኃላ ደረሰበት የተባለውን ውሳኔ ዛሬ ነሐሴ 22፣2008 ዓም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተነበበው።

መግለጫው በእራሱ የኢህአዴግ ነው ወይ? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው።ምክንያቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብአዴን እና ኦህዴድ ቀድሞም በህወሓት መዋቅር የመታዘዛቸው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ በእዚህ ዓመት ይብሱን በሕዝባዊ አመፁ ሳብያ ሕልውናቸው ማክተሙን በግልፅ የታየበት ነው።ስለሆነም የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲባል ህወሓት እና ህወሓት ብቻውን ያሰበውን መግለጫ በሚል ስም እንዳወጣው መረዳት ተገቢ ነው።

በተሰጠው መግለጫ ላይ በመጀመርያ ክፍል ላይ ´´ውዳሴ ህወሓት´´ የተሞሉ ቃላት ብቻ ሲገኙበት።በሚልዮን የሚበሉት እና የሚጠጡት ባጡባት አገር ውስጥ ይልቁንም ረሃብ እንደ አዲስ አበባ ያሉ ታላላቅ ከተሞች ውስጥ ተማሪዎች የምግብ ድጋፍ ካልተደረገላቸው ትምህርታቸውን መቀጠል እንደማይችሉ እነዩኒሴፍ የመሳሰሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በገለፁበት ሁኔታ ሁሉ የኢህአዴግ መግለጫ ኢትዮጵያ እንዳደገች ለመስበክ መሞከሩ አሁንም በአስራአንደኛው ሰዓት ላይ ቆመውም ህወሓቶች ለለውጥ ሳይሆን ለበለጠ ግድያ መነሳታቸውን አመላካች ነው።

የመግለጫው ዋና እና ቁልፍ ምክንያት የኢትዮጵያን ሕዝብ አዘናግቶ የበለጠ ጦር ሕዝባዊ አመፁ ወደተነሳባቸው ቦታዎች አዝምቶ ለመጨፍለቅ እና የምዕራባውያንን ውትወታ በሆነች ለውጥ በምትመስል መግለጫ ይሄው እየሰራን ነው ለማለት የታሰበ ነው።ለእዚህም ነው የህወሓት የማኅበራዊ ሚድያ አፈቀላጤዎች  መግለጫውን በተመለከተ በእንግሊዝኛ ለመፃፍ የሚደክሙት።ሌላው አስቂኝ የመግለጫው ሂደት አሁን ኢህአዴግ የሚያደርገው ለውጥ ከአስራ አምስት ዓመት በፊት የተጀመረው አካል ነው ሲል መደመጡ ነው።ይህ ´´ ሃያ አምስት ዓመት በጥይት ስገድሉን ኖረው አሁን ደግሞ በሳቅ ገደሉን ´´የምትለዋን አባባል ያስታውሳል። ስህተት ተሰርቷል ለውጥ ያስፈልጋል ብሎ በድፍረት የለውጥ አስፈላጊነትን አፍን ሞልቶ ለመናገርም ያፈረ ስርዓት ዛሬ በህዝባዊ አመፅ ለለውጥ ተገደድኩ ይሉኛል በሚል ጭንቀት ለውጡን ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ባቀጣጠልነው መሰረት ነው ብሎ መግለጫ ማውጣት ለምንም አይነት እርምጃ አለመዘጋጀታቹን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል። 

ህወሓት በእዚህ መግለጫ ላይ ለችግሩ መነሻ ብሎ ያቀረባቸው ነጥቦች በእራሳቸው ደካማ እና መሰረታዊ የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ ያገለለ ነው።በዛሬው መግለጫ ህወሓት የአገራችን ችግር ብሎ ያቀረባቸው ችግሮች ያሉ ችግሮች ቢሆኑም ዋናው እና መሰረታዊው ችግር ከላይ እንደተጠቀሰው የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት፣ጎጠኛ እና አድሏዊ ስርዓት መስፈን እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ የሚሉት ዋነኛ ናቸው።ለእነኝህ መፍትሄዎቹ ደግሞ በዋናነት ህወሓት ስልጣኑን በፍጥነት እንዲለቅ ማድረግ እና ሕዝባዊ እና የሽግግር መንግስት መመስረት ነው።ከእዚህ ያነሰ መፍትሄ ቁስል የበለጠ እንዲመረቅዝ እና ኢትዮጵያን ወደ ባሰ ማጥ ውስጥ የመክተት ግልፅ ፍላጎትን ብቻ ያመለክታል።ህወሓት በዛሬው መግለጫው ግን ችግሮች ብሎ ጉዳዩን በጥገናዊ ለውጥ ለማለፍ የሞከረበት መንገድ ችግሮቹን  የህዝብ መብዛት፣የሕዝብ ፍላጎት መጨመር፣ስልጣንን የሀብት ማከማቻ የማድረግ ሂደት በኢህአዴግ ውስጥ በመስረፁ ወዘተ ናቸው በሚሉ ቃላት ለማድበስበስ ሞክሯል።

ባጠቃላይ መግለጫውን በሶስት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን።የመጀመርያው ክፍል ህወሓት እራሱን ያሞገሰበት እና ኢትዮጵያውያን ´´ምግብ በልታችሁ ያደራችሁት እኔ ስልጣን ከያዝኩ በኃላ ነው´´ ቀረሽ ሐተታ ሲሆን ሁለተኛው ችግሩን ከህወሓት የስልጣን ጥማት እና አገሪቱን በተሳሳተ የጎጥ ፖለቲካ  መከፋፈል የመጣ መሆኑን ሸሽጎ የችግሩን መነሻ በገሃድ ካሉ ግን ብቸኛ ችግሮች ካልሆኑት የስልጣን መባለግ፣የህዝብ ብዛት መብዛት እና የህዝብ አዳዲስ ፍላጎቶች በሚሉ ቃላት ሊያድበሰብስ የሞከረበት ነው።በመግለጫው የመጨረሻ ክፍል ላይ ደግሞ ሕዝባዊ አመፁን የጥፋት ኃይሎች መሆኑን ሊሰብክ ይሞክርና ከጎኑ ቆመው ሕዝብ የገደሉትን ሲያሞግስ እና አይዟችሁ በርቱ ሲል ታገኙታላችሁ። መግለጫው ባጭሩ ይሄው ነው።ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው።ህወሓት ማር ሊያመነጭ አይችልም።ማር የንብ ሥራ እንጂ የዝንብ ሊሆን እንደማይችል ሁሉ።

ሙሉ መግለጫውን ለመመልከት  ይህንን ይጫኑ።

ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።