ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, August 15, 2016

ከሰባቱ የህወሓት መስራቾች አንዱን ጨምሮ 16 የትግራይ ተወላጆች መግለጫ አወጡ።''ህወሓት ስልጣኑን ይልቀቅ የሽግግር መንግስት ይመስረት'' ብለዋል።



TPLF is at the beginning of the end.
Including the founder of TPLF, former first commander of its army and Ethiomedia editor plus other 13 Tigray province born Ethiopian issued statement. The statement demanded an immediate removal of TPLF from power and establishment of transitional Government in Ethiopia. See the Amharic version of the statement here below.

የመጀመርያው ህወሓትን ከመሰረቱት ውስጥ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን እና የመጀመርያው የህወሓት ኮማንደር አቶ ተስፋዬ አፅብሃ   ጨምሮ አስራ ስድስት የትግራይ ተወላጆች ህወሓት ስልጣን እንዲለቅ እና የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት በይፋ ጠይቀዋል።ሌሎች የክልሉ ተወላጆችም እንዲቀላቀሏቸው ጠይቀዋል።መግለጫውን ዘሐበሻ በድረ-ገፁ ላይ ያሰፈረውን ከእዚህ በታች ይመልከቱ።


ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ 8 ነሓሴ 2008
በአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት በኦሮሞና በአማራ ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናወግዛለን፤ የህዝቡን ተቃውሞ እንደግፋለን።
ስለዚህ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ፣ የህዝባችን አንድነት እንዲጠናከርና የአገራችን ሉኣላዊነት እንዲከበር᎓-
1. ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን መወገድ አለበት
2. በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበሮችና ብቃት ባላቸው ግለሰቦች የሽግግር
መንግስት መቋቋም አለበት።
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት የሚከተለውን ጥሪ እያቀረብን ፣ እኛም ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ለትግሉ መሳካት የአቅማችንን እንደምናበረክት ቃል እንገባለን።
1. ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮና ፋታ ሳይሰጥ አፋኙን አገዛዝ እንዲያስወግድ፣
2. በሰላማዊ ህዝብ ውስጥ የእርስ በርስ ደም መፋሰስ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲደረግ፣
3. ሰራዊቱና ሌሎች የመንግስት ታጣቂዎች በህዝባቸው ላይ እንዳይተኩሱ፣
4. ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ትግሉ እንዲጠናከር፣
5. የትግራይ ህዝብ በራሱ ላይ ብዙ ግፍ የሚፈፅመውንና በስሙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን
የሚጨፈጭፈውን ህወሓት አውግዞ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን እንዲሰለፍ
በተጨማሪ ነፃነት ባላቸው አገሮች ውስጥ እየኖሩ የግፍ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም የሚሞክሩት ግለ ሰቦች፣ በተለይም የህወሓት ደጋፊዎች አደብ ካልገዙ የኢትዮጵያ ህዝብ አንደሚፋራዳቸው እንዲያውቁ፣ ማሳሰብ እንፈልጋለን።
የስም ዝርዝር᎓
1. ህይወት ተሰማ
2. ሕሉፍ በርሀ
3. ስልጣን ኣለነ
4. በየነ ገብራይ
5. ተስፋዬ መሓሪ
6. ተስፋይ ኣፅብሃ
7. ታደሰ በርሀ
8. ነጋሲ በየነ
9. ናትናኤል ኣስመላሽ
10. ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ
11. ኣብራሃ በላይ
12. ኪዳነማርያም ፀጋይ
13. ካሕሳይ በርሀ
14. ዘልኣለም ንርአ
15. ደስታ ኣየነው
16. ዶክተር ግደይ ኣሰፋ
በዚህ መግለጫ ይዘት ሊስማሙ ከሚችሉ ሰዎች ጋር በሙሉ ስላልተነጋገርን በዚህ የሚስማሙ ስሞቻቸውን ወደሚከተለው ኣድራሻ ከላኩልን መግለጫውን በድጋሚ እናወጣዋለን᎓:
ethiocivic@gmail.com



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...