ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, May 5, 2016

''በ1928 ዓም ለዓለም ማኅበር ለተናገርነው ይሄው ታሪክ መሰከረ። ዛሬም በሚያሳፍር መንገድ የፈረሰው የዓለም ማኅበር ወራሽ ለሆነው የተባበሩት መንግስታት ቃላችንን ለማሰማት ቆመናል '' ቀ/አፄ ኃይለ ስላሴ በ1956 ዓም (1963 ዓም እ ኤ አ) ጄኔቭ ያደረጉት ሙሉ ንግግር (ኦድዮ-ቪድዮ)

ዛሬ ሚያዝያ 27/ 2008 ዓም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከአምስት ዓመታት ከጣልያን ጋር ከተደረገ የነፃነት ትግል በኃላ ተመልሶ በቦታው የተተከለበት ዕለት ነው።ኢትዮጵያ በአምስት ዓመታቱ የትግል ወቅት በዓለም ማኅበር (አሁን የተባበሩት መንግሥታት በሚባለው) የነበራት መቀመጫ እንዳይነሳ የተደረገበት አንዱ ምክንያት የንጉሡ በጄነቭ ተገኝቶ መከራከር ነው።ጣልያኖች እና አንዳንድ የእነርሱ የጥቅም ተጋሪ መንግሥታት ''የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ያለበት የዓለም ማህበር ወንበር ይነሳ ኢትዮጵያ በኢጣልያ ስር ነች'' እያሉ ሲደነፉ ንጉሰ ነገስቱ ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጋር መክረው ያመጡት ሃሳብ ታሪካዊ እና አሸናፊ ሆነ። 

ይህም ሃሳብ ኢትዮጵያ የንጉሰ ነገስት መንግስቷ አልፈረሰም።አዲስ አበባ ተያዘች ማለት ኢትዮጵያ ተያዘች ማለት አይደለም።ይልቁንም የመንግስታችንን መቀመጫ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ጎሬ (የዛሬዋ ኢሊባቦር) አዙረናል።እዚያ የሚገኘው መንግስታችንም ትእዛዝ እየተቀበለ እየሰራ ነው።ለእዚህም ከአርበኞች ጋር ያደረጉት የመልክት ልውውጥ ሁሉ በእጄ አለ።የሚሉ ማብራርያዎች የኢትዮጵያን ቦታ ከዓለም ማህበር እንዳይነሳ አስደረገ። ይህ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ተገዝታ እንደማታውቅ ትልቁ የመከራከርያ ሃሳብ ነው።ብዙ የታሪክ ምሁራን ይህንን ነጥብ ስዘነጉት ይታያል።አንድ መንግስት በዓለም ማኅበር (የተባበሩት መንግሥታት) ላይ ቦታው ካልተነካ በመንግሥትነት አለ ማለት ነው።የንጉሰ ነገስቱ ጄኔቭ መገኘት የሰራው ትልቁ ነገር ይህ ነው።ከእዚህ በላይ ጣልያን ንጉሱን ይዞ አስሮ ወይንም ገድሎ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አንድነት በኃላ ምን ይሆን ነበር? የሚለው ሌላው ሃሳብ ነው።ከእዚህ በታች ንጉሡ የተባበሩት መንግሥታት የሚገጥመውን መፃኢ ተግዳሮት የገለጡበት ንግግር እነሆ: 
ንግግሩ በ1956 ዓም (1963 ዓም እ ኤ አ) ጄኔቭ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተደረገ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...