ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, November 26, 2015

ሰበር ዜና - አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌድሬሽን (IAAF) የ2015 ምርጥ አትሌትነትን ውድድር አሸነፈች! ''ቤተሰቤን፣እህቶቼን እና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አመሰግናለሁ!'' ገንዘቤ ሽልማቱን ስትቀበል የተናገረችው።

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ (Photo -AFP )
ዝነኛዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ  ማኅበር ፌድሬሽን (IAAF) የ2015 ምርጥ አትሌትነት ድል ተጎናፅፋለች።በወንዶች አሜሪካዊው አሽቶን ኤቶን (Ashton Eaton) የዓመቱ ምርጥ ተብሏል።
በሽልማቱ ወቅት የ1500 ሜትር ሪከርድ ባለቤት ገንዘቤ ንግግር አድርጋለች።በንግግሯ ሽልማቱን ማሸነፍ መቻሏ ደስታን እንደፈጠረላት ገልፃለች።በመጨረሻም ስለመጪው የፈረንጆች ዓመት ትኩረቷ ስትገልፅ እንዲህ ነበር ያለችው :-
''የ2016 ትኩረቴ የሚሆነው በፖርትላንድ ለሚደረገው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፈድሬሽን  ውድድር እና በየካቲት 17 ስቶኮልም ለሚደረገው የቤት ውስጥ ውድድር ዝግጅት ማድረግ ነው።በተለይ ለስቶኮልሙ የማደርገው ዝግጅት ሪከርድ ለመስበር እሞክራለሁ '' ብላለች።
“My focus in 2016 will be the IAAF World Indoor Championships in Portland and as preparation for that I will try to break the world indoor mile record in Stockholm on 17 February.''
ይህንን ከማለቷ በፊት ግን ''ድምፃቸውን ለእኔ በመስጠት ድጋፋችሁን ያሳያችሁትን ሁሉ አመሰግናለሁ።
ምስጋናዬ ለቤተሰቤ፣ለእህቶቼ፣ለአሰልጣኘ፣ለባልደረቦቼ እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይድረስልኝ'' ብላለች።
“Thank you to all the people who voted for me and supported me. My family, my sisters, my coaches, my partners, my agents and all the people from Ethiopia!
ገንዘቤ ዲባባ  እና እህቷ ጥሩነሽ ዲባባ በኢትዮጵያ እጅግ የሚወደዱ እና የሚከበሩ አትሌቶች ናቸው።በተለይ በወጣቱ ዘንድ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው በዓለም የቴሌቭዥን መስኮት ላይ የሚያሳዩት ኢትዮጵያዊ ትዕይንት ብዙዎች በአእምሮአቸው ቀርፀውታል።
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ እና አሜሪካዊው አሽቶን ኤቶን (Ashton Eaton) 
Photo - IAAF 
የዜናው ምንጭ -IAAF  
ከእዚህ በታች ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌድሬሽን በድረ-ገፁ ላይ የዘገበው ዘገባ ነው።
===========================================
USA’s Ashton Eaton and Ethiopia's Genzebe Dibaba were named the male and female IAAF World Athletes of the Year for 2015 on Thursday (26).
Both athletes set world records during 2015, Eaton in the decathlon and Dibaba in the 1500m, and won gold medals in these events at the IAAF World Championships Beijing 2015.
Ashton Eaton became the first decathlete to win the male World Athlete of the Year award after his spectacular performance in the Chinese capital, his only decathlon of the year, when he set a world record of 9045 and improved his own three-year-old mark by nine points. Notable among his individual events in Beijing was a 45.00 400m at the end of the first day, the fastest one lap of the track ever run within a decathlon.
“Athletes spend the most vigorous years of human life, arguably called the ‘best years’, working to hone their abilities. So, when an athlete competes, what people are witnessing is the manifestation of what a human being is capable of when they choose to direct all of their time and effort towards something.
“I’m grateful and thankful to the IAAF for excellent competitions, the canvases that allow us to display our work.
"While I’m honoured that I am considered the ‘artist’ of the year, I did not beat Usain and Christian; my work simply differed in design. They are some of the most talented and beautiful performers of all time. I’m flattered to be among them.
"I accept this award on behalf of all of us athletes who love what we do.”
Genzebe Dibaba, after setting a world indoor 5000m record of 14:18.86, was then unbeaten in her five 1500m races during the summer. Firstly, she ran an African record of 3:54.11 in Barcelona, the fastest time in the world for almost 12 years, and then topped that with a stunning world record of 3:50.07 in Monaco to beat a mark that had been on the books since 1993. In Beijing, Dibaba was majestic through all three rounds of the 1500m, winning every race comfortably, and she also took a 5000m bronze medal.
“I am humbled and honoured to receive this award from the IAAF," said Dibaba. "It feels so good to be the World Athlete of the Year.
“After being a finalist and narrowly missing out on this award one year ago, I am very proud to be recognised by the fans and experts of our sport.
“I had a great season and truly enjoyed competing around the world, from Monaco where I managed to establish a world record, to Beijing where I finally captured my first world outdoor title.
“I would like to pay tribute to Dafne Schippers and Anita Wlodarczyk who have been incredible all year round. Maybe your time will come next year!
“Thank you to all the people who voted for me and supported me. My family, my sisters, my coaches, my partners, my agents and all the people from Ethiopia!
“My focus in 2016 will be the IAAF World Indoor Championships in Portland and as preparation for that I will try to break the world indoor mile record in Stockholm on 17 February.
“This is a difficult time for our sport and with the Athletes’ Commission we stand together with Sebastian Coe as he deals with the challenges.”
IAAF President Sebastian Coe commented: “While the athletics family is not gathering together as usual in Monaco, we rightly celebrate the marvellous 2015 achievements of the athletes. Foremost, I offer congratulations to our World Athletes of the Year, world champions Ashton Eaton and Genzebe Dibaba. Your performances in 2015 are an inspiration and examples of true sporting excellence.
“A world record when winning a world title is a rare feat and capped two unequalled days of decathlon brilliance from Ashton in Beijing. Genzebe, your win in Beijing was as assured and your 1500m world record a few weeks earlier a run of true grit and determination. We salute you both as we do all our award winners who have been announced today. 
“Finally I wish to thank all the athletes, coaches, officials who work tirelessly for our wonderful sport. Our appreciation also goes to the media for relaying the excitement of competition and to the fans watching in stadiums, in homes and on the move around the world. Your enthusiastic support made the IAAF World Championships in Beijing the most talked about sports event of the year.”

How the award was decided

Last month the IAAF Family* was asked to vote for athletes from each of the following categories: sprints, hurdles, middle and long distance, road running, race walking, jumps, throws, combined events and multi-terrain.
The top-voted athletes in each category formed the longlist for the World Athlete of the Year, from which an international panel of 10 experts** selected the three finalists. The panel cast their own vote to determine the IAAF World Athletes of the Year.
Source - IAAF

ጉዳያችን GUDAYACHN
ህዳር 17/2008 ዓም (November 27/2015)

ይሄው ስንት ዓመታት አለሁኝ ሰግቼ፣ በገዛ አገሬ ላይ አገር ተቀምቼ (የግጥም ምሽት ቪድዮ)

...ይሄው ስንት ዓመታት አለሁኝ ሰግቼ፣
        በገዛ አገሬ ላይ አገር ተቀምቼ።
አየሩም የኔ አይደል የምተነፍሰው፣
        አፈሩም የኔ አይደል እግሬ የሚረግጠው።
ፀሐይ ጨረቃየን ቀምቶኝ የበላይ፣=
         ባይተዋር ሆኛለሁ በገዛ አገሬ ላይ።
አለሁኝ አልልም ምኑን አለሁኝ፣
         በገዛ አገሬ ላይ አገሬን ቀሙኝ።
ትናንትም አይደለ ይሄው አሁን ዛሬ፣
        ክፍቱን ያደረ ቤት ሆናለች አገሬ።...

የአንድነት ፓርቲ ወጣቶች የግጥም ምሽት (ከዩቱዩብ) 



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Monday, November 23, 2015

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 961፣ህዳር 14 እና ወጣት ትሑት ዘመድ (እውነተኛ ታሪክ ከማስታወሻ ደብተሬ)




ከጌታቸው በቀለ 
ኦስሎ፣ኖርዌይ 

ሁሉን አክባሪው አቶ ሰለሞን 

ከትምህርት ዓለም ለመጀመርያ ጊዜ የስራ ዓለምን የተቀላቀልኩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መስርያቤትን ነበር።ለገሃር የሚገኘው ቴሌ አጠገብ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጭ ህንፃ አምስተኛ ፎቅ የሰው ኃይል አስተዳደር እና ቅጥር ክፍል ቢሮ በርን ቀስ ብዬ ቆረቆርኩት እና  ቀስ ብዬ ከፍቼ ወደ ውስጥ ዘለኩ።ምቹ በሆነ ሰፊ ወንበር ላይ ''አቶ ሰለሞን የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍል ኃላፊ'' የሚል ፅሁፍ ጀርባ ትከሻው ሰፊ በስፖርት የዳበረ እና ንቁ ሰው ተቀምጧል።አቶ ሰለሞን።

''ይግቡ!'' አለና በሩን ከፍቼ ወደ ውስጥ ስገባ በመነፀሮቹ አናት ላይ ተመለከተኝ እና ከመቅፅበት ከመቀመጫው ተነሳ። በጣም ደነገጥኩ። ቀጠለና ''ጤናይስጥልኝ ምን ልርዳህ? ግባ ግባ'' አለና እጆቹን ዘረጋልኝ።በፍጥነት ጠጋ ብዬ የተዘረጉ እጆቹን ማክበሬን ለመግለጥ በግራ እጄም ጭምር ደግፌ ጨበጥኩት።ቀጠልኩ እና መናገር ስጀምርም አቶ ሰለሞን እንደቆመ ሲያናግረኝ ይበልጥ ትህትናው አስገረመኝ።በቀን ስንት ጊዜ ይነሳል? ሰው በገባ በወጣ ቁጥር እንዴት ይችለዋል? ብዬ ከእራሴ ጋር እየተሟገትኩ -

'' እ እ ደውላችሁልኝ ነበር።እዚህ መስርያቤት ለስራ'' ስለው ይበልጥ ፈገግ ብሎ እንድቀመጥ በእጁ በድጋሚ ወንበሩን አሳይቶኝ ከፊቱ ካለው ቀይ የወረቀት ትሪ ላይ አንድ ወረቀት አንስቶ እያየ 

''ስም ማን ልበል?'' አለኝ። ''ጌታቸው በቀለ'' አልኩት። አገኘው እና በእስክርብቶው ምልክት አደረገበት እና ቀና ብሎ በፈገግታ እያየኝ።''አቶ ጌታቸው የመስርያቤታችን ባልደረባ በመሆንህ ደስተኛ ነኝ'' አለና ወረቀቶች እየመረጠ በአንድ ክላሰር ላይ ካደረገ በኃላ  ''እነኝህን ፎርሞች  ትሞላለህ፣ይህንን ፖሊስ ጋር ወስደህ አሻራ ትሰጣለህ፣ይህንን ደግሞ ተያዥ ሥራ ላይ ያለ ሰው ታስፈርማለህ፣ይህንን ለሆስፒታል ምርመራ፣ይህ ላንተ ቀሪ'' እያለ ካሳየኝ በኃላ በመጪው ሳምንት ሁሉን ጨርሼ እንድመጣ ነግሮኝ እንደገና ከመቀመጫው ተነስቶ ከጨበጠኝ በኃላ ከክፍሉ ወጣሁ።

ከንግድ ባንክ ቢሮ እንደወጣሁ ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ የቀድሞ የክፍሌ ልጆች ጋር አምባሳደር ኬክ ቤት ጋር ተቀጣጥረን ስለነበር ወደዚያ አመራሁ።እዚያ እንደደረስኩ የክፍሌ ልጆች አምባሳደር ኬክ ቤት በር ላይ ቆመው ይጠብቁኝ ኖሮ ወደውስጥ ለመግባት ቦታ እንደሞላ እና ዋናው ፖስታ ቤት ስር የሚገኘው ''ራንዴቭኦ'' ካፍቴርያ ማምራት እንዳለብን ቀድመው መወሰናቸውን ነገሩኝ። ''ራንዴቭኦ'' በተለይ በውጭ በረንዳው በኩል ሰፊ በመሆኑ ለሰባታችንም በሰፊው ከበን ለመቀመጥ ተመቸን።ሁላችንም ከትምህርት ዓለም በኃላ ስለገባንበት መስርያቤት ማውራት ጀመርን።ልማት ባንክ የገቡት ወድያውኑ የሳምሶናይት ቦርሳ እንደተሰጣቸው እና ስልጠና መጀመራቸውን ኮራ እያሉ ሲነግሩን፣ የግል ድርጅት የገቡት ደግሞ ስለገንዘቡ ክፍያ የቀረነውን ማቁለጭለጭ ያዙ።ንግድ ባንክ የገባነው ደግሞ የንግድ ባንኩ የሰው ኃይል ኃላፊ የአቶ ሰለሞን ትሕትናን እያደነቅን ነገርናቸው።ንግድ ባንክ የገቡት  ለካ ሁሉም በልቡ የአቶ ሰለሞን ፍቅር የተላበሰ ትህትና እያወጣ እያወረደ ነበርና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ገና ሥራ ሳይንጀምር ወደድነው።በተለይ ሁለት የክፍላችን ልጆች ሥራ ባገኙበት መስሪያ ቤት የነበረውን የንቀት አስተያየት እያነሱ ሲነግሩን የኛውን ንግድ ባንክ ገና ሳንገባበት ሳሳንለት።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ እየሰሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አካል መሆን 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞችን ሲቀጥር በቻለው መጠን ሰራተኞች በሚኖሩበት አካባቢ እንዲሆን ይጥራል።የስራ ምደባችን ሲደለደል ሁሉም በሚኖርበት ቀበሌ አካባቢ ሲመደብ የእኔዋ ሰፈር የወሎ ሰፈር ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለሚቀርብ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ እንድመደብ ተወሰነ።

''አቶ ጌታቸው በቀለ ከፍተኛ ---ቀበሌ --- ማለት ወደ አይቤክስ ሆቴል የሚወስደው መንገድ ወሎ ስፈር ጥሩ እዚያጋ የባንካችን ሰርቪስ አለ አመቺ ይመስለኛል።ስለዚህ አቶ ጌታቸው ''ኤርፖርት ቅርንጫፍ'' ተመድበሃል'' አለኝ አቶ ሰለሞን የቅጥር ደብዳቤዬን ሲሰጠኝ እና ለቅርንጫፍ ሥራ አስያጅ የሚሰጠውን ደብዳቤ እያሳየኝ።ያን ጊዜ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የነበሩት ፒኮክ ሬስቱራንት እና አየር መንገድ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ነበር።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ባንኩ በወቅቱ ብቸኛ የባንክ አገልግሎት ሰጪ ነበር።ማለትም ምንም የግል ባንኮች አልተከፈቱም።አየር መንገዱ ውስጥ የሚገኘው የተርሚናል አገልግሎት እና ግቢው ውስጥ ሁሉንም የባንክ አገልግሎት የሚሰጠው ''አየር ማረፍያ ቅርንጫፍ'' የሚሉት ነበሩ።

አቶ ሰለሞን በተለይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰራሁባቸው አመታት በሥራ አጋጣሚ በደንብ ያወኩበት ጊዜ ነበር።አቶ ሰለሞን አሁን ድረስ በሕይወቴ የማልረሳው ሰው ነው።ትልቅ ትንሽ የለም ሁሉን ያከብራል።ትህትናው ነገሮችን የሚያስረዳበት አግባብ ሁሉ ምናልባት ከሺህ ሰው አንድ ይገኝ ይሆናል።በኃላ በሥራ አጋጣሚ እንደተረዳሁት ከልጅነቱ ጀምሮ ኮትኩታ ያሳደገችው የመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል (ግቢ ገብርኤል) ሰንበት ትምህርት ቤት ''አምደ ሃይማኖት'' ለእርሱነቱ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረገች ለማወቅ ችያለሁ።ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን አቶ ሰለሞን እኔ እዚያው መስርያ ቤት እያለሁ ወደ አሜሪካ መሄዱ ነበር።በአቶ ሰለሞን መሄድ በመላው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰራተኞች በጣም ማዘናቸው ትዝ ይለኛል።

የሐዋሳው ባንክ ሥራ አስኪያጅ የገጠማቸው ፈተና 


በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አየር ማረፍያ ቅርንጫፍ ስራዬን በጣም ወደድኩት።በተለይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወቅቱ ከነበሩት ቅርንጫፎች ውስጥ ለሰራተኞቹ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው ለአየር ማረፊያ ቅርንጫፍ እና ለአቃቂ ቅርንጫፍ ነበር።ይህ የሆነበት ምክንያትም አየር መንገዱ ውስጥ ለመግባትም ሆነ ወደ አቃቂ ቅርንጫፍ ለመሄድ በቀላሉ ታክሲ ስለማይገኝ የሰራተኛ ማኅበሩ በህብረት ስምምነቱ ላይ ከተደራደረበት የመብት ጥያቄ ውስጥ አንዱ የሁለቱ ቅርንጫፎች ጉዳይ ነበር።በመሆኑም ከወሎ ሰፈር አየር መንገዱ ውስጥ የሚሄድ ሰርቪስ ማግኘቱ ለእኔ ተስማምቶኝ ነበር። በሌላ በኩል ንግድ ባንክ አሰራሩም ሆነ ያለው ዓለም አቀፍ አሰራሩ ሁሉ እንደ ሌላ መስርያቤት በቀላሉ ለሥርዓት አልባ ሰራተኛ አመቺ አይደለም። በእርግጥ በዘመነ ኢህአዴግ በተለይ ገና ኢህአዴግ ስልጣን እንደያዘ ሰሞን የባንክ አሰራርን ባህሪ የማይረዱ ካድሬዎች እንደ ግላቸው ሊያዙት ሞክረው ነበር።

እዚህ ላይ አንድ አስቂኝ ታሪክ በወቅቱ የነበሩት የቅርንጫፋችን ሥራ አስኪያጅ የነገሩኝ አሁን ድረስ ያስቀኛል።ሥራ አስኪያጁ በወቅቱ ሐዋሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንታት ነበሩ።ታሪኩ እንዲህ ነው።

ወቅቱ   ኢህአዴግ ገና ስልጣን መያዙ ነበር።አንድ ቀን ጧት ሥራ ላይ እያለን ሁለት ታጣቂዎች የታጀበ አንድ የደቡብ ክልል ባለስልጣን ወደ ሥራ አስኪያጁ ይጠጋና ማነጋገር ይጀምራል።በጉዳዩ ላይ ባለመስማማት እራሳቸውን ስነቀንቁ ከማዶ ሆኘ እመለከታለሁ።በኃላ እንደተረዳሁት ሥራ አስኪያጁ ነገሩ ግራ ቢገባቸው  ከባንኩ ሌሎች ኃላፊዎች ጋር ልነጋገር ይሉ እና ሰዎቹን አሰናብተው የዛሬውን የቅርንጫፋችን ሥራ አስኪያጅ የያኔውን የሐዋሳ ባንክ ቅርንጫፍ አካውንታት እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ይሰበስቡ እና ጧት ስለመጡት  ሰዎች ይነግሯቸዋል።ጉዳዩን በኃላ እንደተረዱት ከኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ባንኩ ውስጥ ኃላፊ ሰው መመደቡን እና  ደብዳቤ መያዛቸውን እንግዶቹ ለስራ አስኪያጁ ገልጠው ኖሯል።ሥራ አስኪያጁ የባንክ ሥራ በምድብ ሳይሆን በባንኩ ቅጥር በኩል ማለፍ እንዳለበት እና ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ማመልከት እንዳለባቸው ነግረዋቸዋል።ሆኖም ሰዎቹ አልተስማሙም።የክልሉን ጉዳይ የሚመለከተው ክልሉ እንጂ አዲስ አበባ አለመሆኑን በዘመኑ የብሄር ብሔረሰቦች መብት ንግግር ይናገራሉ።ይልቁንም  በሥራ አስኪያጅነት የተቀመጠ ሰው እንዴት የአገሪቱን ለውጥ አለማወቁ በስራው ላይ የብቃት ችግር እንደሚያሳይ በቁጣ ይናገራሉ። አሁን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሥራ አስኪያጁ ለመመካከር ይህንን ስብሰባ ለመጥራት መገደዳቸውን ገለጡልን ።
''መጨረሻው ምን ሆነ?'' ብዬ ጠየቅሁ።የቀድሞው አካውንታት የአሁኑ ሥራ አስክያጃችን ሳቃቸው እንደመጣ ሁኔታውን ማብራራት ጀመሩ።'' ከሁሉ በወቅቱ የገረመን ዋናው መስሪያ ቤት ጉዳዩን መፍታት አልቻለም።ግን ብልህ ሰዎች ነበሩ።ነገሩን ከክልሉ ጋር መፍታት ሳይችሉ አንድ ዘዴ አመጡ።ይሄውም ለግለሰቡ  ለጊዜው የስራ አስኪያጅ ወንበር እና ትልቅ ጠረንጴዛ እንዲሰጠው እና ትኬቶች እና ሰነዶች ላይ ግን እንዳይፈርም የሚል ነበር።በተጨማሪም ደሞዙን የደቡብ ክልል እንደሚከፍል እና ባንኩ ምንም ወጪ እንደማያወጣ ተነገረን። በመሆኑም ግለሰቡ ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀናት ያክል በትልቅ ወንበር ላይ ተቀምጠው ጋዜጣ እና መፅሄት ሲያነቡ አንዳንዴ የባንኩን ማንዋል ሲመለከቱ እና በባንኩ ሂሳብ ስልክ ሲደውል ከርሞ አንድ ቀን ክልሉ ሌላ ሹመት ስለሰጠው ቅርንጫፉን ለቆ በመሄዱ ትልቅ እፎይታ ተፈጠረ'' አሉኝ። 

''ራንዴቭኦ ሊንጋፎን ''የፈረንሳይኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት  እና ወጣት ትሑት ዘመድ 

ንግድ ባንክ ሥራ እንደጀመርኩ የምሽቱን ጊዜ በከንቱ እንዳያልፍ እፈልግ ስለነበር እና የፈረንሳይኛ ቋንቋ ለማወቅ ጉጉት ለነበረኝ በእዚያን ጊዜ ዋናው ፖስታ ቤት የሚገኘው ''ራንዴቭኦ ሊንጋፎን'' የቋንቋ ትምህርት ቤት ፈረንሳይኛ መማር ጀመርኩ።በእዚህ ትምህርት ቤት በቆየሁበት ጊዜ  ውስጥ ግን ቋንቋውን ብቻ ሳይሆን እስካሁን ድረስ የማልረሳቸው ጥሩ ሰዎችን ያወኩበት ነበር።ከእነዚህ ውስጥ አንዷ እና ዋናዋ ትሑት ዘመድ ትባላለች።ትሁት የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በናዝሬት ስኩል ተምራለች በወቅቱ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የላይብረሪ ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ትምህርት ተምርቃ መጨረሷ ነበር። በተለይ ከትምህርቱ በኃላ በክፍል ውስጥ ከነበርነው ተማሪዎች ውስጥ ወደ ቦሌ መስመር የምንሄደው አብረን የምናወራበት ጊዜ እንዳያንስ ታክሲ ይዞ መሄድ ትተን እስከ መስቀል አደባባይ በእግር መምጣት አልያም ማኅተመ ጋንዲ መታሰብያ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኙት የጭማቂ ቤቶች ገብቶ ማውራት በዓላት ባሉበት ቀናት ደግሞ  ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሄደን ተሳልሞ መሄድ ስራችን ነበር።

ትሑት ከሁላችንም የበሰለ አስተሳሰብ ያላት ነች።የአንድ ሰው ጥሩነት እና መጥፎነት ለማወቅ ደቂቃ አይፈጅባትም።ለጫወታ እና የሚያስቁ ነገሮችን አስፍታ እና አጉልታ በማቅረብ የሚያክላት የለም።ብሽሽቅ ከተጀመረ የዛሬ ወር የነበረ ታሪክ ጋር አገናኝታ ማብሸቅ ትችልበታለች።ትንሽ ቆይታ ደግሞ ትራራና ማሳሳቅ ትጀምራለች።

አንድ ቀን ''ስንነጋገር በፈረንሳይኛ ብቻ ይሁን'' አለችን።
እኛ ምኑን አውቀን? አልናት።'
'የምናውቃትን ቃላት እየገጣጠምን ማውራት ነው እንዲህ እየተባለ ነው የሚለመደው'' አለች።ትሑት ለካ የተወሰኑ ቃላትን የሸመደደችበት ቀን ነበር እና ግሱን ሳታዛንፍ ታወራን ጀመርን ተደነቅን።እኛ ገና ''ስምህ ማነው?'' ያለፈ ችሎታ ስላልነበረን።እንዴት ባንዴ አወቅሽ? ብለን ወጥረን ያዝናት።እርሷ ለካ ቀን አረፍተ ነገሮችን በእጇ ላይ ፅፋ ተዘጋጅታ ሲጠፋት  ዘወር እያለች ነበር የምትነግረን።ይህንንም የነገረችን በዕለቱ ነበር።አላስቻላትም። ትሑትን ታክሲ ሲያዝ አስቀድሞ ማስገባት የግድ ነው።አለዝያ ወደረዳቱ ጠጋ ብላ ሂሳቡን ሰጥታ ትገባ እና ሂሳብ ልትከፍሉ ስትሉ የታክሲው እረዳት ''ተከፍሏል''ሲላችሁ ወደ ትሑት መመልከት ነው።ያን ጊዜ ቆጣ ብላ ''እና ምን ልትል ነው?የተከፈለ እንደሆነስ?'' ብላ በቁጣ መልስ ታሳጣለች። ለእዚህ መፍትሄው ወደ ታክሲ ስትገባ ከረዳቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳታደርግ ማድረግ ብቻ ነው።

ትሑት ከሁሉ የሚገርም  ሌላም ባህሪ ነበራት።የተቸገረ ሰው ስታይ ሀዘኗ ምን ያህል ልቧን እንደሰበረው ከፊቷ ላይ ይታያል።''የእኔ ቢጤ'' ካጠገቧ መጥቶ ሲለምን ሳንቲም መስጠት ያሳቅቃታል።ጭብጥ አድርጋ አንድ ብር ትሰጣለች።ይህንን የሚያውቁ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የነበሩ ''የእኔ ብጤዎች'' ሌላ ቀን እዝያው ለመሳለም ስንሄድ ከመቀመጫ ተነስቶ ያክል የቀረው ሰላምታ እና ምርቃት ያዥጎደጉዱልናል።አንድ ቀን እንዲሁ ትልቅ ፌስታል ከቦርሳዋ በተጨማሪ ይዛ ወደ ክፍል መጣች። ከክፍል እንደወጣን ''ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን መሄድ አለብን'' አለችኝ።
ቀኑን ሳስበው ምንም በዓል የለም።ዝናብ መጥቷል እና ''አሁን እንደርሳለን?'' ጥያቄ አቀረብኩ።'
'የግድ ነው።እስከ ፍላሚንጎ ታክሲ ይዘን መሄድ እንችላለን'' አለችኝ። 
አንዳንድ ቀን ለእግዚአብሔር ሳልነግረው ማደር የለብኝም የሚባል ጉዳይም አለ እና ''እሺ ! '' ብዬ አብረን ሄድን በቦሌ በኩል ባለው የቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ በኩል እንደገባን ''መጀመርያ ይህንን ዕቃ ለእማማ መስጠት አለብኝ''አለች እና ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የአፍሪካ ህበረት በር በኩል ወዳሉት  ለልመና የተቀመጡት እናት አቅጣጫ አመራች። ትሑት ''እማማ'' የምትላቸውን እናት አውቃቸዋለሁ።በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ምዕራብ በር በኩል የሚቀመጡ እናት ናቸው።ትንሽ ነገር ስትሰጡዋቸው ምርቃታቸው ከልብ ነው። ትሑት ደግሞ ከልቧ ትሳሳላቸዋለች።ያን ቀን በፌስታል የያዘችውን ቀስ ብላ ''እማማ እንዴት አመሹ? ይችን ዕቃ አምጥቸልዎታለሁ'' አለቻቸው። እማማ የቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ሊዘጋ ገርበብ በማለቱ እና ዝናቡ መጣሁ እያለ በማጉረምረሙ ይመስላል ጭብጥ ብለው መሬቱ ላይ ተኝተው ላስቲክ ከላያቸው ላይ ደርበዋል። ስማቸውን ትሑት ስትጠራ ቀና አሉ። ያመጣችላቸውን ፌስታል ቀና ብለው ተቀብለው በእጃቸው ዳበሱት ልብስ እና ጫማ እንደሆነ ወድያው አወቁት  ከደስታቸው የተነሳ እንባቸው ዝርግፍ  አለ። 

ትሑት  ብዙ መቆየቱ ስሜታቸውን መጉዳት እንደሆነ ገብቷታል እናም ቶሎ ብላ ''በሉ ደህና እደሩ ቀሰቀስኩዎት? ይቅርታ! እማማ'' እያለች እኔ ወደ ቆምኩበት መምጣት ጀመረች። እማማ ግን መልሰው ጠሯት። ''ልጄ ቤትሽ የት ነው? በምሽት ይህን ተሸክመሽ፣ ተባረኪልኝ! ብቻሽን ልጄ!'' አሉ እና ቀና ብለው አዩኝ። ትሑት ''ይሄው ወንድሜ አለ'' አለቻቸው።''ወንድምሽ ነው? ተባረኩ በደከመ አቅማቸው ቀስ ብለው ተነሱና እጆቻችንን ይዘው ሳሟቸው። ''ተባርኩ እናት አባታችሁን ይባረኩ።እጆቻችንን ሲስሙ የእንባቸው ጠብታ እጆቼ ላይ አረፉ።ትሑት ቀድሞ የነበረው ለተቸገረ ማዘን ይብስ ተቀሰቀሰባት።እንባዋ ወድያው መውረድ ጀመረ።እማማን ተሰናብተን ተመልሰን ፍላሚንጎ ጋር ቆመን ታክሲ ስንይዝ ሁሉ በተሰበረ ልብ ነበር።ትሑት መኖርያ ቤቷ በጃፓን ኤምባሲ መግቢያ ገባ ብሎ በመሆኑ እኔ ቀድሜ ሰፈሬ ወሎ ሰፈር ላይ ወረድኩ።ታክሲው ከመቼው ሰፈሬ እንደደረሰ አላውቅም።ብቻ በሃሳብ ተውጠናል።በድንጋጤ፣በሃዘን እና በተሰበረ ልብ ሆነን እማማን እያሰብን ነበር የታክሲ ጉዟችን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛዋ ትሑት ዘመድ 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አየር ማረፍያ ቅርንጫፍ ሥራ የሚጀምረው ከጧቱ 2 ሰዓት ነው።ይህ ማለት ሰራተኛው ቢያንስ ቀድሞ 15 ደቂቃ ገብቶ ተዘጋጅቶ መጠበቅ አለበት።ይህ ቅርንጫፍ ከሌላው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚለየው ባብዛኛው አገልግሎት የሚሰጠው ለፈጣኖቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች መሆኑ ሲሆን እነርሱ ደግሞ ከስራ ገበታቸው ተነስተው ወደ ባንኩ መጥተው የሚፈልጉትን አገልግሎት በፍጥነት መስጠት ግዴታችን ነበር።ምክንያቱም ጊዜ የላቸውም።የስራ ሰዓት 'ዲሲፕልናቸውም' እጅግ የሚያስደስት በመሆኑም 2 ደቂቃ ማርፈድ ማለት ትልቅ ቀውስ የመፍጠር ያክል ነው።

አንድ ቀን ቀትር ላይ  ከስራ ሰዓት ቀድሜ ምሳ እንደጨረስኩ በሥራ ገበታዬ ላይ ሆኘ ጧት የተሰሩ ትኬቶችን አስተካክላለሁ።ባንኩ ገና የምሳ ሰዓት አገልግሎት መስጠት ያልጀመረበት ጊዜ ነበር እና በምሳ ሰዓት ደንበኛ ወደ ባንኩ አይመጣም።በመካከል እኔ ወዳለሁበት ወንበር  የጥበቃው ሰራተኛው መጥቶ  ጮክ ብሎ -
''ጌች  ሰው ውጭ ይፈልግሃል። ሰዓት ስላልደረሰ ጠብቂ ብላት ጥራልኝ አለችኝ'' አለኝ።  
በእዚህ ሰዓት ማነው? የፈለገኝ እያልኩ ከሃሳቤ ጋር እይተሟገትኩ ወደ ውጭ ወጣሁ። ከውጭ በኩል የባንኩን መከፈት የሚጠብቁ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ብዙዎቹ ከአየር መንገዱ ዩኒፎርም ጋር እንዳማረባቸው ቆመዋል።የማውቃቸውን ሰላምታ እየሰጠሁ እናባንኩ ሊከፈት የቀረው 10 ደቂቃዎች ነው የሚል የማፅናኛ ቃል እየተናገርኩ።ወደ ፈለገኝ ሰው ፍለጋ አይኖቼን ወረወርኩ። ትሑት ነበረች።በጣም መደሰቷ ከፊቷ ይታወቃል።የዕለቱን ደስታዋን  ለመንገር ቃላት አጥሯታል። ባጭሩ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ አስተናጋጅነት ማለፏን ልትነግረኝ ነበር። 

ትሑት ለበረራ አስተናጋጅነት ትክክለኛ ሰው እንደሆነች አውቃለሁ።ይህ ደግሞ እግዚአብሔር በሰጣት ውበት ብቻ አይደለም እንደስሟ ሰውን በጥንቃቄ እና በትሑትና የማናገር እና  የመርዳት ፍላጎቷ ብቻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትሑትን የመሰለች ሰራተኛ በማግኘቱ በጣም እድለኛ ነው አልኩ።እውነት ለመናገር የመስርያቤቱን የቅጥር ክፍልም አደነኩት።የሰው አመራረጡ በትክክለኛ መስፈርትም  በመምረጡ።

በቀጣዩ ጊዜያት ትሑት የአየር መንገዱ አስተናጋጅነት ስልጠና ስትወስድም ሆነ ከተመረቀች በኃላ በሥራ ላይ እያለች የወር ደሞዝ ለመውሰድ ወደ ባንኩ ስትመጣ በቀጥታ እንደምትቸኩል መንገር እና ቼኩን ከጀርባው ፈርማ ከመታወቂያ ጋር ቶሎ እንዳሳልፍ ሰጥታኝ ገንዘብ ቤት መጠበቅ ነው።ደንበኛን በፍጥነት እና በጥራት ማስተናገድ ደግሞ ስራዬ ነው።ያውም ለትሑት ሆኖ። ትሑት እኔ በሌለሁበት ቀን ከመጣች የስራ ባልደረቦቼ እንደ እኔ ሆነው ማስተናገዳቸውን እና ውለታ እንደዋሉ እየቀለዱ የሚነግሩኝ ብዙ ጊዜ ነበር። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 961 እና ህዳር 14 

ቀኑ ቅዳሜ ህዳር 14 ቀን ነው። የአዲስ አበባ አየር እንደ ወትሮው በውብ የፀሐይ ብርሃን እና ነፋሻማ አየር ሆድ ያባባል።ከረፋዱ 4:30 ገደማ ከባንኩ ውጭ ማክያቶ ጠጥቼ ተመልሼ ወደ ባንኩ እየገባሁ ነው።ከኃላዬ የበረራ አስተናጋጅ ወ/ሮ የሺመቤት ሁለት ልጆቿን ይዛ ባንድ እጇ የአየር መንገድ ቼክ ይዛ ጠራችኝ ዘወር አልኩ።

''ሳትገባ ይችን ቼክ ቶሎ ካሽ አስደርግልኝ መጣሁ አሁን በረራ አለኝ'' አለችኝ ብላ ከቼኩ ጀርባ ፈርማ ከመታወቂያዋ ጋር ሰጠችኝ። ወድያው የባንኩን ካውንተር ሳላልፍ ከውጭ ሆኘ ለተናኘ ለባንኩ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ፊርማ አረጋጋጭ ሰጠሁ።ተናኘ ፈገግታ በማይለያት መስተንግዶ ''ኦ! የሺእመቤት'' አሁን አላየኃትም እንዴ?'' አለች እና ፊርማውን አረጋግጣ ቼኩን ወደ ገንዘብ ክፍል አሳለፈችው።ወዲያው የሺመቤት መጣች።ቼኩ ማለፉን ነገርያት ገንዘቧን ይዛ አመስግና ሕፃናት ልጆቿን ለሚረከባት ሰው ሰጥታ፣ አቅፋ እና ስማቸው  ወደ በረራዋ አመራች።ወደ በረራ ቁጥር 961።

ህዳር 14 ቀን 1989 ዓም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767፣ የበረራ ቁጥር 961  አስራሁለት የበረራ አስተናጋጅ፣ ካፒቴን ልዑል አባተ (የሺ እመቤት እና ወጣት ትሁት ዘመድም በረራው ውስጥ አሉ)  እና 163 መንገደኞችን ይዞ ወደ አቢጃን  አቀና።ከበረራው ጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ግን አይሮፕላኑ ተጠለፈ።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ግንቦት ወር 1998 ዓም የበረራውን ጠለፋ አስመልክቶ ባቀረበው የውስጥ ሪፖርት ላይ እንደገለፀው አይሮፕላኑ ከምድር እንደለቀቀ ከ20 ደቂቃዎች በኃላ ሶስት ጠላፊዎች በፍጥነት አይሮፕላኑን እንደጠለፉት እና ማንም ተሳፋሪ እንዳይንቀሳቀስ እንዳስጠነቀቁ ሪፖርቱን ይጀምራል።ሁለቱ ጠላፊዎችም በፍጥነት ወደ ካፒቴን ልዑል የበረራ ክፍል ገብተው ብዛታቸው 11 እንደሆነ እና አይሮፕላኑን ይዞ ወደ አውስትራሊያ እንዲበር በኃይል እና በጉሸማ ነገሩት።ካፒቴን ልዑል አይሮፕላኑ ነዳጅ እንደሌለው እና አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል ደጋግሞ ነገራቸው።ጠላፊዎቹ ግን በአየር መንገዱ ''ሰላምታ'' የተሰኘው መፅሄት ላይ  ቦይንግ 767 ለ11 ሰዓታት ነዳጅ ቆጥቦ እንደሚበር አንብበናል እያሉ አዋከቡት።ካፒቴን ልዑል በማስታወቂያ እና በነባራዊውሁኔታ መሃል ልዩነት መኖሩን እና በአሁኑ ወቅት ግን ነዳጅ እንደሌለው ደጋግሞ ነገራቸው።አልሰሙትም።

ካፒቴን ልዑል አባተ እጅግ አዘነ።ከእራሱ ሕይወት ይልቅ የተሳፋሪው ሕይወት አሳዘነው።አንድ አይነት ውሳኔ መወሰን እንዳለበት ተረድቷል።በሪፖርቱ ዝርዝር ላይ እንደተገለፀው የበረራ አስተናጋጅ ትሁት እና ፅጌረዳ በተቀመጡበት አንዱ አሸባሪ ሁለቱን ትክ ብሎ ከተመለከተ በኃላ ፅጌረዳ እንድትነሳ እንዳዘዛት ያትታል።በመካከል አሸባሪዎቹ ተሳፋሪዎቹን ለማስፈራራት ከካፕቴን ልዑል ክፍል ወጣ እንዳሉ ካፕቴን ልዑል የመናገርያውን ድምፅ ማጉልያ አንስቶ ተሳፋሪዎቹን በጠላፊዎች ላይ አንድ አይነት እርምጃ እንዲወስዱ አስታወቀ።በእዚህ ጊዜ ግን የአይርፕላኑ አንዱ ሞተር ስራውን አቁሞ አይሮፕላኑ ኮሞሮስ አጠገብ ወደ ሚገኘው ወደ ህንድ ውቅያኖስ እያሽቆለቆለ ነበር።በመጨረሻም አይሮፕላኑ በግራ ክንፉ በኩል ውቅያኖሱ ላይ ወደቀ።163 መንገደኞች፣ ያች ለሰው የምታዝነው ሩህሩህ እንደ ስሟ ትሑት የሆነቸው ወጣት ትሑት ዘመድ፣የልጆቿ ነገር የማይሆንላት  ሕፃናት ልጆቿንም ''መጣሁ! ቶሎ ነው የምመጣው'' ብላ የባንክ ቼክ ቶሎ እንዲመነዘርላት የጠየቀችው ወ/ሮ የሺመቤት ወ/መስቀል፣እውቁ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካፒቴን ልዑል አባተ ሁሉም ባህሩ ውስጥ ገቡ።የዓለም የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ''ሰበር ዜና'' ብለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 961 በኮሞሮስ ደሴቶች አጠገብ መከስከሱን ዘገቡ።
ኢትዮጵያ አየር መንገድ  ንብረት የሆነው ቦይንግ 767 ኮምሮስ ደሴት አጠገብ አደጋው ሲደርስበት 

በአደጋው ከበረራ ክፍሉ ባልደረቦች 
በሕይወት የተረፉ 
1/ ካፒቴን ልዑል አባተ፣
2/ ኦፊሰር ዮናስ መኩርያ፣
3/ የበረራ አስተናጋጅ ወ/ሮ የሺመቤት ገ/መስቀል፣
4/ የበረራ አስተናጋጅ ህይወት ታደሰ፣
5/ የበረራ አስተናጋጅ ግርማይ ለምለም እና 
6/ መካኒክ ሺበሺ መልካ ሲሆኑ 

ሕይወታቸው ያለፈው 
 1/ የበረራ አስተናጋጅ ፅገረዳ እስጢፋኖስ፣ 
2/ የበረራ አስተናጋጅ ዮዲት ሰብስቤ፣
3/ የበረራ አስተናጋጅ ትሑት ዘመድ አገኘሁ፣
4/ የበረራ አስተናጋጅ ፀሐይ ዘውዴ እና 
5/ የበረራ አስተናጋጅ ስሜ ጉልማ ነበሩ።

ከመንገደኞች ውስጥ 44ቱ ከአደጋው ሲተርፉ የቀሩት 119ኙ ሕይወታቸው አልፏል።

ዜናው በባንካችን ውስጥ እንደተሰማ ሁላችንም አለቀስን።እጅግ የሚያሳዝን በሕይወት የማይረሳ ስብራት ነበር።ሽብር እና አሸባሪን በዜና መስማት ይቀላል።እንደ ትሑት አይነት ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ማወቅ ግን የልብ ስብራት ሆኖ ለዘለዓለም ይኖራል።ሌላው አሳዛኝ ቀን የትሑት እና በአደጋው የሞቱ ኢትዮጵያውያን አስከሬን ቦሌ አየር መንገድ የደረሰ ቀን ነበር።

የትሑት አባት እጃቸውን እንዳጣመሩ በሃዘን የቆሰለ ሆዳቸውን ይዘው ወደ አየር መንገዱ አውቶብስ ገቡ።አስከሬኖቹ ከአውቶብሶቹ ፊት ሄዱ።ብዙ ሕዝብ ከውጭ ሆኖ ሀዘኑን በለቅሶ ይገልጣል።

ወጣት ትት ዘመድ 

ነገ ህዳር 14/2008 ዓም የትሑት እና የሌሎችን ሕይወት የቀጠፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 961 የሚረሳው የለም።አመታት ቢያልፉትም ዛሬ ድረስ እየቆየ ያሳቅቃል።ትሑት እና በአደጋው የሞቱት ኢትዮጵያውያን ቀብር የተፈፀመው ብዙ ሺህ ሕዝብ በተገኘበት፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስትተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ፣የእስልምና እና የሌላ እምነት ተከታዮች በተገኙበት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ነበር ።በቀብሩ ሰዓት ከሚተራመሰው ሕዝብ መካከል ሆኘ ሳስበው ትሑት እንዲህ በአጭር ጊዜ ሕይወቷ መቀጠፉን መቀበል አልቻልኩም። አሁንም ድረስ እውነት አይመስለኝም።ሽብር ምን ማለት እንደሆነ ለማያውቁ ሽብር ማለት ይህ ነው።ፍፁም ንፁሃን እና የዋሃንን ካለ ጊዚያቸው መቅጠፍ።

ከቀናት በኃላ የበረራ አስተናጋጅ ወ/ሮ የሺመቤት ወደ ባንካችን ስትመጣ ሁላችንም እየወጣን አቀፍናት።ልጆቿን በግራ እና በቀኝ ይዛለች ስታየን እንባዋን ለቀቀችው።አልቅሳ አስለቀሰችን።ጥቁር በጥቁር ለብሳለች።ውስጧ ተጎድቷል።ወደ በረራው እየተጣደፈች ቼክ የሰጠችኝ ቀን የነበረችውን የሺመቤት ያየ ያን ቀን አያውቃትም።የደረሰባት ብርቱ ሃዘን ነበር።እርሷ በእግዚአብሔር ቸርነት ተረፈች።የሞቱት ሁኔታ ግን ልብ ይሰብራል።የሺመቤት ባንካችን በመጣች ቀን ከመሄዷ በፊት ትሑት ባህሩ ውስጥ ስትገባ ምን አለች? እንዴት እንዴት ነበር የሆነችው? ብዬ መጠየቅ አማረኝ።ጊዜውም፣ አግባብም አደለም።የሺመቤትን ሸኝተን ወደ ወንበሬ ተመለስኩ።የስራ ሰዓት መውጫዬ ሲደርስ እቤቴ ሄጄ ተኛሁ።ምሳም እራትም አላስፈለገኝም።ውስጥ ሲያዝን ምግብ ትዝ አይልም።ትሑት የበረራ አስተናገጅነቱን ሥራ ከጀመረች በኃላ ብዙም አልወደደችውም ነበር።ትምህርቷን መቀጠል እንዳለባት አምና ነበር። በበረራ በምትሳተፍባቸው ጊዜዎች ሁሉ ደግሞ ከበረራ በፊት ተንበርክካ ፀሎት ማድረግ ልማዷ ነበር።በሥራ ባልደረቦቿ ዘንድም''ያች ፀሎት የምታደርገው ልጅ'' በሚል ነበር የምትታወቀው።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ እና በተለይ ለትሑት ቤተሰቦች መፅናናቱን እመኛለሁ።እኛ ወደእነርሱ  እንሄዳለን እንጂ ያረፉት ወደ እኛ አይመጡም።በረራ 961 መሪር ትዝታ ይዞ አለፈ።እሱ አለፈ።ዛሬም ድረስ ጥቁር ትዝታው ግን አይጠፋም።



ጉዳያችን GUDAYACHN

ህዳር 13/2008 ዓም (November 23/2015)

Friday, November 20, 2015

የዘር ማፅዳት ወንጀል በኢትዮጵያ (Ethnic cleansing crime in Ethiopia) ከአለምአቀፍ እና አህጉራዊ ሕግ አንፃር

photo -foreign policy 
በቤንሻንጉል ጉምዝ  መተከል ዞን፣መስከረም ወር ላይ ከአስራ አምስት በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች ተገድለው አስከሬናቸው በጆንያ ታስሮ ተገኘ።ሚያዝያ ወር ላይም በጥይት ሰማንያ የአማራ ተውላጆች ካለ አንዳች ምክንያት ተረሽነዋልበቤንሻንጉል ነዋሪ የሆኑ የአማራ ተወላጆች ለኢሳት ህዳር 9/2008 ዓም በምሬት የተናገሩት። ድርጊቱ  በአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ ለደረሰው የዘር ማጥፋት እና የማፈናቀል ተግባር የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሕይወት እስካሉ ድረስ በዓለም አቀፍም ሆነ አህጉራዊ ሕግያስጠይቃቸዋል።ጉዳያችን ''ኢትዮጵያ ''የዘር ማፅዳት'' ወንጀል (Ethnic cleansing crime in Ethiopia) ከአለምአቀፍ እና አህጉራዊ ሕግ አንፃር'' በሚል ከእዚህ ቀደም 2006 ዓም ያቀረበችው ፅሁፍ እነሆ-
በዘር ወይንም በቋንቋ ሳቢያ የተለየ ህዝብን ለማጥቃት የሚደረጉ ድርጊቶች የተወገዙ ናቸው።በአለም ላይ በአምባገነኖች የግፍ ድርጊት፣በዘር ወይንም በቋንቋ ሳቢያ የተለየ ህዝብን ለማጥቃት የሚደረጉ ድርጊቶች የተወገዙ ናቸው።በእዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ ደግሞ ተግባራቸውን በረቀቀ መንገድ ሲከውኑት ማየት የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል።

በሀገራችንበአፋር፣በሱማሌ፣በኦሮሞ፣በሲዳማ፣በጋምቤላ ሰሞኑን ደግሞ በአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ ተመሳሳይ በአይነቱ ግን የተለየ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ጀርመኖች በአይሁዶች ላይ ይፈፅሙት የነበረው  አይነትግፍ እየተፈፀመ ነው።አምና በጉርዳፈርዳ፣በጅጅጋ፣በመቱ ሲፈፀም የነበረው የአማርኛ ተናጋሪኢትዮጵያውያንን የመግፋት እና የማባረር ተግባር ዘንድሮ በቤንሻንጉል በሺህ የሚቆጠሩትን ቀያቸውን አስለቅቆ የመንገድ ዳር ተመፅዋች አድርገዋቸዋል።ድርጊቱ በግብርና ሥራ የተሰማሩትን ብቻ ሳይሆን ከወፍጮቤት ባለቤትእስከ የትልልቅ ሆቴሎች ባለቤቶች ድረስ ንብረታቸውን ትተው ካለ አንዳች ካሳ እና ውክልና የመስጠት መብት ተባረዋል። ይህ ተግባር በዓለም አቀፍ ሕግ ''የዘር ማፅዳት ወንጀል'' (ethnic cleansing) ተብሎ ይጠራል።

''የዘር ማፅዳት ወንጀል'' (ethnic cleansing) ምንድነው? 

ታህሳስ 81989 ዓም እኤአ  በተባበሩት መንግሥታት 1948 ዓም እኤአ የፀደቀውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ ወንጀለኞችን ለመቅጣት የፀደቀውን አለም አቀፍ ሕግ 50 አመት ሲከበር በወቅቱ የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ የነበሩት ኮፊ አናን የወጣው ዘገባ ''የዘር ማፅዳት ወንጀልን'' ትርጉም እንዲህ ያስቀምጠዋል ''Ethnic cleansing has been defined as ''the elimination of an unwanted group from society,as by genocide or forced migration.'' Genocide and ethnic cleansing by Karin Becker (http://www.munfw.org/archive/50th/4th1.htm).
''የዘር ማፅዳት ትርጉም ''አንድ ያልተፈለገ ቡድንን(ህዝብን) ከሚኖርበት ማህበረሰብ ለይቶ በጅምላ መፍጀት አልያም በግድ ከመኖርያው የማፈናቀል እና ስደተኛ የማድረግ ተግባር ነው።''

የአለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች በተለይ በገዛ ሀገራቸው ተገፍተው ስደተኛ ለሆኑት (Internally displaced persons) ዜጎች አለምአቀፍ ጉዳይ ከሆነ እና ተግባሩን የሚፈፅሙት ላይ በሕግ የመጠየቅ ሂደት የሀገሮችሮች ሁሉ ኃላፊነት መሆኑን አለም ተስማምቷበታል።በ ታህሳስ 6፣2012 ዓም እኤአ ''የ ካምፓላ ኮንቬንሽን'' በመባል የሚታወቀው በገዛ ሀገራቸው ስደተኛ የሆኑ አፍሪካውያንን ላይ ትኩረት ያደረገው ጉባኤ መንግሥታት በገዛ ሀገራቸው ለተሰደዱ ዜጎች የመደገፍ፣የመንከባከብ እና ሙሉ የከለላ እና ልዩ ጥባቆት እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ሕግ ከመውታጡም በላይ የአፍሪካ ህብረት በ ኮንቬንሽኑ መሰረት ከ 37 በላይ የሚሆኑ ሃገራት እንዲፈርሙ ሆኗል። የስደቱ መንስኤ እራሳቸው መንግሥታቱ ለሆኑባቸው ሀገሮች ግን አለም አቀፍ ሕግ የሚዳኘው ''በዘር ማፅዳት'' ወንጀል ነው።'የካምፓላው ኮንቬንሽን' ለአፍሪካ አህጉር በተለይ በጎሳ እና በዘር ላይ የተመሰረቱ መንግስታትን አደብ የሚያስገዛ የሕግ መነሻ ወደፊት እንደሚሆን ይጠበቃል።ኮንቬንሽኑ ከያዛቸው ነጥቦች ውስጥ-

The Kampala Convention in Brief :- 
- Reaffirms that national authorities have the primary responsibility to provide assistance to internaly displaced people (IDPs)
- Comprehensively addresses
different causes of internal displacement: conflict, generalised violence,
human-caused or natural disasters, and development projects, like building dams or clearing land for large-scale agriculture.
- Recognises the critical role that
civil society organisations, and the communities which take them in, play in
assisting IDPs and obliges governments to assess the needs and vulnerabilities
of the forcibly displaced, and the host communities, in order to address the
plight of people uprooted within their borders,
- It Was adopted by the African Union and currently legally binds 15 African countries to prevent displacement, assist those who have been forced to leave their homes, and find safe and sustainable solutions to help people to rebuild their lives
- A total of 37 African countries have demonstrated their commitment to the convention by
signing it.’’ 
(http://www.internal-displacement.org/kampala-convention).

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ አለምአቀፍ የሕግ መርህ በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሕዝብ አንፃር የሚያስቀምጠው መመርያ(UN Under Secretary-General for Humanitarian Affairs Guiding principles of Internal displacement) አንቀፅ 5 ላይ እንዲህ የሚል ይነበባል- ''All authorities and international actors shall respect and ensure respect for their obligations under international law, including human rights and ons that might lead to displacement of persons.'' humanitarian law, in all circumstances, so as to prevent and avoid conduit'' 
http://www.brookings.edu/~/media/Projects/idp/GPEnglish.pdf.

''በማንኛውም የስልጣን ተዋረድ ያለም ሆነ አልምአቀፍ አካል ሰዎችን  ከሚኖሩበት ቦታ የሚያፈናቅሉ ማናቸውንም ሁኔታዎችን የመከላከል ግዴታ እንዳለባቸው  በሰብአዊም ሆነ አለምአቀፍ ሕጎች መሰረት ይገደዳሉ።'' ይላል።
ኢትዮጵያ ከአውሮፓውያን አቆጣጠር 2000 ዓም ወዲህ የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ቁጥር በእጅጉ ካደገባቸው ሃገራት ትደመራለች።ለእዚህም ዋነኛው መንስኤ የመንግስት የ ጎሳ ፖለቲካን የተከተለ የፌድራል አስተዳደር ዘይቤ መነሻ ያደረገ ግጭት፣መንግስት ለምመሬቶችን ለውጭ ባለሀብት የመሸጥ አወዛጋቢ ፖሊሲ እና አንድ ሕብረተሰብ ላይ ያነጣጠሩ'' የዘር ማፅዳት'' ተግባራት ናቸው።
Trading Economics  የተሰኘ ድህረ-ገፅ ከ 2002 እስከ 2010 ብቻ በኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉትን ተፈናቃዮች ብዛት ከ ሩብ ሚልዮን በላይ መሆናቸውን ይገልፃል።

ባጠቃላይ በቅርቡ በአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ''የዘር ማፅዳት'' ዘመቻ ላለፉት ሃያ አመታት ሲከናወን የነበረ (ብልጭ ድርግም በሚል መልኩ ሲከሰት የነበረ) መሆኑን የምንረዳው ጉዳይ ነው።የምጣኔ ሀብት እድገት በሌለበት መንግስት አድሏዊ አሰራሮች ባሰፈነበት እንደኢትዮጵያ ላለች ሀገር የእዚህ አይነቱ ዜጎችን ለፍተው ጥረው ያገሩትን ንብረት በኃይል ቀምቶ በገዛ ሀገራቸው ስደተኛ ማድረግ አለም አቀፍ ሕግን የጣሰ እና በየደረጃው ያሉ ባለስልጣናት በሕግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩ ምንም አያጠራጥርም።አሁን የሚያስፈልገው መረጃዎችን በበቂ ሁኔታ ማጠናቀር እና መያዝ ነው።
በመጨረሻም የሰሞኑን ድርጊት የተቃወሙ ግለሰብ በተናገሩት ንግግር ፅሁፌን ልደምድም  ‘‘ኤርትራውያን ሲባረሩ ንብረታቸውን በውክልና የመስጠት መብት ያልተነፈጉባት ሀገር እንዴት ዜጎች የገዛ ንብረታቸውን የማውጣት እና የመያዝ መብታቸው ልትነፍግ ቻለች? ሰባራ እንስራም ለእነርሱ ንበረት ነው ያውም ከወፍጮቤት እስከ ትላልቅ ሆቴሎች የተነጠቁትን ትተን  ’’

በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳያ አገራት ግዴታ የገቡበት ''የካምፓላ ኮንቬንሽን'' ቪድዮ  
Kampala Convention




ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
www.gudayachn.com 

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...