ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, June 27, 2015

የመሀይማን ቁጥር በሚልዮን ጨምሮ ዕድገት እንዴት አለ ይባላል? ኢህአዴግ/ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ ወዲህ በኢትዮጵያ ማንበብ እና መፃፍ የማይችሉ ጎልማሶች (የመሃይማን) ብዛት ከሰባት ሚልዮን በላይ መጨመሩን የዩኔስኮ ሰነድ ያመላክታል (ትኩረት - ጉዳያችን )

ኢትዮጵያ በዘመናዊ መንግስት ስሪቷ የጎልማሶች ትምህርትን ለማስፋፋት በቀዳማዊ  ኃይለ ስላሴ ዘመን ''የፊደል ሰራዊት'' በሚል በደርግ ዘመን ደግሞ ''የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ'' በሚል ሁለት አበይት ጎልማሶችን የማስተማር ዘመቻ አድርጋለች።በተለይ በደርግ ዘመን መሃይምነትን በማጥፋት ዘመቻ ከአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትም በበለጠ መልክ በመስራቷ ''የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣የሳይንስ እና የባህል ድርጅት'' (UNESCO) ኢትዮጵያን ተሸላሚ እንድትሆን ማድረጉ ይታወቃል።በወቅቱ በርካቶች ለማንበብ እና ለመፃፍ ከመቻላቸውም በላይ በመደበኛ ትምህርት እራሳቸውን አሻሽለው ለከፍተኛ ትምህርት ደረጃም የበቁ ነበሩ።

የዩኔስኮ መረጃ እንድሚያሳየው ኢትዮጵያ ከዘመነ ደርግ ወዲህ በኢህአዲግ/ወያኔ የስልጣን ዘመን ይህ ነው የሚባል የጎልማሶች ትምህርት ዘመቻ ካለመደረጉም በላይ ሀገሪቱ ለዘርፉ የመደበችው በጀት እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ይታወቃል።የጎልማሶች ትምህርት አለመስፋፋት ማለት ባብዛኛው ሕዝብ በግብርና በሚተዳደርባት ሀገር ውስጥ ህዝቡ የተፃፈ ማስታወቂያ ማንበብ አለመቻሉን ብቻ ሳይሆን የጤና ማስታወቂያዎች፣መመሪያዎች እና የመንገድ ላይ ማስታወቂያዎችንም አያነብም ማለት ነው።

''ትምህርት የእድገት ሁሉ ቁልፍ ነው''።ስለ እድገት ስናወራ ቁልፉ የትምህርት መስፋፋት ብሎም የጎልማሶች ከመሃይምነት መላቀቅ ነው።የኢህአዲግ/ወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያ አድጋለች የትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ ወዘተ የሚለው እንግዲህ የእድገት ትልቁን ቁልፍ ጉዳይ ህዝብን ከመሃይምነት ማላቀቅ የሚለውን ታሳቢ ሳያደርግ መሆኑ የእድገት እቅዱ ምን ያህል ሳይንሳዊ መንገድን እንዳልተከተለ አመላካች ነው።

እንደ ዩኔስኮ መረጃ መሰረት  ኢትዮጵያ ባለፉት 21 ዓመታት ውስጥ የጎልማሶች መሃይማን ቁጥር ከሰባት ሚልዮን በላይ መጨመሩን ያመላክታል።ጉዳዩ የስርዓቱን መሰረታዊ ችግር ያመላክታል።በእዚህ አይነት የስታስቲክስ ስሌት የጎዳና ተዳዳሪ ቁጥር ከጥቂት ሺዎች አሁን በኢትዮጵያ ከተሞች የሚንከራተቱት የጎዳና ተዳዳሪዎች ቁጥር በመቶሺህ መቆጠሩ ወዘተ እያልን ብናሰለው በእውነት ኢትዮጵያ ያለችበትን ችግር እና በትራንስፎርሜሽኑ እቅድ መሰረት አደገች! ተመነደገች! ተብሎ የሚነገረን ከልማት መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ ጋር የተቃረነ መሆኑን ለመረዳት ይረዳን ነበር።

ለኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ለውጭው ዓለም የኢትዮጵያ እድገት ተብሎ ከስርዓቱ የሚነገረው በጥቂት ሰዎች እና ድርጅቶች እጅ የሚገኘውን ሀብት ለጠቅላላ ሕዝብ እያካፈሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገቢ ይህንን ያክል ደረሰ እየተባለ መሆኑ ፈፅሞ ከእውነታው ጋር አይገናኝም።ይህ ትክክል ስሌት አለመሆኑን ስርዓቱም ሆነ ጋሻ ጃግሬ የሆኑት የውጭ መንግሥታት ያውቁታል።ሆኖም ግን እያወቁ በሕዝቡ የመኖር ተስፋ ላይ ይቀልዳሉ።


በመጨረሻም ይህችን አነስተኛ ማስታወሻ ከመደምደሜ በፊት  ዩኔስኮ የሀገራት የጎልማሶች መሃይማን ቁጥር ያመላከተበት ሰንጠረዥ  ይመልከቱ።በመቀጠል በቀደመው መንግስት በከፍተኛ ስኬት የተከናወነው ''የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ'' ተሳታፊ የነበረው ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ ያዜመው ''ማንበብ እና መፃፍ የተሰኘው ዜማ በወቅቱ ከፍተኛ የሕዝብ አትኩሮት ስቦ ነበረ።



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።