ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, January 21, 2015

ፖሊሲ አውጪ ስህተቱን ማመን ካቃተው ፖሊሲውን ብቻ ሳይሆን ፖሊሲ አውጪው ከስልጣን መውረድ አለበት። የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም UNDP የ2014 አመታዊ ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ አሁንም ከዓለም 'ጭራ' ሃገራት ውስጥ ነች።የኢቢሲ ሁለት አኃዝ እድገት የት ነህ?



በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የ2014ዓም (እኤአ) 'የዓለም ሀገሮች ልማት ሪፖርት'  ይፋ መሆኑ ይታወቃል።እኛ ኢትዮጵያውያን በዓለም ላይ ካሉት ሃገራት ዘንድሮም እንዳለፉት አመታት ሁሉ እጅግ ወደኃላ ከቀሩት ሃገራት ተርታ ነን።ከ187 ሀገሮች ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ ጭራ ሀገሮች 173ኛ ስትሆን ለማነፃፀር እኛን የሚበልጡ ሀገሮችን እንመልከት- 
ሱዳን  በሰባት ደረጃ ቀድማን 166ኛ፣
ጋና በሰላሳ ሰባት ደረጃ ቀድማን 138ኛ፣
ኬንያ በሃያ ስድስት ደረጃ ቀድማ 147ኛ፣
ዑጋንዳ በዘጠኝ ደረጃ ቀድማ 164ኛ፣
ናሚብያ በአርባ ስድስት ደረጃ ቀድማን 127ኛ፣ይቀጥላል 

የኢህአዲግ/ወያኔ ሁለት ዲጅት ዕድገት የት ገባ??? ህዝቡ ኑሮው አልተሻሻለም፣የኑሮ ውድነት ተባባሰ፣ጥቂቶች በናጠጠ ሕይወት ብዙሃን በተጎሳቆለ ሕይወት ውስጥ ወደቁ ሲባል ዘንድሮም ስርዓቱ መናገርያ እንጂ መስሚያ ጆሮ የለውም።እድገትን ''በካልዲስ ኬክ ቤት'' እና በብድር በተዘረጋ የከተማ ባቡር እየለኩ ለዘመናት የምንጠቀምበትን የበሬ ማረሻ ሳንቀይር ''አድገናል!!'' እየተባለ ይፎከራል።

የተባበሩት መንግሥታት አመታዊ ሪፖርት ባይነግረንም የህዝቡ ኑሮ ይብሱን እየተጎሳቆለ መሆኑ ከተጎጂው ሕዝብ በላይ እማኝ አያስፈልግም።ሰሞኑን ደግሞ  ስርዓቱ ''ያለፈው ፖሊሲ ስህተት አለው'' የሚለውን ጩሀት ችላ ብሎ  ያለፈውን የፖሊስ ስህተት የሰሩቱ እነኝሁኑ ሰዎች ለሚመጣው አምስት ዓመታት ዕቅድ ሊያወጡ ነው የሚል ወሬ ''ሪፖርተር'' እያስነበበን ነው።በመጀመርያ ደረጃ ለምርጫ እየተዘጋጀሁ ነው ያለ መንግስት ለሚመጣው አምስት አመታት ብሎ እቅድ ሊይዝ አይችልም።ይህ በእራሱ ምርጫውን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው።ምክንያቱም መጪው ተመራጭ እቅድ ያወጣል እንጂ ለምርጫ የሚቀርብ መንግስት ዕቅድ ሲያወጣ እና ለመስርያቤቶች መመርያ እንዲሆን ሲያዘጋጅ አይሰማም።
ጥያቄው ግን የዓለም ጭራ ሆነን እስከመቼ እንኖራለን? ፖሊስ አውጪ ስህተት ማመን ካቃተው ፖሊሲውን ብቻ ሳይሆን አውጪው ከስልጣን ማውረድ ብቸኛው አምራጭ ነው። 

1/ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም UNDP የ2014 ዓም እ ኤአቆጣጠር የዓለም ሀገሮች የልማት ሪፖርት ለመመልከት ይህንን ይጫኑ

2/ አሁንም ለመጪዎቹ አምስት ዓመታት ሌላ ፖሊሲ ሊቀረፅ  መሆኑ የተሰማው በእዚህ ሳምንት ነው።ዜናውን ይህንን በመጫን ያንብቡት።

ጉዳያችን
ጥር 13/2007 ዓም (ጃንዋሪ  21/2015 ዓም)



No comments: