ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, January 8, 2015

የዘንድሮው የ2007 ዓም የከተራ እና ጥምቀት በዓል በአራቱም የኖርዌይ ከተሞች የሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት በሕብረት እና በአንድቤተ ክርስቲያን ይባርካሉ።

የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በኦስሎ፣ኖርዌይ የሚከበርበት የማየሽትዋ ቤተ ክርስቲያን 

የዘንድሮው የ2007 ዓም የከተራ እና ጥምቀት  በዓል በአራቱም የኖርዌይ ከተሞች ማለትም በስታቫንገር፣ክርስቲያን ሳንድ፣ትሮንዳይም እና በርገን የሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት በሕብረት እና በአንድቤተ ክርስቲያን ማለትም በኖርዌይ ዋና ከተማ በኦስሎ፣ማየሽትዋ ሺርከን 84 (Majorstuen kirks, Kirkeveien 84)፣ያከብራሉ።በበዓሉ ላይ ከመላዋ ኖርዌይ እና ከኖርዌይ ውጭ የሚመጡ ምዕመናን ይታደማሉ።አቡነ ኤልያስ ህዝበ ክርስቲያኑን ይባርካሉ።

ቦታ - ማየሽትዋ ሺርከ፣ሺርከ ቫየን 84 (Majorstuen kirks, Kirkeveien 84)
ቀን - ጥር 16 እና 17/2007 ዓም (ጃንዋሪ 24 እና 25/2015)
ሰዓት - ጥር 16/2007 ዓም (ጃንዋሪ 24/2015) ከቀትር በኃላ 8 ሰዓት (2Pm) ማለትም  (14 ሰዓት ) ላይ ይጀመራል።





No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...