ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, July 22, 2014

ኢህአዲግ/ወያኔ በ1983 ዓ ም ስልጣን ሲይዝ የአንድ የኮሌጅ ምሩቅ ደሞዝ ከ250 ዶላር በላይ ነበር።ዛሬ በ2006 ዓም ግን የአንድ ተመራቂ ደሞዝ 72 ዶላር ነው። እድገት ወዴት ነሽ?




የኑሮ ውድነት መድረሻው አይታወቅም 

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት በብርሃን ፍጥነት እየተመነጠቀ ነው። እኛም ከሶስት እና አራት ዓመታት በፊት የነበረውን ዋጋ እየጠቀስን ለዛሬ ልጆች ''በእኛ ጊዜ እኮ በ 90 ሳንቲም ታክሲ እንጠቀም ነበር፣በእኛ ጊዜ እኮ አንድ ኪሎ ስጋ በ 22 ብር እንገዛ ነበር፣በ እኛ ጊዜ እኮ አንድ ብር ካለን በ 75 ሳንቲም እስክርቢቶ ገዝተን በ 25 ሳንቲም ጀላቲ ገዝተን ዘነጥ ብለን ጀላትያችንን እየመጠጥን ወደ ቤት እንመጣ ነበር።'' ልንል ነው።
የኑሮ ውድነቱን ከሕዝቡ ገቢ ጋር ለማነፃፀር ፈፅሞ የማይታሰብበት ደረጃ ተደርሷል።እውነት ነው ጥቂቶች በሙስና እና በሕገወጡ የሀገሪቱ አድሏዊ የምጣኔ ሀብት ድልድል ሳብያ የተቀናጣ ሕይወት እየመሩ ነው።የ አራት እና የአምስት ሚልዮን ብር የሚያወጣ መኪና በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ላይ እየነዱ ነው።ምንም ሳይሰሩ የባንክ ሂሳባቸው እያሻቀበ ነው።
በሙስና የነቀዙት ባለስልጣናት በድሃው ሕዝብ ኑሮ እየተሳለቁ ብቻ ሳይሆን ድህነቱ ባለመስራቱ እና ባለመቆጠቡ  የመጣ መሆኑን ነጋ ጠባ በራድዮ እና በቴሌቭዥን ሲነዘንዙት መመልከት ሌላው እራስ የሚያም የሀገራችን ገፅታ ነው።
ሙሰኞቹ ገዢዎቻችን በእዚህ ብቻ አልተመለሱም።ህዝቡ አናት ላይ መሳርያ ደግነው አድገሃል እያሉትም ነው።አላደግንም፣ኑሮ ከበደኝ ማለት በራሱ ወንጀል በሆነባት ሀገር ውስጥ ሕይወት ምን እንደሚመስል በውስጡ ያለ ብቻ ይረዳዋል።
ሰሞኑን የደሞዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ተነግሯል።ይህ የደሞዝ ጭማሪ የሚያመላክተው ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን ነው።አንደኛው የብር የመግዛት አቅም መቀነሱን በእዚሁም ሳብያ ገበያ ላይ ያለችውን ምርትም ሆነ ከውጭ የሚገባውን ለመግዛት አለመቻሉ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ላለፉት ዓመታት የደሞዝ ጭማሪ ያላየውን ሰራተኛ የኑሮ ውድነቱን የሚመጥን ጭማሪ የተደረገ በማስመሰል መጪውን ምርጫ አስታኮ የሚደረግ ጭማሪ ነው።
ለእዚህም አብነት የሚሆነን ባለፉት 23 የኢህአዲግ/ወያኔ አገዛዝ ዓመታት ውስጥ ምን ያህል የህዝቡ ኑሮ እንዳሽቆለቆለ ስንረዳ ነው።አሁን ባለው የኑሮ ጉስቁልና አንድ ሰራተኛ እንደ ሰው ለመኖር ያውም ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አይኖርም ብለን ብናስብ ከ1000% በላይ የሚደረግ የደሞዝ ጭማሪ በትንሹ መታሰብ አለበት።ከእዚህ ባነሰ ግን ምንም አይነት ለውጥ አያመጣም።

እድገት ወዴት ነሽ?

በ1983 ዓም  1 ዶላር = 2.07  ሲሆን የአንድ ምሩቅ ደሞዝ 500 ብር  ወደ ዶላር ሲቀየር 250 ዶላር ይሆናል።
በእዚህ ዘመን ኑሮ እርካሽ ነበር። ለምሳሌ፣ የአንድ ኪሎ ስጋ ዋጋ 5 ብር ነበር። አዲስ አበባ የሸዋ ዳቦ ቤት አንድ ዳቦ በ 10 ሳንቲም ይሸጣል። በ 1 ብር ከ 50ሳንቲም  ሽሮ ወጥ ከተሰነገ ቃርያ ጋር አዲስ አበባ ይሸጥ ነበር። አንድ ሊስትሮ ፓስታ በስጎ ከዳቦ ጋር በ 1 ብር መመገብ ይችላል።ለእዚህ ብዙዎች ምስክር ናቸው።በወቅቱ አንድ 200 ብር የሚያገኝ ጡረተኛ  በትንሹ የቤት ኪራይ ከፍሎ 5 የቤተሰብ አባላት ያስተዳድራል።ይህ ማለት ከወር ወር የጤፍ እንጀራ እየበሉ ማለት ነው።

ዛሬ አንድ ዶላር =19.75ሳንቲም ይመነዘራል።ዛሬ የአንድ ተመራቂ ደሞዝ ካልተጋነነ 1,400 ብር(መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች) ከእዚህ ላይ የመንግስት ግብር እና የጡረታ ይቀነሳል።ይህ  በዶላር 72  ይሆናል ማለት ነው። ይህ ማለት አንድ ምሩቅ የዛሬ 23 ዓመት ያገኝ የነበረው 250 ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን እያገኘ ያለው ግን 72 ዶላር ብቻ ነው።ይህ ማለት አንድ ምሩቅ ከዩንቨርስቲ እንደወጣ ማግኘት ያለበት 4,840 ብር ነበር ማለት ነው።ይህም የኑሮ ውድነቱን የሚያግዝ ሳይሆን በልቶ ለማደር ብቻ ነው።ዛሬ የሸቀጦች ዋጋ ስንት ነው? ጤፍ ኩንታል 1,600፣ስጋ 90 ብር፣ወዘተ

በእዚህ ስሌት መሰረት የደሞዝ ጭማሪው 200% ቢሆንም የኑሮ ለውጥ አያመጣም።በተለይ በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ የነዳጅ ጭማሪ መኖሩ ሲታሰብ ነገሩ ሁሉ ''የእንቧይ ካብ'' ያደርገዋል።
ጉዳያችን
ሐምሌ 7/2006 ዓም (ጁላይ 14/2014)

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...