Thursday, May 29, 2014

ሐገራችንን እንወቅ ''ቅዱስ ያሬድ የጉባኤያት አባት'' (ቪድዮ)

የቅዳስ ያሬድ  አባቱ አብድዩ /ይስሐቅ/ እናቱ ክርስቲና /ታውክልያ/ ይባላሉ፡፡የትውልድ ሥፍራው አከሱም ነው፡፡ የተወለደው በ505 ዓ.ም/  ሚያዝያ 5 ቀን  ሲሆን በተወለደ በ7 ዓመቱ ወላጅ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ጽዮን መምህር ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እያስተማረ እንዲያሳድገው ሰጠችው፡፡

ቅዱስ ያሬድ የኢትዮጵያውያን ሀብት ብቻ ሳይሆን መላው ዓለምን ከእግዚአብሔር በተሰጠው ፀጋ ያጣፈጠ ትልቅ ሊቅ ነው።ዓመታዊው በዓል በያዝነው ወር ግንቦት 11 ይውላል።የማኅበረ ቅዱሳን ሳምንታዊ ቴሌቭዥን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ስለ ቅዱስ ያሬድ የተናገሩትን እንዲህ አቅርቦታል።ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Wednesday, May 28, 2014

ኢህአዲግ ከ70 ዓመት በፊት በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን በተገነባ ስታዲዮም ውስጥ ሆኖ ግንቦት 20 እያከበረ ኢትዮጵያ አድጋለች ይላል።ለዘንድሮው በዓል ክብረ በዓል በመላ ሀገሪቱ ከግማሽ ቢልዮን (500 ሚልዮን) ብር በላይ ወጪ እንደሆነ እየተነገረ ነው።በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ለማወቅ ብዙ ምርምር የሚጠይቅ አይደለም።ህዝቡ የመሰረታዊ ፍጆታዎችን የመግዛት አቅሙ ተዳክሟል።ቀድሞ እናት ልጇን እንጀራ በሽሮ ብቻ ማብላቷ ያሳስባት ነበር።ዛሬ ይህ ዘመን በተለይ በከተሞች አካባቢ በቁጥርም ከፍተኛ በሆነው ሕዝብ ዘንድ ችግሩ ከፍቶ ዳቦ ገዝቶ ማብላት ከባድ ሸክም ሆኗል።አብዛኛው ሕዝብ ስለ ዳቦ ብቻ አይደለም ጭንቀቱ።የሚጠጣ ውሃም ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ የሚናፍቀው እና ለማግኘት የሚታትርበት አንዱ ተግባሩ ሆኗል የውሃ ነገር።ውሃ ፍለጋ ጀርካል ይዘው የሚንከራተቱ ሕፃናት እና እናቶችን ማየት የተለመደ ነው።በአዲስ አበባ ብቻ አደለም ሐረር፣ድሬዳዋ፣ሐዋሳ እና በርካታ ከተሞች የውሃ እጥረት ላይ ናቸው።

ይህ  ከሰው ልጅ መሰረታዊ ፍጆታ አንፃር ብቻ የምናየው ኢህአዲግ/ወያኔ 23 ዓመት ሙሉ ሊያስተካክለው ያልቻለውን ጉዳይ ጠቀስኩ እንጂ ባለፉት 23 ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ በፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት  ዘርፍ ሁሉ ወደ አደገኛ መንገድ እያመራች ነው።እርግጥ ነው ከስርዓቱ በመጠቀማቸው የሀገራቸውን ችግር እና የሌላውን እሪታ ላለመስማት የወሰኑ ወገኖች የሚሉት በተቃራኒው ነው።እውነታው ግን  ከእነርሱ አስተሳሰብ ብዙ የራቀ ነው።

ፖለቲካው 

- ፖለቲካው በጥቂት በጎሳ የሚያምኑ ኢትዮጵያዊነትን በሚያጥላሉ እና የጎሳ ግጭትን ለመለኮስ እስከ 20 ሚልዮን ብር አውጥተው የእጅ እና የጡት ሃውልት በሚሰሩ ጉድ አመራር ስር ነው፣
- ፖለቲካው ለኢህአዲግ/ወያኔ ማጎብደድ እና መልመጥመጥን ብቻ እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ እና በዙርያው ተስፋ ቢስ ግን ለገንዘብ እና ለጥቅም ባደገደጉ አድር ባዮች ተከቧል፣
- ፖለቲካው ዲሞክራሲ ላይ እየተሳለቁ እና እያፌዙ በሚናገሩ የተቀመጡበትን የህዝብ ትከሻ በዘነጉ ባለግዜዎች ተተራምሷል፣
- ፖለቲካው በአንድ ወቅት በጠበንጃ ስልጣን በያዙ ኃይሎች ስር ወድቆ ለዘላለም ገዢዎች እኛ ነን ብለው እራሳቸውን በሾሙ ሹመኞች ተይዟል።

ምጣኔ ሃብቱ - 

- ምጣኔ ሃብቱ  አቅጣጫውን የማያውቅ በፖለቲካው እና በጎሳቸው ስም በተሰበሰቡ ግለሰቦች ፍላጎት እንጂ በሀገር ራዕይ እና እድገት መሰረት አይመራም፣
- ምጣኔ ሃብቱ ከ70 በመቶ በላይ በስርዓቱ ስር በተደራጁ ኩባንያዎች የሚሽከረከር እና ሀብት ለማጋበስ ባሰፈሰፉ የውጭ ጥቅመኞቹ እየታገዘ በአስፈሪ እና አደገኛ ኃይሎች እየተሽከረከረ ነው።
- ምጣኔ ሃብቱ ሙስና የገንዘብ ብቸኛ ምንጫቸው የሁኑ ግለሰቦች ኢንቨስተር ተብለው የሚጠሩበት ነው፣
- ምጣኔ ሃብቱ ብሔራዊ ባንክ የተጭበረበረ ወርቅ ከመግዛት አንስቶ እስከ ግምሩክ ኃላፊ ድረስ በሀብት የሚ ምነሸነሹበት ተቋማት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ከምንገምተው በላይ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነች

ኢህአዲግ ኢትዮጵያን የዛሬ 23 ዓመት ከነበረችበት ከፍ አደረኩ እያለ ቢናገርም ዕውነታው ኢትዮጵያ ከምንገምተው በላይ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነች።ከምጣኔ ሃብቱ እና ከፖለቲካው የተገለለው ሕዝብ ምሬቱ ገፍቶ የሚወስደው ጫፍ ለማወቅ ይከብዳል።የእዚህ ዓይነቱ ምሬት የኃይል እርምጃም ስለማይቀርለት ከትናንቱ ይልቅ መጪው አስፈሪ እንዲሆን አድርጎታል።

የዘንድሮው ግንቦት 20 እንደባለፈው ሁሉ ካለፈው ይልቅ መጪውን አስፈሪ አድርጎታል።ሃያ ሶስት ዓመት ደቡብ ኮርያ እና ብራዚል የድሃ ህዝባቸውን ቁጥር ቀንሰው ሀብት በፍትሃዊነት እንዲከፋፈል ያደረጉበት እረጅም የተባለ ብዙ ታምር የሚሰራባቸው ዓመታት ናቸው።በኢትዮጵያ ደግሞ  23 ዓመታት ሀብት የተወሰኑ ቡድኖች ውስጥ የተሰበሰበበት፣ ከአስር ሺዎች ወደ መቶ ሺህ ሕፃናት የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑባቸው ዓመታት ናቸው።ህንፃ እና መንገድ መስራት ሕዝብ ማስተዳደር አደለም።የአረና አባል አቶ አሰግደ እንዳሉት ''መንገድ መስራት አስደናቂ ነገር አደለም።ጣልያን በአምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቆይታው ከስድስት ሺ ኪ ሜትር በላይ መንገድ ሰርቷል።ይህንን ማድረጉ ፋሽሽታዊ ስራው ይቀጥል አያስብልም።

 የሆነው ሆኖ ኢህአዲግ ከ70 ዓመት በፊት በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን በተገነባ ስታዲዮም ውስጥ ሆኖ ግንቦት ሃያን እያከበረ ኢትዮጵያ አድጋለች ይላል።ከየቀበሌው እና ትምህርት ቤቶች በልፈፋ አዲስ አበባ ስታድዮም ውስጥ ለተሰበሰበው ሕዝብ አቶ ኃይለማርያም ሲናገሩ ''በምግብ እራሳችንን ችለናል'' ሲሉ ተደምጠዋል።''የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም'' እና ይችን ንግግር በመጪው የእህል መሰብሰብያ ወቅት ላይ እንደማይደግሙት እራሳቸውም ያውቁታል።እንዳፋቸው ቢሆንልን ጥሩ ነበር።እውነታውን እርሳቸው የቤተ መንግስት እንጀራ ከሚበሉት ይልቅ የሚያውቀው ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።

ለዘንድሮው በዓል ክብረ በዓል በመላ ሀገሪቱ ከግማሽ ቢልዮን (500 ሚልዮን) ብር በላይ ወጪ እንደሆነ እየተነገረ ነው።የግማሽ ቢልዮን ብር ብክነትን አስቡ እና በውሃ ጥም የሚንከራተቱ የከተማ እና የገጠር ነዋሪዎችን አስቡ።ስንቱ በእዚህ ገንዘብ ንፁህ ውሃ ባገኘበት ነበር። ስንት ገበሬ ከባህላዊ የበሬ አስተራረስ ወደተሻሻለ የትራክተር ማረሻ በተሻገረበት ነበር።ከሃያ ሶስት ዓመታት በኃላም በበሬ እያረስን ነው።ከ 23 ዓመታት በኃላም  ኢህአዲግ/ወያኔ ከ70 ዓመት በፊት በተሰራ ስታድዮም ውስጥ ሆኖ አደጋችሁ እያለ መፎከሩ  የጤና ይሆን?

ጉዳያችን
ግንቦት 20/2006 ዓም/ ሜይ 28/2014

  

Monday, May 26, 2014

ኦስሎ ትጣራለች (ማስታወቂያ)  • በሰሜን አሜሪካ፣ጀርመን፣እንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ሌሎች ሀገሮች በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ታይቷል፣
  • ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ጎብኝቶታል፣
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋኅዶ ቤ/ክርስቲያን የቅዱሳን ገዳማት ያሳለፉት ታሪክ፣ምንነት፣አሁን ያሉበት ሁኔታ እና በመጪው ዘመን እንዴት መያዝ እና ማልማት እንደሚገባ አቅጣጫ ያሳያል፣
  • የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በኢትዮጵያ የነበረበትን ሂደት እና ስራው የተጀመረ ግን ደግሞ አዲስ እና ልዩ በስብከተ ወንጌል ላይ የተቀረፀ ፕሮጀክት ያስተዋውቃል፣
  • በዓይነቱ ልዩ አውደ ጥናት ይቀርብበታል፣
  • የምዕመናንን እና የሰው ልጅ ቅርስ አክባሪዎች ሁሉ ድርሻቸው ምን እንደሆነ ያሳያል፣
  • እነኝህን እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን የሚያገኙት በአንድ ስፍራ ነው።ማኅበረ ቅዱሳን በኦስሎ ባዘጋጀው ዓውደ ርዕይ እና አውደ ጥናት ውስጥ።


ቀን - ከሰኔ 6 እስከ 8/2006 ዓም (ጁን 13-15/2014)

ቦታ - ማየሽትዋ ሺርክ፣ሺርከን ቫየን 84፣ኦስሎ   

         (Majorstuen   Kirke,Kirkefeien 84,Oslo)


ማሳሰብያ - በመርሐ ግብሩ ላይ ለመገኘት ሃይማኖት፣ሀገር፣እና ሌላ ምንም አይነት ገደቦች አይጣሉበትም።ማንም ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ መገኘት ይችላል።ለምሳሌ ኖርዌጅያንም ከታዳሚዎቹ ውስጥ ናቸው።

Friday, May 23, 2014

በሕግ አምላክ! የኢትዮጵያን ታሪክ የቆነፀላችሁበት እና ያደበዘዛቹበት አቀራረብ ይስተካከል።የመንግስት የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ድረ-ገፅን ይመለከታል።
'ስለ ኢትዮጵያ' በሚለው ስር ''ታሪክ''  አምድ ላይ 'የመንግስት የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች' ድረ-ገፅን ኢትዮጵያን ያቀለለ ወረድ ሲል ደግሞ ያጣመመ የታሪክ አቀራረብ ይታይበታል።
ለመጨረሻ ጊዜ ድረ ገፁ የታረመው በ 2011 ዓም እ አ አቆጣጠር ነው ይላል ከድረ-ገፁ ላይ የሚነበበው የቀን ፅሁፍ።ያኔ አቶ በረከት አርመው አሳልፈውት ከሆነ ዛሬ በታሪክ ባለሙያዎች እንደገና መታየት አለበት።ድረ-ገፁ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቅበት አገላለፅ 'ውስጠ ወይራ' ነች።

ይህ ገፅ ማለት ለውጭ ሃገራት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርጉት ማናቸውም ግንኙነት በተለይ በሚድያ ዘርፍ ላሉት እንደ ዋና በር የሚታይ ነው።ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ጋዜጠኞች መሙላት የሚገባቸው ፎርም ሁሉ የሚገኘው በእዚሁ ገፅ ላይ ነው።ስለ ሀገራችን በውጭ ሃገራት የትምህርት ተቋማት ሁሉ ''ኦፊሻል''  የመንግስት ድረ-ገፅ ስለሆነ የተፃፈው ሁሉ ለማጣቀሻነት ሊቀርብ ይችላል ማለት ነው።ለእዚህ ነው ድረ-ገፁ የሚለው ነገር ሁሉ አነሰም በዛ አዲስ ለሚወለዱትም ሆነ ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጠው ፋይዳ የበዛብኝ እና ኢትዮጵያዊ አቀራረቡ የኮሰሰብኝ።

እነኝህን አንብቡ እና ቁንፅልነቱን እና የትኩረት አቅጣጫውን ታዘቡ።የመጀመርያዎቹ መንግሥታት በሚለው ስር እንዲህ ይላል።

''የመጀመሪያዎቹ መንግስታት''
''በ፰፻ ዓመተ ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ ዓመተ ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር።''
በኢትዮጵያ እና ''በኤርትራ ተቋቋመ'' ሲል በወቅቱ ኤርትራ የምትባል ሀገር መች ነበረች? ብላችሁ ብትጠይቁ ልክ ብላችኃል። ታሪክ በወቅቱ በነበሩት የቦታ ሁኔታዎች ወይንም ደግሞ  ''አሁን ኤርትራ ተብላ በምትጠራው'' ብሎ መፃፍ አንድ ነገር ነው። ''በኢትዮጵያ እና በኤርትራ'' የሚለው አፃፃፍ ግን ፈፅሞ ስህተት ነው።

በሌላ በኩል ንግስት ሳባም ሆነች ሳባውያን እንዲሁም የሳባ ፅሁፍ መነሻው ኢትዮጵያ እንደሆነ ታሪክ ያስረዳናል።''የሳባ ታሪክ ከየመን ይነሳል'' የሚሉ የታሪክ መሰረት የሌላቸው ፅሁፎች የሚነዙት ከየመን ነው።መቀመጫዋም ኢትዮጵያ መሆኑ ተፅኖ የነበረው ከኢትዮጵያ ሳባ ነው እንጂ ከየመን አይደለም።

በስድስተኛው ክ/ዘመን የቅዱስ ያሬድ ታሪክን ቀጥሎም የመሐመድ ቤተሰቦች ወደ ኢትዮጵያ መምጣትን እና በ12ኛው ክ/ዘመን የነበረው የቅዱስ ላሊበላ ታሪክን በሙሉ ይዘል እና  15ኛው ክ/ዘመን ላይ እንዲህ ይላል -''

በ፲፭ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ኢትዮጵያ ከአክሱም ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ ጋር ግንኙነት ጀመረች'' ይላል።
ኢትዮጵያ ከአክሱም መንግስት መውደቅ በኃላ ከውጭ ሃገራት ጋር የነበራት ሌሎች ግንኙነቶች አልነበሩም?

ይቀጥላል -----

አፄ ቴዎድሮስ መውደቅ ምክንያቱን ሲናገር ''የሰሜን አሮሞዎችና ትግሬዎች አመፅና የግብፆች ተደጋጋሚ ድንበር መጣስ የአፄ ቴዎድሮስ ስልጣን እንዲዳከም አደረጉት።''
እዚህ ላይ ፀሐፊው ወይንም አራሚው  በአራዳ ልጆች አባባል ''እራሱን አስፎገረ'' ተመልከቱ ''በዘር የተቃኘች ማሲንቆ'' ስትመታ።ለአፄ ቴዎድሮስ መውደቅ ምክንያቱ የዘር ጉዳይ ነው? እርግጥ ነው እንግሊዞችን እየመሩ መቅደላ ድረስ በማምጣት በኃላ አፄ ዮሐንስ ተብለው የነገሱት (በቀድሞ ስማቸው ደጃች በዝብዝ ካሳ) ይሁኑ እንጂ አፄ ቴዎድሮስን ከዳር ሃገሩ ሕዝብ አጠገባቸው ያለው የመሃል ሀገር ሕዝብ ብዙ ችግር ፈጥሮአል።ለመሆኑ ''የሰሜን ኦሮሞ'' የሚባል በኢትዮጵያ ታሪክ አለ?

ዝቅ ስትሉ ኢትዮጵያ በእንግሊዝ እና በአርበኞች ጣልያንን እንዳሸነፈች ይናገር እና ግን ጣልያን ስታሳዝነው ፈፅሞ እዚህ ቦታ የመግባቱ ፋይዳ እስከማይገባችሁ ድረስ ጣልያኖች እንዴት ሽምቅ ይዋጉ ነበር ለማለት እንዲህ ያላል - ''ግን እስከ 1943 እ.ኤ.አ. ድረስ አንዳንድ ጣልያኖች በደፈጣ ያለ ስኬት ይዋጉ ነበር።'' ጉዳዩ ውግያ ነው ከድል በኃላ አንዳንድ ተባራሪ ጣልያን እንደሚኖር ይታወቃል። ታሪክ ላይ ግን መክተብ እና ሽምቅ ይዋጉ እንደነበር ለመፃፍ መዋተቱ የኢትዮጵያን ድል ማድረግ ላያደበዝዘው የመጨነቁ  ፋይዳው ምንድነው?

ይቀጥላል----

የሱማሌ ጦርነትን ''የኡጋዴን ጦርነት'' ይላል ድረ-ገፁ።በእዚህ ጦርነት ከ 300 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ሚሊሻ ከአባት ጡረተኛ ጋር ዘምተው የሀገራቸውን ድንበር ማስከበራቸውን አንዳች ነገር ሳይተነፍስ ሙሉ በሙሉ በውጭ ኃይል ኢትዮጵያ እንዳሸነፈች ሊነግረን ይሞክራል።ሌላውን ዋሹን ግን ይህንን ታሪክ የሚነግሩን አባቶች ዛሬም በሕይወት አሉ እና አትዋሹን፣ታሪኩን አታደብዝዙ።
አዎን የውጭ እርዳታ ነበር የኩባ ወታደሮችም ተራድተውናል ግን ''የኢትዮጵያ መንግስት'' የተባለ የቃል አቀባዩ ቢሮ የፃፈው የኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ በሙሉ የሀገሩ ሰማዕታትን ክዶ በውጭ ኃይል ነው ያሸነፍነው ብሎ መፃፍ ምን አይነት ሞራላዊ ሥራ ነው?
 ስለ ሱማሌ ወረራ ድረ-ገፁ የፃፈው ይህንን እና ይህንን ብቻ ነው።
''በ1977 እ.ኤ.አ. ሶማሊያ ኦጋዴንን በመውረሯ የኦጋዴን ጦርነት ተነሳ። በሶቪየት ሕብረት፣ ኩባ፣ ደቡብ የመን፣ ምስራቅ ጀርመንና ሰሜን ኮሪያ የመሳሪያ እርዳታ እንዲሁም ወደ 15 ሺህ በሚቆጠሩ የኩባ ወታደሮች ድጋፍ አማካኝነት ደርግ ኦጋዴንን እንደገና መቆጣጠር ቻለ።''
በመሰረቱ ጦርነቱ የደርግ ጦርነት አይደለም።የኢትዮጵያ ጦርነት ነው።15 ሺህ የኩባ ወታደርን ለመጥቀስ የተጋ ብእር ምነው በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሚሊሻዎችን እረሳብን?

ድረ - ገፁ የኢትዮጵያን ታሪክ ''የቅርብ ጊዜ'' በሚል ስር ማጉላት የፈለገው ዋናውን አላማውን የሚያመላክት ነው። ልብ በሉ የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ ይልና የሚናገረው ስለ ኤርትራ ነው። እንዳለ ላስነብባችሁ።

''በቅርብ ጊዜ''

''በ1993 እ.ኤ.አ. በተካሄደውና የተባበሩት መንግሥታት በታዘበው ሕዝበ ድምፅ፣ ከ99 ከመቶ በላይ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብና በውጭ ሀገር የነበሩ ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ መገንጠልን መርጠዋል። በሜይ 24፣ 1993 እ.ኤ.አ. ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አወጀች።
በሜይ 1998 እ.ኤ.አ. የድንበር ውዝግብ እስከ ጁን 2000 እ.ኤ.አ. ወደቀጠለው የኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት አምርቶአል። ይህ ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን ጎድቶአል''

 እዚህ ላይ የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ ተብሎ  የኤርትራ ከኢትዮጵያ መነጠል ከተፈፀመ ከ20 ዓመት በኃላ በ 2011 ዓም እ አ አቆጣጠር ለመጨረሻ ጊዜ የታረመው እና የኢትዮጵያን ታሪክ የፃፈው የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ድረ-ገፅ የሚነግረን ሌላ ነው።99% ከኢትዮጵያ መነጠላቸውን ለመተረክ ከመሮጥ ለምን የታሪኩን መነሻ አትነግሩንም?
በመንግስት ቢሮክራሲ ውስጥ ገብተው የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያጣምሙትን ማጋለጥ ይገባል።ታሪካችን በኢትዮጵያውያን ይፃፍ!

ጉዳያችን 
ግንቦት 15/2006 ዓም/ሜይ 23/2014 

ኤርትራ 23 የመከራ እና የፍዳ ዓመታት - አቶ ኢሳያስ በኤርትራውያን ''በነጠላ ጫማ የገባ ሌላ ደርግ'' የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል።በሺህ ለሚቆጠሩ በግፍ ለታሰሩ ማሳያ የሆነችው ከአስር ዓመት በላይ ካለፍርድ በኤርትራ እስር ቤት የምትማቅቀው አስቴር ዮሐንስ ማን ነች? (ቪድዮ)

ኤርትራ የዛሬ 23 ዓመት ከኢትዮጵያ መነጠሏ ቢነገርም አዲስ የመከራ እና የስቃይ ዘመን እንጂ ለሕዝቡ አንዳች ለውጥ አለማግኘቱ የአደባባይ ምስጢር ነው። ቀድሞውንም ቢሆን የመገንጠል እና የብሔር ጥያቄን የችግሮች ሁሉ መፍትሄ አድርጎ የሚወስደው የአቶ ኢሳይስ እና አቶ መለስ የተሳሳተ የፖለቲካ እይታ ዛሬም ድረስ ለብዙ ሺዎች ስደት፣እስር እና ጉስቁልና ምክንያት ሆኗል። ጥቂት የስርዓቱ አቀንቃኞች ግን ዛሬም አስመራ እና አዲስ አበባ ላይ የግንቦት ወር በዓል ለማክበር ሽር ጉድ እያሉ ነው።

ፀጥ ለጥ አድርገው ለመግዛት የሚያስቡት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ አብረዋቸው በረሃ የነበሩ ወዳጆቻቸውን እና  ሌሎች ሺዎችን በእስር ቤት አጉረው፣ በመቶ ሺዎችን ደግሞ በሊብያ፣በግብፅ፣በሱዳን እና በየመን ሀገር ጥለው እንዲሄዱ አድርገው፣ዛሬም የግንቦት 16 በዓል ሊያከብሩ አስመራ ላይ ሽር ጉድ እያሉ ነው።የኤርትራ እናቶች ግን አንድ ኩንታል ጤፍ 10 ሺህ ናቅፋ እየከፈሉ ልጆቻቸውን መመገብ አቅቷቸው ተቀምጠዋል።

በደርግ ዘመን ሻብያ አስመራን  በከበበት፣ህወሓት ትግራይን ከመላው ኢትዮጵያ ነጥሎ በያዘበት 1982 ዓም ምንም አይነት የመንገድ ትራንስፖርት ከመሃል ሀገር ወደ አስመራ ለመውሰድ የማይቻልበት ሁኔታ ነበር። የአስመራ ሕዝብ ግን ከመሰረታዊ የኑሮ ሸቀጥ ጀምሮ እስከ ጤፍ እና ልዩ ልዩ ጥራጥሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደሌሎች ሃገራት የሚያደርገውን ካርጎ በረራ እየሰረዘ  የአቅርቦት ዋጋው አስመራ ላይ  ከአዲስ አበባ ብዙም የተለየ እንዳይሆን ለማድረግ ትልቅ ወጪ የጠየቀ ሥራ ይሰራ እንደነበር በወቅቱ በአየር መንገዱ ሰራተኛ የተናገሩትን አስታውሳለሁ።ይህ ደግሞ የአንድ መንግስት ግዴታ ነው እና ደርግ አሁን አስመራ ካለው የኑሮ ውድነት በማይገናኝ መልኩ አቅርቦቱን በቀበሌ እንዲዳረስ ያደርግ ነበር። ዛሬ አቶ ኢሳያስ ይህንን ማድረግ አልቻሉም።የስሕተታቸው መሸፈኛ ማሰር፣መግደል እና ማሰደድ ሆኗል።
ዛሬ በኤርትራ መፃኢው ምን እንደሆነ የማያውቅ ግን በገዥው እንደ ህዝቡ አጠራር ''በነጠላ ጫማ የገባው ሌላው ደርግ'' አማካይነት ማንነቱን ያጣው ሕዝብ ዛሬም የሰሚ ያለህ እያለ ነው።ለእዚህ ሁሉ አብነት እናንሳ አስቴርን። በሺህ ለሚቆጠሩ በግፍ ለታሰሩ ማሳያ የሆነችው  ከአስር ዓመት በላይ ካለፍርድ በኤርትራ እስር ቤት የምትማቅቀው አስቴር ዮሐንስ ማን ነች? ቪድዮውን ይከታተሉ።ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Thursday, May 22, 2014

ይሻል መጣ ብዬ ምርኩዝ አስጨበጨ መንገድ ያሳየሁት፣ ለካ ሌላም አይደል 'ደርጉ'ን ኖሯል እና 'ኢህአዲግ' ነው ያልኩት።
ይሻል መጣ ብዬ ምርኩዝ አስጨበጨ መንገድ ያሳየሁት፣
ለካ ሌላም አይደል 'ደርጉን' ኖሯል እና 'ኢህአዲግ' ነው ያልኩት። የደርግ እና የኢህአዲግ መመሳሰል ታወሰኝ እና  የኢትዮጵያ ገበሬ ምን ብሎ ያስብ ይሆን? እያልኩ ሳስብ የመጣልኝ ግጥም ነው።

በ 1967 ዓም የንጉሱን ስርዓት ከስልጣን ሲወርዱ በትረ መንግስቱን የተረከበው ደርግ የኢትዮጵያ ሰራዊት አካል በመሆኑ እና በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አንድነት ላይ የማይደራደር ቢሆንም በአገዛዙ አምባገነንነት ኢህአዲግ ደርግን ተስተካክሎታል ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ረቀቅ ባሉ ተንኮሎች ''ደርግ የዋህ አልነበር እንዴ!'' የሚሉ ድምፆች እንዲበራከቱ እያደረገ ነው። በደምሳሳው ስንመለከተው አይመስልም።ወደ ዝርዝር ነገሮች ስንገባ ግን ኢህአዲግ በትክክል የደርግ አምባገነናዊ አገዛዝ ግልባጭነቱ ፍንትው ብሎ ይታየናል።
እስኪ እነኝህን ነጥቦች እንመልከት -

ደርግ ስልጣን ለሕዝብ እመልሳለሁ ብሎ ምሎ ተገዝቶ መልሶ መለዮውን እያወለቀ ስልጣኑን ያዘ።''ሕዝባዊ መንግስት አሁኑኑ'' ያሉትን ገደለ። ኢህአዲግም ስልጣንን ለሕዝብ እሰጣለሁ ብሎ ምርጫ አደረገ ተሸነፈ።''ድምፃችን ተሰረቀ'' ብለው አደባባይ የወጡትን አያሌዎችን በአደባባይ ገደለ።

ደርግ ልማቱ እየተፋጠነ ነው።''እየተዋጋን እናመርታለን'' ይል ነበር። ኢህአዲግም ''እድገታችን ሁለት አሃዝ ነው '' ፀረ ሰላም ኃይሎችን በአንድ በኩል እየተዋጋን ምርታማነትን እንጨምራለን'' ይላል።

ደርግ ሕዝቡን በዘር ሳይለይ አኢወማ (አብዮታዊት ኢትዮጵያ ወጣቶች ማኅበር)፣አኢሴማ (አብዮታዊት ኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበር) እና ኢገማ (ኢትዮጵያ ገበሬዎች ማኅበር) እያለ ያደራጅ ነበር።
ኢህአዲግ/ወያኔ ረቀቅ አደረገው። በቋንቋ እየሰነጠቀ አማራ፣ኦሮሞ፣ትግሬ፣ሱማሌ እያለ አደራጀው። የኢህአዲግ የከፋ የሚያደርገው  ማህበራትን ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶችን ነው በጎሳ የሚያደራጀው።

ደርግ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ ጤፍ አምራች ገበሬዎች ምርታቸውን በአህያ ጭነው አዲስ አበባ ወፍጮ ቤቶች ድረስ አምጥተው እንዲሸጡ ይፈቅድ ነበር (ጅንአድ ከገበሬው መግዛቱን ሳንዘነጋ)። ኢህአዲግ ገበሬዎቹ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ማገድ ብቻ አይደለም ከመሬታቸው ካለ በቂ ካሳ (ይሰመርበት ካለ በቂ ካሳ) ልቀቁ አለ።

ደርግ የብሔር በሄረሰቦች ኢንስቲትዩት መስርቶ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦችን ባህል፣ወግ፣ ቋንቋ በምሁራን እንዲጠኑ ያደርግ ነበር።ኢህአዲግ ብሔር ብሔረሰቦች በዓመት አንዴ ሞቅ ያለ ዘፈን እየከፈተ በቲቪ እንዲደንሱ በማድረግ እና አብዝቶ ስለነሱ በማውራት ደርግን አስንቆታል።

ደርግ የድሀውን ሕዝብ የኑሮ ችግር ለመደገፍ በእየቀበሌው ከክብሪት ጀምሮ እሰክ ኩንታል ጤፍ እና የተማሪዎች ደብተር ሳይቀር በቅናሽ ዋጋ እንዲዳረስ ያደርግ ነበር። ኢህአዲግ በዘመኑ የኑሮ ውድነቱ ጣርያ ደርሶም እራሱ ''ኑሮ ተወደደ'' ብሎ መናገር የሚያሳስር መሆኑን በተግባር አሳየ።(ባለፈው ሰሞን ኑሮ ከበደን ያሉ ሴቶች የደረሰባቸውን ማሰብ በቂ ነው)

ደርግ አንድ ሰው ከቦታ ወደ ቦታ ሲሄድ ስሙ እና ፎቶው ያለበት መታወቅያ እንዲይዝ ያስገድድ ነበር። ኢህአዲግ ግን ስምና ፎቶ ብቻ ሳይሆን 'ብሔር' የሚል ጨምሮ ሕዝቡን ለያየው።

ደርግ አዋጅ ሲያወጣ አዋጁን ለምሳሌ የሰዓት እላፊ፣የመሰብሰብ ነፃነት ወዘተ ሲያግድ በራድዮ እና በቲቪ እንዲነገር ለጋዜጠኞች ይሰጥ ነበር።ኢህአዲግ እራሳቸው አቶ መለስ ''ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጭ የሚደረግ ስብሰባ ተቃውሞ በሕግ ተከለክሏል'' ብለው ሲናገሩ አሰማን።(ግንቦት 7/1997 ዓም አቶ መለስ በምርጫ ሲሸነፉ ያወጁትን አዋጅ አስታውሱ)።

ደርግ የኢትዮጵያ ዳር ድንበርን ሳያስደፍር ሲጠብቅ ኖረ።ኢህአዲግ ከባህር በር እስከ ኢትዮ-ሱዳን ድንበር ድረስ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ ሰጠ።

ደርግ ሕዝብ ሁሉ ማንበብ እና መፃፍ መቻል አለበት ብሎ የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ጀመረ።ኢህአዲግ ሕዝብ ሁሉ እስከ ቤተሰብ ወርዶ አንድ ለ አምስት መጠርነፍ (እንደ እርሱ አጠራር መደራጀት) አለበት ብሎ አንዱ ሌላውን እንዲሰልል አደረገ።

ደርግ ባለስልጣናቱ ከስልጣን እስኪወርዱ ድረስ ብዙዎቹ ባለስልጣናት እና የጦር መሪዎች በመንግስት ቤት ውስጥ እንዲኖሩ አደረገ። ኢህአዲግ ባለስልጣናቱ ሁለት እና ሶስት ቪላ እና መኪና እንደ ግምሩክ ባለሥልጣኑ ያሉት ደግሞ አልጋቸው ስር  'የፎረክስ' ቢሮ እስኪመስል ድረስ በሺህ የሚቆጠሩ የውጭ ምንዛሪዎች የሚይዙ ሆኑ።

ደርግ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁትን በሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ሥራ ይቀጥር ነበር። ኢህአዲግ ዩንቨርስቲ የጨረሱ ተማሪዎችን ሲመርቅ ገና ከዩንቨርስቲ እያሉ የስነ ልቦና ዘመቻ ይከፍትባቸዋል።ከምረቃ በኃላ ኮብል ስቶን እንደሚሰሩ ያረዳቸዋል። (አቶ ጁነዲን የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሆነው ለአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተመራቂዎች የተናገሩትን እናስታውስ)።

ደርግ መብራት፣ውሃ እና ስልክ ከመቋረጡ በፊት በራድዮ እና በቲቪ ለምን፣መቼ እና ለምን ያህል ሰዓት እንደሚቋረጥ ይገልፅና ደንበኞቹን ከባድ ይቅርታ ይጠይቅ ነበር። ኢህአዲግ መብራት እና ውሃ ለሰዓታት አይደለም ለቀናት  ሲቆም ይቅርታ ሲያልፍም አይነካው። ለምሳሌ አዲስ አበባ አንድ ሚልዮን ህዝቧ ውሃ አለመኖሩ ብዙ አስጊ የሚባል አለመሆኑን የገለፁት የኢህአዲግ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው።''ውሃ የማያገኘው ሕዝብ 25% ብቻ ነው'' ነበር ያሉት አቶ ኃይለማርያም ለጋዜጠኞች ሲመልሱ።

ደርግ ሕዝብ በግዳጅ ሰልፍ እንዲወጣ ያደርግ ነበር። ኢህአዲግ ሕዝብ ከኖረበት ቦታ ተባሮ እንዲወጣ በባለስልጣናቱ ሲደረግ እንዳለየ ለመምሰል እንደ አቶ መለስ ስለምፈናቀሉት ወገኖች ሲጠየቁ  ደግሞ ነዋሬውን ''ድሮም ሞፈር ሰበር ነው'' ሲሉ ተናገሩ።(እዚህ ላይ ከጉርዳ ፈርዳ፣ሐረር ጋምቤላ እና ሌሎች ቦታዎች የተፈናቀሉትን አስቡ።)

እንዲህ እንዲህ እያልን ደርግ ተመልሶ በከፋ አገዛዙ መመለሱን እና በአንዳንዶቹማ ይብሱን ደርግ የተሻለባቸው ሁኔታዎች እንደነበሩ ብዙ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል።

ይሻል መጣ ብዬ ምርኩዝ አስጨበጨ መንገድ ያሳየሁት፣
ለካ ሌላም አይደል ደርጉን ኖሯል እና  'ኢህአዲግ' ነው ያልኩት።

ጉዳያችን
ግንቦት 11/2006 ዓም 

Friday, May 16, 2014

Free Zone 9 Bloggers And Journalists! የዞን 9 ጦማርያን፣ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ!

'''ታስሬ አልጠየቃችሁኝም'' የሚለው ቃል ትዝ ሲለኝ ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው (በተለይ በውጭ ሀገር ላሉቱ)  -
ሰው ሲታሰር ዝም ማለት።ቢያንስ መጠየቅ ባንችል በፌስ ቡካችን ላይ ሃዘናችንን በመግለፅ ለመለጠፍ መፍራት ሃይማኖተኛነታችንን አይፈታተንም?

''ታስሬ አልጠየቃችሁኝም'' የሚለው ቃል መጠየቅ ያልቻለ ሰው እርቀት ቢያግደው ቢያንስ መጮሁ እንደጠየቀ አይቆጠር ይሆን?

''እምነት ሆይ ወዴት ነሽ? ሃይማኖት ሆይ ወዴት ነሽ? በግፍ ለታሰሩት መጮህ እኮ ሃይማኖት ነው ጎበዝ!

አሁንም ''ታስሬ አልጠየቃችሁኝም'' ሲታወሰኝ የታሰሩትን ለመጠየቅ ያልፈሩቱ ሲታሰሩ መጠየቅ ያልቻለ ከተፈረደበት ለታሰሩት  አዘንኩ ብሎ ፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይ ለመለጠፍ የፈራ (ያውም በውጭ ሆኖ) ፍርድ የለበት ይሆን? ሰው ፈራጅ አለመሆኑ እንጂ ሲታሰብ ስራችን ከበድ ያለ ነው። ''እምነት ሆይ ወዴት ነሽ?ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Thursday, May 15, 2014

ዛሬ ግንቦት 8/2006 ዓም በኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም ላይ የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት 25ኛ ዓመቱ ነው።በኢትዮጵያ የቢቢሲ ዘጋቢ የነበረው አሌክስ ላስት ያልሰማናቸው ታሪኮች ይነግረናል።(ኦድዮ)

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት መንግስታቶቿ ያልተሳኩ የወታደራዊ መፈንቅል ሙከራዎች ተደርገዋል።ሶስተኛው የዘመኑ መንግስት ኢህአዲግም ከእዚህ ነፃ ይሆናል ማለት አይቻልም። አንዳንዶች የአሁኑ መንግስት የጦር ሰራዊት አወቃቀር የተለየ ነው ይላሉ።ለእዚህም የሚያቀርቡት ምክንያት አብዛኞቹ የጦሩ ከፍተኛ መኮንኖች በትጥቅ ትግል ላይ የሚተዋወቁ ብቻ ሳይሆኑ ከአንድ አካባቢ የመጡ መሆናቸውን እንደ ምክንያት ያቀርባሉ። ነገር ግን ቀድሞም ቢሆን በተለይ በ 1967 ዓም ንጉሱን ከስልጣን ያወረደው የጦር ኃይል ባብዛኛው በዝቅተኛ እና ባለመስመር መኮንኖች የተመራ መሆኑን ነው። ከእዚህ አንፃር ኢህአዲግም የተለመደ የተሳካ ወይንም ያልተሳካ ወታደራዊ መፈንቅል ሊታደል ይቻላል።ይህ በጊዜ የሚፈታ ነው።

ከእዚህ በታች በኮ/ል መንግስቱ ላይ የተሞከረው መፈንቅል ጉዳይ በወቅቱ በኢትዮጵያ የቢቢሲ ዘጋቢ አሌክስ ላስት ምስክርነትን ከእዚህ በታች ያለውን ኦድዮ ከፍተው ያዳምጡ-
አፈንዲ ስለ መፈንቅሉ በመጦመርያ ገፁ ላይ  ለመፈንቅሉ መክሸፍ ምክንያት የሚላቸው በወቅቱ የደህንነት ቢሮ ኃላፊን ኮ/ል ተስፋዬን ነው።እርግጥ ነው ሌሎች ፅሁፎች ላይ የእርሳቸው መጨረሻ ሰዓት ላይ መክዳትን በምክንያትነት ቢያስቀምጡም ሌሎች የሚሰጧቸው ምክንያቶችም አሉ።ዝርዝሩን ይህንን በመጫን ያንብቡ።ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Wednesday, May 14, 2014

ከታሪክ ማህደር ከ26 ዓመታት በፊት መስቀል አደባባይ የቀረበ ትይንት እና በወቅቱ ፅንፈኛ አስተሳሰብ የነበራቸው የጎረቤት እና ሌሎች ሃገራት ኢትዮጵያን ይፈሩበት የነበረበት ምክንያት (ቪድዮውን ይመልከቱ)

ይህ መረረም ጣፈጠም የታሪካችን አካል ነው።ወቅቱ ልጆች የምንባልበት ገና በወላጆቻችን ዕይታ ስር የነበርንበት ዘመን ቢሆንም ዛሬ ላይ ሆኖ የነበረውን ሁኔታ ማሰብ ጥሩ ነው።ግንቦት 8 የነበረው የመፈንቅለ መንግስት 25ኛ ዓመቱ ሊደፍን ሰዓታት ቀሩት።ኢትዮጵያ የሞቱላት፣ቤት ንብረታቸውን ትተው የተሰዉ ልጆቿን ማሰብ ይገባል።ሌላውን ለታሪክ እንተወው።


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG 

ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይን እና ጆሮ ለመሆኑ ማስረጃዎቹ እና የዋልድባ ገዳምን መደፈር በመቃወም ከአንድ ዓመት በፊት የተደረገ ሰልፍ(ቪድዮ)

ኢሳት ለኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መረጃዎችን በመስጠት በቀዳሚነት የሚገኝ ሚድያ ነው።
ኢሳት አቦይ ስብሃትን አነጋግሯል፣
ኢሳት የኦነግ መሪዎችን አነጋግሯል፣
ኢሳት የኢሕአፓ አመራሮችን አነጋግሯል፣
ኢሳት የአርበኞች ግንባር ቃል አቀባይን አነጋግሯል፣
ኢሳት አረና ትግራይ አመራሮችን አነጋግሯል፣
ኢሳት ኮ/ል መንግስቱን አነጋግሯል
ኢሳት በአረብ ሃገራት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን የመጀመርያ አደጋ ለሕዝብ ያደረሰ ብቸኛ ሚድያ ነው።
ኢሳት በጉርዳፈርዳ የተባረሩ ዜጎችን ችግር በመጀመርያ ደረጃ ለሕዝብ ያደረሰ ነው።
ኢሳት ቦረና ጉጂ ዞን የተሰደዱ ስደተኞችን ችግር ለሕዝብ ያደረሰ የመጀመርያ ሚድያ ነው።
ኢሳት የአቶ መለስን ሞት ከቀናት ቀድሞ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በመንገር በዓለም ላይ የመጀመርያው ሚድያ ነው።
ኢሳት የሙስሊሞችን ሰልፍ ዘግቧል።
ኢሳት የክርስቲያኖችን ሰልፍ አሳይቷል።
ኢሳት ሚድያ ነው።ሚድያ ወደድነውም አልወደድነውም።ጣመንም አልጣመንም ያለውን እውነታ እንዳለ ማቅረብ ግዴታው ነው።
ትናንት በወለጋ ጊምብ የሆነውን እየሆነ ያለውን ዕውነታ ነው ያቀረበው።አንድ ሚድያ እየሆነ ያለውን ነገር ማቅረብ ኃላፊነቱ ነው።መረጃውን አግኝቶ ለችግሩ መፍትሄ መሻት ደግሞ የህዝብ እና ኃላፊነቱን የወሰዱ ወገኖች ተግባር እና ኃላፊነት ነው።ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ኢትዮጵያን በተመለከተ ግልፅ የፖለቲካ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል (ከጉዳያችን ጡመራ)ማሳሰቢያ-ይህንን ፅሑፍ በየትኛውም ድረ-ገፅ ላይ ማውጣት ይቻላል።ግን ምንጩን 'ጉዳያችን ጡመራ' መሆኑን መግለፅ ጨዋነት ነው።

በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከተካተቱት ንዑስ አርዕስቶች ውስጥ -

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ እርምጃ ምን መምሰል ይገባዋል?
የኢትዮጵያ የቅርብ ወቅታዊ ተግዳሮት ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ህዝብን የሚንጥ እና ሚልዮኖችን ከጎናቸው የሚያሰልፍ የፖለቲካ ራዕይ ለሕዝቡ ማሳየት ለምን አልቻሉም?
እና ሌሎችም...

መግቢያ 

ኢትዮጵያን ውክፕድያ በድህረ ገፁ ላይ እንዲህ ይገልፃታል-

''ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ርዕሰ ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ ዓመት የሚያንስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ ነገሥታት እና ንግሥተ ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።'' ይላል

ወግ አጥባቂ የአረብ መንግሥታት እና ፍላጎታቸው

የዛሬ ሰላሳ ሰባት አመት በምዕራቡ አለም የተከፈተው የቀዝቃዛው ጦርነት እጅግ በተፋፋመበት፣ የኢትዮጵያ አብዮት ተጠምዞም ይሁን በጥቂት የወቅቱ 'ልሂቃን' ለደርግ በቀረበ ሃሳብ ወደ ሶሻሊዝም ስርዓት ሀገሪቱን ለማስገባት በሚውተረተርበት፣በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን ክፍል በወቅቱ ከሶቭየት ህብረት ባገኘው የመሳርያ ድጋፍ የተመካው የሱማልያ-ዚያድባሬ መንግስት የኢትዮጵያን መሬት በኃይል የወረረበት ወቅት ነበር።በእዚህ ጊዜ ነበር የ’ፋይናንሻል ታይምስ’ ጋዜጣ የአፍሪካ ቀንድን ፖለቲካ ከቀዝቃዛው ጦርነት በዘለለ እይታ የሚያመላክት አንድ ፅሁፍ ይዞ የወጣው። ፅሁፉ እንዲህ የሚል ነበር

’’በወግ አጥባቂ የአረብ መንግሥታት በሳውድ አረብያ ቀንደኛነት በግብፅ፣ሱዳን እና ሶርያን ጨምሮ በቀይባሕር እና በአካባቢው ሃገራት የአረብ ወይንም የእስልምና መንግሥታት እንዲመሰርቱ የሚደረጉ ጥረቶች አሉ።’’
’’the conservative Arab states, marshalled by Saudi Arabia and including Egypt, Sudan and Syria, want to create a band of Arab or Muslim states along the shores of the Red Sea and its approaches.'' (Financial Times May 2 1977)

የ ሶስት ሚልዮን ሕዝብ አናሳነት  በፖለቲካ ስሌት አንፃር 

ከሱማልያ ጎን ቆማ የቀዝቃዛውን ጦርነት ትዋጋ የነበረችው ሶቭየት ህብረት (የዛሬዋ ሩስያ) ከቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ መውረድ በኃላ ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ ለማዞር አፍታም አልቆየችም።ለእዚህ ውሳኔ ካበቃት ጉዳይ አንዱ የኢትዮጵያ ስልታዊ ጠቀሜታ ዘለቄታዊ ጥቅሟን የሚያረጋግጥባቸውን ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነበር።እነኚህም ኢትዮጵያ በአካባቢው ያላት በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ መካከል እንደ ድልድይ የምትጠቅም ብቸኛ መሬት መሆኗ እና በሕዝብ ብዛትም ሆነ በተፈጥሮ ሃብቷ ከአካባቢው ሃገራት የምታማልል መሆኗ ነበር።በሕዝብ ብዛት አንፃር ካላት ጠቀሜታ አንፃር ሶቭየት ህብረት ኢትዮጵያን እንደምትመርጥ የገለፀችበትን ሰነድ የሚያመላክተው አሁንም ከዛሬ ሰላሳ ሰባት አመት በፊት እ ኤ አቆጣጠር ግንቦት 14/1977 ዓም በሱማልያ የሶቭየት ህብረት አምባሳደር የተናገሩትን  'ዘ ኢኮኖሚስት' መፅሄት እንዲህ ፅፎት ነበር-
''መንግስቱ ኃይለማርያም ጥሩ ልጅ ነው።ሶሻሊዝም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሸነፈ 30 ሚልዮን ወዳጆች በተጨማሪም የአሰብ እና ምፅዋ ወደብ ይኖሩናል።እናንተ ሱማሌዎች እኮ 3ሚልዮን ብቻ ናችሁ'' ነበር ያሉት።
‘Mengistu Haile Mariam is a good boy. If socialism wins in Ethiopia we will have 30 million friends there plus the ports of Assab and Massawa. You Somalis are only 3 million.’ (The Economist, May 14 1977)

እዚህ ላይ የ 3 ሚልዮን ሕዝብ አናሳነት  በፖለቲካ ስሌት አንፃር ኢትዮጵያን ዛሬም ከአካባቢው ሀገሮች በበለጠ ባላት የህዝብ ብዛት እና የተፈጥሮ ሀብት በተለየ ተመራጭ ሀገር እንደሚያደርጋት አያጠራጥርም።እዚህ ላይ ይህንን ተመራችነቷን ለመጠበቅ እና እንደሀገር እንዳትቀጥል ከገዛ መንግስቷ የሚገዳደሯት ፈተናዎች የመኖራቸውን እውነታ ሳንዘነጋ ማለት ነው።

መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ 

ይህ ከሆነ ዛሬ ሰላሳ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል።በእነኝህ ሰላሳ ሰባት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆኑ አንድ ትውልድ አልፎ አዲስ ትውልድ ተተክቷል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ 30 ሚልዮን  በሶስት እጥፍ ወደ 90 ሚልዮን ተተኩሷል፣የባሕር በሯ ተዘግቷል፣ወጥ የነበረው የመንግስት ስሪት በጎሳ እና ቋንቋ ላይ በተመሰረተ አስተዳደር ተቀይሯል፣ከተሞች በመጠን ሰፍተዋል።በከተማ የሚኖረው ሕዝብ ከገጠሩ ጋር ሲነፃፀር ግን በእነኝህ ሁሉ ከ ሶስት አስር አመታት በኃላም ከ 90 በመቶ ወደ 85 (83) በመቶ ነው ዝቅ ያለው።የህዝቡ የኑሮ ደረጃ እ አ አቆጣጠር በ 1970 ዎቹ ነፃነታቸውን ከተቀዳጁት የአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች አንፃርም ገቢው ዝቅተኛ የሚባል እና ከእጅ ወደ አፍ ነው።ከላይ የተጠቀሱት 'ፋይናንሻል ታይምስ' እና 'ዘ ኢኮኖሚስት' ፅሁፎች ሲወጡ በአፍሪካ ቀንድ የነበረን አማላይነት በምድር ጦር፣በአየር ኃይል እና በባህር ኃይል የነበረን የበላይነት የተገለፀ ሲሆን ዛሬ በሕዝብ ብዛት እና ዙርያችንን ያሉት የትናንሽ ደካማ ሃገራት መኮልኮል አጉልቶ ካሳየን የበላይነት ባለፈ መድረስ የሚገባንን ደረጃ አለመድረሳችንን ለማረጋገጥ ብዙ ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልግም።

ባለፉት 37 አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ የገጠማት ተግዳሮቶችን በሁለት መልክ ማስቀመጥ ይቻላል።እነርሱም የውስጥ ቁርሾ በአምባገነንነት መታገዝ እና የውጭ ግፊቶች ናቸው።የውስጥ ቁርሾው በተቻለ መጠን የሚቀልባቸው መንገዶች እንዳይኖሩ እልህ የተጋባው የአምባገነንነት እርምጃዎች በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ ያክል ብዙዎች ሳያስቡት ቁርሾውን ለማባባስ ሰበብ እንዲሆኑ አደረጋቸው።ደርግ የእርስ በርስ ጦርነቶቹ በተቻለ መጠን ለማቅለል ከውስጥ የነበረበትን የህዝብ ድጋፍ ማጣት ስልጣንን ለሕዝብ በማስረከብ ሊያቀለው አልፈለገም።ይልቁንም ጦርነቶቹ የሰራዊቱን በሥራ መጠመድ ማምጣቱ የታያቸው ወገኖች እንደ መልካም እድልም ተመለከቱት።በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ ደግሞ የውስጥ ቁርሾው በደርግ ዘመን ከነበረው የህዝብን ስልጣን ለሕዝብ ማስረከብ ብቻ ሳይሆን ''መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ'' በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነት ላይ አደገኛ ጥላ አጠላ።የጎሳ ግጭቱ ከክልሎች የመሬት ግጭት አልፎ እስከ መንደር የከብቶች መሰማርያ ሜዳ ድረስ ኢትዮጵያውያን ተጋጩ።በእነኝህ የጎሳ ግጭቶች የተነሱ ፀቦችን ለማስቆም ዋናው ችግር ''የመንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ'' መሰረት ያደረገውን የፌድራል  ስርዓት በትክክለኛ የመሬት አቀማመጥ እና የህዝቦች ታሪካዊ አሰፋፈር መሰረት ያደረገ የፌድራል ስርዓት መቀየር መሆኑ እየታወቀ ኢህአዲግ/ወያኔ የተጋጩትን የጎሳ አባላት መዳኘትን እንደ ትልቅ ግብ እየቆጠረ በዜና እወጃው ላይ በስኬት ዜናነት ማውራቱን ቀጠለ።

የመንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ መዘዝ ለአፍሪካውያን እየተረፋቸው ነው

የመንግስታዊው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ከሀገር ውስጥ አልፎ ለጎረቤት ኬንያ የእራስ ምታት የሆነባቸው ብዙ ጊዜያት ነበሩ።ይህም ምን ያህል ኢህአዲግ/ወያኔ ''የፌድራ ስርዓቱ ለአፍሪካ ምሳሌ ሆነ''  እያለ የሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ ባዶ መሆኑን ያረጋግጣል። መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ ለቅርብ ኬንያ የየዕለት እራስ ምታት መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ዜና ነው።ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና ለእዚህ ጥሩ ማስረጃ ነው።ዜናው እንዲህ ይነበባል -

’በደቡብ ኢትዮጵያ የተፈጠረው የጎሳ ግጭት ድንበር ተሻግሮ ኬንያ ውስጥ የሚገኙ ጎሳዎችንም እያተራመሰ ነው ተባለ በደቡብ ኢትዮጵያ በቦረናና በገርባ ጎሳዎች መካከል ከግጦሽ መሬትና ከውሀ ጋር በተያያዘ በተነሳው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል።
ግጭቱ ወደ ኬንያም ተስፋፋቶ በአካባቢው የሚገኙ 17 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ታወቋል።
ከአካባቢው ርቀት አንጻር እስካሁን ድረስ የተጠናከረ መረጃ ባይቀርብም፣ በሞያሌ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደሚሉት በግጭቱ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፤ ብዙዎችም አካባቢውን እየለቀቁ ተሰደዋል።በኢትዮጵያ ሞያሌ ከተማ ደግሞ በሶማሊ እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል በቅርቡ የተፈጠረው ግጭት ፣ ዳግም ያገረሻል የሚል ፍርሀት መኖሩን የአካባቢው ነወራዎች ገልጠዋል።ሞያሌን የሶማሊ እና የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ከሁለት ከፍለው የሚያስተዳድሩዋት ሲሆን፣ በሁለቱ ብሄሮች ግጭት የከተማው ሰላም በተደጋጋሚ ሲደፈርስ ቆይቷል።
በቅርቡ ከትምህርት ቤት ንብረት ጋር በተያያዘ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች አሁንም አካባቢውን እንደተቆጣጠሩት ነው።’’ የዜናው መጨረሻ

በሌላ በኩል ከውጭ በኢትዮጵያ የውስጥ ፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ ገብተው ወደሚፈልጉት አቅጣጫ የመዘወር ግፊት የሚሰሩት ኃይላት ፍላጎት ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋብ ማለት በስተቀር ሌሎቹ ምክንያቶች ማለትም የአካባቢው እስልምና ተከታይ ሃገራት(ሳውዲ አረብያን ጨምሮ) በኢትዮጵያ ላይ የነበራቸው ግብም ሆነ ተግባራት ምንም ለውጥ አላመጡም።  ከእዚህ በተለየ የአለም ሃያላን መንግሥታት በሽብርተኝነት ጉዳይ፣በምጣኔ ሀብታቸው መዛባት እና ቻይና አዲስ አማራጭ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ በታዳጊ ሃገራት ላይ ያላቸው የበላይነት የመርገብ አዝማምያ አሳይቷል።ይህ መርገብ ግን ምናልባትም ከያዝነው አመት ጀምሮ ባለበት ላይቆይ ይችላል።የአራቱ የዓለም ኃይላት ማለትም የአሜሪካ፣የቻይና፣የአውሮፓ እና የሩስያ በግልፅ በወጣ የመገፋፋት ሂደት አለመኖር እና በተሸፈነ ዲፕሎማሲ ነገሮችን ማቀዝቀዛቸው ደካማ ሃገራት በጥቅማቸው ጉዳይ ላይ ከአንዱ ጋር የመቦደን ግዴታ  ውስጥ እንዳይገቡ እረድቷቸዋል።ይህ ሁኔታ ግን እሰከመቼ ድረስ እንደሚዘልቅ የምናየው ይሆናል።በተለይ ከባድ የምጣኔ ሀብት ቀውስ መምጣት እና እጅግ በተሳሰረው የአለም ምጣኔ ሃብት አንፃር ከአራቱ ሃያላን አንዱ ወይንም ሁለቱ አልያም ሶስቱ ተነጥለው የመሄድ አዝማምያ ከመጣ የአለም የኃይል ቁርሾ ወደ 1970ዎቹ የማይወርድበት ምክንያት አይኖርም።ምናልባት ‘ሲ ኤን ኤን’  ''ቀዝቃዛው ጦርነት'' የሚለውን የቀድሞ ፕሮግራሙን   ሰሞኑን እንደ አዲስ ልከልስልን የተነሳው በመጪው ላይ ያለው ስጋት አይሎበት ይሆን?

የኢትዮጵያ የቅርብ ወቅታዊ ተግዳሮት ምንድን ነው?

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ከ ሁለተኛው አለም ጦርነት አንስቶ  እስከ 1980ዎቹ እ አ አቆጣጠር ተጋግሎ የቆየው የቀዝቃዛው ጦርነት ኢትዮጵያ ወደራሷ የችግር ፈቺነት አቅም ሳያሸጋግር ''ለመንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ'' አስረክቧት ቀዘቀዘ።ቀድሞ በምዕራባውያን ትምህርት የተዋከበው የእድገት ስልት ቀጥሎ በመጣው በደርግ ሶሽያልስታዊ አስተሳሰብ ተተራምሶ ከዛሬ 22 አመት ገደማ ደግሞ በ''መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ'' ቅርፁም ሆነ ይዘቱ ትውልድ አሻጋሪ እንዳይሆን ሆነ።

ዛሬ የምዕራባውያን ''ሌክቸር'' መሰል አመራርም ሆነ የሶሻልስቱ አለም የማያላውስ ቀጭን ትዛዝ የኢትዮጵያ እራስ ምታቶች አይደሉም።የአካባቢ የአረብ መንግሥታት ግፊት ግን የቅርብ እና ከባድ የኢትዮጵያ ተግዳሮት ነው።ከኢህአዲግ/ወያኔ በፊት የነበሩት መንግሥታት በማዕከላዊነት ይዘውት የነበረውን የሀገር ጉዳይ በጎሳ ስለሸነሸነው ለአካባቢ ''ኢትዮጵያን አረብ ማድረግ አለብን'' እንቅስቃሴዎች እጅግ አመቺ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።ኢትዮጵያን አረባዊ የማድረጉ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በጥቁር ህዝቦች ላይም የተሞከረ እና የታቀደ ይልቁንም እስልምናን ከሃይማኖት ይልቅ ፖለቲካዊ ጥቅሙን ብቻ ነቅሶ የመንቀሳቀስ አላማ የያዘ ነው።


ኢትዮጵያን አረባዊ (እስላማዊ ሀገር ) በማድረግ ሂደት ላይ በጉልህ የተሳተፉ ውስጣዊ ኃይላት አሉ።እነርሱም-

 1/  የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስ እና ‘ፅፈኛ አጋር’ ተብዬ የጎሳ ድርጅቶቹ

  2/  ኢህአዲግ/ወያኔን እንቃወማለን የሚሉ ግን የመገንጠል አላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ለምሳሌ የ ዑጋዴን ነፃነት ግንበር የመሳሰሰሉ ናቸው።

እነኝህ ኃይላት የተለያዩ ይምሰሉ እንጂ ያጣላቸው የበላይ ለመሆን የሚደረግ ግፍያ ካልሆነ በቀር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።ለምሳሌ ትግራይን የመገንጠል አላማ ይዞ በፕሮግራሙም አካቶ ይንቀሳቀስ የነበረው ህወሓት ዛሬም መንግስት ከሆነ በኃላም የቀድሞ የጎሳ ስሙን ካለመቀየሩም በላይ ለስልጣን ያበቃቸው አጋር ድርጅቶቹ ባብዛኛው በአንድም ሆነ በሌላ ኢትዮጵያን አረባዊ (እስላማዊ) ለማድረግ ከሚሹ ኃይላት በተገኘ የስልጠና፣የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ የተመሰረቱ ናቸው።ይህ ድጋፍ ዛሬም ድረስ እያገኙ ነው።

እነኝህ ኃይላት አላማቸውን ለማስፈፀም የሚሞክሩት እና የሚተገብሩት በአፈሙዝ ነው።ይህ ማለት በሌላ አገላለፅ መጭውም  የፖለቲካ መድረክ የሚስተናገደው በአፈሙዝ ስልጣን ላይ የሚወጣ የሚደመጥበት ነው ማለት ነው።አሁንም ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር አልታደልንም ማለት ነው።በእዚህ ሁሉ ውጥንቅት ውስጥ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነበረው አካሂድ ምን መምሰል ይገባዋል?

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ እርምጃ ምን መምሰል ይገባዋል? 

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ያለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግርም ሆነ ወደ ነፃነት እና ዲሞክራሲ የሚደረገው ጉዞ በሁለት ጉዳዮች  የተወጠረ ነው።እነኝህ ሁለት ጉዳዮች ላይ የተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ግልፅ እና ጥርት ያለ መስመር ማሳየት አለባቸው።ይህ መስመር ዛሬ ያለውን ጥቂቱን ወይም ብዙውን ያስከፋል ወይንም ያስደስታል ከሚል አንፃር ሳይሆን መሰመር ያለበት መጪውን ዘመን ያገናዘበ ብሎም አዋጪ እና አማራጭ መስመር ከመሆን አንፃር ብቻ  መታየት ይገባዋል።እነኝህ ሁለት ጉዳዮች-

1/ ባለፈ ታሪክነት ማንነት ላይ የጠራ አቋም ማሳየት

2/  ከባለፈ ታሪክ፣ባህል፣ማንነት፣ከአሁኑ እና ከመጪው ትውልድ ማንነት አንፃር ወደፊት ሊኖር ስለሚገባው የመንግስት ቅርፅ በግልፅ ማሳወቅ


1/ ባለፈ ታሪክነት ማንነት ላይ የጠራ አቋም ማሳየት

የኢትዮጵያን  ያለፈ ታሪክ በአንድ ገላጭ አረፍተ ነገር ሊጠቃለል ወይንም ይህንን ከማለት ውጭ ይህንን ማለት አይቻልም የሚል አስተሳሰብ የሚራመድበት ወቅት ላይ አይደለንም።በሌላ በኩል ደግሞ በድፍኑ የጋራ የሚያደርገንን ታሪክን እንደምናምን ቆጥሮ በዝምታ እና በብዥታ መቀጠልም ህዝብን ከሚመራ የፖለቲካ ኃይል የሚጠበቅ አይደለም።ይህ ያለንበት ወቅት የአንድን የፖለቲካ ድርጅት ባለፈ ታሪክ ላይ ያለው አመለካከት በራሱ የፖለቲካ ፓርቲውን የወደፊት ራዕይ የሚያመላክት ያክል እንደማሳያ እየሆነ ለመምጣቱ ብዙ ማሳይዎችን መጥቀስ ይቻላል።

እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ዛሬ ያለው ትውልድ ስለአለፈው በጎም ሆነ በጎ ያልሆነ ታሪክ ቅንጣት ታክል ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።እርሱ የሚጠየቀው ዛሬ በሚሰራው እና ነገ ሊሰራ ስለሚያስበው ታሪክ ነው።በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ እና ታሪክን ተመርኩዘው ነገን በሚማትሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው ዘንድ ሁለት አይነት ስሜቶች ይንፀባረቃሉ።

አስተሳሰብ አንድ - የባለፈው ታሪክን በዛሬ መነፀር የሚመለከት

የመጀመርያው ክፍል ባለፉት ዘመናት የተደረጉትን ታሪካዊ ሁኔታዎች ዛሬ 21ኛው ክ/ዘመን ላይ ሆኖ ለመገምገም የምፈልገው ነው።የዛሬ 600 አመት አፄ ዘርያቆብ ለምን እንዲህ አላሰቡም? እንዴት እንዲህ ይላሉ? እያለ በወቅቱ የነበረውን ስነ-ልቦና የማኅበረሰቡን ባህል፣እምነት እና ወግ ሳያጠና እንዲሁ ለዛሬ የኢትዮጵያ እሷነት መነሻ ሰበብ ሲፈልግ ከድሮ ታሪክ ጋር እያዛመደ መማሰን ሙያ ተብሎ ተይዟል።ይህ ክፍል ትልቁ ግቡ ስልጣን ነው።ስልጣን ለመያዝ ደግሞ ዛሬም ሆነ ነገ እንቅፋት ይሆኑኛል የሚላቸው ሁለት ''ደንቃራዎች'' ከፊቱ ይታዩታል። እነርሱም- በረጅም ዘመናት የተገነባው ያለፈው እና አሁን በሕዝቡ ልብ ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊነት ነው።ይህ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ባለፈ ማንነት፣ታሪክ፣ባህል እና እምነት ላይ የተመሰረተ ነው።ስለዚህ ዛሬ ሰበብ አስባብ ፈልጎ ያለፈ ማንነትን የሚንዱ ናቸው ያላቸውን የህዝብ ግጭቶችን፣በነበሩበት ጊዜ ጀግና ያስብሉ የነበሩ በ 21ኛው ክ/ዘመን ግን ክፉ ተግባራትን እና ፈፅመው የሌሉ ታሪኮችን በመፍጠር የኢትዮጵያዊነት መሰረቶች እንዲናዱ ይሞክራል።

ለምሳሌ የብሔር ብሔረሰቦች ጉዳይ እና ፌድራሊዝም አስተዳደሮች  በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ባልተፈጠሩበት ዘመን ለምን አልታወጁም ነበር? በሚል ውኃ ቀጠነ ንግግር ኢትዮጵያዊነትን ይሳደባል።ይልቁን ፌድራልዝም በአለም ሳይታወቅ እነ አባ ጅፋር የራሳቸውን ግዛት በራሳቸው ያስተዳድሩ እንደነበር ግን በጋራ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር በሚያገናኛቸው ጉዳይ ላይ አብረው ይሰሩ እንደነበር አያስተውልም።በዚህ ክፍል ውስጥ የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስትን ጨምሮ በፅንፈኛ የእስልምና እምነት የፖለቲካ አላማቸውን ለማሳካት እስከሚፈልጉት ኃይሎች ድረስ የባለፈውን ታርክ በዛሬ መነፀር እያዩ ህዝብን ማደናገር እና የዛሬውን ትውልድ በማያውቀው ጉዳይ አበሳውን ሲያሳዩት መመልከት የተለመደ ነው።አሁን ባለንበት ዘመን በእዚህ አስተሳሰብ ሺዎች ተገለዋል፣ሌሎች አያሌ ሺዎች ከመኖርያቸው ተፈናቅለዋል።ከእዚህ ሲዘል ደግሞ ማስረጃ ለሌለው ተረት ሁሉ ሃውልት ይሰራ ባይ ነው። የእዚህ አስተሳሰብ አራማጆች ዋና ግባቸው ''እኛ ስልጣን ላይ ከሌለን እና የምንፈልገውን ካልፈፅምን ጭር አይልም ባዮች ናቸው።ለእዚህ እኩይ ተግባር የምተባበራቸው ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይል ጋር ለመተባበር ዝግጁ ናቸው።ኢትዮጵያዊነት፣አንድነት እና ህብረት ሲጠነክር ይደነግጣሉ።ምክንያት የእነርሱ አስተሳሰብ በጠንካራ ኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ፊት ሞገስ እንደሌለው እና እነርሱንም ወደ ስልጣን ኮርቻ ላይ እንደማያፈናጥጣቸው ይረዳሉና።

አስተሳሰብ  ሁለት - የባለፈው በጎውን ይዘን ክፉውን ወቅሰን ያሁኑን ትውልድ ተጠያቂ ሳናደርግ ለወደፊቱ እናስብ

ሁለተኛው አስተሳሰብ የብዙ ኢትዮጵያውያን አስተሳሰብ ነው።ኢትዮጵያ በአንድ ምሽት በቤተ-ሙከራ ውስጥ የተሰራች ሀገር አይደለችም።የብዙ ዘመናት የህዝቦቿ አብሮ የመኖር፣የመተሳሰብ፣የመሰደድ፣የጦርነት፣የሰላም ሁሉ ውጤት ነች።ባለፈው ታሪካችን ብዙ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች አሉ።ብዙ የዛሬ ማንነታችን ላይ አሻራ ያላቸው ማንም በቀላሉ እንዲነቅላቸው የማይፈቀዱለት የጋራ ታሪክ አለን።በአንፃሩ ደግሞ የሚያሳዝኑ ታሪኮች ባለቤትም ነን።ዛሬ የሚያስፈልገን ያለፈው አንድ የሚያደርጉንን አጉልተን ባለፈው ለተሰሩት ስህተቶች ምንም ተጠያቂ ባንሆን ወደፊት እንዳይሰሩ አርመን መኖር ብቸኛ አማራጫችን ነው።ከእዚህ በዘለለ ባለፈ አሳዛኝ ታሪክ ሊሽር የሚችለው በዛሬው ትልውድ በጎ የታሪክ ተግባር ነው ብለው ያምናሉ።

አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ የሚታዩት አስተሳሰቦች ከላይ ከተጠቀሱት ከሁለቱ አንዱ እንደሆኑ ይታወቃል።የኢትዮጵያ ሕዝብም የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያላቸውን ግልፅ አስተያየት እና ይህ እይታቸው የነገውን የሀገራችንን መፃኢ ዕድል ማሳያ እንደሆነ አመላካች ነው።ኢትዮጵያ ነገ እንዴት እንድትሆን እንደሚፈልጉ ሁሉ የባለፈው ዕይታቸውም በግልፅ መቀመጥ ያለበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።


 ከባለፈ ታሪክ፣ባህል፣ማንነት፣ከአሁኑ እና ከመጪው ትውልድ ማንነት አንፃር ወደፊት ሊኖር ስለሚገባው የመንግስት ቅርፅ በግልፅ ማሳወቅ


አሁን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ፣በሰላማዊ ትግልም ሆነ በትጥቅ ትግል ላይ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ የጋር ነጥብ እና አሰልቺ ቋንቋ አለ። ይሄውም ''ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግስት'' ይመሰረታል የሚል ነው።ደርግም ሆነ ኢህአዲግ/ወያኔ ''ዲሞክራሲያዊ'' ያሉትን መንግስት ኢትዮጵያ እንዳጣጠመች ነግረውናል።ነገም ይህንኑ ተረኛው ስደግምልን መስማት ምንኛ ዘግናኝ ታሪክ መሆኑን ለአፍታም ማሰብ ይከብዳል።የብዙ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ችግር እና ሚልዮኖችን በአጭር ጊዜ ማሰለፍ ያልቻሉት ነገ የሚመሰርቱት መንግስትን በደፈናው ''ዲሞክራሳዊ'' ከማለት ባለለፈ መልክ አሁን ያለውንም ሆነ መጪውን ትውልድ የሚያማልል የኢትዮጵያን ታሪካዊ ዳራ ያገናዘበ ብሎም ነገ ተመንጥቃ የምታድግበትን አዲስ ሃሳብ ማፍለቅ አልቻለም።ኢህአዲግ/ወያኔ በትጥቅ ትግል ላይ ሳለም ይህንን ማድረግ አልቻለም ነበር።ግን ያስቀመጠው አንድ ሕዝቡን ያማለለ ጉዳይ ነበር ይሄውም ደርግ ይገረሰሳል የሚል ራዕይ ነበር።

ራዕይ ያሸፍታል፣ራዕይ ካላገኙት በቀር እረፍት ይነሳል፣ ራዕይ አያስበላም፣አያስጠጣም፣ዛሬን በጨለማ ያሳያል ነገን ግን በብሩህ ብርሃን አንቆጥቁጦ ያሳያል።የፖለቲካ ራዕዩን በትክክል የገለፀ እና ያ ራዕይ ደግሞ የሕዝብ ስስ ብልትን የነካ ሲሆን ሚልዮኖችን ያነቃንቃል፣ይፈነቅላል፣ሺ መትረጌስ ቢደገን ተራምዶት ይሄዳል።በትክክል የተቀመረ የፖለቲካ ራዕይ እንዲሁ ነው።ከእዚህ በተለየ ''ዲሞክራሲያዊ'' መንግስት ይመጣል በሚል ንግግር የትም አይደረሰም።በ 1997 ምርጫ ቅንጅት የሰራው ተአምር ይህ ነው።የራሱ ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ሳይኖረው የህዝቡን ሥሥ ብልት የሚነካ ጉድለቱን የሚሞላ የፖለቲካ ፕሮግራም እና ራዕይ ብልጭ አደረገ በአንድ ቀን ሚያዝያ 30/1997 ዓም ሰልፍ ብቻ በአዲስ አበባ ከ አንድ ሚልዮን ሕዝብ በላይ ደግፎት ተሰለፈ።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ህዝብን የሚንጥ እና ሚልዮኖችን ከጎናቸው የሚያሰልፍ የፖለቲካ ራዕይ ለሕዝቡ ማሳየት ለምን አልቻሉም?


ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሁለት መሰረታዊ ችግሮች በፖለቲካ ፓርቲዎቹ ላይ ይስተዋላል። አንደኛው የአመሰራረታቸው ሂደት ችግር ሲሆን ሁለተኛው የሕዝቡን ባህል፣እምነት እና ታሪክ ያገናዘበ ፕሮግራም ለማስተዋወቅ ድፍረት ማጣት ናቸው።

ሀ/ የአመሰራረታቸው ሂደት ችግር 


የፖለቲካ ፓርቲዎቻችን በሰላማውም ሆነ በትጥቅ ትግል ላይ ያሉት መካከል ነገ ሊያመጡልን ይችላሉ በምንላቸው በጎ ነገሮች ላይ አንዳቸውን ካንዳቸው የምንለይበት ነጥብ ካጣን ቆይተናል።ብዙዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲመሰረቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና እና ብቸኛ ችግር የዲሞክራሲ እጦት ችግር ብቻ ነው በሚል ትምህርት ቤት በተማሩት የምዕራቡ ፍልስፍና መግባብያነት ብቻ ይመሰረታሉ ወደ ትግል ይገባሉ።ኢትዮጵያን የሚያህል ከሶስት ሺህ አመታት በላይ የመንግስት ስሪት ያላት ሀገር ግን   ችግሯ የዲሞክራሲ ብቻ ሊሆን አይችልም።የማንነት መከበር፣በራስ ላይ ተመስርቶ የመፍጠር ክህሎት ማሳየት፣የራሷ የሆኑ የፖለቲካ ፍልስፍና እና ምጣኔ ሃብታዊ ተምኔቶች ማሳየት እነኝህ ሁሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንገዱን በተጠና እና ሊደረስበት በሚችል ራዕይ ለሕዝቡ እንዲያሳዩ ተደርገው አልተመሰረቱም።ለእያንዳንዱ ወቅታውም ሆነ የቆየ የሀገራችን ችግር ''የዲሞክራሲ እጦት'' ነው ችግሩ እያሉ ህዝብን ማዘናጋት ለማንም አይበጅም።

ለ/  የሕዝቡን ባህል፣እምነት እና ታሪክ ያገናዘበ ፕሮግራም ለማስተዋወቅ ድፍረት ማጣት


ይህ ችግር ከመጀመርያው ከአመሰራረት እና ችግርን ከዲሞክራሲ ጋር  ብቻ በማያይዝ ላይ በተመሰረተ የፖለቲካ ፓርቲ አንፃር የሚከሰት ይልቁንም ፕሮግራሙ እራሱ ይህኛውን ቡድን እዳያስከፋ፣ያኛው እንዲደግፍ ወዘተ በሚል ፍርሃት የተሸበበ ማዕከላዊ መንገድ የያዘ ፕሮግራም ለመፈለግ የሚታታር አካህያድ ውጤት ነው።የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የህዝቡን ባህል፣እምነት እና ታሪክ ያገናዘብ የፖለቲካ ፕሮግራም ማንንም ከፋው ወይንም ደስ አለው ሳይሉ በእውነታው ላይ ተመስርተው እንዳይቀርፁ የሚፈሯቸው ያለፉት 40 አመታት የሀገራችን የፖለቲካ መድረክ ክስተትን ነው።ኢትዮጵያ በመንግሥትነት የኖረችው አሁንም ልድገመው ላለፉት 40 አመታት አይደለም ለ ሶስት ሺህ አመታት ከዛም በላይ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲ ፕሮግራሞች ሲቀረፁ ካለምንም ማጋነን መሰረት ያደረጉት ያለፉት 40 አመታት የአለማችንን እና የሀገራችንን የፖለቲካ የተደጋገመ እና አሰልቺ ቋንቋ ነው።የኢትዮጵያ ስነ-መንግስት ታሪክ ግን ሰፊ፣ትልቅ እና ለቀሪው አለም ብዙ ቁም ነገሮችን ያበረከተ ነው።ለሙሴ አስተዳደርን ያስተማረ ኢትዮጵያዊው ዮቶርን የሚያስበው የለም።መገናኛ በሌለበት ዘመን የኢትዮጵያ የስነ-መንግስት ጥበብ መዋቅሩ ምን እንደነበር ሊመለከት የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ የለም።አውሮፓ እና አሜሪካ የተፃፉ መፃህፍትን ግን ለመጥቀስ የምያክለን የለም። ለአለም ልዩ ልዩ መንግሥታት ሕጎች የኢትዮጵያ 'ፍትሃ ነገስት' በምን መልክ ለግብአትነት አውሮፓውያን እንድተጠቀሙበት  ሊመረምር የሚፈልግ የለም።ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚገባው መንግስት ሕዝብ ሊታገልለት እና ሊሞትለት የሚችለው ልዩ ጥበብ እኛው ጋር እንደተደበቀ ለሕዝቡ ገልፆ ካለፍርሃት ሊነገረው፣ሊመራው እና ለእድገት ሊያበቃው የሚችል ጥበብ እንደሚያስፈልገው የፖለቲካ ፓርቲዎች ካላሰቡ ዛሬ የአስተሳሰብ ለውጥ የማመንጫ ሰዓት ላይ ይመስሉኛል። ከእዚህ በኃላ ኢትዮጵያውያን የምሸከሙት የመከራ ጫንቃም ሆነ የአስተሳሰብ ድግግሞሽ ጆሮ ያላቸው አይመስለኝም።

ባጠቃላይ 


የኢትዮጵያ የመንግስት ስሪት ቅጥ ባጣ አምባገነኖች እጅ ከወደቀ አስርተ አመታት አስቆጠረ።ይብሱን ዛሬ ሀገራችን ሕልውናዋን በሚፈታተን ''መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ'' ውስጥ ተነክራ ህዝቧ ተስፋ በቆረጠ ስሜት ውስጥ ይገኛል።ታሪካዊ ጠላቶቿ የዛሬ 40 አመት የደገሱትን ድግስ ዛሬም አልቀየሩም።ኢትዮጵያን አረባዊ ለማድረግም ሆነ የፅንፈኛ እስልምና አላማ ያነገቡ ኃይሎችአንዴ  በኦሮሞ ሕዝብ ስም ሌላ ጊዜ ባለፈ ታሪክ ስም እያሉ የሚፈልጉትን ግብ ለማድረስ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠሩ ነው።የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስትም እንደ ማስፈራርያ ወጥ በብዙ መልኩ ድጋፉን ሲሰጣቸው እና ''ከእኔ ጋር ከልሆናችሁ አደገኛ ሁኔታ ይፈጠራል'' እያለ ሲያስፈራራን ዘመናት አልፏል።አቦይ ስብሐት ይህንን ጉዳይ ደጋግመው  ለተለያዩ የዜና አውታሮች ገልፀውታል።

የህወሓት ፈጣሪው አቦይ ስብሐት አንድ ወቅት ለኢሳት በሰጡት ዘገባ ላይ '' ማንም በኃይል ስልጣን ሊይዝ አይችልም።ከሆነ ሌላው ክልል የራሱ ምክርቤት፣በጀት ወዘተ አለው የራሱን አማራጭ ይወስዳል።ስልጣን የሚይዝ ኃይል አዲስ አበባን ብቻ ይዞ ይቀመጣል እንዴ?'' በማለት ከኢህአዲግ በኃላ ኢትዮጵያ እንደምትበታተን ሁሉም የእራሱን መንግስት እንደሚያውጅ በተዘዋዋሪ ነግረውናል።አቦይ 22 አመት ቆይተው ሕዝቡን አለማወቃቸው አይደንቅም።

ቁም ነገሩ ግን ይህ አይደለም የአቦይ ንግግር የሚያመለክተው ኢህአዲግ/ወያኔ ኢትዮጵያን እየስራት ያለው ከእርሱ ውጭ እንዳትኖር ''እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል'' መርህ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ነው።እዚህ ላይ ነው የተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች የህዝቡን ያለፈ ታሪክ፣እምነት፣ባህል እና ጥበብ ያገናዘበ አዲስ የፖለቲካ እና ምጣኔ ሃብታዊ  ራዕይ የሚያሳይ ፕሮግራም (''ዲሞክራሲ ዲሞክራሲ'' ከሚል መዝሙር ባለፈ) ማሳየት ያለባቸው።

በመሆኑም የተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች እና ፓርቲዎች አዲስ እና ባለ ራዕይ ፕሮግራማቸውን በተናጥል ወይንም ግንባር በመፍጠር አዲስ መንፈስ በመፍጠር ማሳየት ይገባቸዋል።ይህ አዲሱ ሀሳባቸው ኢትዮጵያን በጎሳ እና በፅንፈኛ የእስልምና አስተሳሰብ ለመምራት የሚፈልጉትን ለማቀፍ አይድከም።እነኝህን ኃይሎች በሚቃረን መልኩ የህዝቡን የልብ ትርታ ባዳመጠ እና የማይረገጥ የመሰላቸውን በመርገጥ ለድል ይበቃሉ።ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ በአንድነት ኃይሎች እና በበታኝ ኃይሎች ጎራ ተከፍሏል።ከአንድነት ኃይሎች ጎራ የዲሞክራሲ ጉዳይ ብቻ ሲለፈፍ ከበታኝ ኃይሎች በኩል ደግሞ የጎሰኝነት እና የፅንፈኛ እስልምና አስተሳሰቦች ይንፀባረቃሉ።አሁን ጥያቄው የአንድነት ኃይሎች ኢትዮጵያዊ ታሪክ፣እምነት እና ፍልስፍና የያዘ ጥበብ የተላበሰ ራዕይ ይዘው መውጣት እና ሕዝቡን ከአዙሪት 'ዲሞክራሲ' ከሚል ዲስኩር ማላቀቅ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ዛሬ ዲሞክራሲ አያስፈልገውም እያልኩ አይደለም።የህልውናው ጥያቄ ሲመጣ ግን ኢትዮጵያን በሁለት እግር የሚያቆም እና የሚያራምድ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ፍልስፍና በእጅጉ ተርቧል።ያን ጊዜ በኩራት እና በድፍረትይነሳል።በእዚህም አያቆምም  የበታኝ አስተሳሰብ የተጠናወታቸውን በምክርም በግሳፄም ያስተካክላል።የሩቅ ጠላቶቹን ያሳፍራል።የሚፈለገው ልማት እና እድገትም በራሱ ጊዜ መስመር ውስጥ ይስገባዋል።ከእዝያ በኃላ ማን ያቆመናል?

አበቃሁ

ጉዳያችን ጡመራ
ጌታቸው በቀለ
ጥር 5/2006 ዓም
ኦስሎ፣ኖርዌይ

ይህንን ፅሑፍ በየትኛውም ድረ-ገፅ ላይ ማውጣት ይቻላል።ግን ምንጩን ጉዳያችን ጡመራ መሆኑን መግለፅ ጨዋነት ነው።

Friday, May 9, 2014

ዛሬ አበበ ገላው ፕሬዝዳንት ኦባማን በንግግራቸው መሃከል አቋርጦ የኢትዮጵያን ነፃነት እንደገና አስተጋባ (ቪድዮውን ይመልከቱ)


ዛሬ አበበ ገላው ፕሬዝዳንት ኦባማን በንግግራቸው መሃከል አቋርጦ የኢትዮጵያን ነፃነት እንደገና አስተጋባ። ኦባማ ግን እንደ አቶ መለስ አልተደናገጡም።
አበበ ''አቶ ኦባማ እኛ ኢትዮጵያውያን እንወደዎታለን! ለኢትዮጵያ ነፃነትን እንሻለን!  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ይቁሙ! ጨቋኞችን አይደግፉ! በኢትዮጵያ ጨቋኞች መንግስት አለ! እኛ ኢትዮጵያውያን እንወድዎታለን!''

ፕሬዝዳንት ኦባማ መለሱ  ''በሀሳብህ እስማማለሁ፣ልክ ነህ፣ንግግሬን እንደጨረስኩ እንነጋገራለን፣እኔም እወዳችኃለሁ (ኢትዮጵያውያንን ማለታቸው ነው) '' ካሉ በኃላ መጨረሻ ላይ ''የእዚች ሀገር የመናገር ነፃነት ይሄው አየን'' በማለት ተሰብሳቢውን አስቀውታል።ከንግግራቸው በኃላ አበበ ደብዳቤውን ለፕሬዝዳንት ኦባማ ሰጥቷል።


የደብዳቤውን ይዘት ለማንበብ ይህንን ይጫኑ(Click to read his Open letter to President Barack Obama) የአበበ ደብዳቤ ለፕሬዝዳንት ኦባማ

US president Obama and Ethiopian activist and journalist Abebe Gelaw in San Jose’s Fairmont Hotel

While Obama was wrapping up his speech last night at a glitzy Democratic National Committee reception in San Jose’s Fairmont Hotel, journalist and activist Abebe Gellaw interrupted the president and called support for freedom in Ethiopia. The event jointly hosted by Yahoo CEO Marissa Mayer and and Y Combinator CEO Sam Altman was mainly attended by Silicon Valley business and political leaders.Journalist and activist Abebe Gellaw interrupted president Obama

Abebe began his message with a positive note. “Mr. Obama, we Ethiopians love you. We demand freedom for Ethiopia,” he said.

The President, who was talking about winning both Congress and the Senate from the Republicans in the next election, replied “I agree with you although why don’t I talk about it later because I am just about to finish. You and me will talk about it. I am going to be coming around.”

But Abebe continued his message and loudly called for help to free jailed bloggers and journalists. “Stand with the people of Ethiopia, don’t support tyranny,” he said to which the president answered again, “I agree with you.”

“We have tyranny in Ethiopia,” Abebe said and added, “We love you!”

“I love you back,” the present replied and noted that his speech was kind of screwed up.

“That is okay. And we got free speech in this country,” he said before wrapping up his speech.

In a letter Abebe handed to the President at the end of the event, he noted that he wanted to take the rare opportunity to raise the voices of the oppressed people Ethiopia.

“Mr. President, as an exiled journalist and freedom activist trying to raise the voices of the oppressed people of Ethiopia, I can tell you that Ethiopians have genuine respect for this great land of freedom and your inspirational leadership,” he wrote.

“But it pains and frustrates me and millions of Ethiopians to see that for over two decades the United States has overridden its core values and forged a questionable alliance with the Tigray People’s Liberation Front, a terrorist group that has continued to oppress, massacre, jail, torture and displace defenseless Ethiopians.”

According to Abebe, the rare opportunity was another unmissable chance to demand our freedom and expose the tyrants at such a high profile platform of the most powerful decision makers in the world. “I am glad I took the chance though security was extremely tight. At the end of the day,we should consistently demand the U.S to the review its questionable foreign policy towards Ethiopia. That was also the heart of my demand,” he said.

http://ecadforum.com/2014/05/09/breaking-news-abebe-gellaw-interrupted-obama-and-obama-agrees-with-ethiopias-call-for-freedom/http://ecadforum.com/2014/05/09/breaking-news-abebe-gellaw-interrupted-obama-and-obama-agrees-with-ethiopias-call-for-freedom/
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Thursday, May 8, 2014

ሰበር ዜና- የዞን 9 ጦማርያን በማዕከላዊ እስር ቤት መደብደባቸውን እና በውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት መፈፀሙ ታወቀ Breaking News -Ethiopia - Zone 9 Bloggers are torched and beaten at 'maekelawi'


ጋዜጠኛ ተስፋለም ወደ ፍርድ ቤት እንደ ወንጀለኛ ታስሮ ሲወሰድ 

ዜናውን አስመልክቶ ዞን 9 ጦማርያን ዛሬ በፌስ ቡክ ገፅ ላይ የሚከተለውን አስፍሯል።

''የዞን 9 ጦማርያን ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል
የዞን 9 ጦማርያንን የጊዜ ቀጠሮ ሊያይ ተሰየመው ችሎት ዛሬ ሌላ አሰቃቂ ዜና አብሮ ሰምቷል፡፡ ሁለቱ የዞን9 አባላት በፍቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ በማእከላዊ መመታታቸውን እና ውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን ፓሊስ ማስረጃ የላቸውም ሲል ተከራክሯል፡፡ ለክርክሩ ምላሽም ውስጥ እግራቸውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቶርቸር ህግ መንግስታዊ አይደለም ሲል "አስተያየቱን" ሰጥቷል፡፡ እነደትላትናው ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 10 ቀናትን ለምርመራ ፈቅዶአል፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጠ ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በሁዋላ ካጨበጨባችሁ እነዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም ተሰጥቷል፡፡ ወ/ ሮ ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር (በተለመደ ቋንቋ በማቃጠር) አጋርነት እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም ሞክረዋል፡፡
ዞን 9 በድጋሚ የዞን 9 አባላት ያወሰድዋቸው ምንም አይነት የአሸባሪነት ስልጠና እንደሌላ እያረጋገጠ በህገ መነግስቱ አንቀጽ 18 መሰረት ማንኛውም ሰው ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ ከሆነ ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው ቢልም በታሰሩ አባላቶቻችን ላይ የደረሰውን ግርፋት አጥብቆ ያወግዛል።''  ይላል ዜናው።

የዞን 9 አባላት እነማን ናቸው? ሊንኩን ከፍተው ጉዳያችን ላይ ያንብቡ።////////////////////////////////።።።።።።።።።።/////////////////////////።።።።።።።።።።።።////////////////////


Wednesday, May 7, 2014

ኢትዮጵያ ''ሁሉም ሰው በአምባገነኑ መንግስት ኢላማ ውስጥ ነው'' (ቪድዮ)-Ethiopia ''Every body is targeted'' (video)

Solidarity Movement for New Ethiopiaጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

ይሉኝታ ያጠቃው ፖለቲካ የትም አያደርስም!ከአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ፕሮግራም ጋር በተያያዘ ሃሳባቸውን የሚገልፁም ሆኑ ምንም አይነት ሃሳብ ሳይገልፁ የኢትዮጵያን ውድቀት ከዳር ሆነው በማየት የህሊና እረፍት የሚያገኙ የሚመስላቸው ሁለቱም ነገሮችን የሚያዩበት ጥግ የእየራሱ ቦይ አለው።እርግጥ የሁሉንም መብት መከበር አለበት።እኔን መሰሎች ፍቅረ ኢትዮጵያ ይዞናል።''ይህ ጠቃሚ ነው ፣ይሄኛው ደግሞ እንደ ሀገር ጎጂ ነው'' እያልን የምንናገር እና ጥጋችን ፍቅረ-ኢትዮጵያ ብቻ የሆንን የምንለው አሁንም ሚዛን ደፍቶ የሚገኘው ከጊዜ በኃላ መሆኑ ይገርመኛል።
እኛ የምናነሳውን ከአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ፕሮግራም ጋር የተያያዙት የነገሮችን አመጣጥ ቀድመው ቢያውቁትም ለተራው ሕዝብ ግን አይነግሩትም።ምክንያቱም ፖለቲካ ነው እና ብዙ ቀመር ይወጣለታል ወይንም ጊዜው አሁን አይደለም ይባላል።ከእዚህ ውጭ ግን ያለው ሌላው አባዜ (የእኔ አስተያየት ነው) ይሉኝታ ያጠቃው ፖለቲካ ነው።ለምሳሌ የሰሞኑ በኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ የተፈጠረው ችግር አድራጊው ኢህአዲግ ይሁን እንጂ የችግሩ ምንጮች ግን ሁለት ናቸው።

1ኛ/ የመጀመርያው የኢህአዲግ የተሳሳተ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የፌድራል ስርዓት።

የመጀመርያው ችግር የኢህአዲግ የተሳሳተ ጎሳን መሰረት ያደረገ የፌድራል ስርዓት ነው። ይህ ፅንሰ ሃሳብ ኢህአዲግ/ወያኔ ገና በጫካ ሳለ ሲኮነን የነበረ።ኢትዮጵያን የበታተን ዕድል ያለው መሆኑ የተመሰከረለት። በአንፃሩ ኢህአዲግ ደግሞ ''የለም እንደ ብረት አንድነታችንን እያጠነከረው ነው'' እያለ ሲዋሸን የነበረ ጉዳይ ነው።ከእዚህ በፊት ዜጎች ከኖሩበት ቀዬ እየተባረሩ እንዲሄዱ፣ጎሳ በጎሳ ላይ እንዲነሳ እና እንዲጋደል ያደረገ፣ድሮ በሀገራት መካከል ይነሱ የነበሩ የድንበር ፀቦች በኢህአዲግ ዘመን ጎሳ ከጎሳ ድንበር ጋር መጋጨት እና ጦርነት የከፈቱበት (ለምሳሌ በሱማሌ እና በኦሮሞ መካከል እና በጉጂ እና በኦሮሞ መካከል የተነሱት ግጭቶች) ሁሉ ምክንያት ይሄው የ ኢህአዲግ  ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌድራሊዝም ተብዬው ነው።

2ኛ/ ሁለተኛው ለዘመናት ኢትዮጵያን ለማመስ ሲያደባ የነበረው የፅንፈኛ የእስልምና እንቅስቃሴ በኢህአዲግ የጎሳ ፖለቲካ ማዳበርያነት ዳብሮ የኢትዮጵያን ችግር ለማወሳሰብ ከመቼውም ጊዜ በላይ አመቺ ጊዜ ማግኘቱ።

ወቅቱ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንዳትቀጥል የሚፈልጉ በርካታ ሃገራት የእየራሳቸውን አጀንዳ ይዘው የተሰለፉበት ወቅት ነው።ለእዚህም በዘመነ ኢህአዲግ ሁለት አመቺ ሁኔታዎች ተፈጥረውላቸዋል።አንደኛው ለዘመናት ዕድል ያላገኘው ፅንፈኛው የእስልምና ኃይል በብሄር ስም ተደራጅቶ የኢህአዲግ አጋር ድርጅት ተብሎ ወደ ክልሎች እና አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ስልጣን መምጣት መቻሉ ሲሆን ሁለተኛው ይሄው ኃይል በገንዘብ፣በቁሳቁስ እና በሰው ኃይል ሀገርቤት ውስጥ እራሱ ኢህአዲግ ውስጥ የጠነከረ እንዲሆን መቻሉ ነው።በተለይ ይህንን ኃይል የሚደግፉት እና በኢንቨስትመንትም ሆነ በተለያየ ድርጅት ስም ሀገርቤት የገቡ የቅርብም ሆኑ የሩቅ ከኢትዮጵያ መዳከም እንደሚጠቀሙ የሚያስቡ ኃይሎች ለቡድኑ ከፍተኛ ሽፋን እራሱ ኢህአዲግ ውስጥ ሆነው እየሰጡ ይገኛሉ።

አሁን ጥያቄው የኢትዮጵያ የአንድነት የፖለቲካ ኃይሎች እነኝህ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት ነገሮች አንጥረው መቃወም እና ሕዝቡን ከጎናቸው ማሰለፍ ሲገባቸው እነርሱ ግን ግዝያዊ ወይንም ስልታዊ ሥራ እየሰሩ እየመሰላቸው ሁለት የተሳሳቱ ተግባራትን ሲሰሩ ይታያሉ።

አንደኛው በኦሮምያ እና በሌሎች ቦታዎች የተነሱት የጎሳ ግጭቶች መሰረቱ የኢህአዲግ የተሳሳተ  ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌድራሊዝም መሆኑን ሳይፍሩ መናገር አለባቸው።የተወሰኑ ጎሳዎች ስሜት ይነካል ተብሎ ዘላቂ አሸናፊውን ሃሳብ ወደጎን ማድረግ አርቆ ማየት አይመስለኝም።

ሁለተኛው ፅንፈኛው የእስልምና ኃይል (ኢህአዲግ የእስልምና ጉዳዮች ኮሚቴዎችን የሚከስበትን ማለቴ አይደለም) ኢትዮጵያን ለዘመናት ሲያተራምስ የኖረ መሆኑን እያወቁ ሰሞኑን በኦሮምያ በተነሳው ችግር ላይም እጁን እንዳስገባ እያወቁ ለስልታዊ አቀራረብ ነገሩን ወደጎን ትቶ ማለፍ ተገቢ አይደለም። አዎን! በፌድራል የተገደሉት ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ሞትን መቃወም ተገቢ ነው።ነገር ግን ሁለት አደገኛ ኃይሎችን መቃወም ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ነው።እነርሱም የኢህአዲግን ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌድራልዝም እና በጉዳዩ ላይ በኦሮሞ ሕዝብ ስም መነገድ የሚፈልገው ፅንፈኛው አክራሪ ኃይልን።

በነገራችን ላይ ሁለቱ ማለትም ኢህአዲግ/ወያኔ እና ጎሳ ውስጥ ለመወሸቅ የሚውተረተረው ፅንፈኛው ኃይል እርስ በርስ እየተመጋገቡ መሆኑን ማየት ይቻላል።ሁለቱንም አንድ የሚያደርጋቸው ነጥቦች አሏቸው።ሁለቱም የኢትዮጵያን ያለፈ ታሪክ ጥላሸት መቀባት ይፈልጋሉ፣ሁለቱም የኢትዮጵያ አንድነት በፍቅር እና በሕብረት ከሚሆን ይልቅ ሁሉም በየጎሳው እንዲያስብ ይጥራሉ።ለእዚህም በብዙ ነገሮች ተገልጧል።ባለፈው አርሲ ላይ በ20 ሚልዮን ብር የተሰራው ሃውልት ላይ ሁለቱም ሲዘፍኑለት ሕዝብ ግን ጥቅሙ ምንድነው? እያለ ስጠይቅ ነበር።አሁንም በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ላይም ሲደጋገፉ እናያለን ትናንት ሚያዝያ 28/2006 ዓም አንድ የኢህአዲግ ደጋፊ እና በስርዓቱም ውስጥ ቦታ ያለው ዳንኤል ብርሃነ የተሰኘ ጦማሪ ጀዋር መሐመድን የገለፀበት ቃል እንዲህ ይላል ‹‹ጃዋር እኮ ታጋይ ነው - ዝም ብለህ አትማው፡፡ ይሄ የሰሞኑ ወሬው ከቀኝ ሀይሎች ድጋፍ ለማግኘት ብሎ እንጂ ለክፋት አይደለም›› መመጋገብ ማለት ይህ ነው።

 ዛሬ ለሕዝቡ ትክክለኛውን ጉዳይ መናገር ካልተቻለ ነገ ኢትዮጵያን የማትወጣበት አዘቅት ውስጥ እየከተትን መሆኑን ማሰብ ይገባል። ይሉኝታ ያጠቃው ፖለቲካ ኢትዮጵያን የትም አያደርሳትም።ሁሉንም ባንዴ መናገር አይቻልም የሚሉት ስልት ለእንደዚህ አይነቱ ተግባር አዋጪ አይደለም።


ጉዳያችን
ሚያዝያ 29/2006 ዓም  

Tuesday, May 6, 2014

''ኢትዮ ፈርስት'' የለቀቀውን ቪድዮ አየሁት።ፊልሙን የተረዳሁት በአራት ደረጃ ነው- በሚያሳዝን፣በሚያስደስት፣ በማይመስል እና የችግሩን ምንጭ ያድበሰበሰ በሚል


1/ የሚያሳዝን 

የተቃጠሉ ሆቴሎች እና ህንፃዎች የአምቦ ፍርድ ቤትን ጨምሮ መቃጠላቸውን ፊልሙ ያሳያል። እዚህ ላይ ያሳዝናል።

2/ የሚያስደስት  

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን በሺህ የሚቆጠሩ ከእስልምናም ሆነ ከሌላ እምነት የመጡትን ሁሉ ጨምራ ምንጣፍ አውጥታ በቅፅረ ግቢዋ እያሳደረች ማፅናናቷ፣ ወጥ እና እንጀራ የአምቦ ሕዝብ እያመጣ ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ መመገቧ እና አሁንም ከሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች መጠለያ መሆኗን ተማሪዎች ሲመሰክሩ ፊልሙ ያሳያል። እዚህ ላይም በጣም ደስ የሚል ሥራ ተሰራ ያሰኛል።ቤተ ክርስቲያን እናትነንቷን አሳየች።

3/ የማይመስል  

ስለ ጠፋው ሕይወት አንዳች ነገር አልተነፈሰም የሞተውን ቁጥር መንገር አይደለም እንድያውም ''ከተማሪ የሞተ የለም'' የሚል ንግግር ከተማሪዎች ሲነገር ፊልሙ ያሳያል።ከነዋሪም ስንት ሰው እንደሞተም ፊልሙ አይተነፍስም።ይህ ብቻ አይደለም ግጭቱ የተነሳበትን ምክንያት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በዘለለ ፊልሙ ሊያጎላው የፈለገው ''አራምባና ቆቦ'' የሆነ ጉዳይ ነው አንዴ 'ባህር ዳር በነበረው የስፖርት ውድድር በነበረው ግጭት የተናደዱ'፣ይላል መልሶ አፄ ምኒልክን ያነሳል ቀጥሎ ቴዲን ያነሳል። ይህ የተጨመረ ቅመም ነው።ህዝብን ለማጋጨትም የገዢዎቻችን ዝብዘባ ነች። እንበል አንድ ሁለት የዞረባቸው እና ''የሜጫ'' አስተሳሰብ የያዙ ደካማ ተማሪዎች አሉ እንበል የእነርሱን ሃሳብ ሚድያ ላይ መናገር እና ማጉላት  ምን ሊያስከትል እንደሚችል ገዢዎቻችን ያውቃሉ።ግን አሁንም የሚነግሩን የፅንፈኞችን እንጉርጉሮ ነው።ጉዳዩን በባህር ዳር እና በምኒሊክ ዙርያ ማዞር ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው።እናም ፊልሙ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት ያሰበ ይመስላል።ማጋጨት ተክናቹበታል።

4/ ፊልሙ የችግሩን ምንጭ አልጠቀሰም 

ኢህአዲግ ሁሌ የሚረሳው ነገር በብሄር እና  በቋንቋ ምክንያት ለምትፈሰው እያንዳንዷ ጠብታ ደም ኢህአዲግ/ወያኔ ተጠያቂ መሆኑን ነው።ኢትዮጵያ በታሪክ በእንደዚህ ደረጃ በአንድነቷ እና በህልውናዋ ላይ የተቃጣ መንግስታዊ የዘር ፖለቲካ መርዝ ተረጭቶባት አያውቅም።አዲስ አበባ ከኦሮምኛ ጋር ጥያቄውን ያወሳሰበው እራሱ ወያኔ ነው።ኢህአዲግ/ወያኔ በ 1997 ዓም አዲስ አበባን አንዴ ፊንፊኔ ብያለሁ የኦሮምያ ዋና መቀመጫ ሆነች ሲለን መልሶ ደግሞ ወደ አዳማ ቀይሬዋለሁ ሲለን፣ ሌላ ጊዜ አቦይ (የተቀበረውን መርዝ ያውቃሉ እና) እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ በማግስቱ ትከፋፈላለች ሲሉን እንዳልንበር ለአምቦ ብጥብጥ ተጠያቂዎቹ ፅንፈኛ ኃይሎች ብቻ ሳይሆኑ እራሱ ኢህአዲግ/ወያኔ ያፀደቀው የጎሳ ፖለቲካ ፌድራሊዝም ነው።

ይህ እንደሚሆን ደግሞ ሕዝብ የተናገረው ከዛሬ 23 ዓመት በፊት ነበር።''ይህ አይሆንም አንድነታችን እንደ ብረት የጠነከረ እየሆነ ነው'' እያለ ስዋሸን የነበረው ደግሞ ኢህአዲግ/ወያኔ ነው። በመሆኑም የችግሩ ምንጭ ዋናው ጎሳን መሰረት ያደረገ ኢትዮጵያን ለመበታተን የቆመው የኢህአዲግ/ወያኔ ከፋፋይ ፌድራሊዝም ነው። እናም ተጠያቂውም ሆነ የችግሩ ምንጭ እና ፅንፈኞች ኢትዮጵያ ላይ እንዲዘባበቱባት የሕግ ድጋፍ የሰጣቸው አሁንም ኢህአዲግ/ወያኔ ነው። አሁንም የችግሩ ምንጭ እራሱ ኢህአዲግ/ወያኔ እስካለ ድረስ ተመሳሳይ ችግሮች ገና ብዙ ልናይ እንችላለን።እንደ ኢህአዲግ እቅድ የአሩሲው የተቆረጠ እጅ ሃውልት በ ሃያ ሚልዮን ብር ሲገነባ እና ኢቲቪ ባለፈው ወር እንደ ዜና ሲናገር ነገሩን ጨርሶታል።አሁንም ለእያንዳንዷ የደም ጠብታ ዋና ምንጩ የኢህአዲግ የጎሳ ፖለቲካ ነው።ሌላው አጫፋሪ ነው።''ኢትዮ ፈርስት'' የሸሸገን ወይንም ለመናገር የፈራው እውነታም ይህንኑ የችግሩን ዋና ምንጭ ነው።

ጉዳያችን
ሚያዝያ 28/2006 ዓም 

Saturday, May 3, 2014

ኢህአዲግ እና በሐገር ቤትም ሆነ በባህር ማዶ ያሉ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚጠቀሙበት የጎሳ ፖለቲካ ፎርሙላ ይህ ነው።(ጉዳያችን ጡመራ)


ኢትዮጵያውያን በተሸለመ ፈረስ ሲሄዱ 

ፎርሙላ (ቀመር) አንድ 

የጎሳ ፖለቲካ ማለት በመጀመርያ ቤተሰብህን የተለዩ ፍጥረት እንደሆኑ መስበክ መጀመር ማለት ነው።እነርሱ የተለዩ መሆናቸውን በደንብ ማሰብ ሲጀምሩልህ  ደግሞ በመቀጠል የሰፈርህን እና የወንዝህን ሰዎች ልዩ መሆናቸውን በሚገባ መስበክ ነው።የሰፈርህን ሰዎች ልዩ እና የተለዩ መሆናቸውን ስትነግር ግን የአንተ ቤተሰብ ጋር እንደማይደርሱ ግን ደግሞ ከቤተሰብህ ዝቅ ባለ መልክ የተለዩ መሆናቸውን ወትውታቸው። በመጨረሻ አንተ የቤተሰብህም ሆነ የሰፈርህ ብቸኛ አለቃ መሆንህን ትነግራቸውና ከሰፈርህ ማዶ ያሉ ሰዎች ደግሞ እርኩስ፣የተለዩ፣ጥንትም አባቶችን ሲበድሉ እንደነበሩ የሆነ ያልሆነ ተረታ ተረት እየነገርክ ተራራ የሚያህል ጥላቻ እንዲያድርባቸው አድርግ።

ፎርሙላ (ቀመር) ሁለት 

ከእዚህ በኃላ  በሰፈርህ ሰዎች እና ማዶ ባሉ ሰፈር ሰዎች መካከል በአንተ የጦር አበጋዝነት ጦርነት እንዲከፈት አድርግ።ጦርነቱን ልትከፍት ስትል ትልቅ ችግር ሊገጥምህ ይችላል።ለምሳሌ ለዘመናት በክፉም  ሆነ በደግ አብረው የኖሩ ሰዎች ናቸው እና ከአንተ ሰፈርም ሆነ ከማዶ ሰፈር ያሉ የበሰሉ ሽማግሌዎች ወይንም አስታራቂዎች ነገሩን እንዳያበርዱብህ ተጠንቀቅ። ''የፍቅር ዘመቻ'' ብሎ በሰፈርህ መካከል ዘፈን ልዝፈን፣ ፍቅርን ልዝራ፣ ብሎ የሚነሳ ሀገር የወደደው ዘፋኝ ካለ ቀድመህ በቻልከው ነገር በማማሰያም ሆነ በብረት ምጣድ ደብድበህ አባረው።የስም ማጥፋት ናዳ ልቀቅበት።ዘፋኝ እና የሃይማኖት ሰዎች አንድ ናቸው።ሁለቱም ዓለም አንድ ነው፣ምናምን እያሉ አላማህን ያደናቅፉብሃል።'ቀንድ ቀንዳቸውን' በላቸው።ከሃይማኖት በፍቅር የተሰበሰቡ ማሕበራት ካሉም እግር ከእግር እየተከታተልክ አድክማቸው። ከቻልክ ዝጋቸው።

የሃይማኖት እና የኪነት ሰዎች ብቻ አይደሉም የዓላማህ ጠላቶች ጋዜጠኞች፣ብሎገሮች ሁሉ ቀድመው የሰፈርህን ሰዎች ከማዶ ሰፈር ሰዎች ጋር አብረው እንዲኖሩ ሊሰብኩ ይችላሉ እና ፈጥነህ ከእየቤታቸው ፖሊስ ልከህ ልቀማቸው! ያዛቸው! ማዕከላዊ ወስደህ አጉራቸው! ነግሬሃለሁ ጉድህን ይዘከዝኩታል።በሰፈርህ እና በማዶ ሰፈር መካከል ልታጋጭ ያሰብከውን ጉድ ሁሉ ለሀገር ይነዙልሃል።ይህ ብቻ አይደለም ቤተሰብህ ከሰፈርህ ሰው የተለየ አለመሆኑን፣አንተም በቤተሰብህ እና በሰፈርህ ሰዎች ላይ መንገስ እንደማይገባህ፣ሌላ 'በሰፈርህ እና በማዶ ሰፈር ሰዎች መካከል ልዩነት የለም በፍቅር እንኑር' የሚል ሰው መንገስ አለበት ብለው ለሕዝቡ ይነግሩብሃል።እናም ፍጠን! እሰራቸው!ልክህን አሳያቸው!።

ፎርሙላ (ቀመር) ሶስት 

ይህንን ሁሉ ከጨረስክ በኃላ አንተ እና ቤተሰብህ ጥንቱንም የተለያችሁ ፍጥረቶች መሆናችሁን በተለይ አዲስ ለሚወለዱት ልጆች እየሰበክ በሰፈርህ ሰዎች እና በማዶ ሰፈር ሰዎች መካከል  እረጋ ብለህ ቡናህን  እየጠጣህ ጦርነት እንዲከፈት ማዘዝ ትችላለህ።ተቀናቃኝህን ሁሉ እንደሆነ እስር ቤት ሰደሃቸዋል።የዘፋኙንም ስም ከማዶ ሰፈር ካሉ መሰሎችህ ጋር ሆነህ ስሙን አስጠፍተሃል። ከእዚህ በኃላ ማዶ ያሉ መሰሎችም ሆኑ አንተ አንድ አይነት ጫወታ ላይ ገባችሁ ማለት ነው።መንደር ከመንደር እየቆጠረ ህዝቡ ሲባላ እነርሱ በውስኪ አንተም በኮኛክህ መዝናናት ፈታ! ማለት ነው።

ፎርሙላ (ቀመር) አራት 

ጦርነቱ  ሲደረግ አንተ በሰፈርህ ሰዎች ላይ ንጉስ  ሆነህ ''ካለእርስዎ አመራር የት እንደርሳለን?'' ስትባል  ጀነን፣ጎምለል ማለት ነው።አሁን ጥሩ ጊዜ መጣልህ የሀብት መጠንህ ይጨምራል።ምክንያቱም የሰፈርህንም ሆነ የማዶ ሰፈር ሰዎችን ገንዘብ ወደ ኪስህ እየከተትክ አለምህን መቅጨት ትችላለሃ!። በመካከል ታድያ ሥራ አትፍታ እዛኛው ማዶ የራሱ የሰፈሩን ሰዎች የመሰሉ ሰዎች ሰው እየላክ ''የእዝህኛው ሰፈር ሰዎች እናንተን ይጠላሉ ተጠንቀቁ!'' ማለት ለእራስህም ሰፈር ሰዎች እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር ጣል ማድረግ።ግጭቱ በደንብ አልጋጋልም  ካለህ ቀድሞ ከመቶ ዓመት በፊት የነበሩ የአንተ ሰፈር ሰዎች ''የሰሩት ኃጢያት አለ'' የሚል የሐሰት ታሪክ ማዶ ሰፈር ካለው መሰልህ ጋር በሚስጥር ተነጋግረህ  ''ማስታወሻ'' በሚል ስም የቂም ሐውልቶችን በየሰፈሩ መደርደር በተለይ ሴቶች ስሜታቸው የሚነካ የሰውነት ክፍል ለምሳሌ ጡት እና ጣት የመሳሰሉ የሰውነት ክፍሎች ተቆርጠው ነበር ብለህ ሃውልት መስራት።ያኔ ወጪ ወራጁ ''ህም! ድሮ እንዲህ አድርገዋል አሉ'' እያለ ከንፈር እንዲነክስ ማገዝ።አዎ ማገዝ።

ፎርሙላ (ቀመር) አምስት 

የሰፈርህ እና የማዶ ሰፈር ሰዎች አንድ መሆናቸውን ሊሰብኩ የሚነሱ ከመከከልህ ከተነሱ ወይንም ደግሞ የእዚህ አይነት አስተሳሰብ አላቸው የምትላቸውን ገልሰቦችም ሆነ የሃይማኖት ሰዎች ማኅበራት በሙሉ ተለጣፊ ስም መስጠት   ''አጎብዳጆች፣አሸባሪዎች፣የሰፈሬን ሰዎች ሰላም የሚያናጉ፣ዥንጉርጉር አብዮት ሊያስነሱ ያቀዱ'' እያልክ  ማሰር እና መግደል።

መደምደምያ 

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እና በባህር ማዶ እና በሀገር ቤት በጎሳቸው ላይ እራሳቸውን ያነገሱ እና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጥላሉ ሁሉ ሲጠቀሙበት የሰነበቱት የጎሳ ፖለቲካ ፎርሙላ  ይሄው ነው።ኢትዮጵያ በእናንተ ዘመን አልተፈጠረችም እንዴት እንደምትኖር ታውቅበታለች።ግዴላችሁም ይህች ሀገር አምላክ አላት። በኢትዮጵያዊነት ላይ ጥላቻ ያደረበት ለጥላቻውም አስር ምክንያት ቢደረድር በመንግሥትነትም ሆነ በተቃዋሚነት ቢሰየም፣የቂም ሐውልቶችን እንደ አሸን ቢያፈላም ሆነ በነፃነት ስም ከመቶ ዓመት በፊት ይህ ትውልድ ላልኖረበት ዘመን እየጠቀሰ ለስልጣን መወጣጫ ሊጠቀም ቢሞክርም  ከህዝብ ፍርድ አያመልጥም።አሁንም ግዴላችሁም ይህች ሀገር ጎሳ እና ብሔር የማያውቁ ለሰው ልጆች በሙሉ የሚፀልዩ ቅዱሳን እና የሚሰማቸው አምላክም አሏት።አሁንም ኢትዮጵያዊነት የጋራ መጠለያችን ነው።የጎሳ ፖለቲካ ፎርሙላ-ቀመራችሁ  ተነቅቶበታል።

ጉዳያችን
ሚያዝያ 25/2006 ዓም
(ከጉዳያችን ጡመራ ለሚወስዱት ፅሁፍ ምንጩ ጉዳያችን መሆኑን መጥቀስ ጨዋነት ነው)

Friday, May 2, 2014

በአምቦ እና በሌሎች ከተሞች በተማሪዎች እና በነዋሪዎች ላይ የተፈፀመው አሳዛኝ ግድያ በፅኑ እየኮነንን - ዛሬም ለሁላችንም ከጎሳ ፖለቲካ ይልቅ ኢትዮጵያዊነት መጠለያችን መሆኑን አበክረን እንናገራለን። (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)ኢህአዲግ የጎሳ ስሜቶችን በቻለው መጠን ለማራገብ መመሞከሩን እንደ ትልቅ ድል ሲቆጠረው ዓመታት አስቆጥሯል።''ከመቶ ዓመታት በፊት ጡት ተቆርጦ ነበር'' በሚል ከ ሃያ ሚልዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ  በአርሲ ሃውልት መመረቁን ኢቲቪ ሲነግረን እና በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ላይ የስርዓቱ ደጋፊዎች መሆናቸው የሚናገሩ ግለሰቦችም የቀደሙ የኢትዮጵያን መሪዎች እየነቀፉ የሃውልቱ መሰራት ''የኢህአዲግ የጎሳ ፖለቲካ ድል'' እንደሆነ ሲነገሩን ገና ሳምንታት መቆጠራቸው ነው።  

ኢህአዲግ በአምቦ ባዶ እጃቸውን ለጥያቄ ሰልፍ የወጡ ወጣቶችን በጠራራ ፀሐይ ሲገድል ፍትሃዊ እንደሆነ ሊነግረን ይሞክራል።ይህ በእውነት በኢትዮጵያዊነታችን እጅግ የሚያም ነው።አሁንም ሁኔታዎች ሁሉ የሚያረጋግጡት የኢህአዲግ የጎሳ ፖለቲካ  በሚቃወሙት ዘንድ ብቻ ሳይሆን ተመሳሳይ የጎሳ የፖለቲካ  ዓላማ ለሚያራምዱትም  በቂ ምላሽ ሲሰጥ አለመቻሉን ነው።

ይህ ብቻ አይደለም ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊውን ከኢትዮጵያውነቱ የተለየ ስም በመስጠት ለማስፈራርያነት የሚጠቀሙት ፅንፈኛ የጎሳ ፖለቲከኞች ከኢህአዲግ አስተሳሰብ ብዙም ባልዘለለ መልክ ነገሮችን ጫፍ ከመውሰዳቸውም በላይ የኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ትግል እንደግመል ሽንት ወደኃላ እንዲሄድ ሲያደርጉት እንደነበረ ሁሉ አሁንም ጥያቄዎችን በኢትዮጵያዊነት ስሜት ከማቅረብ ይልቅ የመረጡት የጎሳ ፖለቲካ የትም  ሊያደርስ አይችልም።ሕዝብ በአምባገነንነት ስቃዩን እያየ ከመቶ ዓመት በፊት የነበረ ታሪክ ላይ መከራከር እና አሁንም ከመቶ ዓመታት በፊት የነበሩ ንጉስን በዘፈኑ አሞገሰ እያሉ አንድን ዘፋኝ ላይ ዘመቻ ከፍቶ 'ያዙኝ ልቀቁኝ' የሚሉ ፖለቲከኞች ድሮም ለኦሮሞ ሕዝብ አስበው ነው ብሎ መናገር በራሱ በፖለቲካ መቀለድ ነው።

ሰሞኑን በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች እና በተለይ በአምቦ የተፈፀመውን ግድያ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አውግዘውታል።በመጪው ሰኞ ደግሞ ''ደማችን ደማችሁ ነው'' በሚል መፈክር ስም በዋሽግተን ዲሲ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ እንደሚወጡ ተነግሯል። የኢህአዲግን የተዛባ የችግር አፈታትን እና የጎሳ ፖለቲካውን ስንቃወም አብረን ማስተዋል የሚገባን ታሪክ ትናንትም ዛሬም ያረጋገጠልንን  ቁም ነገር ነው። ይሄውም ለሁላችንም ከኢትዮጵያዊነት ሌላ መጠለያ የለንም።

ጉዳያችን 
ሚያዝያ 25/2006 ዓም ሰበር ዜና - በኤርትራ መንግስት -ሻብያ ውስጥ ቀውሱ ተባብሷል።በሱዳን፣በኬንያ፣በግብፅ እና አሁን በናይጄርያ አምባሳደር የነበሩት ሞሐመድ አሊ ኦማሮ ባለፈው ማክሰኞ አስመራ ላይ በደህንነቶች ተያዙ።

ማክሰኞ ሚያዝያ 21/2006 ዓም የታሰሩት ሞሐመድ አሊ ኦማሮ  (ፎቶ አዋቴ ዶት ኮም)

ሞሐመድ አሊ ኦማሮ ቀደምት እና ለሻብያ እንደ አንድ የድርጅቱ የረጅም ጊዜ አባል አባባል ''ዓይን'' የተባሉ ስራዎችን የሰሩ አንጋፋ ሰው እንደነበሩ ይነገራል።ግለሰቡ
- እ አ አቆጣጠር ከ 1960ዎቹ ጀምረው በሻብያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ሲያገለግሉ ነበር፣
- በጦርነቱ ወቅት የነበረው የሻብያ ራድዮ መስራች ናቸው፣
- በጦርነቱ ወቅት መቀመጫውን በሳውዳረብያ  ያደረገው የአረብ ሀገሮች የሻብያ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፣
- አሁንም በጦርነቱ ጊዜ የሻብያ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ሱዳን ውስጥ ሰርተዋል፣
- ከጦርነቱ በኃላ በሱዳን፣በኬንያ፣በግብፅ እና ባለፈው ማክሰኞ አስመራ ላይ እስክያዙ ድረስ በናይጄርያ አምባሳደር ነበሩ።

ዜናውን የዘገበው አዋቴ ዶት ኮም (awta.com) እንደሚያብራራው በኤርትራ ውስጥ ከፍተኛ የስልጣን ሽክቻ በተለያዩ ቡድኖች መካከል  መኖሩን እና የሞሀመድ አሊ መያዝ በራሱ እንደ ድረ-ገፁ አገላለፅ ''ለዓመታት ሲንከባለል የነበረውን የተለያዩ ቡድኖች የስልጣን ሽምያ  'የሚያፈላው' ነው።'' ብሏል።

ባለፈው ሳምንት የአፋር ቀይባህር ነፃ አውጭ ግንባር በአሰብ አካባቢ የሚገኝ የሻብያ የጦር ካምፕ አጥቅቼ በርካታ ገደልኩ የጦር መሳርያም ማረኩ ማለቱ ይታወሳል።

ጉዳያችን
ሚያዝያ 24/2006 ዓም 

Thursday, May 1, 2014

ሰበር ዜና በጎንደር ተኩሱ ቀጥሏል በግጭቱ እስካሁን 6 ሰው ሞቷል.


ፖሊስ በነዋሪዎቹ ላይ የወሰደው እርምጃ ያስቆጣው የጎንደር ህዝብ በቁጣ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ከጎንደር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በፖሊስ እርምጃ የተቆጡ ወጣቶች የፖሊስ መኪና በመሰባበር ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ ህዝቡ በነቂስ እየወጣ ግጭቱ እየተባባሰ መሆኑንም ምንጫችን ጠቅሷል።

ጎንደር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታቸው አርምጭሆ ሰፈር፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች የከተማው አስተዳደር ‹‹ህገ ወጥ ሰፈራ ነው፡፡›› በሚል ለማፍረስ መዘጋጀቱን ተከትሎ አፍራሾቹ ከህዝብ ጋር በፈጠሩት ግጭት ከ6 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ግጭቱ ከሶስት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ ቀጥሎ የነበር ሲሆን ምንጫችን ደውሎ በሚነግረን ወቅት (6፡ 43) ተኩስ እንደነበር ለመረዳት ችለናል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎቹ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ትዕዛዝ በተላለፈበት ወቅት ህገ ወጥ አለመሆናቸውን፣ ካልሆነም መንግስት ቅያሬ ቦታና ጊዜ መስጠጥ እንዳለበት በመግለጽ አንለቅም ብለው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዛሬው ቀን ግጭቱ የተነሳውም አፍራሾቹ እንዲፈርሱ የተወሰነባቸውን ቤቶች ቀለም በመቀባታቸውና ህዝቡም እንዳይቀቡ በመከልከሉ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

በግጭቱ ፖሊስ፣ ፌደራልና ልዩ ኃይል የተሳተፈበት ሲሆን ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ የአካባቢውን ወጣቶች ላይ ድብደባና እስራት እየፈጸሙባቸው እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ‹‹ወጣቶችን እንደ እንሰሳ በአንድ ገመድ አስረው እየደበደቧቸው ነው፡፡ ህዝብ በጅምላ እየታሰረ ይገኛል፡፡ ግጭቱ ቢያቆምም በአሁኑ ወቅት በሶስቱም ሰፈሮች ጥይት እየተተኮሰ ነው›› ያሉት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች የተወሰደው እርምጃ የጎንደርን ህዝብ በማስቆጣቱ ከዚህ የባሰ ግጭት እንዳይፈጠር ያሰጋል ሲሉም ገልጸውልናል፡፡ በግጭቱ ወቅት የመጀመሪያዋ የሞት ሰለባ የሆነችው ልዩ ኃይል ቤቷ እንዲፈርስ ቀለም ሲቀባ የተቃወመች የልጆች እናት እንደሆነችም ታውቋ፡፡
ፖሊስ በነዋሪዎቹ ላይ የወሰደው እርምጃ ያስቆጣው የጎንደር ህዝብ በቁጣ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ከጎንደር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በፖሊስ እርምጃ የተቆጡ ወጣቶች የፖሊስ መኪና በመሰባበር ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ ህዝቡ በነቂስ እየወጣ ግጭቱ እየተባባሰ መሆኑንም ምንጫችን ጠቅሷል።

ምንጭ - የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን ''ነገረ ኢትዮጵያ'' ዛሬ በፌስ ቡክ ገፁ  እንደገለፀው።


በኢትዮጵያ ሃሳብን መግለፅ የወደቀበት የአደጋ መጠን (ቪድዮ)- የዞን 9 ጦማርያን፣የውብሸት ታዬ ባለቤት፣የርእዮት ዓለሙ እህት እና ሌሎችም ሃሳባቸውን የሰጡበት ቪድዮ ይመልከቱት። Freedom of expression at risk in Ethiopia (video)ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
http://gudayachn.blogspot.no/2014/05/9_1.html

GUDAYACHN BLOG started on August 28/2011 ኢሜይል አድራሻዎን በመሙላት ጽሁፎቹን መከታተል ይችላሉ/Follow by Email

በብዛት የተነበቡ/Popular Posts

ጉዳያችን በፌስ ቡክ ገፅ / GUDAYACHN ON FACE BOOK

https://www.facebook.com/gudayachn/?pnref=story