ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, November 10, 2013

''እኛ መንግስት የለንም! የሌላው ሀገር መንግስት ሕዝቡን አስከብሯል አንድ የሌላ ሀገር ሰው ጨርቁ አልተነካም 'አበሽ ነህ? ኢትዮጵያዊ ነህ ?' እየተባለ ነው የሚቀጠቀጠው''


እሁድ ህዳር 1/2006 ዓም በአረብኛ የሚታተም የሳውዲ ጋዜጣ ኢትዮጵያውያን እጃቸው ታስረው የሚያሳየው ፎቶ 

የዛሬ አርባ ዓመት በ 1965 ዓም ኢትዮጵያ በመላው ዓለም የታወቁ እና የተመዘገቡ ስደተኞች ቁጥር 2 ብቻ ነበር።ዛሬ ከሁለት ነጥብ አምስት ሚልዮን በላይ ደርሷል። የተከበረች የታፈረች ሀገር ዛሬ በእዚህ ደረጃ መዋረዷ ያሳዝናል።ቆም ብሎ ማሰብ አይገባም ወይ? ኢትዮጵያዊነት ከተዋረደበት ደረጃ መነሳት የለበትም ወይ? ክምንጊዜውም በላይ ህብረት እና አንድነታችንን ማጠንከር የሚገባን ወሳኝ ጊዜ  ላይ አይደለንም ወይ?

ሳውዲ አረብያ ያሉ ወገኖቻችን በቀጥታ በስልክ ዛሬ እሁድ ህዳር 1/2006 ዓም ከተናገሩት -


''እኛ መንግስት የለንም! የሌላው ሀገር መንግስት ሕዝቡን አስከብሯል አንድ የሌላ ሀገር  ሰው ጨርቁ አልተነካም 'አበሽ ነህ? ኢትዮጵያዊ ነህ ?' እየተባለ ነው የሚቀጠቀጠው''

''ወገን ይስማን!! ወገን ይድረስልን!!! ''

''እዚህ ሀገር ብዙ ሺዎች  የሚሆኑ የሌላ ሀገር ዜጎች እቃቸውን ይዘው አደባባይ ወጥተዋል ግን አንድ ሰው አልተነካም።እነሱ ኢምባሲ አላቸው።እኛ ማንም ዘወር ብሎ የሚያየን የለም።''

''ወንዶቹን ደብድበው ሴቶቹን ለ 7 እና ለ 8 እየሆኑ 'ሽባብ' የተባሉት የአረብ ወጣቶች ይደፍሯቸዋል''

'' ፖሊሶቹ ሆን ብለው ከዘራፊ እና ከሚደፍሩ ወጣቶች ጋር ይመጣሉ ሊያዘርፉን እና ሊደፍሩን''

''ንብረት የለፋንበትን በሙሉ ነው የነጠቁን መንገድ ላይ ወርቅ ያደረገች ሴት አልቀረችም በወጣቶቹ ተዘረፉ''

''ወንዱን እየጫኑ እየወሰዱ ሴቶቹን 'ሸባብ' ለተባሉ ወጣቶች እንዲደፈሩ ትተዋቸዋል።''

''ኢትዮጵያ ያለውን የሳዑድ አረቢያ ኢምባሲ ለምንድነው ሀገርቤት ያለው ሕዝብ  ወጥቶ የማይቃወመው ?ከየቤቱ አንድ ወይ ሁለት ሰው ወደ አረብ ሀገር ያልላከ ማን ነው? ለምንድነው ህዝቡ ዝም የሚለው?''

''የኢትዮጵያ ሕዝብ እባካችሁ ስሙን አንድ ነገር አድርጉልን አሁን በራችንን እስኪሰብሩ እና እስኪመጡ እየጠበቅን ነው።''

''ነገ እኔን አህትህን ላታገኘኝ ትችላለህ ወይ ለ አራት እና ለአምስት ተጫውተውብኝ አይምሮዬን ላጣ እችላለሁ።''

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።