ይህ ዜና ከ ጀርመን ድምጽ ራድዮ የሚያዝያ 23/2013 እ ኤ አቆጣጠር አማርኛው አገልግሎት ድህረ ገጽ ላይ የተገኘ ነው።እንዲህ ይላል።
''ሮም ለግራዝያኒ ሐውልት የተሰጠው ገንዘብ ታገደ
ለኢጣልያው ፋሺስት ጀነራል ግራዝያኒ መታሰቢያ ሐውልት መሥሪያ የተመደበው ገንዘብ ትናንት እንዲታገድ መደረጉን የኢጣልያ ባለሥልጣናት አስታወቁ ። ሐውልቱ የተሰራበት አፊሌ የተባለችው የግራዝያኒ የትውልድ ከተማ የሚገኝበት የላዝዮ ግዛት ባለሥልጣናት ገንዘቡን የሰጠነው ተጭብረብረን ነው ሲሉ አስታውቀዋል ። የላዝዮ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ዚንጋሬቲ የአፊሌ ባለሥልጣናት የገንዘብ እርዳታ የጠየቁት ለመናፈሻ ግንባታና ላልታወቀ ወታደር ሐውልት መሥሪያ እንጂ ለአወዛጋቢው ጀነራል ለግራዝያኒ ሐውልት መሥሪያ እንዳልነበር ተናግረዋል ። የላዝዮ ግዛት ለእርዳታ የመደበው 180 ሺህ ዩሮ ወይም 235 ሺህ ዶላር ለግራዝያኒ እስካሁን የተገነቡት መታሰቢያዎች ከአካባቢው እስኪነሱ ድረስ እንደማይሰጥ አስታውቋል ። ጀነራል ግራዝያኒ በኢጣልያ ወረራ ወቅት በኢትዮጵያ የኬሚካል የጦር መሣሪያዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉና በርካታ ሠላማዊ ሰዎችም እንዲጨፈፈጨፉ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ፣ጨፍጫፊው የሚል ቅፅል የተሰጠው የጦር አዛዥ ነበር ። የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበርና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለፋሽሽቱ ግራዝያኒ ሐውልት መቆሙን በማውገዝ ጠንካራ ተቃውሞ ሲያስሙ ቆይተዋል ። ፋሺስት ኢጣልያ ከተሸነፈች በኋላ ግራዝያኒ ለፈፀማቸው የጦር ወንጀሎች በወታደራዊ ፍርድ ቤት 19 ዓመት ቢፈረድበትም 2 አመት ብቻ ታስሮ በነፃ ተለቋል ።''
Source-http://www.dw.de/ይዘት/ዜና/s-11648
No comments:
Post a Comment