ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, December 4, 2012

''እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ '' ሐዋርያት ሥራ 20፣28

ሀገር ውስጥ ያሉት እና ውጭ ያሉ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል እዚህ በያዝነው ወር ውስጥ እርቅ ውይይትበ ደቡባዊቷ የ አሜሪካ ግዛት በ ቴክሳስ ዳላስ  ይደረጋል። ምእመናን እጅግ ጉጉት እየጠበቁት ያለ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የምትሄድበትን መንገድ የሚያመላክት ወሳኝ ውይይትም ነው። እኔም አባቶቻችን ውይይት እንደ ቤተክርስቲያኒቱ ልጅነት ምን መጠበቅ አለብን? ብዬ ሳወጣ ሳወርድ ቆየሁ። እናም ውይይቱ ውጤት እነኚህ ነጥቦች ባያንስብን ብዬ ተመኘሁ።

1 / '' ሁለት ሲኖዶስ'' ወደ አንድ ሲኖዶስ የሚያመጣ

2 / እውነተኛ ቤተክርስቲያንን አንድነት የሚያሳይ እና

3/ ሁሉም ያለፈውን እረስቶ ለነገዋ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት  የሚተጋበት እንዲሆን

አንድ ግን መርሳት የሌለብን ነገር አለ።የ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሀገሪቱ አሻራ እንደመሆኗ ሀገራችን የነገ ሁለንተናዊ እሷነቷ ትልቅ ተፅኖ ያለው መሆኑን መዘንጋት የለብንም። እዚህም ነው አባቶችን መጪ ውይይት ኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በጎ ምኞት የሚጠብቁትን ያህል ኢትዮጵያ ላይ ካላቸው የጠላትነት ስሜት ይህን ውይይት በጎ ፍሬ እንዳያፈራ ተግተው የሚሰሩ መኖራቸውን መዘንጋት የሌለብን።

ምእመናንም የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ፣ፍልስፍናዊ፣ወዘተ አስተያያት ቢኖረን እዚህ ውይይት መርሃግብር ላይ ግን አንዳች ልዩነት ሊታይ አይገባም። ሁሉም እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ ሁሉንም አባቶች ቤተክርስቲያንቱን አንድነት ላይ እንዲተጉ፣ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን በማስገንዘብ ሊያበረታቷቸው ይገባል።

''እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ እኔ በኋላ ለመንጋይቱ የማይራሩ ነጣቂዎች ተኩላዎች እንደሚመጡ እኔ አውቃለሁ '' ሐዋርያት ሥራ 2028-30 የሚለው ቅዱስ ቃል ዛሬም ሕያው ነው እና።

ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያለው ታምሩ አንድ ወቅት ያስተማሩት ትምህርት እዚህ በታች ያዳምጡ።

ቸር ወሬ ያሰማን
ጌታቸው
ኦስሎ


 

2 comments:

Anonymous said...

Anjet aris!

Anonymous said...

egziabher ytebkh berta endih yal lg lebetekrstiyn yasfelgatal dingl bemlgewa betecrstiyann ttebkln

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።