ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, November 18, 2012

'ሉሲ' የት ገባች? (የ ሉሲ 38ኛ አመት መታሰብያ)

ከሁሉ አስገራሚው ነገር የ ኢትዮጵያ መንግስት ሉሲን ከ ሀገር አንድትወጣ ያደረገበትን ምክንያት ሲገልፅ ''መልካም ስምን ለማደስ '' በሚል 'ታርጋ' ይሁን እንጂ አለም አቀፍ ሕግን የሚፃረር መሆኑን የተገነዘበ አይመስልም። ማንኛውም ጥንተ-አፅም ከተገኘበት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር እንዳይሄድ የሚለውን ውል እንደ፣ሚፃረር ልብ ያለው አይመስልም።
እ ኤ አ በ 1998 ከ ሃያ ሀገሮች የተውጣጡ ሳይንቲስቶች በ ዩኔስኮ አስፈራሚነት ''ማንኛውንም አይነት ጥንተ-ሰው አፅም ለሳይንሳዊ ስራዎች ምክንያት ካልሆነ በቀር ከተገኘበት ሀገር ውጭ እንዳይንቀሳቀስ '' የሚል ሕግ ሲያፀድቁ ትልቁ ስጋታቸው የ ቅርሶች መንገላታት ያውም በሚልዮን ለሚቆጠር እድሜ ላስቆጠረ ቅርስ ተስማሚ ያልሆነ የ አየርንብረት እና ከቦታ ወደ ቦታ መነቃነቅ ምን ያህል እንደሚጎዳ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባታቸው ነበር። redorbit.com የተሰኘ ድህረ ገፅ 'Lucy’ Exhibit Worries Some Scientists' (የ ሉሲ ለ አውደ ርዕይነት መቅረብ ሳይንፅቶችን አስጨንቀ) በሚል አርስት በፃፈው ፅሁፍ ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ሕግን እንደሚፃረር ገልፅዋል።
''Bringing Lucy to the United States for a museum exhibit also disregards a 1998 UNESCO resolution, signed by scientists from 20 countries, that says such fossils should not be moved outside of the country of origin except for compelling scientific reasons''
(ሉሲን ወደ አሜሪካ መምጣት በ 1998 በ ዩኔስኮ ከ ሃያ ሃገራት በተውጣጡ ሳይንቲስቶች የተፈረመውን ማንኛውንም አይነት ጥንተ-ሰው አፅም ለሳይንሳዊ ስራዎች ምክንያት ካልሆነ በቀር ከተገኘበት ሀገር ውጭ እንዳይንቀሳቀስ የሚያዘውን ውል ይፃረራል።)redOrbit(http://s.tt/16715) http://www.redorbit.com/news/science/1045002/lucy_exhibit_worries_some_scientists/

ሉሲ
 

ዛሬ አራት አመት በፊት ብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ግራ ያጋባ ውሳኔ ኢትዮጵያ መንግስት መወሰኑ ተሰማ። ዜናው ሉሲ (ድንቅነሽ) 3.2 ሚልዮን አመት በላይ እድሜ እንዳላት የሚነገርላት ጥንተ -ሰው አፅም አምስት ኪሎ ከሚገኘው ብሔራዊ ሙዜም '' ቀሪው አለም እንድትታይ'' በሚል ሰበብ ሰሜን አሜሪካ ደቡባዊ ግዛት ወደ ሚገኘው ቴክሳስ ክፍለሀገር ሁስተን ከተማ ''ሁስተን ተፈጥሮ ሳይንስ ሙዝየም ''(Houston Museum of Natural Science).እንድትሄድ ኢትዮጵያ መንግስት የመወሰኑ አስደንጋጭ ዜና ነበር።በ እዛው ሰሞን  እንግዳ ሲኖርብኝ ለ እንግዶቼ ብዙ ጊዜ ወደምወስዳቸው ብሔራዊ ሙዜም ገብቼ ሁኔታውን እና የሰራተኞቹን ስሜት ለመረዳት ፈለግሁ እና  ወደ አምስት ኪሎው ብሔራዊ ሙዝየም ጎራ አልኩ። እንደገባሁ ውስጠኛው ደንበኞች መስተንግዶ ክፍል ገባሁ እና ይቅርታ ጠይቄ ፊት ለፊት በኩል ለተቀመጠው ባለ ክራቫት ሰው ተጠግቼ:-

'' ሉሲ ልትሄድ ነው የሚባለው እውነት ነው?'' አልኩት  

እንዳቀርቀረ አገጩን ወደላይ እና ወደ ታች በማድረግ እውነትነቱን ገለፀልኝ። ቀጠልኩና -

'' እንደ ሙዝየሙ ሰራተኝነት ምን አልክ? ሰራተኛውስ ምን አለ?'' አልኩት።

ቀና ብሎ አየኝ እና 'ያምሃል?' በሚል ስሜት '' ምን የምንል ይመስልሃል? አንተ ልጅህን ከቤትህ እንውሰደው ብትባል ምን ትላለህ?''

አለኝ። ቀጠልኩና ''እሺ ካልተስማማችሁ እንዴት ጥያቄ አላነሳችሁም?'' አልኩት።በ ሰራተኛው ስብሰባ ላይ ተነስቷል ።ተቃውመናል። ማን ይሰማናል?'' አለ እልህ እና ቁጣ በተናነቀው ስሜት ቀጥሎ  አካባቢውን መልከት አደረገ። የመግቢያ ገንዘቡን ከፈልኩ እና የመጨረሻ ጥያቄ ሰነዘርኩ።

''መቼ ነው የምትሄደው አሉ?'' አልኩት። '' ሄዳለች ሳምንት ሆነ እኮ። አሁን ከ ሙዘሙ የምድር ክፍል ( ሉሲ ክፍል) የምታገኘው ተመስሎ የተሰራው 'አርተፍሻሉ' ነው።'' አለኝ። አለሁበት ክው አልኩ። ጋዜጦች ስለ ሉሲ መሄድ አለመሄድ ሲፅፉ ለካ እርስዋ ከሀገር ወጥታለች!
         ሉሲ (ድንቅነሽ)


ሉሲ (ድንቅነሽ) ማን ነች?
ሉሲ አንድ ሙሉ ሰው 40% የሚሆን አፅም ስብስብ (Australopithecus afarensis) የያዘች እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር 1974 ዓም አፋር ሸለቆ 'ሀዳር' በተባለ ቦታ የተገኘች፣ 3.2 ሚልዮን አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረች ብርቅዬ ኢትዮጵያዊት ቅርስ ነች።
1972 እኤአ  ፈረንሳዊው ጅኦሎጅስት ማውርስ ታይብ አለም አቀፍ አፋር ምርመር ቡድን(International Afar Research Expedition (IARE) የተሰኘ ሶስት ሀገሮች የተውጣጡ ሶስት ሳይንቲስቶችን አባልነት የያዘ ቡድን መሰረቱ።በ ቡድኑ ውስጥ ሶስቱ ሳይንቲስቶችም አሜሪካ ስነ-ቅሪት አካላት ተመራማሪው ዶናልድ ጆንሰን ፣ከ እንግሊዝ ማሪ ላኪ እና ፈረንሳይ ተወላጁ ይቨንስ ኮፐንስ ይገኙበታል።አሰሳው በተጨማሪ እረዳትነት አራት አሜሪካውያን እና ሰባት ፈረንሳውያን እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ኢትዮጵያውያን ይታገዝ ነበር።
ህዳር 24/1974 እኤአ ከቀትር በሁዋላ ሉሲ አካል ቀስ በቀስ መሟላት ጀመረ። አፋር ሃሩር ቀን ምሽት ሲታትር የነበረው ቡድን ደስታ ተዋጠ።ምሽት ላይ ምርምር ቡድኑ እንግሊዝ ሮክ ሙዚቃ 1960ዎቹ ዝነኛ የነበሩት '' ቢትልስ' ባንድ ታዋቂ የነበረው ሙዚቃ ምሽቱ ቡድኑ ደስታ ላይ አፋርን በረሃ ሰንጥቆ የሚሄደው ሙዚቃ የደስታው ተካፋይ ነበር። ዶናልድ ጆንሰን ሙዚቃ ማጫወቻ ''Lucy in the Sky with Diamonds'' (ሉሲ ባለ አልማዛዊው ሰማይ) የተሰኘው 'ቢትልስ ' ባንድ ሲያጫውት አንድ ነገር ብልጭ አለላቸው። 'አዲሱን ቅሪተ- አፅም ለምን 'ሉሲ' አትባልም?' የሚል ጥያቄ ጫረ። ''ሉሲ'' ሀገርኛ ''ድንቅነሽ'' ተባለች።
ሉሲ ኢትዮጵያን  ባለፉት ዘመናት መላው አለም  በደንብ እንዲያጠናት፣ስለ ኢትዮጵያ በሚገባ እንዲያነብ፣ እዚህም በላይ ብዙ ቱሪስቶች ወደሀገራችን እንዲመጡ ምክንያት ሆናለች

ሉሲ የሄደችበት ''ሁስተን ተፈጥሮ ሳይንስ ሙዝየም ''(Houston Museum of Natural Science,)
ዛሬ ሉሲ የት ነች?
ሉሲ ሀገር የወጣችበት አግባብ ማንንም ሰው የሚያሳምን አለመሆኑ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ማንም ሃገሩ ላይ ያለውን ቅርስ በውጭ ሀገር ሰዎችም ሆነ ሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እንዲጎበኝ እና ውጭ ምንዛሪም ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኘው ቅርሱ ሀገር ውስጥ ሲገኝ ነው።ኢትዮጵያ አመት እስከ ሶስትመቶ ሺህ ጎብኚዎች እንደሚጎበኝዋት፣ ይህ ቁጥር ጎረቤት ኬንያ አንፃር ሲታይ በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ይታወቃል።
አንድ ቱሪስት ሀገርቤት ከገባበት ጀምሮ ሀገር ትቶ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ለምግብ፣ለሆቴል፣ለትራንስፖርት እና ሙዜም ወዘተ እየደረጃው የሚከፍለው ክፍያ ውጭ ምንዛሪ መሆኑ ሀገራችን የሚሰጠው ጥቅም በቀላሉ የሚገመት አይደለም።ሉሲ ሀገር መውጣቷ ''ያለውን ጥቅም '' መንግስት ለማስረዳት በጣም ሲደክም እራሳችንን ያዞረን ሰዎች ቀላል አይደለንም።
አዎን አንዳንድ ዜና ዘገባዎች ሉሲ ወደ ውጭ ጉዞ ምትክ ሉሲን ተቀብለው የሚያስተናግዱት ሙዝየሞቹ የሚከፍሉት ክፍያ ሀገር ውስጥ ሙዜም ግንባታ ይውላል የሚል አይነት ዘገባዎች አስደምጠዋል። ጥያቄው ግን ገንዘብ ጥያቄ በላይ ነው። ሉሲ በሀገር ውስጥ የበለጠ ብዙ ቱሪስቶችን በመሳብ ከሆቴል እስከ ተያያዥ ወጪዎች ጎብኚዎች እንዲከፍሉ በማድረግ የ እረጅም ጊዜ ገቢ አስገኝነቷ አዋጪ ንግድ አስተሳሰብ ነው።
ከሁሉ አስገራሚው ነገር የ ኢትዮጵያ መንግስት ሉሲን ከ ሀገር አንድትወጣ ያደረገበትን ምክንያት ሲገልፅ ''መልካም ስምን ለማደስ '' በሚል 'ታርጋ'  ይሁን እንጂ  አለም አቀፍ ሕግን የሚፃረር መሆኑን የተገነዘበ አይመስልም። ማንኛውም ጥንተ-አፅም ከተገኘበት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር እንዳይሄድ የሚለውን ውል እንደ፣ሚፃረር ልብ ያለው አይመስልም። 
እ ኤ አ በ 1998   ከ ሃያ ሀገሮች የተውጣጡ  ሳይንቲስቶች  በ ዩኔስኮ አስፈራሚነት ''ማንኛውንም አይነት ጥንተ-ሰው አፅም ለሳይንሳዊ ስራዎች ምክንያት ካልሆነ በቀር ከተገኘበት ሀገር ውጭ እንዳይንቀሳቀስ '' የሚል  ሕግ ሲያፀድቁ ትልቁ ስጋታቸው የ ቅርሶች መንገላታት ያውም በሚልዮን ለሚቆጠር እድሜ ላስቆጠረ ቅርስ ተስማሚ ያልሆነ የ አየርንብረት እና ከቦታ ወደ ቦታ መነቃነቅ ምን ያህል እንደሚጎዳ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባታቸው ነበር። redorbit.com የተሰኘ ድህረ ገፅ 'Lucy’ Exhibit Worries Some Scientists' (የ ሉሲ ለ አውደ ርዕይነት መቅረብ ሳይንፅቶችን አስጨንቀ)  በሚል አርስት በፃፈው ፅሁፍ ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ሕግን እንደሚፃረር ገልፅዋል።
''Bringing Lucy to the United States for a museum exhibit also disregards a 1998 UNESCO resolution, signed by scientists from 20 countries, that says such fossils should not be moved outside of the country of origin except for compelling scientific reasons''
(ሉሲን ወደ አሜሪካ መምጣት በ 1998 በ ዩኔስኮ ከ ሃያ ሃገራት በተውጣጡ ሳይንቲስቶች የተፈረመውን ማንኛውንም አይነት ጥንተ-ሰው አፅም ለሳይንሳዊ ስራዎች ምክንያት ካልሆነ በቀር ከተገኘበት ሀገር ውጭ እንዳይንቀሳቀስ የሚያዘውን ውል ይፃረራል።)
redOrbit(http://s.tt/16715) http://www.redorbit.com/news/science/1045002/lucy_exhibit_worries_some_scientists/

 
በመጨረሻ  ልብ ማለት ያለብን በእዚህ ተራቀቀ እና ቴክኖሎጂ የታገዘ  ማንኛውንም ነገር 'አስመስሎ የመስራት' ባህል በበዛበት ምዕራቡ አለም ሉሲ ተመሳስላ ብትሰራ ዋስትናችን ምንድነው? አንድ አይነት ውል ጭቅጭቅ ሙዝየሞቹ ሆን ብለው አንስተው ሉሲን አልሰጥም ቢሉስ? በመካከል ሉሲን ላለመመለስ ሙስና ሕጉ ቢጣመምስ? ግን ሉሲ መጣች? ወይስ  ቀረች? ካልመጣች መቼ ነው የምትመጣው? ከሀገር ለመውጣቷ ተጠያቂዎቹ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዴት እንደዚህ አይነት ውሳኔ ደረሱ? ሉሲ የት ነች? ብሔራዊ ሙዝየም? ወይስ ባህር ማዶ? ሰሚ ያለህ!
 
አበቃሁ

ጌታቸው

ኦስሎ

2 comments:

Anonymous said...

Thank you thank you. Lucyn endastawesk Egziabher yastawsih. Bemejemerya Lucy ke hager sitweta Ethiopian tastewawqalech yemil simet neberegn. Ahun sasibew gin gudatu endemiamezn gebagn.

Anonymous said...

Lucy china heda eyetengelatach new tamagn zena new. Atsim mangelatat yelemede mengst alen.